ሰዋስው ☘☘☘☘
Kanalga Telegram’da o‘tish
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Ko'proq ko'rsatish1 161
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሐንስ አፉሁ ዘወርቅ ለጳጳሳት ሊቅ እለ ይነባ ከናፍሪሁ ምድራሳተ ጽድቅ። ትርጉም፦ ከናፍሮቹ የእውነት ድርሳናትን (ትርጓሜያትን፤ ስብከቶችን) የሚናገሩ፤ የጳጳሳት አለቃቸው አፉ የወርቅ የተባለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፲፯ (17) ቀን።
❤ እንኳን ለዓለም ሁሉ መምህር ለቊስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሥጋው ለፈለሰበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቡሩክ አብርሃምና ከሚስቱ ሐሪክ፣ ከወጺፍ ጻድቃን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የሥጋው ፍልሰት፦ ይህም እንዲህ ነው መበለቲቱን ቦታዋን በግፍ ነጥቃታለችና እርሱም እንድትመስላት ቢያዛት ስለአልሰማችው ስለ መበለቲቱ ቦታ ቅዱስ ዮሐንስ ንግሥት አውዶክስያን በአወገዛት ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጣች ሰይጣንም በልቧ አደረና ስለ ክፉ ሥራቸውና ስለ በደላቸው አውግዞ የለያቸውን ኤጲስቆጶሳት በእርሱ ላይ ሰበሰበች። እርሱንም ስለ መሰደዱ ከእርሷ ጋር ተስማምተው አድራኮስ ወደምትባል ደሴት አጋዘችው በዚያም ጥቂት ዓመታት ኑሮ ወደ መንበረ ሢመቱ ተመለሰ።
❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መናፍቃን የሆነ ኤጲስ ቆጶሳትን ሰበሰበችና ወደ አርማንያ አጋዙት ከዚያም በረሀ ወደሆነ ሩቅ አገር ሰደዱትና በዚያ ዐረፈ። የአርቃዴዎስም ልጅ ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ መልክተኞችን ልኮ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ብዙ በመዘመርና በማመስገን በታላቅ ክብር ወደ ቊስጥንጥንያ አፍልሶ አስመጣው ይህም ከዕረፍቱ በኋላበሠላሳ አምስት ዓመት ነው።
❤ በሌላ በቅብጢ መጽሐፍ በግንቦት ወር ሃያ ሁለት ቀን እንደ ደረሰ ይነገራል በሮሜውያን መጽሐፍ ግን በየካቲት ወር ሃያ ሁለት ቀን ተባለ የዕንቊ ፈርጾች ባሉት የዕብነ በረድ ሳጥን ውስጥ አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት ከሥጋውም ታላላቅ የሆነ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።
❤ ሁለተኛም የእስክንድርያ ግጻዌና የአገረ ቅብጥ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ የጻፈው ግጻዌ የመለካውያንም ግጻዌ በዚች በኅዳር ዐሥራ ሰባት ቀን ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዳረፈባት ተባበሩ። ሁለተኛም ደግሞ የመለካውያን ግጻዌ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዐይሉል በሚባል ወር በዐሥራ አራት እንዳረፈ ይናገራል ይህም በመድኃኒታችን በመስቀል በዓል መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ነው። ስለዚህም ራሱን ለማሰሰቻል ወደ ኅዳር ዐሥራ ሰባት ቀን ለወጡት።
❤ የቀደሙ መጻሕፍት ግን ዕረፍቱን ግንቦት ዐሥራ ሁለት ቀን እንደሆነ ያወሳሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ በከበረ አባት በዮሐንስ አወ ወርቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦የኅዳር 17 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን። እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን። ወይትዌከፎሙ ለዕቤራት ወለእጓለ ማውታ"። መዝ 145፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 1፥12-19፣ 1ኛ ጴጥ 2፥10-18 እና የሐዋ ሥራ 16፥14-25 የሚነበበው ወንጌል ማቴ10፥16- ፍጻሜ ምዕራፍ። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅድስት ወለተ ጴጥሮስና የአቡነ ሲኖዳ የዕረፍታቸው በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜና ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፲፯ (17) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ሰማዕት ወጻድቅ ለሆነችው በጣና ባሕር ላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ለነበረችው ለታላቋ እናት ለቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ዐፅማቸውን የተሸከች በቅሎም ለወለደችና ለመካኖች ልዩ ቃል ኪዳን ለተሰጣቸው ለታላቁ አባት ለአቡነ ሲኖዳ ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
+ + +
❤ ሰማዕት ወጻድቅ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፦ የትውልድ ሀገሯ ጎንደር ደዋሮና ፈጠጋር ነው፡፡ አባቷ ቅዱስ ባሕር ሰገድ እናቷ ቅድስት ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ በሕግ በሥርዓት በሊቀ ጳጳሱ ትእዛዝ የንጉሥ ሱስንዮስን የአማካሪዎች አለቃ የሆነውን መልክአ ክርስቶስን አግብታ ሦስት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ባሏም ታላቅና እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከልጆቿ ጋር በተድላ በደስታ መኖር እንደ ጀመረች "አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ እነዚህ ሦስት ልጆቼ አንተን የማያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው" ብላ ከጸለየች በኋላ እንደፍላጎቷ ሦስቱም ልጆቿ በሞት ተወስደውላታል፡፡
❤ ባለቤቷም እጅግ እየወደዳት እርሷ ግን"ይህ ዓለም እንደ ጤዛ ያልፋል" ብላ ከሞላ ሀብቷ ከሞቀ ቤቷ ተለይታ ወጥታ በመመነን ጣና ገባች በዚያም በተጋድሎ ስትኖር ባሏ ሄዶ አበምኔቱን "ለምን ገዳም አስገባሃት?" ብሎ ከሰሳቸውና ከገዳሙ አስወጣት፡፡ እርሷ ግን ተደብቃ አክሱም ሄዳ ደብረ በንኰል ገዳም ገባች፡፡ ተመልሳም መጥታ በጣና ባሕር ላይ ቆማ መጸለይ ጀመረች፡፡
❤ በዘመኗም የነበረው ገዢ ጨካኝና ለጣዖት የሚሰግድ ስለነበር በትልቅ ገደል ወርውረው እንዲጥሏት አደረጋት፡፡ ነገር ግን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ በክንፉ ተቀብሏት ወስዶ ብሔረ ብፁዓንን አሳይቶ መልሶ አምጥቶ ዋልድባ አደረሳት፡፡
❤ ቅድስት እናታችን ወደ ጉምዝ አገርም ተሰዳ ሳለ በነደደ እሳት ውስጥ ቢጨምሯት እሳቱ ምንም ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ ተመልሳም በጣና ባሕር ላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ነበር፡፡ ባሏም እምነቱን ቀይሮ ከካቶሊኮች ጋር ስለተዛመደ ቅድስት እናታችን ካቶሊኮችንና ባሏን አጥብቃ ስለተቃወመች በገመድ አስረዋት በጎንደር ከተማ ጎዳና ላይ ጎትተው አሠቃይተዋታል፡፡
❤ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ሰባት ገዳማትን ያቀናች ሲሆን ከ700 በላይ በሚሆኑ ወንዶች መነኰሳትና ሴቶች መነኰሳይት ላይ እመ ምኔት ሆና ተሹማ አገልግላለች፡፡ ከመነነችበትም ጊዜ ጀምሮ ምግቧም የመረረ ቅጠል፣ ኮሶና አመድ ነበር፡፡
❤ ቅድስት እናታችን ታላቁን የሬማ መድኃኔዓለምን ቤተ ክርስቲያን ሠርታ ሙታንን እያስነሣች፣ ድውያንን እየፈወሰች በታላቅ ተጋድሎ እያገለገለች ሳለ ኅዳር 17 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፋለች፡፡ ጌታችንም ድንቅ የሆነ ቃልኪዳን ገብቶላታል፡፡ በዕረፍቷም ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡
❤ የእናታችን የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ መላ ዕድሜዋ ሃምሳ ዓመት ነው። ከመመነኗ አስቀድሞ ሃያ አራት ዓመት ከመነነች በኋላ ሃያ ስድስት ዓመት ኖራለች። ከእናታችን ከቅድስት ወለተ ጴጥሮስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ ወለተ ጴጥሮስና መዝገበ ቅዱሳን።
+ + +
❤ አቡነ ሲኖዳ፦ ሲኖዳ ማለት "ታማኝ" ማለት ነው፡፡ ትውልድ አገራቸው ጎጃም ሲሆኑ የሸዋ ባላባት ልጅ ናቸው፡፡ በጎጃም ደብረ ዲማህ አጠገብ ደብረ ፅሞና በተባለው ቦታ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያመልኩት የነበረውን ትልቅ ዘንዶ አቡነ ሲኖዳ በመስቀል ባርከው ከሁለት ሰንጥቀውታል፡፡ ሰዎቹንም አስተምረው አሳምነው አጥምቀው የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸዋል፡፡ ጻድቁ የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓይነት ገድል አላቸው፡፡ ለዘንዶ ምግብ እንዲትሆን ግብር ሆና የተሰጠችውን ሴት ልጅ ከጫካ አግኝተው ዘንዶውን በመስቀላቸው አማትበው ገድለው ልጅቷን አድነዋታል፡፡
❤ በዘመናቸው ነግሦ የነበረው "ሕዝበ ናኝ" የተባለው ንጉሥ በሰዎች ወሬ "ንግሥናዬ ለሌላ ይሰጣል ትላለህሳ" በማለት ጻድቁን እጅና እግራቸውን አስሮ ካሠቃያቸው በኋላ እጃቸውን አስቆረጣቸው፡፡ ነገር ግን ለአቡነ ሲኖዳ እመ ብርሃን የብርሃን እጅ ተከለችላቸው፡፡ በጌቴሴማኒ ያለችው ሉቃስ የሳላትና ስርጉት የተባለችው የእመቤታችን ሥዕል በየጊዜው እየተገለጠች ታነጋግራቸው ነበር፡፡ ንጉሡ በስደትና በግዞት ብዙ እያሠቃያቸው ሳለ መልአክ መጥቶ ዕለተ ዕረፍታቸውን ነግሯቸው እሳቸውም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ጠርተው ከተሰናበቷቸው በኋላ ነው ንጉሡ በኅዳር 17 ቀን አንገታቸውን ያሰየፋቸው፡፡ ከአንገታቸው ውኃ፣ ደምና ወተት ፈሷል፡፡
❤ ጻድቁ በሐይቅ ደሴት የተቀበሩ ቢሆንም ቀድሞ በሚያገለግሉበት በድፍን ምስራቅ ጎጃም ድርቅና ርኃብ ስለሆነ በደብረ ፅሞና ገዳም ይኖሩ የነበሩት አባ መቃርስ ዐፅማቸውን አፍልሰው በማምጣት በደብረ ዲማህ አጠገብ በስማቸው በተሰራው በደብረ ፅሞና ቤተ ክርስቲያን በክብር ሲያሳርፉት ወዲያው ዝናብ ጥሎ ድርቁም ጠፍቷል፡፡ ዐፅማቸውን ተሸክማ ያመጣችው በቅሎም ወልዳለች፡፡ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ሲኖዳ ለማይወልዱ መካኖች እጅግ ልዩ ቃልኪዳን ነው የተሰጣቸው፡፡ መቃብራቸውን
እየዞሩ እምነታቸውን እየተቀቡ ገድላቸውን እየታሹ የማይወልዱ መካኖች የሉም፡፡ ከሩቅም ሆነው በስማቸው ተስለው እምነታቸውን ተቀብተው የሚወልዱ በጣም ብዙዎች ናቸው፣ እንኳንስ ሰው ይቅርና ዐፅማቸውን የተሸከች በቅሎም ወልዳለችና!።
❤ የጻድቁ ሌላኛው በስማቸው የተሰየመውና እጅግ ተአምረኛው ታቦታቸው ዛሬም አቡነ ሲኖዳ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከአ.አ 180 ኪ.ሜ ርቆ ከጣርማ በር አልፎ ሞላሌ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ በሰሜን ሸዋ በሚገኘው በዚህ ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በዘመናችንም በጣም በርካታ ተአምራት ይደረጋሉ፡፡ ለጻድቁ የተሰጠችውን የስዕለት በግ ጅብ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ገብቶ ሊበላ ሲል ቀንዱን ነክሶ ደርቆ ሞቶ ሲገኝ በጉ ግን ምንም አልሆነም፡፡ አቃቢቷም እንዲሁ ከትልቁ ተራራ ሥር በትልቅ ቅል ውኃ ቀድተው ሲመለሱ ገመዱ ተበጥሶ ቅሉ ከነውኃው ከትልቁ ገደል ገብቶ ድንጋይ ላይ ቢያርፍም ቅሉ ሳይሆን ድንጋዩ ነው የተሰበረው፡፡ የአካባቢው ነዋሪም "በጉ ጅብ ገደለ፣ ቅሉ ድንጋይ ሰበረ" እያሉ ጻድቁን ያወድሷቸዋል፡፡ ከአባታች ከአቡነ ሲኖዳ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለአኖሬዎስ እንዘ ባዕል ዘተጸነሰ። ወለዳንኤል ሱታፋ አስኬማ መላእክት ዘለብሰ።እንበይነ አንጽሑ ሥጋ ወእንበይነ ቀደሱ ነፍሰ። እምበዓት መነኰሰ ወእምነ መንበር ንጉሠ። እግዚአብሔር ዮም ኅቡረ አፍለሰ። ትርጉም፦ ባለጸጋ ሳለ የተቸገረ ለኾነ አምሳያው ለአኖሬዎስና ገድል ተባባሪው የመላእክት አስኬማ የለበሰ ለኾነ ለዳንኤል ሰላምታ ይገባል፤ ሥጋቸውን ስላነጹና ነፍስን ስለቀደሱ ከበኣት መኵሴን ከዙፋኑ ንጉሥን እግዚአብሔር ዛሬ በአንድነት አሳረፈ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 16።
https://t.me/Eotcw
1 161
ሚስትም ባልም በገዛ ስጋቸው ስልጣን የላቸውም ..ስልጣኑ የትዳር አጋራቸው ነው ማለት። ባል ወይም ሚስት ከሁለት አንዳቸው ግብረ ስጋ ግኑኝነት ቢፈልጉ ሌላውን ወገን "አካሉ የኔ ነው" ብሎ መከልከል የለበትም ፤ ስልጣኑ የሱ አይደልም……ይልቁን ለትዳር አጋራችሁ ፍላጎት የነቃችሁ ሁኑ ማለት ነው…...ነገር ግን ሁሌ መፈጸም አትችሉም አለ እና የማይፈጸምበት ጊዜን ሲገልጽ ‹‹ ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ ፤›› 1ኛ ቆሮ 7፡5፡፡
☞ መቼ ነው ለጸሎት የምንተጋው?….
ክርስቲያን በትጋት የማይጸልይበት ጊዜ አለን?
መልሱ ፦ ክርስቲያን ሁሌም የጸሎት ሰው ነው…..ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ተስ5፡17 ‹‹ሳታቋርጡ ጸልዩ ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና›› ነው ያለው ስለሆነም ክርስቲያን ሁሌም ይጸልያል……ነገር ግን ከጸሎትም ብርቱ ጸሎት አለ፡፡
☞ ቅዱስ ጳውሎስ‹‹ለጸሎት ትተጉ ዘንድ›› ብሎ የገለጠው ጸሎት የቱ ነው ቢባል?
አንደኛው ባለጾም ጸሎቶች ሲሆኑ..በጸሎት እና በምሰጋና የምንተጋባቸው ሰንበታት እና በዓላት ናቸው ፡፡ የተነሳንበት ዓላማ ጾም ነውና በእሱ ላይ ትኩረት እንሰጣለን… ጾም የሌለው ጸሎት አለ፤ ጸሎት የሌለው ጾም ግን የለም። ስለሆነም ትጉህ ጸሎት ከሚባሉት ውስጥ ዋነኛው የጾም ጊዜ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ጾምን የሀዘን ጊዜ ብሎ ነው የሚጠራው፡፡
‹‹ በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ።ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ
አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም›› ት.ዳን 10፡3፡፡
ጌታም የጾም ሀዘን ጊዜነትን ሲያረጋግጥ የማቴዎስ ወንጌል 9:15
‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።››
ታዲያ በዚህ ምግብ በሚከለክልበት ጊዜ ……. ሰዎች በምድር ዓለም ጥልቅ የስጋ ደስታ ምንጭ በሆነው በወሲብ የደስታ ርካታ ሰውነታቸውን እንዲያጠግቡ እንዴት መፍቀድ ይቻላል? የሚገባው በሁሉም አቅጣጫ እንዲጾሙ ማድረግ ነው ነው እንጂ፡፡
ነገር ግን ግብረስጋ ግኑኝነት መቆም ያለበት በአንዱ አካል መንፈሳዊ ብቃት አይደለም ….በጾም ሆነ በፍስክ….መቆም የሚችለው በስምምነት ብቻ ነው፡፡ ‹‹ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ›› ሰምምነት ካልተደረሰ…የጿሚው ወይስ የፈላጊው ይፈጸም ብለው ቢጠይቁ ??….መልሱ የፈላጊው ይሆናል፡፡ ለምን ቢሉ ከወሲብ መታቀብም ልክ እንደ መንፈሳዊ ደረጃ …..ወጣኒ..ማዕከላዊ … ፍጹማዊ እንደሚባለው ልዩ ልዩ ደረጃዎች በአንዴ ወደ መከልከል መድረስ ከባድ ሊሆን ይችላልና ። ስለሆነም ከፍ ያለ መከልከል አቅም ላይ የደረሰው የትዳር አጋር የትዳር ጥንዱን ወደእሱ ደረጃ በሂደት ማብቃት እንጂ በሱ ደረጃ ላይ በግድ ይድረስ ብሎ መግፋት ከባድ ችግር ውስጥ ሊያስገባ ይችላል። ስለሆነም ‹‹ ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ ፤›› 1ኛ ቆሮ 7፡5 እንዳለው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል እየተስማሙ..ከንስሀ አባት ጋር እየተመካከሩ ግብረስጋ ግኑኝነት መፈጸም ወይም መከልከል ይቻላል። በነገራችን ላይ ዛሬ በአብዛኛው ባይፈጸምም ቤ/ክ ከመነኩሴ ይልቅ ቄሶች ለባለትዳር የንሰሀ አባት ይሁኑ ብላ ነው ሕግ ያወጣችው፡፡
እዚህ ላይ ከጥቂት አመታት በፊት ሸንኮራ ዮሐንስ በነበርኩ ጊዜ ስለአንድ የትራክተር ሹፌር የሰማሁትን ታሪክ የጽሁፌ አካል ማድረግ እፈልጋለው፡፡
ሰውየው የዝዋይ እርሻ ልማት የትራክተር ሹፌር ነው። ሚስቱ ደግሞ የምትኖረው በአቅራቢው ባለቸው በመቂ ከተማ ነበር። ባልየው የእረፍቱ ቀን እሁድ ብቻ ስለ ነበረ እሁድ ወደ ሚስቱ ይሄድና "ጉዳዩን እንጨዋወት" ሲል "አይሆንም ሰንበት ነው" ትለዋለች። "እሺ አድሬ ሰኞ ይሁን" ሲላት ደሞሜ "ሚካኤል ነው" ስትለኝ "በሳምንቱ ስላት ደግሞ በገብርኤል ቀን አይደረግም" ስትለኝ 'ከሁለት ቀን በኋላስ ስል በእመቤቴ ቀን ስትለኝ" … "እሺ አንቺ ራስሽ ክፍት በሆነ ቀን ተሳፍረሽ እኔ አለሁበት ቦታ ነይ" ስላት ደግሞ "እኔ ደግሞ ለዚህ ብዬ በመኪና ተሳፍሬ አንተ ጋር ልምጣ" ስትለኝ ታዲያ ከኔ ምን ፈልጋ አገባችኝ ብዬ……. ተበሳጭቼ…… ገብርኤልና ሚካኤል እኔን ለመከልከል ነው እንዴ ቀኑን ሙሉ የተቆጣጠሩት ብዬ/እዚህ ላይ መታሰቢያ የሌለው ቀን የለም/ በአለሁበት የስራ ቦታ ካላንደር የማይቆጥሩ ከአንድም ሶስት አግኝቼ… ከሚስቴ ያጣሁትን እንደልቤ አግኝቻለው አለኝ››፡፡
ይሄ ታሪክ የብዙ ባለትዳሮች ችግር ሊሆን ይችላል ብዬ አስባላሁ። ሀላፊነቱን መውሰድ ያለባት ደግሞ ቤ/ክ ናት። ተጋቢዎችን በአግባቡ በግልጽ ማስተማር አለባት፡፡ ሰው ከትዳሩ ውጪ ወሲብ ከፈጸመ ዝሙት ነው፡፡ ሰው በጾም ወራት ወሲብ ባይፈጽም ይመረጣል ። ከፈጸም ግን ዝሙት አይደለም፤ በተጋድሎ ጸጋ ውስጥ ባለ እድገት ጀማሪ መሆኑን ያሳይበታልና፤ በጸጋ አለማደጉን ያረጋግጣል፤ በቅድስና ደረጃ በጽድቅ ትሩፋት ጉድለት እንዳለበትም ያሳያል ማለት ነው፡፡
ይህቺ ባለትዳር ሴት በጽድቅ ትሩፋት ሕግ ምክንያት ለመታቀብ ወስና ባለቤቷ ለዝሙት ስህተት እንዲጋለጥ ምክንያት መሆኗ… አለመማሯ ነው። የባሏ ዝሙት በትዳሩ ውስጥ በሽታ እና የዝሙት መርገም ያመጣ ይሆናልና …ታዲያ በዚህን ጊዜ የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ማስታወስ ነው
....
ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤›› 1ኛ ቆሮ 7፡5፡፡
ፈጣሪ አምላክ ሁላችንንም በተቀደሰ አኗኗር እንኖር ዘንድ ይርዳን!!
ምርጫችንን እንድናውቅ እሱ በፈቀደልን የሕይወት ምርጫ እንድኖር ይርዳን!!
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ
1 161
እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ።
በጾም ወራት ባለትዳሮች ከግብረ-ስጋ ግንኙነት እንዲታቀቡ ቤተክርስትያን የምትመክረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?
ሼር ይደረግ
በቤተክርስትያችን ትምህርት ሰው ለአቅመ አዳም እና ለአቅመ ሔዋን ከደረሰ በኋላ ሕይወቱን የሚመራበት ሁለት አይነት ምርጫ አለው፤ ጋብቻ ወይም ምንኩስና።
❖ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለምንኩስና እንዲህ ብሎ ነበር።
መነኩሴ ፡- ማለት መናኝ ፣ ብቻውን የሚኖር ፣ሴት የማያውቅ ድንግል፣ የገዳም ሰው፣ ባተሌ፣ ከዓለም ከሕዝብ ከገንዘብ የተለየ ማለት ነው / አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት እና ምንኩስና በኢትዮጵያ ላይ እንደተገለጠው/፡፡
ምንኩስና- ለሴትም ለወንድም ይሰራል፤ ዓላማው በትዳር አሳብ ሳይጠላለፉ በሙሉ ጊዜ ፈጣሪን የማገልገያ መንገድ ነው፡፡
በአንድ ወቅት ጌታ ስለጋብቻ ሕግ ባስተማረ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ‹‹የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም ›› ሲሉት እንዲህ ብሎ ዘርዝሮ ነገራቸው።
ከሴት ርቆ ከወንድ ርቆ ንጽህናን ጠብቆ መኖር ስጦታ ነው እንጂ ሁሉ የሚችለው አይደለም ሲል ‹‹ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም›› አለ ማቴ 19፡11፡፡
ቀጠለና ቁጥር 12 ላይ‹‹በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው።›› አለ ፡፡
ይሄ የጌታ ንግግር የሚያረጋግጠው..ሶስት ነገሮችን ነው። ደግሞም ብልቶቻቸውን ለግብረስጋ ግኑኝነት የማይጠቀሙበት ሰዎች አሉ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ጃንደረባ ማለት ብልቱ የተቆረጠ ማለት ነውና፡፡
1. የመጀመሪያዎቹ በጌታ አገላለጽ በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የሚወለዱ ያላቸው ፦ አካል ሳይኖራቸው የሚወለዱ ወይም አካሉ ቢኖርም ተፈጥሮአዊ ሙቀት ሳይኖራቸው የሚወለዱት ናቸው።
2. ሁለተኛዎቹ ደግሞ ሰው የሰለባቸው ጃንደረቦች ናቸው / ይሄ በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች በጎሳዎች መካከል ሲጣሉ እና ለጋብቻ ማጫ እንደሚሰልቡ የሚታወቁ ቦታዎች አሉ…የሚገርመው ነገር እነሱ በጉዳዩ ሊጠቀሙ የሌላውን መጠቀሚያ አካል ቆርጦ ማጫ ማቅረብ…ምን ያህል…ኢ ፍታዊነት እንደሆነ መረዳት ይቻላል/፡፡
3. ፠ በጌታ አነጋገር ሶስተኛው አይነት ጃንደረባነት ‹‹ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ›› ያላቸው ሲሆኑ....ይሄም ምንኩስና ነው፤ ለመንግስተ ሰማያት ተብሎ ከጾታ ግኑኝነት ራስን ማራቅ ማለት ነው።
❖ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሰለምንኩስና ምን አለ?
1ኛ ቆሮ 7፡17 ቅዱስ ጳውሎስ "እንዳያገቡ አወዳለው" ማለቱ ሲሆን ነገር ግን ‹‹ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ።>> በማለት ሁሉ ተመሳሳይ ጸጋ እንደሌለው አረጋግጧል…አንዱ እንደዚህ /አያገባም/
ሁለተኛው እንደዚያ ሲል ደግሞ /ያገባል/ ማለት ነው፡፡ ልክ ጌታ በማቴ 19 ፡12 ‹‹ ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው ›› እንዳለ ሊቀበለው የሚችል ሁሉ አይደለም፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ዘርዘር ሲያደርገው፦
1ኛ ቆሮ 7፡32 ‹‹ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል።.......በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው›› ስለሆነም ቅዱስ ጳውሎስ በአጠቃላይ መልዕክቱ ልባቹ እንዳይከፈል ከቻላችሁ አታግቡ ብሎ መክሯል …በመጨረሻው ንግግሩም ‹‹ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ።›› በማለት ድንግልን ማግባት መልካም ቢሆንም የተሻለው ግን አለማግባት ነው፡፡
ስለዚህ ነገር አንድ የቤ/ክ ሊቅ እንዲህ ብለው ነበር ጳውሎስ ጋብቻን ክቡር ነው ቢልም እርሱ አላገባምና ይ ብልጠቱን ተመልከቱ ብለው ነበር፡፡
እንግዲህ ይሄን የቅዱስ ጳውሎስ ብልጠቱን ማየት/አለማግባት/ ሳይቻለን ቀርቶ ጸጋችን ጋብቻ መሆኑን አውቀን ለማግባት ከመረጥን ደግሞ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ እንደማይገባ አውቀን የምንጋባው በድንግልና ነው፡፡ ‹‹ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ።›› 1ኛ ቆሮ7፡36፡፡
ስለድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር ማለት…. ቆሞ ቀረ ተባልኩ ብሎ ያፈረ ሰው ቢኖር…ያግባ ነው የሚለው…….ድንግል ሆኖ በመኖሩ ያፈረ ሰው ድንግልናውን በጋብቻ ብቻ ነው የሚያጣው ማለት ሲሆን ይሄም የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ሰው ድንግልናውን ጠብቆ እስከጋብቻ መጽናት እንዳለበት ያረጋግጣል……. ‹‹ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ›› 1ኛቆሮ7 ፡38፡፡ የሚለው ቃል መጋባት በድንግልና መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
አረ ቅዱስ ጳውሎስ እንደዚህም ብሏል ‹‹ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤>>1ኛተሰ 4፡5፡፡
አንድ መተርጉም ቅዱስ ጳውሎስ "የራስን ዕቃ በክብር ማግኘት" ያለው ..የሚገኝ የራስህ የሆነ የትዳር አጋርህን አካል ነው….እሱም ያንተ የሆነ ንብረት ነው….ግን በቅድስና እና በክብር ያገኝ ዘንድ የተባለው ደግሞ በህጋዊ ትዳር በሰርግ ደስታ….በጋብቻ ስርዓት ተቀበለው ሲል ነው ብሎ ተርጉሞታል….ይሄን የሰማች አንድ እህት በወቅቱ ….እኔማ… ‹‹ብር አምባር ሳላሰኝ›› ሞቼ ነው ብላ ፎክራ ነበር…እኛም ይበል ብለን አልፈነዋል….. እንዲህ አይነቱን አቋም እናበረታታለን…እስካሁን ጉዳዩ ተጠብቆ ካለ…..እንዲው አልሆነ ቦታም ከወደቀም…ድጋሚ አይነሳምና ከተክሊል ርቆ በመዓስባን ጋብቻ ለመጋባት የነፍስን ድንግልና በንስሐ መመለስ ነው፡፡
ከተጋባን በኋላስ ድንግልና ሳይሆን ወሲብ ቦታውን ይይዛል ።
በጋብቻ ውስጥ ግብረ ስጋ ግኑኝነት በመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይገለጻል ??
ዕብ 13፡4‹‹ መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል››፡፡
ስለሆነም በጋብቻ ውስጥ ያለው መኝታ/ግብረ ስጋ ግኑኝነት/ ንጹሕ ነው ፤ ነውር የለበትም። ይሄ ማለት ግን…..ባል እና ሚስት ሌላ ስራ የለባቸውም፤ ሁሌም ከአልጋ አይውረዱ ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉ ነገራችን መመሪያ አለው….. ‹‹ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።›› 1ኛቆሮ 14፡40፡፡
☞ ስለሆነም ወሲብ በቤ/ክ ገደብ ይጣልበታል ሁሌ አይፈጸምም… መቼ እንዴት ብንል?
1ኛ ቆሮ 7፡4‹‹ ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።› ይሄ የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ግልጽ መመሪያ ነው፡፡
1 161
በነገው ዕለት በቅዳሴ ጊዜ የሚባል #ምስባክ ፦
መዝ ፳፥፩-፫
እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ።
ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ።
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ።
#ትርጉም ፦
አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል
በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው
1 161
❤ በማግስቱም አኖሬዎስ አይን የሚበዘብዝ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ በአባ ዳንኤልንም አስገቡት በአየው ጊዜ ፈርቶ ተንቀጠቀጠ ረዳቱም መፍራቱ አይቶ ወደ ማደርያው መለሰው ንሡም ችሎቱ ሲጨርስ ልብስ ለብሶ አባ ዳንኤል ወደ አለበት ገባ አባ ዳንኤልንም ባየው ጊዜ "ወንድሜ ሆይ በልቤ ያለው ነግሬው ወደ ቦታዬ እመለስ ዘንድ ወደ ንጉሡ ለምን አላስገባኝ" አለው። አኖሬዎስ "አባቴ ሆይ አልገባህም? ለዝች ምድር ንጉሥ ብለው የሰየሙኝ በኀላፊ ዙፋንም ላይ ተቀምጨ ያየኸኝ እኔ አኖሬዎስ ነኝ" አለው።
❤ አባ ዳንኤልም በሰማ ጊዜ ከእግሩ በታች ሰገደለት አኗኗሩን ሁሉ ይነግረው ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን ስም አማጸነው ንጉሥ አኖሬዎስ በእጅ ሥራው ደክሞ ከሚያገኘው በቀር ይህም ሰሌን መታታት ነው ሳይበላ፣ ሳይለብስ አርባ ዓመት እንደሆነው የሚተርፈውን ለድኆች እንደሚሰጥ ምግቡም እንጀራና ጨው ቅጠል መጻጻ እንደሆነ የማንንም ገንዘብ ለመቀማት እንዳልደፈረ ድንግልናው እንደጠበቀ ነገረው። አባ ዳንኤል ከእግሩ በታች ወድቆ "በአንተ ላይ ስለተመካው ይቅር በለኝ" አለው። ከዚህ በኋላ አባ ዳንኤል ፈጽሞ እያዘነ ወደ ቦታው ተመለሰ።
❤ ከሁለት ወሮችም በኋላ መምህሩ አውሎጊስን ተሰጋብቶ አኖሬዎስ ከቤተ መንግሥቱ ውስጥ ወጣ እግዚአብሔርም መልአኩን ላከለትና ተሸክሞ ወደ አባ ዳንኤል አደረሰው በተጋድሎ በመጠመድ ኑረው ገድላቸውን ፈጽመው በአንዲት ዕለት ዐረፉ እንዲሁም አውሎጊስና ረዳቱ በዛች ዕለት በአንድነት ዐረፉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ቅዱሳን ፀሎት ይማረ በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ኪስጦስ፦ ይህንንም ቅዱስ ኪስጦስን መኰንኑ በያዘው ጊዜ ጽዕኑ ስቃይ ሳሰቃየው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፋ ቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። የቅዱስ ኪስጦስ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 16 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለጣጡስ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ። በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ሥሉጥ። አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ። አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ። ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ። ትርጉም፦ በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለጣጡስ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች(መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 16።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ። ወብዙኀ ይትኀሠይ በአድኅኖትከ። ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ"። መዝ 20፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት የሚነበበው 2ኛ ቆሮ 9፥5-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 5፥2-12 እና የሐዋ ሥራ 14፥23-ፍ.ም። ወንጌል ሉቃ 14፥7-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ ኅዳር ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን በሮሜ አገር በከሀዲ መኰንን በእስክድሮስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለች ለቅድስት ጣጡስ ለዕረፍት በዓል፣ ለመነኰስ አባ ዳንኤልና ለንጉሥ አኖርዮስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለእስክድርያ አገር አርባ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበረና ለተመሰገነ የገዳማዊ አቡናፍር ከምስር ከተማ ውጭ ለተሰራች ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት፣ ለቅዱስ ኪስጦስ በመኰንኑ በመክሲሞስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ በሐይቅ ዳር እንዳለ ጽጌ ረዳ መዐዛው ከሚጥም ከቅዱስ ፊቅጦር ከመታሰቢያው፣ ከንጉሥ አኖሬዎስ መምህር ከአባ አውሎጊስና ከንጉሥ አኖሬዎስ ረድኡ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለጣጡስ ዘኮነት ስምዐ በእንተ ክርስቶስ ዘከለላ እምሰማይ ሞገስ"። ትርጉም፦ በሰማይ ያለ ሞገስ የጋረዳት ስለ ክርስቶስ ምስክርን የነበረች ለኾነች ለጣጡስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ቅድስት ጣጡሳ፦ ወደርሱም በቀረቧት ጊዜ እለስክድሮስ "ለአማልክት ሠዊ" አላት እርሷም "ከፈጠረኝ ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አልሠዋም" ብላ መለሰች። መኰንኑም የፊቷን መሸፈን እንዲገልጡ አዘዘ ውበቷንም አይቶ አደነቀ ዐይኖቿ እንደ አጥቢያ ኮከብ ናቸውና ቁመቷም እንደ ዘንበባ ደም ግባቷም እንደ ጽጌ ረዳ ነው በዚያም ወራት የሚመሳሰላትየለም ነበር።
❤ ንጉሡም በአያት ጊዜ እርሷም በመውደዱ ልቡ ተነጠቀ እንዲህም አላት "እሺ በይኝና ለታላቅ አምላክ ለአጵሎን ሠዊ እኔም ለቤተ መንግሥቴ እመቤት አደርግሻለሁ" አላት። ቅድስት ጣጡስም "እኔ ክብር ይግባውና ከክርስቶስ ከመንጋዎቹ ውስጥ ነኝ ከእርሱ በቀር ለሌላ አልሠዋም ነገር ግን ወደ አማልክቶችህ መሠዊያ ቤት ገብቼ ኃይላቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ" አለችው። በዚያንም ጊዜ ወሰዷት በገባች ጊዜ ጣዖታቱ ይጠፉ ዘንድ ክብር ይግባውና የኃይል ባለቤት ወደ ሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየች ወዲያውኑ ንውጽውጽታ ሁኖ ጣዖታቱ ከመቀመጫቸው ወድቀው ተሰባበሩ ታላቁ አምላካቸው አጵሎንም ቊልቊል ወድቆ ተቀጠቀጠ ከጣዖቱ አገልጋዮችም ብዙዎች ሞቱ በአጵሎን ላይ አድሮ የሚኖር ርኩስ መንፈስ እዲህ ብሎ ጮኸ "ጣጡስ ሆይ እኔ ካንቺ ምን አለኝ አንቺስ ከእኔ ምን አለሽ እነሆ ማደርያዬን ቀጥቅጠሽ ከእርሱ አውጥተሽኛልና" ንጉሡም ይህ አይቶ ተቆጣ በግንባሯ ደፍተው በበትሮች እንዲደበድቧት በአለጋዎችም ንዲገርፏት አዘዘ ከሥጋዋም በወተት አምሳል ነጭ ደም ፈሰሰ ወደ እግዚአብሔርም በለመነች ጊዜ የሚደበድቧትን የእግዚአብሔር መላእክት የሚያሰቃዪቸው ሆኑ ቅድስት ጣጡስን ግን ሥቃያቸው የማይነካት ሆነ።
❤ ሁለተኛም ለተራበ አንበሳ እንዲሰጧት ንጉሡ አዘዘ አንበሳውም በደረሰ ጊዜ በፊቷ ሰገደ የእሮቿንም ትቢያ ላሰ ከሰማይም "እኔ ከአንቺ ጋራ ነኝና ንጽሕት ጣጡስ ሆይ ደስ ይበልሽ" የሚል ቃል መጣ። ንጉሡም ከክፉ ነገር የደረሰባት እደሌለ አይቶ እራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ተጋድሎዋንም ፈጸመች በሌሊትም የሮሜ ጳጳስ መጥቶ በከበሩ ልብሶ ገነዛት በወርቅና በብር ከተለበጠ የእብረ በረድ ሳጥን ውስጥ ጨመራትና በአማረ ቦታ አሮራት ከስጋዋም ብዙዎች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለቅዱስ አኖርዮስ ዘፈጸመ ግብረ ምንኵስናሁ እንዘ ሀሎ በመንግሥቱ ዘንኩር ኂሩቱ ከመ እንጦስ ወመቃርስ ፍኖቱ ወከመ መንፈሳውያን ሕይወቱ"። ትርጉም፦ ሕይወቱ እንደ መንፈሳውያን፤ መንገዱ እንደ እንጦስና መቃርስ፤ ቸርነቱ በተደነቀ መንግሥቱ እያለ የምንኵስናውን ሥራ የፈጸመ ለኾነ ለቅዱስ አኖሬዎስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ አባ ዳንኤልና ንጉሥ አኖሬዎስ፦ ይህ አባ ዳንኤል ታላቅ ገድለኛ ነው። እንጀራን፣ ዓሳንም ቢሆን ማርንም ዛይትን ቢሆን ከብቻው ቅጠል በቀር ሳይቀምስ አርባ ዓመት ተኩል በአስቄጥስ ገዳም ኖረ።
❤ ከብዙ ዘመንም በኋላ የመመካት ኀሳብ መጣበት በልቡም "እንደኔ ትርሕምት መቆምን የታገሰ በገዳም በውኑ አለን?" አለ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ብርሃናዊ መልአኩን ላከለት መልአኩም "ዳንኤል ሆይ በጎ ያልሆ እንዲህ ያላ ትምክትን ለምን ትመካለህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትሕትና በቀር ትምክህትን አይሻምና" አለው።
❤ አባ ዳንኤልም መልአኩን "ጌታዬ ከእኔ የሚሻል ከአለ ንገረኝ ወደርሱ ሆጄ አየው ዘንድ በመመካቴም ወደ ፈጣርዬ እለማመጥ ዘንድ" አለው። መልአኩም "ንጹሕ ቅዱስ እግዚአብሔርን ሚፈራ ሰው የሮሜና የቊስጥንጥንያ ንጉሥ አኖሬዎስ በመንግሥተ ሰማያት ባልጀራህ ነው" አለው። አባ ዳንኤል በሰማ ጊዜ በምድር ላይ ተደፋ በራሱም ላይ አመድ ነስንሶ ክብር ይግባውና በአምላካዊ ጥበቡ ወደ ሮሜ አገር አድርሷ እርሱን አኖሬዎስ ያሳየሆን ዘንድ ጌታችንን ለመነው።
❤ እንዲህ ሲጸልይም ደመና መጣች ተሸከመችውና ከሮሜ ንጉሥ ከአኖሬዎስ ቤተ መንግሥት ደጅ አደረሰችው የንጉሥ አኖሬዎስም ረዳት አገኘው ረድኡም እጅ ነስቶ ከርሱ ቡራኬ ተቀበለና "አባቴ ሆይ ወደዚህ የመጣህበት ጉዳይህ ምንድነው?" አለው። አባ ዳንኤል "ልጄ ሆይ የሚቻልህ ከሆነ ከአገር መኳንንት ወደ አንዱ አድርሰኝና ወደ ንጉሡ እንዲያስገባኝ" አለው። ረዳቱም "እኔ ባስገባህ መግባትን አትሻምን?" አለው። "ልጄ ሆይ እሻለው አስገባኝ እግዚአብሔር ይባርክህ" አለው። ዳግመኛም ረድኡ "አባቴ ሆይ ማች የሆነ ንጉሥን በማየት ምን ታገኛለህ" አለው። አባ ዳንኤል "ፈጣሪ ባያዘኝ ወደዚህ ባልጣው ነበር" አለው። ረዳቱም "ለጌታዬ የሚያሻው እስከምገዛ ጥቂት ታገሰኝ" አለው።
❤ በዚያንም ጊዜ አንባሻ ጨውና መጻጻ የጎመን ቅጠልም ገሽቶ ወደ ጌታው ወደ ንጉሥ ወደ መምህሩ አውሎጊስ ወደሰ አባ ዳንኤልን በውጪ ተወው ንጉሡም ረዳቱን "አንተ አላዋቂ ነህን አባ ዳንኤል በውጪ የሚታቆመው" አለው። ይህንንም ብሎ ንጉሡ ከመምህሩ ከአውሎጊስ ጋር ወጣ ለአባ ዳንኤል ሰገዱለት ሰላምታም ተሰጣጥተው ወደ ቤተ መንግሥት አስገቡትና በአንድነት ተቀመጡ። ዘጠኝ ሰዓትም በሆነ ጊዜ ረዳቱ የሚበሉት አቀረበላቸው በአንድነትም ተነስተው ጸለዩ አባ ዳንኤል እንዳይታመም እጀራ መብላት ፈርቶ "ጌቶቼ እንጀራ ባለብላቴ በእኔ ላይ አታጉረምርሙ እንዳልታመም ፈርቼ ነው እንጂ በትዕቢት አይደለም" አላቸው። ቅጠልንም ሰጡት ማዕዳቸውም በጽመው ጸሎትን ጸለዩ ከዚህ በኋላ ንጉሥ አኖሬዎስ አባ ዳንኤልን ስላመጣጡ መረመረው አባ ዳንኤልም "ወንድሜ ሆይ የሚቻልህስ ከሆ ወደ ንጉሡ አስገባኝ በጌታ ክርስቶስ ትዕዛዝ መጥቻለሁና" አለው። ንጉሡ ነገ አስገባኀለው አለው።
1 161
7/3/2015 ዓ.ም (፯/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ።
በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ።
ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን፡፡ መዝ 78:10
🕯 ትርጉም
አሕዛብ አምላካቸው ወ ዴት ነው? እንዳይሉ።
የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል።
በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯