ሰዋስው ☘☘☘☘
Kanalga Telegram’da o‘tish
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Ko'proq ko'rsatish1 161
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥር ፮ (6) ቀን።
❤ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ ለግዝረት (ለኢየሱስ) ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ፦ ሃሌ ሉያ "ተወልደ እምድንግል ሰከበ ውስተ ጐል እሙነ ኮነ ልደቱ ለክብረ ቅዱሳን ወለቤዛ ብዙኃን አብ ፈነዎ ለበኲሩ ውስተ ዓለም"። ትርጉም፦ ከድንግል ተወለደ፣ በዋሻ ውስጥ ተኛ፣ በእውነት ልደቱ ለቅዱሳኑ ክብር ለብዙኃንም ቤዛ ሆናቸው፣ አብ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከው።
+ + +
❤ የዕለቱ እግ.ነግ ዓራራይ ዜማ፦ "ወአመ ስሙን ዕለት ወሰድዎ ለሕጻን ከመ ይግዝርዎ በሕገ ኦሪት ሰመይዎ ስሞ አማኑኤል በከመ ሰመዮ መልአክ እምቅድመ ትፀንሶ"፡፡ ትርጉም፦ በኦሪት ሕግ መሠረት ይገዝሩ ዘንድ በስምንተኛው ዕለት ሕፃኑን ወሰዱ ስሙን አማኑኤል ብለው አወጡለት (ሰየሙት) ከመፀነሷ አስቀድሞ መልአክ እንደሰየመው (እንደተናገረው)። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ ልሳነ ዕረፍት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ" ብሎ እንደተናገረ። ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር ጌታችን ግን ግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን።
❤ የከበረ ወንጌል "ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት" እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን "እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ" አለችው። ዮሴፍም ሔዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው "እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቆ ያዙት" አላቸው። ሕፃን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልሶ እንዲህ አለው "ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆች መድኃኒት ይሆናል"።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችን ማርያም "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው" አላት።
❤ ሕፃኑም ለዚያ ባለሙያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው "እኔ ነኝ ትገዝረኛለህ ወይስ ተውክ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ" ያም ባለሙያ "የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?" አለው ሕፃን ጌታችንም "አብርሃም፣ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው" ባለሙያውም "እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና" አለው። በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ "አባት ሆይ ለአብርሃም፣ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ" አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች።
❤ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማሕፀን እንደ መውጣቱ የጌታችን ግዝረቱ የማይመረመር ሆነ እንዲሁ ወደ ሐዋርያት በተዘጋ አዳራሽ መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እንዲሁ እንደ ፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ። አዳምንና ልጆቹን ያድናቸው ዘንድ በፈቃዱ ከጐኑ በመስቀል ላይ የሚፈሰው ደምና ውኃ ካልሆነ በቀር ብዙም ሆነ ጥቂት ሊሆን አይችልም እርሱ በፈቃዱ ሕጉ እንዲፈጸም አስቀድሞ አዘዘ እንጂ።
❤ ያም ባለሙያው ገራዥ ይህን ተአምር ባየ ጊዜ የሕፃኑንም ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ሦስት ጊዜ ሰገደና "በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ" አለው። ከዚህም በኋላ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተአምራቱ ያየውንና የሰማውን እየተናገረ ወደ ቦታው ሔደ ለእርሱም ለጌታችን ከቸር አባቱ ጋራ ማሕየዊ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋራ ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 6 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወይከውን ቡሩከ ስሙ ለዓለም። እምቅድመ ፀሐይ ሀሎ ስሙ። ወይትባረኩ ቦቱ ኵሎሙ አሕዛብ ምድር። መዝ 71፥17-18። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥8-22።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ 104፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 15፥8-14፣ 2ኛ ጴጥ 2፥1-9፣ የሐዋ ሥራ 7፥2-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 4፥24-33። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የኢየሱስ ክርስቶስ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@Eotcw @Eotcw @Eotcw
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥምቀት
💧💧💧💧💧💧💧💦💦💦💦💦
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአእዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ፤ ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘይተልዎ ርእይ፤ በአብትረ ያዕቆብ በርሀ ሥላሴክሙ ፀሐይ፤ ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዓ ላባ ወማይ፤ ለኀበ አባግዕ ዘዮም ወጥምቀት ዓባይ።
ዚቅ
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ፤ ክርስቶስ ውእቱ ዘወጽአ እማይ፤ እመንፈስ ቅዱስ ሠለስቲሆሙ፤ እለ አሐዱ እሙንቱ ፫ቲሆሙ፤ እለ ይከውኑ ሰማዕተ ፫ቲሆሙ፤ ለሊሁ ወረደ መንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ይቀድስ ማያተ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ጸጋ ወጽድቅሰ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ።
ነግሥ
ሰላም ለማየ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ዘአተቦ፤ መንፈስ ቅዱስ ከመ አጥበቦ፤ ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ፤ ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ፤ ማይ ኀበ የሐውር ጸበቦ።
ዚቅ
ርእዩከ ማያት እግዚኦ፤ ርእዩከ ማያት ወፈርሑ፤ ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ።
ወረብ
ርእዩከ 'እግዚኦ'/፪/ ርእዩከ ማያት/፪/
'ደንገፁ'/፪/ ቀላያተ ማያት ደንገፁ ቀላያተ ማያት/፪/
ትምህርተ ኅቡዓት
እምሰማያት እምኀበ አብ አይኅዓ፤ በሕማማተ ሥጋሁ ቤዘወነ፤ ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት፤ ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ፤ ወማየ መንጽሔ ዚአነ።
ወረብ
'ወደሞ ክቡረ'/፪/ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ/፪/
ወማየ መንጽሔ ዚአነ/፬/
አንገርጋሪ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ፤ ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ፤ እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።
አመላለስ፦
አማን በአማን መንክር ፤
መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።
ወረብ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ክርስቶስ ተወልደ/፪/
'ወለደነ ዳግመ'/፪/ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ/፪/
እስመ ለዓለም
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ፤ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፤ ወወጺኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ፤ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።
አመላለስ፦
መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤
ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።(4)
ወረብ
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ/፪/
ከመ ያጥምቆ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ/፪/
ዕዝል
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል፤ ቃለ እግዚአብሔር፤ ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ፤ ወተገሠ በሥጋ፤ መንፈስ ዘኢይትገሠሥ ወዘኢይትለከፍ፤ ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ፤ ወረደ ዲበ ምድር፤ ወአንሶሰወ ውስተ ዓለም፤ በበህቅ ልህቀ በ፴ ክረምት፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ።
@EOTCW
@EOTCW
ምልጣን
ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ።
አመላለስ
ወገብረ መንጦላዕተ/፪/
ሥጋ ሰብእ መዋቲ/፪/
አቡን
በ፭: እስመ ሰምዓ ይቀውም ሎቱ አብ ናዛዚ በርእየተ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል፤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ ዘኪያሁ ሠምርኩ ይቤ፤ ወበይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ መድኅን እምቅድስት ድንግል፤ ኪያሃ ሠምረ አብ በሥጋ ምጽአቶ።
ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።
ምልጣን
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።
ወረብ
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/
ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር/፪/
👇👇👇👇👇
👉@EOTCW 👈
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
👆👆👆👆👆
@EOTCW
#Join & share
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የበአለ ጥምቀት ዋዜማ
በ፩-ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን ወተስፋ ቅቡፃን፤ክርስቶስ አስተርአየ ውስተ ዓለም፤እምድንግል ተወልደ ክሡተ ኮነ፤እንዘ ይትኤዝዝ ለአዝማዲሁ፤ ከዊኖ ሰብእ፣ በዮርዳኖስ ተጠምቀ
ምልጣን፦
እምድንግል ተወልደ ክሡተ ኮነ፤እንዘ ይትኤዝዝ ለአዝማዲሁ፤ ከዊኖ ሰብእ፣ በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤ ከዊኖ ሰብእ፣ በዮርዳኖስ ተጠምቀ
አመላለስ፦
ከዊኖ ሰብእ በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤
ከዊኖ ሰብእ፣ በዮርዳኖስ ተጠምቀ
@EOTCW
ሰላም በ፬-
በሰላም አስተርአየ ወልደ አምላክ ፍጹም ወተወልደ በሀገረ ዳዊት በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይቤዝወነ ወልደ አምላክ ፍጹም አስተርአየ
አመላለስ፦
በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይቤዝወነ፤
ወልደ አምላክ ፍጹም አስተርአየ
ሰላም (ታቦት ሊወጣ ሲል)፦
ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት በፍስሐ ወበሰላም
ምልጣን፦
በፍስሐ ወበሰላምወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት
አመላለስ፦
በፍስሐ በፍስሐ ወበሰላም፤
ወልድ ወልድ ወረደ
መልካም አገልግሎት!
@EOTCW
#Join & share
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ስርአተ ማህሌት ዘበዓለ ግዝረት
መልከአ ስላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ለብሰ አባለ ዘይትዓፀፍ ነበልባለ በማህጸነ ድንግል ናሁ ተስእለ ዘወሀቦ ለሙሴ አሥረ ቃለ፤ተወልደ እምድንግል ዘአልቦ መምሰለ
ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ፦
ክቡራት ዕንቁ መሠረታ፤ብእሲ ተወልደ በውስቴታ፤ይሰግዱ ሎቱ ኩሎሙ ነገስተ ምድር አምኃሁኒ ወርቀ ከርቤ ወስኂን፤ወነዋ ተወልደ መድኀኔዓለም ፍስሐ ኩሎ ዘየአምን
ነግስ፦
ሰላም ለልደቱ እምቅድመ አለም ዘአብ፤ወዮም ልደቱ እምድንግል ጠባብ፤እሳተ ነዳዴ በጎል ስኩብ ፤ብሁተ ልደት ይቤሎ መክብብ፤ወልድ ማእመር ጠቢብ ሰሎሞን
ዚቅ፦
ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ በጎል ሰከበ ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ በከርሥ ተፀውረ፤ እሳተ መለኮት ውስተ ማህጸነ ድንግል ኃደረ፤ ሀሊብ ጠበወ፤ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ አምኃሆሙ ወርቀ ወለዱ፤ረኪቦሙ ህጻነ ለዘተወልደ ለነ፤ በሰላሳ ክረምት፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ በበህቅ ልህቀ
መልክአ ኢየሱስ፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤ አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።
ዚቅ፦
አብርሃምኒ ገብረ ትምህርተ ግዝረት፤ለተነበዮ ቅድመ እግዚአብሔር፤ ወኢያሱኒ በኀበ ደቂቀ እስራኤል፤ወአመ ሰሙን ዕለት ወሰድዎ ከመ ይግዝርዎ፤ ወሰመይዎ ስሞ አማኑኤል
መልክአ ኢየሱስ፦
ሰላም ለአዕዳዊከ ጽቡረ እለ ገብራ፤በምራቀ አፉከ ቅዱስ አዕይንተ ዕውር ይፍጥራ፤ትምህርተ ኅቡአት ክርስቶም ዘትትነገር እምጵስፎራ፤ነገስታት በእንቲአከ ይገድፉ ጌራ፤ወዕጠቆሙ ይፈትሑ ሐራ
ዚቅ፦
ነገስተ ተርሴስ ወደለያት አምኃ ያበውዑ፤ነገስተ ሳባ ወአረብ ጋዳ ያመጽኡ፤ወይሰግዱ ሎቱ ኩሎሙ ነገስተ ምድር
መልክአ ኢየሱስ፦
ሰላም ለአጽፋረ እዴከ ዘኅበሪሆን ፀዓዳ፤ በምገባር ወግእዝ እለ ይትዋሐዳ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስፍና አባሉ ለይሁዳ፤ ለመንግሥትከ ሰፋኒት እንዘ ይትመሐለሉ ዓውዳ፤ ሰብአ ሰገል አወፈዩ ጋዳ።
ዚቅ፦
ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ፤ አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤ ሰብአ ሰገል አምጽኡ ሎቱ ጋዳ፤ ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ።
መልክአ ኢየሱስ፦
ሰላም ለልብከ ቅሩበ ኩልያት ምንታዌ፤እንተ ያንሰሐስሕ ቦቱ መንፈሰ ኅሊናከ አበ ኅላዌ፤ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹመ መለኮት ወሥጋዌ፤ በቀለ በእንቲአከ አመ ትትፋታሕ ነነዌ፤ ውስተ መቅደስከ ረስየኒ ሰርዌ።
ዚቅ፦
ሰብአ ኮነ ከማነ አኮ ኃዲጎ እግዚአብሔር ከዊኖ መጽአ ይቤዝወነ እምኩሉ አበሳነ
መልክአ ኢየሱስ
እምኲሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ፤ ወበወላዲትከ ተማኅፅኖ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እምቤተ መንግሥት ወተክህኖ፤ ተሰብኦትከ እመቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ፤ ያንኮርኲር ታሕት ደይን ግዱፈ ከዊኖ
ዚቅ፦
ተወልደ መድህን ክብረ ቅዱሳን ክርስቶስ ዘይስዕሎሙ ለህጻናት በውስተ ማህጸን፤ ክብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ዓቢይ ወክብር ዲበ ርእሱ
ማኅሌተ ጽጌ
ኦ ዝ መንክር በዘዚአኪ አምሳል፤ ኮከበ ትንቢት ዘቦቱ መልክአ ሕፃን ሥዑል፤ ሠረቀ ያርኢ ተአምረኪ ድንግል፤ ወመርሖሙ ለሰብአ ሰገል እምርሑቅ ደወል፤ ጽጌኪ ኀበ ሀሎ ይሰክብ በጎል።
ዚቅ
ወኖሎት በቤተ ልሔም፤ አንከሩ እምዘርእዩ ወሰምዑ፤ ሰብአ ሰገል ርእዮሙ ኮከበ፤ መጽኡ እምርኁቅ ብሔር፤ ከመ ይስግዱ ለወልድኪ ወይግነዩ ለኪ።
ምልጣን፦
ተወልደ እምድንግል ሰበከ ውስተ ጎል እሙነ ኮነ ልደተ ለክብረ ቅዱሳን ወለቤዛ ብዙሃን አብ ፈንዎ ለበኩሩ ውስተ አለም
እስመ ለአለም፦
አብርሃምኒ ተገዝረ እንዘ ፻ ክረምቱ ፤እስመ ገነየ ለሥርዓቱ አመ ተገዝረ ወልደ በሕገ ኦሪት ዘልማድ አእመራ ዮሴፍ ከመ እሙ፤ ኃይል ወጽንዕ ለዘመጽአ እምአርያም
1 161
#.... አመ ፬ ለጥር ወበዛቲ ዕለት ኮነ ተዝካረ ፍልሰቱ ለቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ....
እንደእውነቱ ከሆነ ስለዚህ ቅዱስ ሐዋርያ ክብር እና ቅድስና ኦ ዝ መንክር ወዕፁብ ከማለት ወጪ ምን እላለው ክብሩ እንደእኔ ባለ ኃጢያተኛ አንደበት ሊጠራ አይችልምና
"ተዘከሩኒ ኦ አኃውየ በጸሎትክሙ ቅድስት'' ብዬ ለመፃፍ እሞክራለው እናንተም ደግሞ "እግዚአብሔር ይስማዕከ ኩሎ ጸሎትከ" እንድትሉኝ አደራ ለማለት እወዳለው።
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሰረት የቅዱሳን ሐዋርያት ፣ ጻድቃን ፣ ሰማዕታት በዓለ ልደታቸውን እና በዓለ ዕረፍታቸውን አልያስ ተአምር ያደረጉበትን አንዳንዴም በዓለ ፅንሰታቸውን በማክበር ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣቸውን ቃል ኪዳን ድልድይ በመሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ምዕመናን ታስተላልፋለች። በእንዲህ መልኩ ከሚከበሩ በዓላት መካከል ደግሞ አንዱ ጥር ፬ ቀን የሚከበረው የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ሥዋሬ ነው።
#ይህ ቅዱስ ከ ፲፪ ሐዋርያት በእድሜ ትንሹ ሲሆን በክብር እና ጌታውን በመውደድ እና በጌታው በመወደድ ግን ከሁሉ የላቀ ነው።
ይህ ቅዱስ ሐዋርያ በጌታችን ዘንድ የመወደድን ሞገስን ያገኘ ታላቅ ሐዋርያ ነው። ጌታችን በታቦር ተራራ ምስጢረ መለኮቱን በገለፀ ጊዜ ይዟቸው ወደ ተራራ ካወጣቸው #ከ ፫ቱ የምስጢር ሐዋርያት ከሚባሉት ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ነው።
ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ከሰማንያ አሐዱ መፃህፍት ውስጥ ፭ቱን እና ከአዋልድ መጻሕፍት ደግሞ እንደ ነገረ ማርያም ፣ ራዕየ ማርያም ...ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን መጻሕፍት አበርክቷል።
ለዚህ ቅዱስ ሐዋርያ በጣም ብዙ መጠሪያ ስሞች ያሉት ሲሆን ከብዙው ጥቂቱን ለማየት እንሞክራለን
#፩ ወልደ ዘብድዮስ
ዘብድዮስ የሥጋ ወላጅ አባቱ ሲሆን
የዘብድዮስ ልጅ እየተባለ ይጠራል
#፪ ነባቤ መለኮት
ከሌሎቹ ወንጌላውያን እና ሐዋርያት
መካከል ስለ ነገረ መለኮት አምልቶ
አስፍቶ በመፃፉ በማስተማሩ ነባቤ
መለኮት እየተባለ ይጠራል።
#፫ አቡቀለምሲስ
ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይ ወደፊት
የሚሆነውን ነገር በራዕይ ስለተገለፀ
ለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብ
ሎ ይጠራል ትርጓሜውም የራዕይ አባ
ት ማለት ነው
#፬ ወንጌላዊ
ከ፬ቱ ወንጌላት አንዱን በስሙ የተሰየ
መውን ወንጌለ ዮሐንስ በመፃፉ ወንጌላዊ ይባላል።
#፭ ታዖሎጎስ
ምስጢረ ሥላሴን እና ምስጢረ ሥጋዌን
አምልቶ አስፍቶ በመፃፉ የመለኮትን ነገር የሚናገር እየተባለ ይጠራል።
#፮ ንስር
ንስር በሰማይ እየበረረ በምድር ያለውን ነገር ጠንቅቆ ፤ አጣርቶ ይመለከታል ዮሐንስም ሌሎቹ ሐዋርያት ያላዩትን ያልዳሰሱትን የመለኮትን ነገር አራቆ አምልቶ ፅፏልና ንስር ይባላል።
#፯ ድንግል
በድንግልናው ፍፁም በመሆኑ በዚህ ስም ይጠራል ልክ እንደ ድንግል ማርያም እንደሚባለው ሁሉ በተግባሩ አልያም የሰራው ስራ ቅፅል ሆኖ ተጠቅሶለታል ለምሳሌ፦ ዮሐንስ ሐፂር ፣ አባ ኤውስጣጤዎስ ከፋሌ ባህር እየተባሉ በስራቸው በተግባራቸው እንደሚጠሩት ሁሉ።
ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፈ ሰዐታት
# ዮሐንስ ድንግል በአምሳለ ትጉኀን መላዕክት
ዮሐንስ ድንግል እንደ ተጉ መላዕክት....
# ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን
ዮሐንስ ድንግል የቅዱሳን መመኪያ
# ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን
ዮሐንስ የቤተ ክርስቲያን በገና
# ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን ይስዐል ለነ ስርየተ ለኃጥዐን
በኤፌሶን አዋጅ የሚናገር ዮሐንስ ኃጥዐን ለምንሆን ለኛ ይቅርታን ለምንልን ። ብሎ በመጽሐፈ ሰዐታቱ ያመሰግነዋል
# ከመ ዝ ኮነ ነገረ ፍልሰቱ ለቅዱስ ዮሐንስ ........
ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎ አድርጎ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ በኃላ በመጨረሻም ደቀመዝሙሩን ቅዱስ አብሮኮሮስን ( ቁጥሩ ከ ሰባ ሁለቱ አርድዕት) እና ሌሎች ሁለት ደቀ መዝሙሮችን መርጦ ይከተሉት ዘንድ አዘዘ። ከዚህም በኃላ ጉድጓድንም ይቆፍሩ ዘንድ አዘዘ። ከዚያም ወርዶ መጎናፀፊያውን እና ጫማውን ከራሱ ላይ አስወግደ ከበፍታ ቀሚስም በቀር እላዩ ላይ አልነበረም ነበር።
ደቀመዛሙርቱንም # በሀይማኖታቹ ፅኑ እኔ ከሁላቹህ ደም ንፁህ ነኝ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ እና ሕግ ሳልነግራቹ የቀረሁት ምንም ምን የለም እናንተም ከእንግዲህ ፊቴን ከቶ አታዩም አላቸው።
እነሱም እጁን እና እግሩን ስመውት ሄዱ ሲመለሱም ከልብሱ እና ከጫማው በቀር ምንም ምን አላገኙም ።
ቅዱስ ዮሐንስም እንደ ሄኖክ እና እዝራ እንደ ኤልያስም ሞትን ሳይቀምስ በዘጠና ዓመቱ ተሰውሯል።
ከቅድስናው ፦ ቅድስናን
ከንስርነቱ ፦ አርቆ ማስተዋልን
ከንጹሕናው ፦ ንጽሐ ሥጋ ወነፍስን
ከቃለ ወንጌሉ ፦ ትርጓሜ ወንጌል በተግባር ከመፈፀሙ ጋር አምላከ ዮሐንስ ከቅዱስ ዮሐንስ ያሳትፈን። አሜን ወአሜን
ጥር ፬ .....
1 161
❤ በሆሣዕና ዕለት ወደ አበ ምኔቱ ሒዶ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ፈቃድ ለመነው ፈቀደለትም በማግሥቱም ፊታቸው የሚያበራ ሦስት ሰዎች ሲጠብቁት አብሮዋቸው ሔደ። ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ የአባ ዘካርያስን ቤት ሊጐበኝ ሔደ ሦስት ታላላቅ ዘንዶዎች በምድር ላይ ሲርመሰመሱ አግኝቶ በአያቸው ጊዜ ፈራቸው እነርሱም በስሙ ጠሩት ወደነርሱም ዘወር ሲል "አባት ሆይ ሲመግበን የነበረው ጌታችን ዘካርያስ ከዚህ ወደየት ሔደ" ብለው በሰው አንደበት ተናገሩት። አበ ምኔቱም ሰምቶ አደነቀ መብልንም ሰጣቸው። አባ ዘካርያስም ወደ መኖሪያው ተመልሶ በብዙ ተጋድሎ ኖረ። ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዘካርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ30 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሐንስ ዘአኅረመ ሕይወቶ። እምነጽሮ አንስት ዘያስሕቶ። ይቤላ በሕልም በእንተ ጽሕቀት ርእዮቶ። ትርአዪ ዘተመነይኪ ገጽየ ከንቶ። ሚ ሊተ ወለኪ ብእሲቶ"። ትርጉም፦ የሚያስተው ለኾነ ሴቶችን ከማየት ሕይወቱን የከለከለ ለኾነ ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባል፤ ፊቱን ለማየት ለወደደች ሴት በሕልም ተገልጦ ከንቱ ፊቴን ታዪ ዘንድ የተመኘሽ ለኔ ምን ጥቅም አለኝ! ሴትዮ ላንቺስ!። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ30።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 3፥15-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥12-21 እና የሐዋ ሥራ 19፥8-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ2፥1-13። ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃን ልደቱ በዓል ሰሞን። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@Eotcw @Eotcw @Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ታኅሣሥ ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት ለተመሰገኑ አባት አርባ ዓመት ሙሉ የሴቶች ፊት ሳያይ ለኖረ ለአቡነ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ለሆነ ለከበረ አባት ለአቡነ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመኰንኑ ከአርያኖስ የጥፍሮቹ ታላላቆች ለቅዱሳን ለኮርዮንና ፊልሞና ከእናርሳቸው ጋር ካሉ ከአርባ ወታደሮች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋድይ ለሆነ ለአባ ዘካርያስ ዕረፍትና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ኄሮድስ ከገደላቸው ከከበሩና ከነጹ ሕፃናት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለዮሐንስ መነኰስ ንጹሕ ዘገጹ ብሩህ ቃለ አፉሁ ለዘ ይሰምዖ ረባሕ ዘፈጸመ ገድሎ በብዙኅ ትጋህ"። ትርጉም፦ ገድሉን በብዙ ትጋት የፈጸመ የአንደበቱ ትምህርትም ለሚሰማው ጠቃሚ የኾነ ፊቱ የሚያበራ፤ ንጹሕ መነኰሴ ለኾነ ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ አባ ዮሐንስ፦ ይህም ተጋዳይ የምንኵስና ልብስን ከለበሰ ጀምሮ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው ዜናውም በአገሩ ሁሉ ተሰማ። ይህም አባ ዮሐንስ ሁል ጊዜ የሚጐበኘው አንድ መኰንን ነበረ የመኰንኑም ሚስት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ እንዲወስዳት ባሏን ታምለውና ታስገድደው ነበር እርሱም "የከበረ አባ ዮሐንስ ከአርባ ዓመት ጀምሮ የሴቶችን ፊት አላየም" አላት። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሒዶ ሚስቱ ያለችውን ለአባ ዮሐንስ ነገረው አባ ዮሐንስም "በእግዚአብሔር ፈቃድ የፈለገችውን እፈጽምለሠታለሁ" አለው።
❤ በዚያችም ሌሊት የከበረ ዮሐንስ ለዚያች ሴት በሕልም ተገልጾ እንዲህ አላት "ጻድቅ ያልሆንኩ ወይም ነቢይ የኔን ፊት ታዪ ዘንድ የምትሺ አንቺ ሴት ከእኔ ምን አለሽ እኔስ ካንቺ ምን አለኝ እንግዲህስ ፊቴን ማየት አትሺ" ይህንንም ብሎ በላይዋ ጸልዮ ባረካት። በማግሥቱም የከበረ አባ ዮሐንስ በመንፈስ እንደታያት ለባሏ ነገረችው። መልኩንና አምሳያውን አመለከተችው ከዚያም በኋላ ከብዙ ሙገሳና ምስጋና ጋር ባሏን ወደ አባ ዮሐንስ ላከችው።
❤ የከበረ ዮሐንስም ባሏን በአየው ጊዜ ፈገግ ብሎ "የሚስትህ ምኞቷ የተፈጸመላት አይደለምን በዚች ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ አግኝታኛለችና" አለው መኰንኑም ሰምቶ ከትሩፋቱና ከደግነቱ የተነሣ እጅግ አደነቀ። ይህም አባ ዮሐንስ ጭንቅ በሆነ ተጋድሎ ዘጠና ዓመት ያህል ኖረ ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
1
❤ የአስቄጥ ገዳም አበ ምኔት አባ ዮሐንስ፦ ይህም አባት በተሾም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በራች ለብዙ ቅዱሳንም አባት ሆነ ከእርሳቸው ውስጥ ታላላቅ ከዋክብት የሆኑ አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም የአገረ ተሙዝ ኤጲስቆጶስ አባ ሚናስ የአገረ ስሐ አባ ዘካርያስ ለብዙ ሰዎች ነፍሳት ወደብ የሆኑ እነርሱን የመሰሉ ሌሎች ብዙዎች አሉ። ለሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን በሚያቈርብ ጊዜ ኃጢአተኞውና ጻድቁ ይገለጥለታና ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንም በመሠዊያው ላይ ብዙ ጊዜ አየው።
❤ በአንዲትም ዕለት ሥራው የከፋ አንዱን ቄስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጠሠ አየው ከእርሱም ጋር ያሉ ብዙዎች ርኩሳን የረቀቁ አጋንንት ከበውት አፉ ውስጥ ልጓም አድርገዋል ወደ ቤተ ክርስቲያንም ከመግባቱ በፊት የእግዚአብሔር መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ በእሳት ሰይፍ ከእርሱ ከቄሱ መናፍስትን አሳደዳቸው ቄሱም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ መቀደሻውን የክህነት ልብስ ለበሰ ሁለመናውም እንደ እሳት ሆነ ቀድሶም ለሕዝቡ ሥጋውና ደሙን አቀበላቸው። ልብሰ ተክህኖውንና የመቀደሻውን ሽልማት ከላዩ አውልቆ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜ እነዚያ የጠቆሩ መናፍስት ርኩሳን ተቀብለው እንደቀድሞው አደረጉበት። አባ ዮሐንስም ይህን ነገር ለመነኰሳቱ ሲያስረዳ እንዲህ አላቸው "በቅዳሴ አገልግሎት ጊዜ ለኃጢአተኛውና ለጻድቁ ቄስ ልዩነት የለም ስለ ሕዝቡ እምነት ያ ኅብስት ተለውጦ የክርስቲያን ሥጋ ይሆናልና ወይኑም የከበረ ደሙን ይሆናልና"።
❤ ዳግመኛም በምሳሌ እንዲህ አላቸው "በብረት በወርቅና በብር ላይ እንደሚቀረጽ እንደ ንጉሥ ማኅተም ነው። ማኅተሙም አይለወጥም እንዲሁ ከካህናትም የክህነት ጸጋ አይለወጥም እርሱ እግዚአብሔር በጊዜው ጊዜ ለሁሉም ለየአንዳዱ እንደሠራው ይከፍለዋል እንጂ"። ይህንም የከበረ ዮሐንስ ታላቅ መከራ ደርሶበታል አረማውያን በርበር ማርከው ወደ አገራቸው ወስደውታልና እያሠቃዩትም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመን ታሥሮ ኖረ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ገዳሙ መለሰው።
❤ ከመሞቱ በፊት የሚሞትበት ጊዜ አውቆ መነኰሳቱን ሰበሰባቸውና የወንጌልን ትዕዛዝ ይጠብቁ ዘንድ በሰማያዊ መንግሥት በጎ ዕድልን ርስትንም ከእርሳቸው ጋር ይቀበሉ ዘንድ እንደ ቅዱሳን አባቶች አካሄድ እንዲጓዙ አዘዛቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ ነፍሱን ሊቀበሉ የቅዱሳንን አንድነት ሲመጡ አያቸውና ፈጽሞ ደስ አለው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መነኰሳቱ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወስደው በመዘመርና በታላቅ ምስጋና ገንዘው ቀበሩት እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ከተገነዘበት ልብስ ቆርጠው በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ለሚታመም ሁሉ የሚፈውስ ሆነ የዚህም አባት ዕድሜ ዘጠና ዓመት ሆነ በግቢግ የሚልዋት መኖሪያው እስከ ዛሬ አለች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱሳን ሰማዕታት ኮርዮንና ፊልሞና አርባ ወታደሮች፦ የሰማዕትነታቸውም ምክንያት የአክሚም ታላላቆች ከሆኑ ከሰማዕታት ዲዮስቆሮስ፣ ከሰከላብዮስና ከብኑድያስ የተደረገውን ተአምራት በአዩ ጊዜ የወታደርነት የማዕርግ ሽልማታቸውን ጣሉ በመኰንኑ አርያኖስም ፊት ቁመው "እኛ በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ የምናምን በግልጥ ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ። መኰንኑም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጥሏቸው ዘንድ አዘዘ ራሳቸውንም ሲወረውሩ ብዙዎች አዩአቸው ገድላቸውንም እንዲህ ፈጸሙ።
+ + +
❤ ተጋዳይ አባት ቅዱስ ዘካርያስ፦ ይንም ቅዱስ ከመመንኰሱ በፊት በጐዳና ሲጓዝ አረማውያን በርበር ተነሡበትና ያዙት ሊያርዱትም ወደዱ በእግዚአብሔርም ፍቃድ የገዳሙ አለቃ በዚያች ጐዳና ሲያልፍ በላያቸው ጮኸ እነርሱም ሠራዊት እንደደረሰባቸው ተጠራጠሩ ፈርተውም ሸሹ ሲሸሹም ከባሕር ገብተው ሰጠሙ። ቅዱስ ዘካርያስም ከመገደል በዳነ ጊዜ ይሸጥ ዘንድ ገንዘባቸውን ይዞ ወደ ከተማ ገባ የአገሩም ገዥ ያዘው ሌባ እንደ ሆነ አስቦ ሊገለው ወደደ ግን ሥራውን በአወቀ ጊዜ ተወው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኲሚስ ገዳም ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ ሰይጣንም እስከ ቀናበት ድረስ በጾምና በጸሎት ተጠመደ ከዚህም በኋላ በአባቱ ተመስሎ በሕልም ታየውና "መሞቻዬ ጊዜ ደርሷልና ትቀብረኝ ዘንድ ና" አለው ቅዱሱም እውነት እንደሆነ አስቦ ወደ አባቱ ሔደ ግን በጤንነት አገኘው። የሰይጣን ተንኰልም እንደሆነ አውቆ ወደ መኖሪያው ተመለሰ ሰይጣንንም ድል እስአደረገው ድረስ በሩን ዘግቶ እየተጋደለ ኖረ።
1 161
❤ ቅዱስ ላሊበላ ሥራውን ከዚህች ቦታ እንደሚጀምርና መጀመርያ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን እንደሚሰራ አወቀ በዚህም መሰረት በመጀመርያ ደረጃ ቤተ ማርያም ሠራ። ከዚያም
ቤተ መድኃኔዓለም፣ ቤተ መስቀልን፣ ቤተ ደናግል፣ ቤተ ጊዮርጊስ፣ቤተ ገብርኤል ወቤተ ሚካኤል፣ ቤተ መርቆሬዎስ፣ ቤተ አማኑኤል፣ ቤተ አባ ሊባኖስ። እነዚህን ቤተ መቅደሶች መንፈስ ቅዱስ ጥበብን ገልፆታልና ግድግዳውን፣ ጣራውን፣ በሩንና መስኮቱን፣ አእማዱን ቅኔ ማህሌቱን ልዩ ልዩ ቅርፅ እያመጣ እያስጌጠና እያሳመረ ከመላዕክት ጋር አመቤታችን እየተራዳችው በ23 ዓመት በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ እነዚህን አስደናቂ ቤተ መቅደሶች ሰርቶ አጠናቀቀ።
❤ ቅዱስ ላሊበላ የአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ በውጭም አገር ብዙ እንደሆኑ ታሪኩ ይገልጻል። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን እንደ ምሳሌ ብንመለከታቸው፦ አዲዲ ማርያም፣ አሸተ ማርያም ጀምሮ ነበር፣ ሶማርያ መቅደስ ማርያምን (መቃዲሾ ውስጥ) ብዙ የተጀመሩና ተሰብስበው አገልግሎት የሚሰጡ በኢትዮጵያ ብቻ 23 እንደሚደርሱ ታሪክ ያወሳል።
❤ ቅዱስ ላሊበላ መዋዕለ ዘመኑን በሰላም፣ በፅኑ፣ በእምነት፣ በፍቅርና በአንድነት ከአሳለፈ በኋላ ንግስናውን ለወንድሙ ልጅ እንዲሁም ለአሳደገውና በረከቱን ለሰጠው ለቅዱስ ነአኵቶ ለአብ አስረክቦ በጾም በፀሎት ተወስኖ ኖረ። ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሃን ሠረገላ ተቀምጦ የሚአስፈራ መብረቅን ተጐናጸፎ አእላፋት ሠራዊቶቹ ዙሪያውን ሁነው ወደርሱ መጥቶ እንዲህ አለው "ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ይሁንልህ እኔ በማይታበል ቃሌ እነግርሃለሁ ማደሪያህ ክብርር ሁሉ ከከበሩ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያቶቼ ጋራ ይሁን። በጸሎትህና በቃልኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ቅዱሳን ጴጥሮስኔ ጳውሎስ ደም መፍሰስ ይሆንለታል።
ወደ ቤተ መቅደስህም የሔደ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደሴ እንደ ሔደ ይሆንለታል መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደ ተሳለመ ይሆንለታል በዓመታቱ ወሮች ሁሉ የተራቡትን እያጠገበ፣ የተጠሙትንም እያጠጣ መታሰቢያህን የሚያደርግ እኔ የተሠወረ መና እመግበዋለሁ የሕይወት ጽዋንም አጠጣዋለሁ። በመታሰቢያህ ቀንም ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋለሁ፤ በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህንና የቃል ኪዳንህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ፣ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይሁን የማይታበይ ቃል የተናገርኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" አለው።
❤ ቅዱስ ላሊበላም ይህን ቃል ኪዳን ስለ አጸናለት ክብር ይግባውና ጌታችንን እያመሰገነ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደ። ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቶት በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ። ከዚህም በኋላ ጥቂት ሕማም ታሞ ሰኔ12 ቀን በ1197ዓ.ም በ96 ዓመቱ በሰላም ዐረፈ። ሲያርፍም ደገኛው ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር ነገራተ እግዚአብሔርን እየተነጋገሩ እንዳለ ድንገት እንደ እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት እንደሆነ ታሪኩ ይገልፃል። ነፍሱንም የብርሃን መላእክት ተቀብለው የዘላለም ሕይወት ማደሪያ ወደሆነ ማረፊያው አስገቡት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ላሊበላ በጸሎቱ ይማረን!። በጸሎቱም እግዚአብሔር አምላክ ይማረን ምንጭ፦ የሰኔ12 ስንክሳርና ቅዱሳንና ድንቅ ሥራቸው የአራቱ ቅዱሳን ነገሥታት ታሪክ ከሚለው መጽሐፍ።
@Eotcw @Eotcw @Eotcw
1 161
ከባድ ሀዘንም ተሰማው። አምላኬን በድያለሁ የማይገባ ሥራ ሰርቻለሁ "ብሎ ቅዱስ ላሊበላ በሕዝቡ መካከል "ከዛሬ ጀምሮ መንግሥት ለአንተ ይገባል በግፍ አስገርፌሀለሁ በድዬሀለሁም ይቅር በለኝ" በማለት ከጫማው ወድቆ ይቅርታ ከጠየቀው በኋላ መንግሥቱን አስረክቦ መንኖ ለመሔድ ወሰነ። የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበት ቅዱስ ላሊበላም "ለይቅር ይቅር ብብያሁ ነገር ግነ መንግሥት የእግዚአብሔር ገንዘብ ናትና መንግሥትህን የምቀበለው ከእግዚአብሔር እንጂ ከአንተ አይደለም አንተም በዙፋንህ መቆየት አለብህ እኔ ግን መልካም ፈቃድ ከአምላኬ እስካገኝ ድረስ እጠይቃለሁ" ብሎ የዐፄ ገብረ ማርያም ጫማ ስሞ በፍቅር ተሰናብቶ ወጣ። በዚህ ጊዜ ሕዝቡና "መንግሥትን ያህል ነገር እንደ ቀላል ነገር ቆጥሮ አልነግሥም ብሎ በመሄዱ እንዴት የእግዚአብሔር መንፈስ ቢያድርበት ነው?" በማለት በችሎት ተቀምጦ ሁኔታውን በግብር ሲከታተል የነበረው ሁሉ እያለቀሰ ቅዱስ ላሊበላን ተከትሎ ወጣ። ቅዱስ ላሊበላ ግን በአላማው ፀንቶ በሰዎቹ ፍቅር ሳይታለል እግዚአብሔር የሰጠውን ረዳቱን ቅድስት መስቀል ክብራን ይዞ ወደ አክሱም ሄደ።
❤ በአክሱም አካባቢ በአባ ጰንጠሌዎን ገዳም በጾምና በጸሎት ተወስነው ፈጣሪያቸውን እየተማፀኑ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መጥቶ "ሰማያዊ ኢየሩሳሌምን እንዳየህ ምድራዊት ኢየሩሳሌምንም አይቶ ህንፃ ቤተ መቅደሱን በሰማያዊትና በምድራዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ያንፅ ዘንድ ኢየሩሳሌም ሔዶ የተወለደበት ቤተልሔም፣ የተጠመቀበትን ዮርዳኖስ፣ የተሰቀለበትን ቀራንዮ፣ የተቀበረበትን ጎልጎታን፣ ደብረ ታቦርን ምስጢረ መለኮቱን የገለጸበትን አጠቃላይ ብዙ ተአምራት ያደረገበትን ሁሉ እንዲያይና እንዲሳለም መልአኩም እንደሚመራው መስቀል ክብራ ግን በዚሁ ከደናግሎች ጋር እንደምትቀመጥና ቅዱስ ሚካኤል እንደሚያጽናናት እንደሚጠብቃት መታዘዙን ነገረው።
❤ በዚህም መሠረት ቅዱስ ላሊበላ ወደ ኢየሩሳሌም በፈቃደ አምላክ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ጠባቂነት በሱዳንና በግብጽ አድርጎ ኢየሩሳሌም ገባ። በዚያም ከላይ የተጠቀሱትን ቅዱሳን መካናትንና ሌሎችንም ቅዱሳት ስፍራዎች ለዐሥራ ሦስት ዓመታት በመዘዋወር ተመለከተ። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ላሊበላ የጉብኝቱንና የተፈቀደለትን ጊዜ ሲፈጸም አሁንም መልአኩ ተገልጾ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ሄደ መንግሥትን ከዐፄ ገብረ ማርያም ተረክቦ የታዘዘውን እንዲሰራና በመንገድ በግብጽ ምድር የተበተኑትን ወገኖችን ወደ ኢትዮጵያ ይዞ እንዲሄድ የታዘዘ መሆኑን ገለጸለት። ቅዱስ ላሊበላም በፈቃደ አምላክ በግብጽ ያሉትን ክርስቲያኖች ሰብስቦ በጊዜው የነበረው የግብጽ መንግሥት የእስላም ሃይማኖት ተከቲይ በመሆኑ እንዴት አድርጎ እንደሚያስተዳድራቸው ጠየቃቸው። ክርስቲያኖቹም እግዚአብሔርን ማምለክ እንደተከለከሉና በሀዘን በሰቀቀን የሚኖሩ መሆናቸውን ገለጹለት። በዚህ ዘመንም በመካከለኛው ምሥራቅ 3ኛው የመስቀል ጦርነት በመኖኑ ግብጻውያን ፊታቸውን ወደዚያ አዙረው ስለነበር ቅዱስ ላሊበላ በፈቃደ አምላክ በርካታ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።
❤ ዐፄ ገብረ ማርያም ወንድሙ ቅዱስ ላሊበላ ሕዝበ ክርስቲያንን ይዞ የኢትዮጵያ ምድር እንደረገጠ በሰማ ጊዜ በክብር የሚቀበሉት ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰራዊት አሰልፎ ወደ ቤተ መንግሥቱ እንዲመጣ ላከበት። ቅዱስ ላሊበላም ከባለቤቱ ጋር እና ከሕዝቡ ጋር በአክሱም ስለነበር የእግዚአብሔር ፍቃድ እንደሆነና ጊዜም እንደደረሰ በማወቁ ልዋል ልደር ሳይል ወደ ቤተ መንግሥቱ መጥተ ከዐፄ ገበረ ማርያም ጋር ተገናኘ። ንጉሡ ዐፄ ገብረ ማርያም ቅዱስ ላሊበላ ወደ እርሱ መምጣቱን በሰማ ጊዜ በፍቅር እንባ ተቀበለውና ሕዝቡን ሰብስቦ አዋጅ ነግሮ "እንሆ የአምላክ ፈቃድ ደርሷል መንግሥት ለዚህ ቅዱስ ሰው ይገባል ብሎ ዙፋኑን ለቅዱስ ላሊበላ አስረክቦ ተሰናብቶ ዛሬ ቅዱስ ሐርቤ እየተባለ ወደሚጠራው ገዳም ዘግቶ በጾም፣ በጸሎት፣ በቀኖናና በንስሐ ሰውነቱን ለፈጣሪው አስገዝቶ በክብር የካቲት16 ቀን ዐርፎአል።
❤ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሥ ነኝ ብሎ ሳመካ ስልጣኑን ለሕዝቡ በመስጠት ሕዝቡን ይመራ ነበር። ሕዝቡም የቅዱስ ላሊበላን የሃይማኖት ጽናትና ደግነት እያየ "ይህን ጻድቅ ንጉሥ ዕድሜውን አርዝምልን" እያሉ ይጸልዩለት ነበር። የቅዱስ ላሊበላን ደግነት በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሕዝቦች ብቻ ሳይሆኑ በውጭም ያሉ ነገሥታትና ሕዝብ ጭምር ያውቁ ነበር በዚህም መሰረት እስላሙም ክርስቲያኑም ቅዱስ ላሊበላን አንስተው አይጠግቡም ነበር። በቅዱስ ላሊበላም ዘመነ መንግሥት ጊዜ ኢትዮጵያ በውጭው ዓለም ያላት ግንኙነት የሰላም፣ የፍቅር፣ የክብርና የደስታ ግንኙነት ነበራት ለዚህም ነበር 1189ዓ.ም አካባቢ ሳላህ አዲን የተባለው የእስላም ንጉሥ በሦስተኛው የመስቀል ጦርነት ኢየሩሳሌምን በያዘ ጊዜ ከክርስቲያን ቅርሶች ዋና ዋናዎቹን በጎልጎታ በሚገኘው በጌታችን መቃብር አጠገብ ያለውን ዕሌኒ ንግሥት ቅዱስ መስቀሉን ያስወጣችበት ዋሻና በቤተልሔም ጌታ የተወለደበትን ጎል (በረት) ለቅዱስ ላሊበላ በስጦታ ያበረከተው።
❤ የቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶች አሰራርና ፍጻሜ፦ ቅዱስ ላሊበላ በዘመኑ ይህን ድንቅ ሥራ የሰራው ጮማ በመቆራረጥ ጠጅ በማማረጥ ልብስ መንግሥትን ለብሶ በመሽሞንሞን አልነበረም። ለአንዲት ደቂቃ መንፈስ እግዚአብሔር ያልተለየው ቅዱስ አባት ነበር። ፈጣሪው የሚመሰገንበትን የእርሱም ስም ለዘላለም የሚጠራበትን ቤተ መቅደስ ለማነፅም ሱባኤ ገብቶ ቦታው የት እንደሆነ ተረዳ። ነገር ግን የተገለጸለት ቦታ ቀይት የምትባል ባላባት ትኖርበት ነበር። ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ሌላ ቦታ ሰጥቶ መጠቀም ይችል ነበር። ግን የትሕትና አባት ነውና መብቷን ሳይነካ እራሱን ዝቅ አድርጐ "ቦታውን ለሥራ ፈልጌዋለሁና በገንዘብ ሽጭልኝ" አላት። እርሷም እጅግ ከፍ ያለ ገንዘብ ጠየቀችው። ይኸውም አርባ ጊደር ላም መግዛት የሚችል ገንዘብ ነበር የጠየቀችው እርሱም ምንም ምን ሳይል ወርቁን ከፈላት። ቀይትም ገንዘቧን ተቀብላ ሔደችና እንደገና ተመልሳ "የምኖርበት ቦታ ስጠኝ" አለችው። እርሱም "ወደፊት ሌላ ቦታ እስክሰጥሽ በዚህ ቆይ" ብሎ ዛሬ ቆይታ የምትባለውን ቦታ ሰጣት ከዚህም የተነሳ ከግዜ ብዛት የቦታው መጠራያ ስም ቆይታ ተባለች። ይህች ቦታ የምትገኘው ከላሊበላ ከተማ በስተ ምሥራቅ በግምት ሁለት ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው። ለዚህ ነበር አባቶቻችን ንጉሥ ላሊበላ በአንጡራ ገንዘቡ የገዛውን ቦታ ስለሆነ በቦታው የሃይማኖት ሸቃጮች የሃይማኖት ሸቀጥ አያካሂዱበትም በማለት ለመስዋዕትነት የተዘጋጁት አሁንም ቢሆን ወደፊትም በዚህ ዙሪያ ላይ መናፍቅ ቦታ እንደሌለው ሊያውቅ ይገባል።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ላሊበላ የህንፃ ሥራውን ለመጀመር ቦታው ጫካ ስለነበር በሰፊው የማጽዳት ዘመቻ ካካሄደ በኋላ የት ቦታ መጀመር እንዳለበትና የማንን ቤተ መቅደስ መጀመሪያ እንደሚሰራ እንደገና በሱባኤ ለፈጣሪው ጥያቄ አቀረበ። በጥያቄው መሠረትም ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ እንዳየው የወርቅ መሰላል ከሰማይ እሰከ ምድር የብርሃን አምድ ተተክሎ ዛሬ ቤተ ማርያም ካለችበት ቦታ አርፎ መላእክት ሲወጡበት ሲወርዱበት ቅዱስ ላሊበላ አየ።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጻድቁ ካህኑ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ
❤ ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ከዐፄ ዛን ስዩም ከእናቱ ከልዕልት ኪሪዮርና በ1101ዓ.ም ታኅሣሥ 29 ቀን በቤተ መንግሥ ተወለደ። ዐፄ ዛን ስዩም ከመንገሡ በፊት የዋግ ሹም ሆኖ ሲያስተዳድር ዑጽፍት ወርቅ የምትባል ሴት አግብቶ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያምና ዮዲት የምትባል ልጅ(ርብቃም) የሚሉ አሉ ከወለደች በኋላ ዑጽፍተ ወርቅ ሞተች። ከዚህ በኋላ የክፍለአገር ገዥ ከሆነው ረዳኢ ከተባለው የተወለደችውን ኪሪዮርናን አግብቶ ቅዱስ ላሊበላን ወለደው። ቅድስት ኪሪዮርና ማለት ቤተ ክረሰስቲያን ማለት ነው።
❤ ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ ጊዜ ነጫጭ ንቦች ሰፍረውበት እንደማር ሲልሱት እናቱ ስታይ በመደንገጥ "ላል ይበላል" በማለት ተናገረች። ይህም በአገውኛ ቋንቋ ልጄን ንብ በላው ማለት ነው። በዚህ መሰረቴ ላልይበላል ተብሎ እየተጠራ እንደሠ ከጊዜ ብዛት ላሊበላ ተብሏል። በነገራችን ላይ የተሳሳተ ትርጉም የያዙ አላዋቂዎች ላሊበላ ማለት ለማኝ እንደሆነ አድርገው በአንዳንድ አካባቢዎች ይናገራሉ። ላሊበላ ማለት ግን ጣፋጭ የንስሃ ጋሻ የጽድቅ አባት ማለት ነው እንጂ ለማኝ ለፍላፊ ማለት አይደለም።
❤ ከዚህም በኋላ እናትና አባቱ ልጃቸው ወደፊት ንጉሥ ሆኖ ብዙ ሰራዊት የሚከተለው ትልቅ ሰውና መንፈሰ እግዚአብሔር ያደረበት መሆኑን በንቦች መክበብ በመረዳታቸው በ40 ቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊትና ካህናት ታጅበው በእልልታና በደስታ ዐፄ ካሌብ በአሰሩዋት ማይ ማርያም በተባለችው ቤተ ክርስቲያን የክርስትናውን ሥነ-ሥርዓት አስፈጽመዋል። የክርስትና ስሙም ገብረ መስቀል ተብሏል። ቅዱስ ላሊበላ በቤተ መንግሥት ውስጥ ለነገሥታት ልጆች እንደሚሰጥ እንክብካቤና ሥነ-ሥርዓት በጥበብና በሞገስ አደገ። ዕድሜውም ለትምህትተ ሲደርስ መምህር ተቀጥሮለት ከፊደል እስከ ዳዊት የሚሰጠውን ትምህርት ያለማዳገም ከፈጣሪ በተሰጠው ፀጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተማረ። በዚህም ላይ እንዳለ የበለጠ ፈጣሪውን ማገልገል በመፈለጉና በመምረጡ ቤተ መንግሥቱን ትቶ ትምህርቱን ለማሻሻል ወደ ምድረ ጎጃም ሄዶ አሉ ከተባሉ መምህራን በተለይም መምህር ኬፋ ከተባሉ ምሁር አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምሮ ወደ ደብረ ሮሃ ተመልሶ ሥርዓተ መንግሥትን ወንድሙ ቅዱስ ገብረ ማርያም እያስተማረው ሳለ ለምቀኝነት የሚያርፈው ሰይጣን በንጉሥ ባለሟሎች(አማካሪዎች) ላይ አድሮ የሁለቱን ፍቅር በጠሰው። ሰዎቹ ወደ ንጉሥ ቀርበው "ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ እነሆ ላሊበላ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን በማግኘቱ አስተባብሮ ንጉሥነትዎን መንግሥቱ ሊቀማዎት ነውና እወቁበት" በማለት ነገሩት። ንጉሡም በነገሩ እጅግ ተቆጥቶ ወደ ማረፊያ ቤቱ ገብቶ እንጀራ አልበላም ውሃም አልጠጣም ብሎም እንደ ንጉሥ ዓክአብ ተጨንቆ ተጠቦ ሳለ እህቱ "ንጉሥ ሆይ ልብህ አይዘን አትጨነቅ ነገሩን ለእኔ ተወው" ብላ አረጋጋችው። ላሊበላ ግን ይህን ሁሉ ነገር አላወቀም ነበርና በንጹህ ልቦናው በቤተ መንግሥቱ እንደ ተቀመጠ ከዕለታት አንድ ቀን ኮሶ ታይቶት መድኃኒት እንድታጠጣው ቂመኛ እህቱን ጠየቃት እሷም የምታጠምድበትንና የምትገድልበትን ስታስብና ስትፈልግ ስለ ነበር ይህን አጋጣሚ በማግኘቷ ሀሳቡን ደስታ ተቀብለችውና ኮሶውን አዘጋጅታ መርዝ ቀላቅላ አቀረበችለት። ከእርሱ ጋራ የሚኖር የማለየው አንድ ዲያቆን ነበር። በባህሉም መሠረት ዲያቆኑ ቀምሶ ስለሚሰጥ ያንን ሲቀምሰው አስታወኮት ሞተ። የዲያቆኑንም ትውኪያ አንድ ውሻ በመላሱ ሞተ። ከዚህም በኋላ ላሊበላ መንፈሱ ታወከ። ከባድ ሀዘንም አደረበት። "እናንተ ንጹሐን ለእኔ በታዘዘው መቅሰፍት በመሞታችሁ እኔም የእናንተን መንገድ እከተላለሁ እንጂ ወደ ኋላችሁ ቀርቼ ነፍስ ገዳይ አልሆንም" አለና በውስጡ ፍቃደ እግዚአብሔር ስላለበት ፈጣሪ ሚስጥር ሊገልጽለት በመፍቀዱ በጽዋው የተረፈውን መርዝ አንስቶ ጠጣው። እርሱም ወዲያው ተዘረረና ወደቀ። በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት መጥተው ነፍሱን ወደ ፈጣሪ ወስዷት። ሥጋው ግን ሙቀት ስላልተለየው ሰዎች ለመቅበር ቢሞክሩ እንደእሳት እየፈጃቸው ሦስት መዓልትና ሌሊት በሚደንቅ ሁኔታ ተቀመጠ።
❤ ቅዱሳን መላእክት ሰባቱን ሰማያት አንድ በአንድ እያሳዩ ወደ ፈጣሪ ነፍሱን ከአቀረቧት በኋላ እግዚአብሔር አምላክ "ወዳጄ ላሊበላ ሆይ የጠራሁህ እኔ ነኝ በማለት ወሰን የሌለውን ፍቅሩን ከገለጸለት በኋላ ሀይሉንና ጥበቡን በእርሱ ላይ አሳድሮ "ከከርሰ ምድር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽና በኢትዮጵያ አገር ላይ አርባ ዓመት እንደሚነግሥ ሕዝበ እግዚአብሔር ድንቅ ሥራውን በመመልከት ድኅነትን፣ በረከትን፣ ፀጋን፣ እንደሚያገኙ በተለይም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ኢየሩሳሌምን ለማየትና ለመሳለም ሲሔዱ የሚደርስባቸው መከራና ሞት ደማቸው ከፊቴ በመጮሁ በእርሱ ሥራ ኢየሩሳሌምን እንደሚያንፅና ለምን እንደሚሰራ ጥቅሙን በመግለጽ ይሰራ ዘንድ መመሪያ ሰጠው። ቅዱስ ላሊበላ ግን ይህን ማድረግ እንማይቻለው ቢገልጽም አምላክ ከእርሱ ጋራ እንደሚሆን ብቻ "ስሙ በአንተ ይሁን እኔ ነኝ የምሰራው" በማለት ገለጸለት። ከላይ እንደተገለጸው በድኑ መንፈስ ቅዱስ ሳይለየው እንደ እሳት ሰዎችን እየፈጃቸው ተጨንቀው ተጠበው በሁኔታው በመገረም ለሦስት ቀንና ሌሊት እንዳሉ በሦስተኛው ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተዋሕዶ ተነሳ።
❤ ቅዱስ ላሊበላም ከሰው ተለይቶ ከዘመድ ርቆ የሰው ድምጽ ከማይደርስበት ቦታ ሄዶ ሌት ከቀን በመጸለይ በጾምና በጾሎት ተወስኖ ከአምላኩ ጋር በበለጠ ግንኙነቱን እያጠናከረ እንዳለ አንድ ቀን ፈጣሪ ቅዱስ ገብርኤልን ላከውና መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ላሊበላን "የእግዚአብሔር አገልጋይ ላሊበላ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን እንሆ እግዚአብሔር አምላክ በኢትዮጵያ ላይ ካህንና ንጉሥ ሆነህ ሰዎችን ለመንግሥተ ሰማያት የምታበቃ ነህና በህገ አብርሃም ትወሰን ዘንድ ወዳንተ መጣሁ ስለሆነም ነገ በአሁኑ ሰዓት የምትመጣ በድንቅ ሥራዋ አምላክን ያስደሰተች አንዳንተ የተመለጠች ቅድስት ሴት ትመጣለችና እርሷን አግብተህ ልጅ ትወልዳለህና በሚያስደስት ቃል ተቀበላት" አለው። ቅዱስ ላሊበላ ግን ፍቃዱ እንዳልሆነ ቢገልጽም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደሆነ በድጋሚ ሲነግረው ቃሉን ተቀበለው። እንደተባለውም በማግስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ እንደ ብርቱካን፣ መዝ፣ የመሳሰሉትን ፍራፍሬዎች ይዛ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ሄደች እርሱም በደስታ ተቀበላት። ከዚያም ነገረ እግዚአብሔርን ተነጋግረው ወደ ቤተሰቦቿ ወሰደችው። ለቤተሰቦቿ መላኩ በህልም ነግሯቸው ስለነበር በደስታ ተቀበሉት። በዚያም በፈቃደ እግዚአብሔር በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጋብቻቸውን ፈጽመው በጾምና በጸሎት ተወስነው በመኖር ላይ ሳሉ ለምቀኝነት የማያርፈው ሰይጣን አሁንም ፈተናውን አዘጋጅቶ ሶስናን በሐሰት ዝሙትን ፈጽማለች ብለው እንደወነጀሏት ሁሉ ቅዱስ ላሊበላንም "ከቤተ መንግሥት ጠግቦ ወጥቶ የሰው እጮኛ ያባልጋል" በማለት ለንጉሡ ሹክተኞች ነገሩት። ንጉሡም ወታደሮችን ልኮ አስመጣውና ቀኑም ዐርብ ቀን በመሆኑ እንዲገረፍ አዝዞ ወደ ቅዳሴ ሄደ። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ወደ ቤቱ ሲሄድ የጅራፍ ጽምጽ በመስማቱ "ምንድነው? የሚሰማው" ብሎ ባለሟሎቹን ሲጠይቃቸው "ቅዱስ ላሊበላ እየተገረፈ ነው" አሉት ንጉሡም ወዲያውኑ እንዲያመጡለት አዘዘ። ሲመለከተውም በሰውነቱ ላይ ምንም የግርፈት ምልክት አላየበትም ንጉሡም ጻጽቅና እውነተኛ መሆኑን ፈጣሪም ከግርፋትና ከጥፍት ከልሎታልና "እንኳን ስ ሊሞት ግርፋቱ አልተሰማውም" በማለት እጅግ አደነቀ።
1 161
❤ ነቢዩ ዳንኤልም አለ "ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቁ እንደ ሰው ልጅ በሰማይ ደመና መጣ ዘመኑን ወደ ሚያስረጅ ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነው።
❤ ዳግመኛም ኢሳይያስ "እግዚአብሔር እንደእኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጸልኝ" አለ። "አሁኑም ደግሞ አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ" አለ ሁለተኛም "ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል" አለ። ዳግመኛም "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው። ስሙም ድንቅ መካር የዘላዓለም አባት የሰላም አለቃ ይባላል" አለ።
❤ ኤርምያስም አለ "እግዚአብሔር እንዲህ አለ ለዳዊት ብርሃንን አወጣለሁ በምድር የቀና ፍርድ ያደርጋል እግዚአብሔር ያመኑበትን ያድናቸዋል"። ኤልሳዕም እንዲህ አለ "እግዚአብሔር ከሰማ ይወርዳል በእስራኤል ልጆች አደባባይም በመመላለስ ለሕዝቡ እውነትን ያስተምራቸዋል ከአብርሃም ልጅነት ልዩ ከሆነች ወገኖቹ በቀር አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል"። ናሆም ነቢይም እንዲህ አለ "እግዚአብሔር በእኔ አርአያ ይመጣል ልብሱም እንደ ልብሴ ነው"።
❤ ነቢዩ ኢዩኤልም እንዲህ ተናገረ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆነች ብላቴና ድንግልን አየሁ እርሷም እንደ እሳት ያልባት ነበር ስለርሷም ይቺ ማናት ብዬ ኪሩብን ጠየቅሁት ከአዳም ልጆች የተመረጠች የእግዚአብሔር ዙፋን ይች ድንግል ናት በርሷም የተጎሳቈሉ ይድናሉ ለአመነባትም ረድኤትና መጠጊያ ናት።
❤ ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ አለ "እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ በተዋሕዶም ወለድኩህ አለኝ። ለምን አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው"። ዳግመኛ "አብ አለ ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ከአንተ ጋር ሳለሁ ከአጥብያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ እንደ መልከጼዴቅ አንተ የዓለም አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ ከማለም አይፀፀትም"።
❤ ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደገኘ በእስራኤል በበርሃ ውስጥ ከኅቱም ዐለት ውኃ እንደ ፈለቀ የደረቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደአፈራች። በሶምሶንም እጅ ወስጥ ከአህያ መንጋጋ ዐጥንት ውኃ እንደፈሰሰ። እንዲሁ የጌታችን ልደት በህቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደነደደች እጺቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁም የመለኮት እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክል ይገባል ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ29 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ነገሥተ ተርሴስ ወደሰያት አምኃ ያበውዑ። ነገሥተ ሳባ ወዓረብ ጋዳ ያመጽኡ። ወይሰግዱ ሎቱ ኵሎሙ ነገሥተ ምድር"። መዝ71፥10-11። የሚነበበው ወንጌል ማቴ1፥1-18።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥4-12፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥16-22። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ2፥1-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልእ ነው። መልካም የብርሃነ ልደቱ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን
@EotcW @Eotcw @Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ታኅሣሥ ፳፱ (29) ቀን።
❤ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታች ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ለተወለደበት የበዓላት ሁሉ ራስ ለሆነች ለብርሃነ ልደቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በእነዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ላሊበላ ከልደት በዓል መታሰብያ፣ ከታላቁ አባት ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከልደታቸ ቀን መታሰቢያ፣ ከኤፍሬም ወገን ከመስፋኑ ከቅዱስ ኢያሱ ልደት፣ ከከበሩ ከያዕቆብ፣ ከፈሊስ ከሌላው ሰማዕት፣ ከቴዎድሮስ ከመታሰቢያቸው፣ ከሮሀ ንጉሥ ከአቃርዮስ ዕረፍት፣ ሰምኑድ ከሚባል አገር ከሆነ ከገመላዊው ከቅዱስ ቆሪል ዕረፍትና ከአክሚም ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ እምቅድስት ድንግል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ"፡፡ ትርጉም፦ ከቅድስት ድንግል ክርስቶስ ስለተወለደ ዛሬ ደስታ ሆነ ለእርሱ ሰብአ ሰገል (የጥበብ፡ሰዎች) ሰገዱለት በእውነት የልደቱ ምስጋና ድንቅ ክቡር ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ፦ "ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው(አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ! ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት! ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡
❤ ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!"።
+ + +
❤ በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ ታላቅ የልደት በዓል ሆነ የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል ማርያም የተወለደባት ዕለት ከበዓላት ሁሉ ተለይታ ከፍ ከፍ ያለች ናት።
❤ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን የከበረ የልደትን በዓል በሁለት ቀኖች ያከብሩ ዘንድ በምክራቸው ተስማሙ ከወደኋላ ባለ በሃያ ስምንት ሌሊቱ የልደት በዓል ነው በሃያ ዘጠኝ መዓልቱ ጳጒሜን ስድስት በሆነ ጊዜ በዚያች ዓመት የልደት በዓል በሃያ ስምንት ከሆነ ግን በሃያ ዘጠኝ ይሆናል ስለዚህ የበዓላት ሁሉ ራስ የሆነ የከበረ የልደት በዓል በሁለት ቀኖች እንዲከበር አዘዙ ወሠኑ።
❤ የበዓላት ራስ ስለሆነ ስለ ከበረ የልደት በዓል የከበረ ወንጌል እንዲህ አለ "በንጉሥ በኄሮድስ ዘመን በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ጌታ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ እነሆ የፍልስፍና ሰዎች ከምሥራቅ መጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ። ኮከብን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ። እሊህ ፈላስፎች ከበለዓም ወገን ናቸው እነርሱም በከዋክብት የሚፈላሰፉ ናቸው በመጽሐፋቸው በበለዓም መጽሐፍም የአይሁድ ንጉሥ ሊወለድ እንዳለው ተጽፎአል እርሱ በለዓም ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤልም ንጉሥ ብሎ ነበርና።
❤ ይቅር ባይ እግዚአብሔር በረቀቀ ጥበቡ አለበማቸው በሚያምኑበትም ሳባቸው እነርሱ ከዋክብትን በመጠባበቅ የሚፈላሰፉ ናቸውና ይህንንም ኮከብ ገለጠላቸው በአዩትም ጊዜ ደስ አላቸው መልኩ በብዙ አይነት ልውጥ ነውና። ሕፃን የታቀፈች ድንግል ብላቴናን ይመስላል እርሱም በቀን ይጓዛል በሌሊትም ይሠወራል ከሰውም ሲገናኙ ይሠወርና ሲቆሙ በሌላ አንጻር ይገለጥላቸዋል።
❤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ያ ኮከብ ተሠወራቸው እጅግ አዘኑ የሚያድረጉትንም አላወቁም ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብተው ስለተወለደው ንጉሥ ጠየቁ። የእሊህም ሰዎች ቊጥራቸው ሠላሳ ሽህ ነው ነገሥታቱ ሦስት ናቸው ለእያንዳንዳንዱ ንጉሥ ዐሥር ዐሥር ሺህ ሠራዊት አለው። ንጉሡ ኄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ ኢየሩሳሌምም በመላዋ ከእርሱ ጋር ደነገጠች። የካህናት አለቆችና የሕዝቡን ጸሐፊዎች ሁሉ ሰብስቦ "ክርስቶስ በየት ይወለዳል?" ብሎ ጠየቃቸው። "በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ነው" አሉት በነቢይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና። "የኤፍራታ ዕፃ ቤተ ልሔም አንቺም ከይሁዳ ነገሥታት አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ካንቺ ይወለዳልና"።
❤ ከዚህም በኋላ ኄሮድስ ሰብአ ሰገልን በጭልታ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከነሱ ተረዳ። "ሔዳችሁ የዚያን ሕፃን ነገር እርግጡን መርምሩ ያገኛችሁትም እንደሆነ እኔም መጥቼ እሰግደለት ዘንድ በኔ በኩል ተመልሳችሁ ንገሩኝ" ብሎ ወደ ቤተልሔም ሰደዳቸው የነገራቸውንም ሰምተው ከንጉሡ ሔዱ እነሆ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ወደ ቤተልሔም እስኪያደርሳቸው ይመራቸው ነበር ሕፃኑ ካለበትም ዋሻ ላይ ደርሶ ቆመ። ኮከቡንም ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር አገኙት ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥናቸውንም ከፍተው ወርቅ ከርቤ ዕጣን እጅ መንሻ አቀረቡለት።
❤ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕፃኑ ጌታ ኢየሱስ በዚያች ዕለት ወደ ቤተልሔም መጡ ስለዚህም ሰብአ ሰገል አገኙአቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ናዝሬት በሌላ ቦታ አላደገምና ከተወለደም ዕድሜው ሁለት ዓመት ሁኖት ነበር። አምላክ ነውና ስለ መንግሥቱ ወርቅን ገበሩለት ክህነትም ገንዘቡ ነውና ዕጣንን ገበሩለት ማሕያዊ ለሆ ሞቱ ምልክትም ከርቤን ገበሩለት። ወደ ኄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ነገራቸው በሌላ መንገድም ወደ አገራቸው ተመልሰው ገቡ። አምላክ በሥጋ ስለመገለጡ ዓዋጅ ነጋሪዎችና ሰባኪዎች ሆኑ።
❤ ይችም ዕለት ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ስለርሷ የተናገረላት ናት እንዲህ ብሎ "እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው"።
ስለዚችም የከበረች ድንግል ነቢይ ሕዝቅኤል እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "እግዚአብሔርም አለኝ ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች አትከፈትም የሚገባበትም የለም የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደተዘጋች ይገባባታልና ተዘግታ ትኑር" አለ።
@eotcw @eotcw
@eotcw @eotcw
1 161
በጌና ጾም #ታኅሣሥ እስራ ወ ፱ቀን
በቅዳሴ ግዜ
#ምንባባት
፩ተሰሎ ም፫፥፩-ፍጻ
፩ጴጥ ፫፥፲-፲፭
ግብ ሐዋ ም፲፬፥፳-ፍጻ
#ምስባክ
መዝ ፵፬፥፲፪
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኲሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
#ትርጉም
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል።
የምድር ባለጠጎች በአሕዛብ ፊትህ ይማለላሉ።
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤
#ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል ም፲፰፥፱-፲፰
#ቅዳሴ
ቅዳሴ ማርያም
@Eotcw @Eotcw @Eotcw
1 161
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ዛሬ ታኅሣሥ ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱስ አማኑኤል ለልደቱ (ለጌና) መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእንዴናው አገር ሰዎች ከሆኑ በሰማዕትነት ካዐረፉ ከመቶ ሃምሳ ወንዶችና ከሃያ አራት ሴቶች፣ ከአባቶቻች ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የታኅሣሥ 28 ዚቅ፦ "በጎለ እንስሳ ተወድየ አምኃ ንግሡ ተወፈየ፤ ወከመ ሕፃናት በከየ፤ እንዘ ይስእል እምአጥባተ እሙ ሲሳየ"። ትርጉም፦ በእስሳት በረት ተጨመረ የንግሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ። የቅዳሴ ዲዮስቆሮስ።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ኢኮነ ነግደ ወፈላሴ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን ንሕነ ሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር ኲልነ አምላክ ኀደረ ውስተ ሥጋ ተዓቁረ እንዘ ኢይትጋባዕ በሙላድ ዘድንግል መናሥግተ እያርኂዎ ዘኪሩቤል ኢርእዩ"። ትርጉም፦ እኛ የእግዚአብሔር የቤቱ ሰው እንግዳና መፃተኛ አልሆንም።፤ የቅዱሳን ሀገር የሆነው አምላክ ክርስቶስ በሥጋ ተወሰነ፤ ኪሩቤል ያላየው ያልመረመረው የእመቤታችን ማኅተመ ድንግልናዋን ሳይከፍት በመወለዱም ከምልአቱ ሳይወሰን ተወለደ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ በዚች ዕለት የጌና በዓል ሆነ። ይኸውም የልደት በዓል ነው”። ይህም እንዲህ ነው በአምላካችን በረቀቀ ጥበቡ ሰዎች ሁሉ ይቈጠሩ ዘንድ ስማቸውንም ይጻፋና ይመዘገቡ ዘንድ ከንጉሥ ቄሣር ትእዛዝ መጣ። ስለዚህም ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል ማርያም ጋር ሊቆጠር ዮሴፍ ከናዝሬት ወደ ቤተልሔም የርሱንና የቡርክት ድንግል ማርያምን ስም ሊስመዘግብ ወጣ እርሱ ከይሁዳ ነገድ ከዳዊት ወገን ነውና ቤተልሔምሜ የዳዊት ቦታው ናትና።
❤ የከበረ ወንጌል እንደተናገረ ከዚህም በኋላ ከዚያ ሳሉ የምትወልድበት ቀን ደረሰ የበኵር ልጇንም ወለደች አውራ ጣቱንም አሠረችው በጨርቅም ጠቅልላ በበረት አስተኛችው ለማደሪያቸውም ቦታ አልነበራቸውምና። በዚያ ሰፈር እረኞች ነበሩ ሌሊትም በየተራቸው ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ነበር። እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ አጠገባቸው ቆመ የእግዚአብሔርም ብርሃን በላያቸው በራ ታላቅ ፍርሀትም ፈሩ መልአኩም "ለእናንተና ለመላው ዓለም ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ" አላቸው።
❤ "እነሆ ዛሬ በዳዊት አገር መድኅን የሆነ ጌታ ክርስቶስ ተወልዶላችኋልና። ለእናንተም ምልክት እንዲህ ነው ሕፃኑ አውራ ጣቱን ታሥሮ በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ" አላቸው። ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም በሰው በጎ ፈቃድ እያለ መጡ።
❤ ከዚህም በኋላ መላእክት ከእነርሱ ዘንድ ባረጉ ጊዜ እነዚህ እረኞች ሰዎች እርስበርሳቸው "ኑ ወደ ቤተ ልሔም ሔደን ይህን እግዚአብሔር የገለጠውንን ነገር እንወቅ" አሉ። ፈጥነውም ሔዱ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በበረት ውስጥ ተኝተ አገኟቸው። አይተውም የነገሩዋቸው ስለዚህ ሕፃን እንደሆነ አወቁ እረኞች የነገሩዋቸውን የሰሙ ሁሉ አደነቁ። እረኞችም ለሕፃኑ ሰግደው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቦታቸውም ተመለሱ። ከወገኖችን ሰው ሁኖ ለጐበኘንና ይቅር ላለን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ28 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ109፥3።የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥26-57።
+ + +
❤የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥3-18፣ 1ኛ ዮሐ 4፥1-9 የሐዋ ሥራ 3፥22-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ1፥1-18። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አማኑኤል በዓልና የገሐድ ጾም። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ
@Eotcw @Eotcw @Eotce
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!
ባለፈው ሳምንት የማህሌት ዜማዎችን ከፋፍለን አይተናል ዛሬ ደግሞ ስለ ዝማሜ እናያለን።
ዝማሜ፦
ዝማሜ ማለት መቆሚያን በመጠቀም አቋቋምን በተማሩ ሊቃውንት የሚቀርብ ምስጋና ነው። ይህ ምስጋና ዋዜማ እና አንገርጋሪ ከተባለ በኃላ፣ ዋዜማው ቅኔ ከተቀኘ በኃላ፣ እጣነሞገር ክብር ይዕቲ ላይ፣እጣነሞገር ቅኔ ከተቀኘ በኃላ እና ምልጣን ባላቸው ሰላም ልክ እንደ ጥምቀት የዋዜማው ሰላም ይዘመማል።
ሁሉም መሪጌቶች አቋቋምን ቢማሩም በደንብ የተማሩ (specialized) ባደረጉት ሲዘመም ዝማሜው ይረዝማል።
ዝማሜ ከተነሳበት ቦታ አንፃር ሁለት አይነት መሆኑ ይታወቃል!
***************
1.ተክሌ ዝማሜ፦ ይህ ዝማሜ ካሉት ሁሉ ረዘም ያለና ከበድ የሚል ነው። ይህ ዝማሜ ከሌላው ዝማሜ አይነት አንፃር በመቋሚያ ቶሎ ቶሎ መሬት የማያርፍበት ነው።
2.ጎንደር ዝማሜ፦ በአብዛሃኛው ቦታዎች የሚታወቀው የዝማሜ አይነት ሲሆን ዜማውም ቀለለ ና ደስ የሚያሰኝ ነው። አብዛኛውን ግዜ ቆሎ ተማሪዎች ሆነ ሰንበት ተማሪዎች ለበዓላት ዝማሜን ካጠኑ የሚያቀርቡት ታዋቂ የዝማሜ አይነት ነው።
***-*********-******
ዝማሜ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር፦
የተዋህዶ ስርአቶችዋ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሣዊ ናቸው።፤ዝማሜም እንደዛው።
ዝማሜ ሚመሰለው በህማማተ ክርስቶስ ነው። መቋሚያው በመስቀል ይመሰላል። በዝማሜ ወቅት መቋሚያውን ወደ ግራ ወደ ቀኝ ማድረጋቸው አይሁድ ኢየሱስን አንዴ ወደግራ አንዴ ወደቀኝ ከነመስቀሉ ማንገላታታቸውን ለማስታወስ ነው። ከዛ ወደታች መሬቱን መምታታቸው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ግርፋቱ ሲበዛበት መሬት ላይ መውደቁን ያሳያል።
ስለ ዝማሜ ይህን ያህል ካየን ይበቃል ፤ በቀጣይ ሳምንት የቀሩትን እናያለን በድጋሚ መልካም በአል ይሁንልን።
👇👇👇👇
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
👆👆👆👆
@EOTCW
#Join & #share
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ታኅሣሥ ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለታላቁ አባት ለአቡነ ዮሐንስ ከማ እጨጌ ለዕረፍት በዓል አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ዮሐንስ ከማ ዘእጨጌ፦ የተባሉት ጻድቅ አባት አገራቸው ሰሜን ጎንደር ነው፡፡ በብዙዎቹ ቅዱሳን ገድል ላይ ታሪካቸው ተደጋግሞ የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስ ያሬድ በድርሰቱ ደጋግሞ ያመሰገናቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ከቀደምት አንጋፋ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ሲሆኑ መጽሐፍ "ኮከብ ዘገዳም" ይላቸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ይህኛውንም አባት ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል፡፡ ነገር ግን ስማቸውን ከላይ ከጠቀስናቸው ከግብፃዊው አባት ከአባ ዮሐንስ ከማ ጋር አንድ አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያዊው አቡነ ዮሐንስ ከማ ትግራይ የሚገኘውን ቀብፅያ ገዳምን የቆረቆሩ ሲሆን ብዙ ቅዱሳን አባቶችንም በማመንኰስ የቤተ ክርስቲያን ከዋክብት የተባሉትን ቅዱሳን መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ በገዳማቸው ቀብፅያ የምትገኘው እጅግ አስገራሚዋና ተአምራትን የምትሠራው መቋሚያቸው ዛሬም ድረስ አለች፡፡
❤ 1250 ዓመት ያስቆጠረችውን ይህችን የጻድቁን ተአምረኛ መቋሚያ ሀገሬው በጠመንጃ ይጠብቃታል፡፡ እንደ ሰው ድምፅ የምታሰማበት ጊዜ አለ፡፡ ጻድቁ ሰሜን ጎንደር ምድረ ጸለምት ትልቅ ገዳም አላቸው። ዕረፍታቸው ታኅሣሥ 25 ቀን ነው። ከአባታችን አቡነ ዮሐንስ ከማ ዘእጨጌ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@Eotcw @Eotcw @Eotcw
