uz
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Kanalga Telegram’da o‘tish

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Ko'proq ko'rsatish
1 161
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
ምቅ ንጉሡን ስለገሠጹት ታስረው ወደ ወለቃ ተጋዙ፡፡ ንጉሡ ሲሞት ሠይፈ አርዕድ ነግሦ የተጋዙት በሙሉ እንዲመለሱ ስላወጀ አቡነ አኖሬዎስም ወደ በዓታቸው ጽጋጋ ተመለሱ፡፡ አቡነ አኖሪዎስ በነገሥታቱ ፊት ቆመው የወንጌልን ሕግ በመመስከራቸው እየታሰሩ ምድረ ጸወን ወደምትባል አገር (ይህውም ደቡብ ወሎ ቦረና የምትገኝ ናት) እንዲሁም ዝዋይ ደሴ ገማስቄ ግድሞ (ባሌ አካባቢ) ወደ ተባለው አገር ተጋዙ፡፡ ለብዙ ዓመታት ገዳም መሥርተው ቆይተው ወደ ጥንት በዓታቸው ተመልሰው ጽጋጋ መጥተው በገዳማቸው ብዙ ተጋድለው በ1471ዓ.ም በዚሁ በጽጋጋ ገዳማቸው ነው ያረፉት፡፡ ❤ በኋላም ወደ አሩሲ በመሄድ ኢስላሞችን አስተምረዋል፡፡ ብዙ ተአምራት ያደረጉላቸው ሲሆን መንደራቸውንም ያማረ መንደር ብለው ሰይመውላቸዋል፡፡ የአሩሲ ኢስላሞች እጅግ ያከብሯቸውና ይወዷቸው ነበር። ከአክብሮታቸውም የተነሣ አቡነ አኖሬዎስን "ኑር ሁሴን" እያሉ ይጠሯቸው ነበር፡፡ ጻድቁ በአሩሲ ቆመው የጸለዩበት ቦታ ዛሬም ድረስ ተከብሮ ይኖራል፣ ሶፍ ዑመር ዋሻ ተብሎ የሚጠራው ታሪካዊ ዋሻ የአቡነ አኖርዮስ በዓት መሆኑ በታሪክ የሚታወቅ ሐቅ ነው፣ ይህም በገድለ ተክለ ሃይማኖትና በድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ላይ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ጻድቁ በኢቲሳ 21 ዓመት ቆመው ሲጸልዩ ብርሃን ተተክሎ ይታይ ነበር፡፡ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ትልቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ መስከረም 18 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ከአቡነ አኖርዮስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ለዘረከብከ ሞገስ። ምስለ ፈጣሪ ትትናገር ሱባዔያተ ሠላሰ። ኤዎስጣቴዎስ ዘሦጥከ ዲበ በድነ ሕፃን ነፍሰ። ጊዜ ዐደውከ ማዕበላተ ዘአልቦ አርማሰ። በዘባነ ባሕር እንዘ ትሰፍሕ ልብሰ"። + + + ❤ "ሰላም ለከ ለዘነሣእከ ኃይሎ። ለመንፈስ ቅዱስ ምሕራመ አጋንንት በአሰስሎ። ዘበእንቲአከ ቃል ለተክለ ሃይማኖት ይቤሎ። አመ ተኀብአ አምኔከ ወአመ ሥውረ ሁሎ። ተረፈ ጣዖታት ያጠፍእ አኖሬዎስ ኵሎ"። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 18። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ወደ አርማንያ አገር ሲሆዱ ኢያሪኮ ባሕር በአጽፍቸው እንጀልባ አድርገው ለተሻገኑ ለከፍሌ ባሕር ለአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ለዕረፍት በዓል፣ አሁን ሶፍ ዑመር ዋሻ እየተባለ የሚጠራው የጸሎት በዓታቸው ለነበረ ለጽጋግ መምህር ለአቡነ አኖሬዎስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ከፋሌ ባህር አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ክርስቶስ ሞዓ የእናቱ ስም ስነ ሕይወት ይባላል ሁለቱም ደጋጎች እግዙአብሔርን የሚፈሩና በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ነበሩ ። ❤ ከዘህም በኋላ በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት ይህን ቅዱስ ወለዱት ስሙን የጌታ ጥብቅ ብለው ሰየሙት። በአደገም ጊዜ የዳዊትን መዝሙርና የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍትን አስተማሩት። ❤ ከዚህም በኋላ የእናቱ ወንድም አባ ዘካርያስ ወደአለበት የመነኰሳት ገዳም ወሰዱት። አባ ዘካርያስም የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዳደረችበት አውቆ የምንኵስናን ሥርዓት አስተምሮ የመላእክትን አስኬማ አለበሰው። ከገድሉ ጽናት የተነሣ በገዳም ያሉ አረጋውያን እስኪያደንቁ ድረስ በጾም በጸሎት የተጠመደ ሆነ እርሱ በጥበብና በዕውቀት የጸና ነውና። ከጥቂት ጊዜ በኋላም ዲቁና ተሾመ የዲያቆናት አለቃ እንደሆነ እስጢፋኖስም ለቤተ ክርስቲያን አገለገለ ። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳን ሚካኤልና ከገብርኤል ጋር ተገለጠለትና ሰላምታ ሰጠው በንፍሐትም መንፈስ ቅዱስን አሳደበረት እንዲህም አለው "ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ሆይ እኔ ከእናትህ ማሕፀን መረጥኩህ ያለ ፍርሀትና ድንጋፄ ወንጌልን ለብዙዎች ሕዝቦች ትሰብክ ዘንድ ከኢትዮጵያ እስከ አርማንያ ድረስ መምህር አደረግሁህ አንተን የሰማ እኔን ሰማ አንተን ያልሰማ እኔን አልሰማም" ጌታችንም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ በክብር ዐረገ ። ❤ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስም ወደ ጳጳስ ሒዶ ቅስና ተሾመ የወንጌልንም ሃይማኖት ይሰብክ ዘንድ ጀመረ ብዙ ሰዎች ወደ ርሱ እስቲሰበሰቡ ድረስ በእርሱም እጅ መንኵሰው ደቀ መዛሙርትን ሆኑት ከእርሳቸውም ታላቁ አባ አብሳዲ ነው። ብዙዎችንም የከፋች ሥራቸውን አስትቶ ከክህደታቸው መለሳቸው ትምህርቱም በሀገሩ ሁሉ ደረሰ በመላ ዘመኑም የሰንበታትና የበዓላት አከባበር የጸና ሁኖ ተሠራ ከሐዋርያትም ሕግና ሥርዓት ወደቀኝም ሆነ ወደ ግራ ሁሉም ፈቀቅ አላሉም ። ❤ ወደ ኢየሩሳሌምም ሁለት ጊዜ ሔደ እግዚአብሔርም በእጆቹ የዕውራንን ዐይኖች በማብራት፣ አንካሶችንና ጎባጦችን በማቅናት፣ አጋንንትን በማስወጣት ቁጥር የሌላቸው ተአምራትን አደረገ ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለመሔድ በአሰበ ጊዜ ልጆቹን ሰብስቦ የመነኰሳትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ከመናፍቃንም ጋር እንዳይቀላቀሉ አማፀናቸው። ልጁ አብሳዲንም በእነርሱ ላይ ሾመውና ወደ ኢየሩሳሌም ሰንበትን እያከበረና የክርስቶስን ሃይማኖት እያስተማረ ሔደ። ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚንም ደርሶ ከእርሱ ቡራኬ ተቀበለ የሃይማኖትንም ነገር ተነጋገሩ ዳግመኛም ከከበሩ ቦታዎች በመሳለም በረከትን ተቀበለ በዮርዳኖስም ተጠመቀ ። ❤ ከዚያም ወደ አርማንያ ሔደ ወደ ኢያሪኮ ባሕርም ሲደርስ በመርከባቸው ያሳፍሩት ዘንድ መርከበኞችን ለመናቸው በከለከሉትም ጊዜ ዓጽፉን በባሕሩ ላይ ዘረጋ በቅድስት ሥላሴ ስም በላዩ ባረከ ራሱንም በመስቀል ምልክት አማተበ እንደ መርከብም ሁኖለት በላዩ ተጫነ ሁለት መላእክትም ቀዛፊዎች ጌታችንም እንደ ሊቀ ሐመር ሆኑለት። ከባሕሩም ግርማ የተነሣ እንዳይፈሩ ልጆቹን አጽናናቸው። ግን እንዲህ አላቸው "ልጆቼ በልባችሁ ቂምንና ሽንገላን እንዳታኖሩ ተጠበቁ ለኔ ግን ከእናንተ አንዱ አንደ ሚጠፋ ይመስለኛል" ይህን ሲናገር ልቡ የቂም የበቀል ማከማቻ ስለሆነ ወዲያውኑ አንዱ ከእነርሱ መካከል ሠጠመ ። ❤ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ባሕሩን ተሻግሮ ወደ አርማንያ ከተማ ደርሶ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ተገናኘ ሰገደለትም ከእርሱም ቡራኬን ተቀበለ ሊቀ ጳጳሱም በአየው ጊዜ ታላቅ ደስታን ደስ አለው በፍቅርም ተቀበለው። አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ሁሉም በትምህርቱ አንድ እስከሆኑ ድረስ የአርማንያን ሰዎች ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው የሠሩትን ሥርዓት እያስተማራቸው ኖረ ። ❤ ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳንን ሰጠው ። በዐረፈም ጊዜ ጳጳሳትና ካህናት በታላቅ ክብር ገንዘው በሰማዕቱ በቅዱስ መርምህናም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገለጡ። ❤ አቡነ አኖሬዎስ ትልቁ፦ አባታቸው ዘርዐ ሃይማኖት ወይም ዘርዐ አብርሃም እናታቸው ደግሞ ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ አቡነ አኖሬዎስ ታላቁ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ዜና ማርቆስና አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር እነዚህ ሁሉም የወንድማማቾች ልጆች ናቸው፡፡ ❤ እነኚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናትም የእኅትማማቾች ልጆች ናቸው፡፡ ማለትም የአኖሬዎስ ታላቁ እናት ክርስቶስ ዘመዳ፣ የሕፃን ሞዐ እናት ትቤ ጽዮን፣ የንጉሡ የዐፄ ይኩኖ አምላክና የማርያም ዘመዳ እናት እምነ ጽዮን እኅትማማቾች ናቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ እኅትማማቾች (እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ) መድኃኒነ እግዚእ የሚባል አንድ ወንድም አላቸው፡፡ እርሱም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እናት የቅድስት እግዚእ ኀረያ አባት ነው፡፡ ማርያም ዘመዳም አቡነ ዜና ማርቆስንና ማርያም ክብራን ወልዳለች፡፡ ማርያም ክብራም ትንሹን አኖሬዎስን ወልዳለች፡፡ ታላቁ አቡነ አኖሬዎስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ ወደ ትግራይ በመሄድ ፀዓዳ ዓንባ ከተባለ ቦታ ገዳም መሥርተዋል፡፡ ❤ ግብፃዊው አቡነ ያዕቆብ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የደብረ ሊባኖሱን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን አስጠርተው ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት "ኢትዮጵያ በአንድ ጳጳስ መወሰን የለባትም፡፡ ስለዚህ ዐሥራ ሁለት አበው መርጠን ክርስትና ይስፋፋ" ብለው ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘሞረት፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘወረብ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘግድም፣ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመርሐ ቤቴ፣ አቡነ አድኃኒ ዘዳሞት፣ አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል፣ አቡነ ኢዮስያስ ዘወጅ፣ አቡነ ዮሴፍ ዘእናርያን መርጠው ሀገረ ስብከት ተሰጥቷቸው ለሐዋርያዊ ተልእኮ ተሠማሩ፡፡ ❤ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱን ንቡራነ ዕድ ለስብከተ ወንጌል በመላዋ አገሪቱ ሲሠማሩ ለአቡነ አኖሬዎስ እንደ ግብጦን የተባለ ቦታ ደረሳቸው፡፡ ይህም ቦታ ከግንደ በረት እስከ ባሌ ያለውን አገር ያካትታል፡፡ እርሳቸውም ሰባት ታቦታት ይዘው በመሄድ አብያተ ክርስቲያናት ተክለው ክርስትናን አስፋፍተዋል፡፡ በአካባቢው ስብከተ ወንጌልን ካስፋፉ በኋላ ባርጋባን የተባለ የአካባቢው ሰው ተአምራታቸውንና ትምህርታቸውን ተመልክቶ በጽጋጋ ገዳም እንዲመሠርቱ ስለነገራቸው አቡነ አኖሬዎስ በጽጋጋ ገዳም መሥርተዋል፡፡ ❤ ይህ የአቡነ አኖሬዎስ ገዳም ደሴ ዙሪያ በጽጋጋ የሚገኝ ሲሆን ከደሴ ወደ መካነ ሰላም በሚወስደው መንገድ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ የተመሠረተው በ1317 ዓ.ም በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ አቡነ አኖሬዎስ በጽጋጋ ገዳማቸው እያሉ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር ተታሎ የአባቱን ሚስት በማግባቱ ጻድቁ እንደ ዮሐንስ መጥ

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ እያልን ቲንሽ ስለ ግሩፑ ህግ የግሩፑ ህግ ፦ ይህ ግሩፕ ኦርቶዶክሳዊ ግሩፕ ነው፤ስለዚህ አላስፈላጊ የሆኑ ከሀይማኖታዊ የወጣ ወይም አለማዊ ሊንኮችም ሆነ ስርአታዊ ያልሆነ ንግግሮችን እንዲሁም ስድ ቃላትን መጠቀም እና መልቀቅ የተከለከለ ነው!! ቻናሉን በእዚኛው ሊንክ ያገኙታል @EOTCW እናም እኛ የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን እየጣር ነው እናንተም ቃሉ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ወደዚህ ግሩፕ እና ቻናል ሰው እንድታቀላቅሉልን እያልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።

ወበእንተዝ አዘዙነ መምህራነ ቅዱስ ወንጌል ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ድንግል ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ትርጉም: - ስለዚህም የቅዱሱ ወንጌል መምህራን አዘዙን ለመስቀል እና ለድንግል ማርያም እንድንሰግድ https://t.me/Eotcw

በዓለ መስቀል መስቀል ማለት አመስቀለ አመሳቀለ ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን የተመሳቀለ ማለት ነው፡፡ መስቀል በዘመነ ኦሪት በዚያ በፍዳ ዘመን የወንጀለኛ መቅጫ የበደለኛ መስቀያ ነበር ፡፡ ጌታ ወደእዚህ ዓለም አመጣጡ ህግን ሊሽር ሳይሆን የላላውን ለማጥበቅ በሥጋ አይን ያላየነውን በመንፈስ አይን ሊያሳየን ነው፡፡ ጌታ የድኅነቱን ነገር የፈፀመውም በብሉይ ዘመን ለወንጀለኛ መቅጫ በነበረው መስቀል ሲሆን ሌላ አዲስ ነገር አምጥቶ አደለም ይህ መስቀልም ☞ ጌታ ከተሰቀለበት በኀላ የወንጀለኛ መቅጫ የነፍስ ማጥፊያ መሆኑ ቀርቶ የድኅነት ምንጭ ሁኗል ☞ በብሉይ ዘመን ይህ መስቀል የሚገኘው በበደሉ ህግን በተላለፉ እጅ ነበር ከጌታ ስቅለት በኀላ ግን የሚገኘው በጥምቀት በከበርነው በእኛ ኦርቶዶክሳውያን ልብ እና አንገት ላይ ነው ፡፡ ★ ከእጸ መስቀል የህይወት ታሪክ ምን እንማር ይህ እጸ መስቀል በህይወቱ ላይ ጌታን ሳያነግስ በፊት ☞ ውሎው አዳሩ ከኃጢያተኛ ጋር ☞ሥራው ነፍስ ማጥፋት ☞የተናቀ ☞አምጻኤ ሀዘን ☞የሞት እና የክፋት ምልክት ነበር በህይወቱ ውስጥ ጌታን ከተቀበለ ካነገሰ በኀላ ደሞ.... ☞ ለታመሙት የድኅነት ምክንያት ☞ምጽዋተኛ (አማናዊው በግዕ በእርሱ ገበታነት ለዓለም በሙሉ መቅረቡ ልብ ይሏል) ☞ በፊት ውሎው በኃጢያት በተጨማለቁ እና ከተዋረዱ ሰዎች የነበረ ቢሆን መንገዱን ከጌታ ጋር ካደረገ በኀላ ግን ውሎው ጭራሹን ተቀይሮ ከከበሩ ጳጳሳት እጅ ጋር እንዲሁም በጥምቀት ከመንፈስ ከተወለዱ ኦርቶዶክሳውያን አንገት ጋር ነው፡፡ ☞ነፍስ እንዳላጠፋ አሁን ከብቃት ደርሶ እረ ሙት ማንሳት እውር ማብራት ደርሷል ጀምሯል፡፡ ★እኛስ ከእፀ መስቀል የህይወት ታሪክ ምን እንማር ???? ☞በሕይወታችን በኑሯችን ጌታን እንደ እጸ መስቀል ካነግስን በፊት ነፍሰ ገዳይ የነበርን አንሳኤ ሙታን , ሰራቅያን የነበርን መፅዋች , ምክራችን ከብኤል ዜብል ወደ ቅዱሳን መላዕክት , ከወንበዴ ጋር የነበረውን ውሏችን ከቅዱሳን ጻድቃን ጋር ማድረግን እንማራለን ነገር ግን ምን ስናረግ ህይወታችን ላይ እንደ እጸ መስቀል ጌታን ስናነግስ ብቻ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ከእጸ መስቀል የሕይወት ታሪክ በመማር መንበረ እግዚዕን በአንገት ከማሰር ብቻ ተላቀን መስቀሉን በሕይወት በመግለፅ ያቺን ብኤል ዜቡል የሚመኛትን ነገር ግን የማያገኛትን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ ያብቃን ፡፡

+1
ምስባክ ዘመስከረም ፲፯ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ዘነግህ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁ፣ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቀሥት፣ ወይድኅኑ ፍቁራኒከ። መዝ ፶፱፤፬ ወንጌል ፦ዮሐ ፫፥፲፬-፳፪ ምስባክ ዘቅዳሴ ፩ጢሞ ፭፥፱-፲፮ ያዕቆብ ፫፥፲፩-ፍ ግብ.ሐዋ ፭፥፳፮-፴፫ ወንጌል ፦ማቴ ፰፥፲፮-፳፰ ቅዳሴ ፦ዘዮሐንስ አፈወርቅ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁ፣ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቀሥት፣ ወይድኅኑ ፍቁራኒከ። ዓዲ(ወይም) ወረከብናሁ ውስተ ፆመ ገዳም ፣ ንበውዕ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሔር፣ ወንሰግድ ውስተ መካን ኃበ ቆመ እግረ እግዚእነ። መዝ ፶፱፤ ፻፴፩፤፮ https://t.me/Eotcw

❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣ ሥርዓተ ማኅሌት ዘመስከረም አስተርእዮተ መስቀል "መስከረም ፲፯" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCW @EOTCW መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ሃሌ ሉያ ለአብ ንሴብሕ፤ በኦሪተ ሙሴ ዘተነግረ ስኑ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ዕፀ አንህዮ ለባሕር ዛህኑ፤ መስቀለ አልፋ ተረክበ ዮም በቅዱስ መካኑ፤ አፅደለ ውስተ ዓለም ብርሃኑ። @EOTCW ነግሥ ኦ ማርያም መንክር ልደትኪ፤ ወዕፁብ ግብርኪ፤ ዓምደ እሳት ዘፆርኪ፤ ወልድኪ መድኃኔዓለም ዲበ ዕፅ ተቀነወ፤ ወዘተጼወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ዮመ መስቀል አስተርአየ እለ ማሰኑ ፍጥረተ አሠነየ፤ ዮም መስቀል ተኬነወ ወዘተጼወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ፤ ዕፀ መስቀሉ ለወልድ ተረክበ ዮም በቀራንዮ መካን፤ ዘደፈኑ አይሁድ መስቀል ዕፀ ሕይወት፤ ዕፀ መድኃኒት። @EOTCW ወረብ በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ/፪/ መስቀል ዕፀ ሕይወት ዕፀ መድኃኒት/፪/ @EOTCW @EOTCW መልክዐ መስቀል ሰላም ለዝክረ ስምከ በመጽሔተ መስቀል ዘተለክዐ፤ ወለስእርትከ ጸሊም ዘደመ ተኮርዖ ተቀብአ፤ ሰዋስወ ፍቅር ክርስቶስ ትኩል ዲበ እንግድዓ፤ አስትየኒ ለተሳትፎ እንተ ሰተይከ ጽዋዓ፤ በዋዕየ ፍቅርከ አምላካዊ ሕሊናየ ጸምዓ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ይትቀደስ ስምከ በኃይለ መስቀልከ፤ በዕፀ መስቀልከ ክቡር ዘአዕበይኮ ለስምከ፤ ስብሐት ለከ ለባሕቲትከ ልዑል፤ ወሠራዕከ በዓለ ለኲልነ ዕረፍት። @EOTCW ወረብ "ይትቀደስ ስምከ"/፪/ በኃይለ መስቀልከ/፪/ ዕፀ መስቀልከ ዘአዕበይኮ ለስምከ ስብሐት ለከ ለባሕቲትከ/፪/ @EOTCW @EOTCW መልክአ መስቀል ሰላም ለመዝራዕትከ በደመ ማዕሠር ዘተሤረየ፤ ወለኲርናዕከ ክቡር እንተ ተመሰለ ብየ፤ ለወሀቤ ዝናም ክርስቶስ ዘከልዑከ ማየ፤ ምንተ እነግር ወእዜኑ ዘመስቀልከ ዕበየ፤ እስመ ኃይለ ነገር ጽኑዕ እምአፉየ በልየ። @EOTCW ዚቅ ርእዩ ዕበዮ ለዕፀ መስቀል እግዚኡ ዘከመ ከለሎ፤ ዮም በምድር ተዝካሩ በሰማያት በላዕሉ፤ ርእዩ ዕብዮ ለዕፀ መስቀል፤ ይቤሎ መድኃኒነ ለዕፀ መስቀል፤ ዕውራን ይሬእዩ ወጽሙማን ይሰምዑ፤ እለ ለምጽ ይነጽሑ እለ መጽኡ ኀቤየ። @EOTCW @EOTCW ወረብ ርእዩ ዕበዮ ዕበዮ ለዕፀ መስቀል/፪/ ዮም በምድር ተዝካሩ በሰማያት በላዕሉ በሰማያት/፪/ @EOTCW @EOTCW መልክአ መስቀል ሰላም ለገቦከ ኲናተ ሐራዊ ዘወግዖ፤ ወለአዘቅተ ማይ ከርሥከ ለደመ ሥርዓት እንተ አንቅዖ፤ ሐዋርያ አብ ክርስቶስ ዘፈጸምከ ግብረ ተሰብኦ፤ ዕቀበኒ በመስቀልከ ለመልአከ ዓለም ዘሞዖ፤ ከመ ኖላዊ የዓቅብ እምተኲላ በግዖ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ እምገቦከ ውኅዘ ነቅዓ ማይ፤ ዘቀደሶ ለፈያታይ፤ መስቀልከ እግዚኦ ምስካይ ለነዳይ። @EOTCW ወረብ እምገቦከ ውኅዘ ነቅዓ ማይ ዘቀደሶ ለፈያታይ/፪/ ለነዳይ ምስካይ መስቀልከ እግዚኦ ለነዳይ ምስካይ/፪/ @EOTCW @EOTCW አንገርጋሪ ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሁድ እመኑ ብየ፤ ወእመኑ በአቡየ፤ ዮምሰ ለእሊአየ፤ አበርሕ በመስቀልየ @EOTCW አመላለስ ዮምሰ ለእሊአየ/፪/ አበርሕ በመስቀልየ/፬/ @EOTCW ወረብ "ይቤሎሙ ኢየሱስ"/፪/ ለአይሁድ/፪/ እመኑ ብየ ወእመኑ በአቡየ አበርሕ በመስቀልየ ለእሊአየ/፪/ @EOTCW እስመ ለዓለም ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ፤ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት፤ በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለ አብ፤ ወበስምከ ነኃሥሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ፤ ወካዕበ ይቤ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ወንሕነኒ ንትፈሣሕ ዮም ወንግበር በዓለ፤ በዛቲ ዕለት በዓለ እግዚእነ። @EOTCW @EOTCW ዓዲ (ወይም) እስመ ለዓለም መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ እምኲሉሰ ፀሐየ አርአየ፤ መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ። 🌼 መልካም በዓል 🌼 https://t.me/Eotcw # Join & share