uz
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Kanalga Telegram’da o‘tish

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Ko'proq ko'rsatish
1 161
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
+ + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ፡፡ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ። ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ"። መዝ 73፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥22-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥7-13 እና የሐዋ ሥራ 4፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳ ለማኅበረ በኵር መታሰቢያ በዓል፣ በእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ ድሜጥሮስ ዘመንና በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመነ መግሥት ሰማዕትነት ለተቀበለ ለቅዱስ መጥራ ለዕረፍት በዓል፣ በከሀዲ መክስምያኖስ እጅ ሰማዕት ለሆነ ለቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ለዕረፍት በዓል፣ እስሙናይን ከሚባል አገር ለሆኑ ለከበሩ ለቅዱሳን ከቢካቦስና ዮሐንስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ጋር ሰማዕትነት ከተቀበሉ ከሠላሳ ሺህ ማኅበርተኞቹ ሰማዕታት፣ ለቅዱሳን ከቢካቦስና ዮሐንስ ከእነርሱ ጋር ሰማዕትነት ከተቀበሉ ከዘጠና አምስት ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ ምልጣን ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ተወከፍ ለነ ዘንተ ግብረ ማኅበረነ በኀበ ንገብር ተጋቢዓነ ኲልነ ዮም በዛቲ ዕለት እግዚኦ ባርክ ማኅበረነ"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ መጥራ፦ ይህም ቅዱስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖት መስገድን የሚያዝ የንጉሡን ደብዳቤ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ ወዲያውኑ ሒዶ ከወርቅ የተሠራ የአጵሎንን ክንድ ሰረቀ በየጥቂቱም ሰባብሮና ቆራርጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው። ❤ የጣዖቱም አገልጋዮች ክንዱ ተቆርጦ አጵሎንን በአገኙት ጊዜ ስለርሱ ብዙዎችን ሰዎች ያዟቸው። በዚያንም ጊዜ ወደ መኰንኑ ቀርቦ ክርስቲያን እንደሆነ በፊቱ ታመነ ሁለተኛም "የአጵሎንን የወርቅ ክንድ የወሰድኩ እኔ ነኝ ለድኆችና ለችግረኞችም ሰጠኋቸው" አለው። መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ አስጨናቂ የሆነ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤና አወጣው። ❤ ከዚህም በኋላ እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ ብዙ ደም ከአፍንጫው ወደ ምድር እስከ ሚወርድ ዘቅዝቀው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ቅዱስ መጥራንን ፈታው ከተሰቀለበትም አውርዶ በመዳሠሥ አዳነው። አንድ ዕውር ሰውም መጣ ከአፍንጫው ከወረደውም ደም ወስዶ ዐይኖቹን ቀባ ወዲያውኑ አየ። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ መጥራ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ሐርስጥፎሮስ፦ ይህም ቅዱስ በንጉሥ መክስምያኖስ ፊት በአቆሙት ጊዜ "ለአማልክት ሠዋ" አለው። የከበረ ሐርስጥፎሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ ለእርሱም እሠዋለሁ"። ንጉሡም ተቆጥቶ ሥጋው ተቆራርጦ በምድር ላይ እስቲወድቅ በበትር ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ወህኒ ቤት ጣሉት በላህያቸውም እንዲአስቱት ሁለት ሴቶችን ንጉሡ ወደርሱ ላከ ቅዱሱ ግን የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራቸው የዛሬ የሆነ የዚህንም ዓለም ኃላፊነት አስገነዘባቸው ወደ መክስምያኖስም በተመለሱ ጊዜ "እንዴት አደረጋችሁ" አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት "በከበረ ሐርስጥፎሮስ አምላክ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ እኛ እናምናለን" ንጉሡም ሰምቶ አንዲቱን በዕንጨት ላይ ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ሁለተኛዋን በአንገቷ ደንጊያ አንጠልጥለው ቊልቊል እንዲሰቅሏት አዘዘና ምስክርነታቸውን እንዲህ ፈጸሙ። ❤ ከዚህም በኋላ ዕንጨቶችን ሰብስበው በማንደጃው ውስጥ አድርገው አነደዱ የከበረ ሐርስጥፎሮስን እጅና እግሩ እንደ ታሠረ ከውስጡ ጨመሩት ያን ጊዜም "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" አለ እሳቱ ከቶ ምንም አልነካውም። ሕዝቡም ይህን አይተው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ዐሥር ሺህ ያህል ሰዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ❤ ሁለተኛም የብረት ሠሌዳዎችን በእሳት አግለው አመጡ ቅዱሱንም በላያቸው በአስተኙት ጊዜ ምንም ምን የነካው የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃያ ሺህ አንድ መቶ ሰዎችና አርባ ሕፃናት አምነው ምስክር ሁነው ሞቱ። ❤ ንጉሥ መክስምያኖስም አይቶ እጅግ ተቆጣ የቅዱስ ሐርስጥፎሮስንም ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።ከንጉሡም ዘንድ በወጣ ጊዜ ጸሎትን አደረገ ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ ከዚህም በኋላ ምስክርነቱን ፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱሳን ሰማዕታት ቢካቦስና ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ቢካቦስ ክርስቲያን ሲሆን በሥውር ወታደር ሆነ። አንጥያኮስ ለሚባል መኰንንም ስለ ዮሐንስና ስለ ኤጲስቆጶስ አባ አክሎግ ከተርሴስ አገር ስለ ናሕር ስለ አባ ፊልጶስም እነርሱ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ነገር ሠሩባቸው። ❤ መኰንኑም እነርሱን አቅርቦ "እናንት ክርስቲያኖች ናችሁን?" አላቸው "እኛ በእውነት ክርስቲያን ነን በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን" አሉት። መኰንኑም "ይህን ነገር ትታችሁ ለአማልክት ሠዉ" አላቸው። ቅዱሳኑም እንዲህ ብለው መለሱለት "እኛስ ለረከሱና ለተናቁ አማልክት አንሠዋም ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከጌታችን ኢየሱስ በቀር"። መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ምስክርነታቸውንም እስከፈጸሙ ድረስ አሠቃያቸው። ❤ ቅዱስ ቢካቦስን ግን ከአሠቃየው በኋላ አሠረውና ከመንኰራኲር ውስጥ ጨመረው ዘቅዝቆም ሰቀለው ሕዋሳቱንም ቆራረጠው ጌታችንም ያስታግሠውና ያበረታው ነበር ያለ ጉዳትም ጤናማ አድርጎ አስነሳው። ❤ ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ከብዙዎች ሰማዕታት ጋራ ላከው በመርከብም ውስጥ እህልና ውኃ ሳይቀምሱ ሃያ ስድስት ቀኖች ኖሩ። በርሙን ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይተው በምሳር ቆረጡት የምስክርነቱንም ተጋድሎ ፈጸመ መንግሥተ ሰማያትም አክሊልን ተቀበለ። ❤ ከሀገረ በርሙን ሹማምንቶችም አንድ ባለ ጸጋ ሰው መጥቶ የቅዱስ ቢካቦስን ሥጋ ወስዶ በአማሩ ልብሶች ገነዘው ወደ አገሩ እስሙናይንም ላከው። በመከራውም ወራት ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ ከእርሱም ጋራ የተገደሉ ዘጠና አምስት ሰዎች ናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ለቅዱሱ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ቢካቦስና ዮሐንስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ይድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 10 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለቢካቦስ ዘኮኖሙ ተበያጼ። ለተስዓቱ ወኃምስቱ ሰማዕታተ ክርስቶስ እንበለ ግጋፄ። ጣዖታተ ይዝልፍ ወንጉሠ ዐማፄ። ለዝ ጥቡዕ ኢመጽኦ ድንጋፄ። እስከ መተሩ ሥጋሁ በማሕፄ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 10። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "በማኅበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር። ወለአምላክነ በአንቅዕተ እስራኤል። ህየ ብንያም ወሬዛ በኃይሉ"። መዝ 67፥26-27። የሚነበበው ወንጌል ማር 11፥23-27።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊ ጻድቅ ለአባታችን ለአቡነ ለዓቢየ እግዚእ ተከዜ ወንዝ እንደ ባሕረ ኤርትራን ከፍለው ለተሻገሩበትና ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብን ላሳመኑበት ዓመታዊ ለተአምር በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ዓቢየ እግዚእ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፦ አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ ዐሥር ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ። ❤ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይሕም ዘወትር ነሐሴ ዐሥር ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል። ከአባታች አቡነ ዓቢየ እግዚእ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳዮስ አበበ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

የዚህን ወጣት የመምህር ዲያቆን ኤልያስ ሳህሌን ዜና ረፍት ዛሬ በተለያዩ ድህረገጾች ላይ ስመለከት ለእርሱ ሞት ጥቅሙ ብትሆንም ለቤተክርስቲያን / ለእኛ ግን በሞት መወሰዱ የሆነ ነገር እንደሚያጎልብን
የዚህን ወጣት የመምህር ዲያቆን ኤልያስ ሳህሌን ዜና ረፍት ዛሬ በተለያዩ ድህረገጾች ላይ ስመለከት ለእርሱ ሞት ጥቅሙ ብትሆንም ለቤተክርስቲያን / ለእኛ ግን በሞት መወሰዱ የሆነ ነገር እንደሚያጎልብን ጥያቄ የለውም። ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ትጉህ አገልጋይ ወጣቶች በብዛት አለመኖር ነው ብዙዎችን ለተኩላ እያስነጠቅን ለመቀጠል ያስገደደን። "መከሩ ብዙ ሠራተኞች ግን ጥቂት" እንዲል። በእርግጥ ከሞት የሚያመልጥ ማንም የለም፤ ምንም እንኳ እግዚአብሔር ለሞት ባይፈጥረንም ከውድቀት በኋላ ግን ለሕያዋን ሁሉ የተሰጠ ስጦታ ሆኖ ቀጥሏል። ሞት ዓለም እስካለች አለ፣ ዓለም ደግሞ ያለ ሞት አትኖርም። ሞት ሲሞት ዓለም ትሞታለች። ዓለም ስትሞት ሞት ይሞታል። “….አስር ዓመትም፣ መቶ ዓመትም፣ ሺ ዓመትም በሕይወት ብትኖር ከሞት ጋር ክርክር የለህም” (መፅሐፈ ሲራክ 41፣4) እንዲል። እንደዚህ ወጣት ግን ሞትን በአሟሟት አሸንፎ እግዚአብሔርን አምኖ እንዳገለገሉት መሞት ያውም ባለብዙ ፍሬ ሆኖ መጠራት መመረጥ ነውና ነፍስህ ከደጋጎቹ ቅዱሳን አጠገብ ትረፍ!!! ለቤተሰብህና ለቅርብ ወዳጆችህ መጽናናትን ይስጥልን!!!!! ለቤተክርስቲያናችን እና ለአገለገልክበትም አዲስ አበባ ፍሬ ሃይማኖትን ሰ/ት/ቤት ተተኪዎችን ያብዛልን!!!!!!!

ነሐሴ ፱ #ምንባባት ፊል ም፩ ቊ፲፪-፳፬ ፪ዮሐ ም፩ ቊ፮-ፍጻ ግብ ሐዋ ም፲፫ቊ፱-፳፭ #ምስባክ መዝ ፵፬ ቊ፱-፲ ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ። #ትርጉም የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፣ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ተቆማለች፣ #ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል ም፩ቊ፳፪ #ቅዳሴ ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ) https://t.me/Eotcw

photo content
+2

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን ለአባታች ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል (በዚች ቀን አባታችን እስትፋሰ ክርስቶስ ከሰማይ የወረደውን የቊርባን ኅብስት ተቀብለው ያቀበሉበት ነው ብሎ ገድላቸው ይናገራል)ና ስጥኑፍ ከሚባል አገር ለሆኑ ለሰማዕቱ ለካህኑ አባ ኦር ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ሚታሰቡ፦ ከሊቀ ጳጳስ ጲላጦስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ስጥኑፍ ከሚባል አገር የሆነ የከበረ ቄስ አባ ኦሪ፦ ይህ ቅዱስ ብዙ ርኅራኄ ያለው በሥጋው በነፍሱም ንጹሕ የሆነ ነው ብዙ ጊዜም አምላካዊ ራእይን ያያል። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት። ❤ ከዚህም በኋላ የአባ ኦሪ ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ ተሰማ ወደርሱም አስቀርቦ "ለአማልክት ዕጣን አቅርብ" አለው እርሱም "ለረከሱና ለተሠሩ አማልክት አልሠዋም" ብሎ እምቢ አለው። መኰንኑም ተቆጥቶ በብዙ ሥራ አስፈራራው ቅዱስ ኦሪም ሥቃዩን ምንም ምን አልፈራውም ጹኑ ሥቃይንም አሠቃየው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ አገር ላከው በዚያም ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃይተው በወህኒ ቤት ጣሉት። በዚያም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ በሽተኞችን ፈወሳቸው ። ዜናውም በተሰማ ጊዜ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ከየአገሩ ብዙዎች ሰዎች ወደርሱ መጥተው አዳናቸው። ይህንንም መኰንኑ ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ። ❤ ከዚህም በኋላ የከበረ ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ ገንዘው ወደ ሀገሩ ስጥኑፍም ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በማመንም ለሚመጡ በሽተኞች ሁሉ ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ ኦሪ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 9 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 1፥12-24፣ 2ኛ ዮሐ 1፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥19-25። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

ነሐሴ ፰ #ምንባባት ሮሜ ም፱ቊ ፳፬-ፍጻ ፩ጴጥ ም ፬ቊ፲፪-ፍጻ ግብ ሐዋ ም፲፮ ቊ፴፭ #ምስባክ መዝ ፶፯ ቊ፰-፱ ውድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ። ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ። ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ። #ትርጉም እሳት ወደቀች ፀሐይንም አላዩአትም እሾኳችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችዋል #ወንጌል የማቴዎስ ወንጌል ም፯ ቊ፲፪-፳፮ #ቅዳሴ ዘእግዝእትነ https://t.me/Eotcw

✨✨✨ መዝሙር ዘሰንበት ❄️❄️❄️ በ 2 ሃሌታ- ዛቲ ይዕቲ ማርያም፤ ማኅደረ መለኮት እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን፤በከመ ይቤ ዳዊት በመዝሙር፤ አንሳዕኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር፤አድባረ ድኁኃን ተሰምየት ዛቲ ይዕቲ ቅድስት ድንግል፤ማ፦ተዓቢ እምኩሉ ፍጥረት፤ኢያውዓያ እሳተ መለኮት አመላለስ፦ ተዓቢ እምኩሉ ፍጥረት እምኩሉ ፍጥረት/2/ ኢያውዓያ እሳተ መለኮት/4/ ምስባክ፦ አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር፤ እምአይቴ ይምጻሕ ረዲኤትየ፤ ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር። መዝሙር ፻፳ ፡ ፩ https://t.me/Eotcw #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን ለካህኑ ቅዱስ አልዓዛርና ለሚስቱ ቅድስት ለሰሎሜ ለሰባቱ ልጆቻቸው አንኤም፣ አንጦኒኃስ፣ ዖዝያ፣አልዓዛር፣ አስዮና፣ ስሙና መርካሎት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕቱ ከቅዱስ አሞን ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ካህኑ ቅዱስ አልዓዛርና ሚስቱ ሰሎሜ ሰባቱ ልጆቻቸው አንኤም፣ አንጦኒኃስ፣ ዖዝያ፣ አልዓዛር፣ አስዮና፣ ስሙና መርካሎስ፦ ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት። ❤ የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው። ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኰል እንዲገባ አደረጉት። ❤ በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የእሊም ቅዱሳንም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛት ይዕቲ ምዕራፍየ ለዓለም"። መዝ 131፥13-14 ወይም መዝ 120፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-19፣ 2ኛ ዮሐ 1፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 27፥31-38። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥39-46። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ከሰባቱ ከዋክብትን አንዱ ለሆኑት ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ በመሔድ ታላቁ ገዳም ደጋ እስጢፋኖስን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት አቡነ ኂሩተ አምላክ ዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ ዘጣና፡- ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኵስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ "ዓቃቤ ሰዓት" እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ ❤ ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡ ❤ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ "ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ" ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ "ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት (ገንፎ)" ብለው በመናገር ምላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡ ❤ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ❤ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ከአቡነ ኂሩተ አምላክ ረድኤት በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw