uz
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Kanalga Telegram’da o‘tish

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Ko'proq ko'rsatish
1 161
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
#ሚካኤል ስዩም ሚካኤል ስዩም ስዩም ሊቀ መላእክት መዝገበ ርህራሄ/3*/ ወየውሃት #ትርጉም የመላእክት አለቃቸው ሆነህ የተሾምክ ሚካኤል የዋስትና እና የርህራሄ መዝገብ በልብህ ያለ አንተ ነህ። ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        ★ https://t.me/Eotcw

#አንተኑ አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ ወአንተኑ ለእስራኤል መና ዘአውረድከ #ትርጉም ለእስራኤል መና ያወረድክ ቅዱስ ሚካኤል አንተ ነህ ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        ★ https://t.me/Eotcw

#ባርከን ባርከን አባታችን ቅዱስ ሚካኤል/3*/ ተቀበል/3*/ ስማን ፀሎታችንን ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        ★ https://t.me/Eotcw

#ነዋ ሚካኤል ነዋ ሚካኤል መልአክ ክሙ ይስአል ለክሙ በእንተ ምህረት/2*/ #ትርጉም እነሆ ሚካኤል መልአካችሁ ስለ እናንተ ምህረት ይለምናል ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        ★ https://t.me/Eotcw

#ንግረኒ ንግረኒ እስመ አጽናዕከኒ ወይቤለኒ ሶበ ተአምር ዳዕሙ ሚካኤል መልአከክሙ #ትርጉም ንገረኝ አፅናኝ እንዲህም በለኝ ሁ ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        ★ https://t.me/Eotcw

photo content
+8

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም 12/03/2015 ዓ.ም

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ሰላም ውድ የማህበረ ሰዋስው ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እያለን የዚህን ግሩፕ መከፈት አንደኛ አመት መሙላት ልናበስራችሁ እንወስዳለን ! ባሳለፍነው ፲፪ ወራት ውስጥ የተለያዩ የትምህርቶችን ፣ የየበአሉን ስርአተ ዋዜማና ስርአተ ማህሌት ፣የየእለቱን ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ስናቀርብ ነበረ አሁንም ይቀጥላል ። ይህ ቻናል ለብዙ ክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶቻችን እንደሚጠቅም ተስፋ ሰንቀን በቀጣይ የምንሰጣቸውን ፕሮግራሞች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለማስፋፋት እየሰራን ነዉ ። ውድ የዚህ ግሩፕ ቤተሰቦች እናንተም በቅርብ ያሉትን እህትና ወንድሞቻችን ቤተሰብ እንደምታደርጉ ተስፋ እያደረግን የዚህ ቻናል እና ግሩፕ እውን መሆን እንዲሁም በተለያየ ነገር ላገዛችሁን በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን በድጋሚ እንደሚታወቀው በነገው እለት አመታዊ የቅዱስ ሚካኤል በአል ይከበራል ስለዚህ እናንተም በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ ሁኑ ወስብሐት ለእግዚአብሔር https://t.me/EOTCWW

+1
#ምስባክ ፦ መዝ ፳፥፩-፫ እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ። ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ። ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ። #ትርጉም ፦ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው

🍀🍀🍀🍀🍀🍀 የኅዳር ፲፪ ምስባክ 🍁🍁🍁🍁🍁🍁 ዘነግህ መዝ ፳፤፩ ወንጌል ፦ሉቃ ፲፱፥፲፩-፳፰ እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ ፣ ወብዙሀን ይትሐሠይ በአድኀኖትከ፣ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ። ምስባክ ዘቅዳሴ ሮሜ፦፱፥፲፯-፳፬ ይሁዳ፦፩፥፱-፲፬ ግብ.ሐዋ፦፳፥፳፰-፴፩ ወንጌል፦ማቴ ፲፰፥፲፭-፳፩ ቅዳሴ፦ተንሥኡ ወይም ዘባስልዮስ ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ፣ ለእለ ይፈርህዎ ወያድኀኖሙ፣ ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ✝ ✝🇪🇹✝መዝ ፴፫፤፯ ✝ 🇪🇹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🇪🇹 ✝ መልካም አገልግሎት ✝ 🇪🇹🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🇪🇹

photo content

photo content

?❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይለ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ይሰአል ለነ ይኩነነ አመ ምንዳቤነ ሰፊሖ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ"። ትርጉም፦ የኃይል መልአክ ሚካኤል ነው (ሚካኤል ኃያል መልአክ ነው) ይለምንልናም ረዳትም ይሁነን በችግራችን ጊዜ ክንፉን ዘርግቶ በላያችን ይጋርደ፡፡ + + + ❤ የዕለቱ እግ.ነግ ዓራራይ ዜማ፦ "ሚካኤል መልአክ ሰኣል ወጸሊ በእንቲአነ ወበእንተ ነፍሰ ኲልነ መልአኪየ ይቤሎ እመላእክት ሰምሮ መልአከ ኪዳኑ ለክርስቶስ"። ትርጉም፦ ሚካኤል መልአክ ስለ እኛ ለምን ጸልይ ስለሁላችን ነፍስ ከመላእክት ወዶ መልእክተዬ አለው፡፡ የክርስቶስ የቃል ኪዳኑ መልአክ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። https://t.me/Eotcw

❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን ለሰው ወገን ለሚያዝንና ለሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረት ሁሉ ለሚማልድ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ሲወጡ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ጋር በሆነ ሕዝብ በመንዳቸው ሁሉ እየመራ የኤርትራ ባሕር ለከፈለበት፣ ለነዌ ልጅ ለነቢዩ ለቅዱስ ኢያሱ፡ለተገለጠለት፣ ዱራታዎስና ሚስቱን ቴዎብስታ ለረዳበት ዓመታዊ በዓልና ለኢትዮያዊው ንጉሥ ለጻድቁ በእደ ማርያም ለዕረፍቱ መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በደብረ ማህው ከታየችበት፣ ከእስክድርያ ስልሳ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት ከአባ ፊላታዎስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለሚካኤል መልአከ ኃይል" ትርጉም፦ የኃይል መልአክ ለኾነ ለቅዱስ ሚካኤል ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። ❤ ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው "ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" አለው። "እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ" አለው። ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና "በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል?" አለው። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን "የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ። እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው "በውስጧ ያለውን ንጉሷን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ"። ❤ ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጽናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው። ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባልክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና። + + + ❤ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፦ እንዲህም ሆነ እግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢ ያደርጉ ነበር ከዚህም በኋላ በአገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ ለዚህም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉት አጡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሔደ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኰንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት ወደ ባለ በጎች ሒዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሒዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ግን መልአኩ ወደ ቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ ወደ ባለ ሥንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ። ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው። እጅግም አደነቀ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደ አደረገ። የተራቡ ድኆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደየቤታቸው አሰናበታቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው። ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሠነጥቅ አዘዘው። በሠነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ተገኘ። ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው "ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሣውና ለባለ ሥንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ። በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል" አላቸው። ❤ እነርሱም ሲሰሙ ስለዚህ ነገር ደነገጡ እርሱም "ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም" አላቸው። ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ። እነርሱም ሰገዱለት ተአምራቱም የማይቈጠር ብዙ ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ፊላታዎስ፦ በእስክንድርያ ከተሾሙ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ ነው። በሹመቱ ወራት የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደ ኖባ ንጉሥ ወደ ጊዮርጊስ እንዲህ ብሎ የመልክት ደብዳቤ ጻፈ "ወንድሜ ሆይ ከሊቀ ጳጳሳት ቆዝሞስ ጊዜ ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ጳጳስ ስለ ሌለን እኛ በታላቅ ችግር ውስጥ እንዳለን ዕወቅ። ይህም የሆነው ተንኰለኛው ሚናስ በተንኰልና በሐሰት ነገር የከበረ ጳጳሳችንን ጴጥሮስን ከሹመቱ ወንበር እንዲሰደድ ስለ አደረገው ነው። ስለዚህ አምስት ጳጳሳት እስቲአልፉ ለአገራችን ጳጳስ አልተላከም። አሁንም ስለ እግዚአብሔር ብለህ ስለ ቀናች ሃይማኖትም በድካም ከእኛ ጋር አንድ በመሆን ስለእኛ ወደ ግብጽ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ ፊላታዎስ ጳጳስ ይልክልን ዘንድ ከራስህ ደብዳቤ እንድትጽፍለት እለምንሃለሁ" የሚል ነበር። ❤ በዚያንም ጊዜ የኖባ ንጉሥ ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስን ይሾምላቸው ዘንድ የልመና ደብዳቤ ወደ አባ ፊላታዎስ ጻፈ ይህ ቅዱስ ፊላታዎስም ልመናውን ተቀብሎ ከአስቄጥስ ገዳም ስሙ ዳንኤል የሚባል አንድ ጻድቅ መነኰስ አስመጣ እርሱን ጵጵስና ሹሞ ወደ ኢትዮጵያ አገር ላከው ወደ እነርሱም በደረሰ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች በታላቅ ደስታ ተቀበሉት። በዚህም አባት ፊላታዎስ ዘመን ብዙ ተአምራት ተገልጠዋል ኅዳር 12 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ፊላታዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 12 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ። ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ። ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ"። መዝ 20፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ19፥11-28።

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ 6፥ 5-16 - "ወሶበሂ ትጼልዩ ኢትኩኑ ከመ መደልዋን" - ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.38 KB

11/3/2015 ዓ.ም (፲፩/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት። ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ። እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ። መዝ 78 ፥ 8 🕯 ትርጉም የቀደመው በደላችንን አታስብብን። ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን። እጅግ ተቸግረናልና። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 3:23-ፍ፡ም፡ " ወየአክል ፴ ክርምቱ ለኢየሱስ" - "ኢየሱስም፡ሊያስተምር፡ሲጀምር፡ዕድሜው፡ሠላሳ፡ዓመት፡ያህል፡ሆኖት፡ነበር፤ እንደመሰላቸው፡የዮሴፍ፡ልጅ፡ሆኖ፥የኤሊ፡ልጅ፥ የማቲ፡ልጅ፥ የሌዊ፡ልጅ፥የሚልኪ፡ልጅ፥የዮና፡ልጅ፥ የዮሴፍ፡ልጅ፥የማታትዩ፡ልጅ፥የዓሞጽ፡ልጅ፥ የናሖም፡ልጅ፥የኤሲሊም፡ልጅ፡ የናጌ፡ልጅ፥ የማአት፡ልጅ፥የማታትዩ፡ልጅ፡የሴሜይ፡ልጅ፥ የዮሴፍ፡ልጅ፥ የዮዳ፡ልጅ፥የዮናን፡ልጅ፥የሬስ፡ልጅ፥የዘሩባቤል፡ልጅ፥ የሰላትያል፡ልጅ፥የኔሪ፡ልጅ፥ የሚልኪ፡ልጅ፥ የሐዲ፡ልጅ፥የዮሳስ፡ልጅ፥የቆሳም፡ልጅ፥የኤልሞዳም፡ልጅ፥የኤር፡ልጅ፥ የዮሴዕ፡ልጅ፥ የኤልዓዘር፡ልጅ፡የዮራም፡ልጅ፥የማጣት፡ልጅ፥የሌዊ፡ልጅ፥ የስምዖን፡ልጅ፥የይሁዳ፡ልጅ፥የዮሴፍ፡ልጅ፥ የዮናን፡ልጅ፥የኤልያቄም፡ልጅ፥የሜልያ፡ልጅ፥ የማይናን፡ልጅ፥የማጣት፡ልጅ፥የናታን፡ልጅ፡ የዳዊት፡ልጅ፥ የእሴይ፡ልጅ፥የኢዮቤድ፡ልጅ፥የቦዔዝ፡ልጅ፥ የሰልሞን፡ልጅ፥ የነአሶን፡ልጅ፥የዐሚናዳብ፡ልጅ፥ የአራም፡ልጅ፥የአሮኒ፡ልጅ፥የኤስሮም፡ልጅ፥ የፋሬስ፡ልጅ፥ የይሁዳ፡ልጅ፥የያዕቆብ፡ልጅ፥የይሥሐቅ፡ልጅ፥ የአብርሃም፡ልጅ፥የታራ፡ልጅ፥ የናኮር፡ልጅ፥የሴሮህ፡ልጅ፥ የራጋው፡ልጅ፥የፋሌቅ፡ልጅ፥የአቤር፡ልጅ፥ የሳላ፡ልጅ፥ የቃይንም፡ልጅ፥የአርፋክስድ፡ልጅ፥ የሴም፡ልጅ፥የኖኅ፡ልጅ፥የላሜህ፡ልጅ፥ የማቱሳላ፡ልጅ፥ የሔኖክ፡ልጅ፥የያሬድ፡ልጅ፥ የመላልኤል፡ልጅ፥ የቃይናን፡ልጅ፥የሄኖስ፡ልጅ፥የሴት፡ልጅ፥ የአዳም፡ልጅ፥የእግዚአብሔር፡ልጅ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.25 KB

11/3/2015 ዓ.ም (፲፩/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን። ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዓይኒሁ ለያዕቆብ። መዝ. 86፥1 🕯 ትርጉም መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራራዎች ናቸው። ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ። እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯