ሰዋስው ☘☘☘☘
Kanalga Telegram’da o‘tish
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Ko'proq ko'rsatish1 161
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን ክርስቶስ ለሚወዱ ለቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ ለመታሰቢያ በዓላቸው በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ፦ እነርሱም ከአንጾኪያ ከተማ ነበሩ። በወርቅና በብርም የከበሩ ባለጸጎች ነበሩ ከገንዘባቸውም ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር።
❤ ከዚህም በኃላ አንድ ወንድ ልጅና አንዲት ሴት ልጅን ወለዱ ወንዱን ዮሐንስ ሴቲቱንም ማርያም ብለው ሰየሟቸው ልጆችም አደጉ እንዱራኒቅስና ሚስቱም እንግዳ በመቀበል ለድኆችና ለምስኪኖች በመመጽወት በጎ ሥራን አበዙ እነርሱም መገናኘትን ትተው ሰውነታቸውን በንጽሕና ጠበቁ።
❤ ልጆቻቸውም ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆናቸው ጊዜ የሆድ ዝማ በሽታ ታመው በአንዲት ቀንም ሞቱ እንዲራኒቆስም አይቶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ራሱን ጥሎ እንዲህ ብሎ አለቀሰ "ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ወጣሁ ወደ እግዚአብሔርም ራቁቴን እሔዳለሁ እርሱም ሰጠ እርሱም ወሰደ የእግዚአብሔር የጌትነቱ ስም የተባረከ ይሁን ለዘላለሙ አሜን"። እናታቸውም ለሞት እስከምትደርስ እጅግ አዘነች ልጆቿ ወደ ተቀበሩበት ወደ ዐፀደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ከኀዘንዋም ብዛት የተነሳ አንቀላፋች በእንቅልፏም ውስጥ "በልጆችሽ ሞተ አታልቅሺ እነርሱ ግን በሰማያት ደስ እያላቸው ናቸው" እያለ በመነኰስ አምሳል ሲነግራት አየች። ይህንንም ሰምታ ሒዳ ለባሏ ነገረችው።
❤ ከዚህም በኃላ ይህን ዓለም ይተዉ ዘንድ ተስማሙ ገንዘባቸውንም ሁሉ ምንም ሳያስቀሩ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጡ በሌሊትም ወጥተው ወደ እስክንድርያ ከተማ ደረሱ ሚስቱንም በዚያ ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ። ከዚያም ተመልሶ ሚስቱ አትናስያን ወደ ሴቶች ደናግል ገዳም ወሰዳት በዚያም ተዋት።
❤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም በኋላ እንድራኒቆስ ከቅዱሳት መካናት ይባረክ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ አባ ዳንኤልን ለመነው ፈቀደለትም በመድኃኒታችንም ቸርነት ሚስቱ አትናስያ በወንድ አምሳል በጉዞ ላይ ተገናኘችው ሚስቱ እንደሆነችም አለወቀም እርሷ ግን አወቀችው ነገር ግን ሚስቱ እንደሆነች አልገለጠችለትም።
❤ ወደ ቅዱሳት መካናትም በደረሱ ጊዜ ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አባ ዳንኤል በአንድነት ተመለሱ። አባ ዳንኤልም ሚስቱ እንደሆነች በመንፈስ ቅዱስ አውቆ እንድራኒቆስን "ባልንጀራ ካደረግኸው ከዚህ መነኰስ ጋራ በአንድ ቦታ ኑሩ እርሱ ቅዱስ ነውና" አለው። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በአንድነት ኖሩ ማንም የአወቀ አልነበረም።
❤ አባ ዳንኤልም ይጎበኛቸውና ስለ ነፍሳቸው ጥቅም ያስተምራቸው ነበር። ከዚህም በኃላ አትናስያ በታመመች ጊዜ ለእንድራኒቆስ "አባታችንን አባ ዳንኤልን ጥራልኝ" አለችው ሒዶም ለአባ ዳንኤል እንዲህ ብሎ ነገረው "ባልንጀራዬ ታሞ ለመሞት ተቃርቧልና ትጎበኘው ዘንድ ና"። በደረሰም ጊዜ በታላቅ ሕመም ላይ አገኛት እርሷም "ታቆርበኝ ዘንድ እሻለሁ" አለችው ያን ጊዜም ተፋጠነና ሥጋውንና ደሙን አቀበላት ከዚህም በኋላ አረፈች በሚገንዟትም ጊዜ ሴት እንደሆነች አገኙ ዳግመኛም ታሪኳንና ለባሏ ያወራቻቸውን ምልክቶች አገኙ።
❤ እንድራኒቆስም በአነበበ ጊዜ እርሷ ሚስቱ እንደሆነች አወቀ ደንግጦም ልቡ ተሠወረ ፊቱንም እየጻፈ ጮኸ ያለቅስ ጀመረ። ከጥቂት ቀን በኋላም ታመመ አረጋውያንም መጥተው በረከቱን ተቀበሉ ሥጋውንና ደሙንም ተቀበሉ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ እንድራኒቆስ በሚስቱ አትናስያ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 28 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰአሉ ለነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ አበወ ሕዝብ ወአሕዛብ ወዘመሐይምናን መክብብ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ"። ትርጉም፦ የምዕመናን ሹሞች የአሕዛብና የሕዝብ አባቶች አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ፈጽማችሁ ለምኑልን፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ላይ፡፡
+ + +
❤ "ሰላም ለእንድራኒቆስ ለምኔተ አስቄጥስ ዘሐወጻ። እንዘ ይዘሩ ብዕሎ ዘኢኮነ ብዕለ ዐመፃ። ወለአትናስያ ሰላም ለነቢር ዘተባየፃ። ከመ ይእቲ ብእሲቱ እንበለ ይጠይቅ ገጻ። እስመ አዕፅምቲሃ በጽምእ ከመ ሣዕር ነቅጻ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 28።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወአንተሰ ብእሲ ዘከመ ነፍስየ። ማእምርየ ወዐውቅየ። ዘኅቡረ አስተጠዓምከ ሊተ መባልዕተ"። መዝ 54፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ 7፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 7፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ፊሊጶስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ስለ አሁኑ ዘመን የአቡነ ፊሊጶስ ትንቢት!፡- በወቅቱ የነበሩት ጳጳስ አባ ያዕቆብ በብዙ ልመናና ምክር አቡነ ፊሊጶስን ጳጳሱ ራሱ የሚለብሰውን የክብር ልብስ አልብሶ በሸዋ አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾመው፡፡ ከተሾሙም በኋላ አቡነ ፊሊጶስን "ሌሎችን ሹምልን" የሚሉ በርካቶች ሲያስቸግሯቸው እሳቸው የሰጡት ምላሽ "በሥልጣን ፍለጋ ምክንያት ይህችን የትርህምትና የፅሙናን ቦታ (ደብረ ሊባኖስን) የጨዋታ የተድላ ቦታ እናደርጋታለን" በማለት በወቅቱ ማንንም አልሾምም ብለው ነበር፡፡
❤ አያይዘውም በዚሁ በሹመት ሽኩቻ ምክንያት ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ መነፅርነት አይተውት የሚከተለውን ትንቢት ተናግረዋል፡- "እውነት እላችኋለሁ በመጨረሻው ዘመን ደጋጎች ሰዎችን ክፉዎችና ተሳዳቢዎች የሚያደርጉ፣ ሐሰተኞችና ዋዛ ፈዛዛ የሚወዱትን ደጋጎች የሚያደርጉ ሰዎች ይመጣሉ፡፡ በመጨረሻው ዘመን ኃጥአን በጻድቃን ይመሰላሉ፣ ጻድቃንን ኃጢአተኞች ያደርጓቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን እውነተኛዎቹ መምህራን አይሾሙም፣ ኃጢአተኞች መማለጃ ሰጥተው ወሬ እያቀበሉ ይሾማሉ፣ እንደ እባብ ክፉ ነገርን ለማድረግ ፍላፃቸውን ያሾሉ ደጋግ ሰዎችን በነገር ያጠፏቸው ዘንድ በእውነት ንጹሕ የሆኑትን ሰዎች አመፅን በተመላ አንደበታቸው ሹመትን ከመውደድ የተነሣ በቅናት ያጠፏቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን መጻሕፍትን የሚያውቁ አይሾሙም፣ ነገርን የሚያመላልሱና የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቁ ከመኳንንትና ከነገሥታት ዘንድ ሔደው ነገርን የሚሠሩ ሰውን የሚያጣሉ በአመፅ ሹመትን የሚያገኙ ብቻቸውን ይሾማሉ እንጂ ደጋጎች አይሾሙም፡፡ በሚመረጡበትም ጊዜ ከአባታቸው ከሰይጣን ጋር ሆነው "እገሌ መጻሕፍትን ያውቃል፣ የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቅ ይሾም" ይላሉ፡፡ ያንጊዜም አመፅ ይበዛል፣ ፍቅርም ትጎድላለች፡፡ ከእኔ በኋላ የሚሆነውን እነሆ ነገርኳችሁ ይህንንም አውቃችሁ በልቡናችሁ ያዙ"፡፡
❤ ጌታችን ለአቡነ ፊሊጶስ የገባላቸው ልዩ ቃልኪዳን፡- "ገድልህንና ስለ እኔ የታገስከካቸውን መከራዎችህን የጻፈውን ከሁላቸው ከቅዱሳንና ከሰማዕታት ጋር በሰማያዊት ኢየሩሳሌም በወርቀ ቀለም ለዘለዓለሙ ስሙን እጽፍልሃለሁ፡፡ ሥጋህ ከተቀበረበት ቦታ ይቅርታዬንና ቸርነቴን አደርጋለሁ፡፡ መቃብርህ የበረከት ቦታ ትሆናለች"። ከአባታችን ከአቡነ ፊሊጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለደብረ ሊባኖስ ሦስተኛ አበምኔት (እጨጌ) ለአቡነ ፊሊጶስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ "አመ ትቀውም በሥልጣንከ እግዚአብሔር ፈጣሪ። እም ዓለም አበው ቀደምት እስከነ ምጽአትከ ዘደኃሪ። ክበደ ጌጋዩ ወንጽሑ እንዘ ለለርእሱ ያጠሪ። ኦ መሐሪ ወወልደ አምላክ መሐሪ። በእንተ ፊልጶስ ረድእ አበሳየ ሥሪ"። መልክዐ አቡነ ፊልጶስ።
+ + +
❤ የደብረ ሊባኖሱ እጨጌ አቡነ ፊሊጶስ፡- በተወለዱ በ15 ዓመታቸው በምናኔ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገቡ፡፡ ከብዙ ጊዜ አገልግሎትም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት እጅ መንኲሰው ከእርሳቸውም ዕረፍት በኋላ ሦስተኛ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከተወለዱት የመጀመሪያ ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ አባታቸው ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በመንፈቀ ኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ነበር፡፡
❤ በመጀመሪያ የአቡነ ፊሊጶስን የጽድቅ ሕይወትና ሹመታቸውን በተመለከተ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድልና በራሳቸው በአቡነ ፊሊጶስ ገድል ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- "ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚህ ዓለም ተለይቶ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ "ከአንተ በኋላ አንተን ተክቶ በዙፋንህ የሚቀመጥ ማነው?" አሉት፡፡ እርሱም "ብዙ ዘመን አይኖርም እንጂ ኤልሳዕ በእኔ ተተክቶ ይቀመጥ" አለ፡፡ ስለ ፊሊጶስ ግን አላነሳም፣ ኤልሳዕ ካረፈ በኋላ በእርሱ ተተክቶ አባት ይሆን ዘንድ ጌታችን የተሸለመ ፊሊጶስን እንደመረጠው ስም አጠራሩ ለልጅ ልጅ ዘመን እንደሚጸና ያውቅ ነበርና ስለዚህ "አልሳዕ በእኔ ተተክቶ አባት ይሁናችሁ" አለ፡፡ ክቡር አባታችንም በታላቅ ክብር ዐረፈ፡፡
❤ አንድ ቀን አንድ ዲያቆን ዐረፈና ሬሳውን ገንዘው አጠቡት፣ ይቀብሩትም ዘንድ አስክሬኑን ይዘው ሲሄዱ በአልጋ ላይ ሳለ አስክሬኑ ተንቀሳቀሰ፡፡ የተሸከሙትም ደንግጠው መሬት ላይ አስቀመጡትና ከመግነዙ ፈቱት፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሦስት ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ወንድሞችም "ምን እያልክ ነው?፣ ወዴትስ ነበርክ?" አሉት፡፡ ያ የከበረና የተመረጠ ዲያቆንም "ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት "ኤልሳዕ ወደኔ ይምጣ፣ ፊሊጶስ ስለ እኔ ተሹሞ በወንበሬ ይቀመጥ እርሱ ለብዙዎች አሕዛብ አባት ይሆናልና የክርስቶስንም መንጋ በጽድቅና በቅን ይጠብቃል ብሎኛል" ብሎ ይህን ተናግሮ ተመልሶ ዐረፈ፡፡ ወንድሞችም ኤልሳዕ እንደልማዱ ጎኑን ሳያሳርፍ በወንበር ላይ እንደተደገፈ በሞት ማረፉን አላወቁም ነበር"፡፡
❤ ወደ ጻድቁ የልጅነት ገድላቸው እንመለስና አቡነ ፊሊጶስ በእግዚአብሔር ተመርጠው የመንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ሆነዋልና ገና በሕፃንነታቸው በተወለዱባት ሰላሌ ክፍለ ሀገር ዝማ በምትባል ልዩ ቦታ ውስጥ ሰይጣን በጠንቋይ ላይ አድሮ በነደደ በእሳት ውስጥ በመግባትና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ በአካባቢው ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን በእሳት ውስጥ እንዳለ በስመ ሥላሴ አማትበውበት አመድ አድርገውታል፡፡ በዚህ በአቡነ ፊሊጶስ ድንቅ ተአምር የጠንቋዩ ቤተሰቦችና የአካባቢው ሰዎችም አምነው ሊጠመቁ ችለዋል፡፡ ይህንንም ያደረገው ገና ሕፃን ሳለ ነው፡፡
❤ መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦለት የትውልድ መንደሩን ትቶ ወደ ግራርያ ሀገር ደብረ አስቦ ሄዶ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን እንዲያገኝ በነገረው መሠረት አንድ ቀን ያህል ተጉዞ ተክለሃይማኖትን አገኛቸውና ባርከውት ከመነኰሳት ጋር እንዲያርፍ አደረጉት፡፡ ሦስት ዓመት እነርሱን በመልካም ሥራ ፍጹም ሆኖ ሲያገለግላቸው ከቆየ በኋላ "ሁሉም በአንድነት አሁን ልብሰ ምንኵስና ይገባዋል" አሉ፡፡ ቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖትም የምንኵስናን ሥራ የሚያሠራ ቅድስናን ሰጠው፡፡ በሌላም ጊዜ ቅስናን ይቀበል ዘንድ ወደ ጳጳሱ ዘንድ ላኩት፡፡ አቡነ ፊሊጶስ በንጉሥ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ሲገረፉ ደማቸው እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያሳደደ ቅዱስና ጻዲቅ አባት ናቸው፡፡
❤ ንጉሥ አምደ ጽዮን በክፉ ጠንቋዮች ምክር ተታሎ "ያልወለደችህን የአባትህን ሚስት ብታገባ መንግሥትህ ትፀናለች" ብለው ክፉ ምክርን መክረውት የእንጀራ እናቱን አገባትና ንግሥት አደረጋት፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ይህን ሲሰሙ ነቢዩ ኤልያስ ንጉሡ አክአብንና አልዛቤልን በድፍረት እንደገሠጻቸው እርሳቸውም በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ዘልፈው ገሠጹት፡፡ ወደ ንጉሡም ከመሄዳቸውም በፊት በዚህ ምክንያት ሰማዕት እንደሚሆኑ አውቀውት ነበርና ልጆቻቸውን ተሰናብተውና የሚተካቸውን ሰው ነግረዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ንጉሡ አምደ ጽዮንም አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ አስገረፋቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም መሬት ላይ እየተቆረሰ የወደቀውን ሥጋቸውን እያነሱ ለበረከት ወሰዱት፡፡ ደማቸውም እንደ እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያቃጥላቸው ነበር፡፡ 300 እንስራ ውኃ አምጥተው ከደሙ በወጣው እሳት ላይ ቢያፈሱትም የውኃው ብዛት እሳቱን ማጥፋት አልቻለም፡፡ ንጉሡም በፍርሃት ከዙፋኑ ላይ ወርዶ ሸሸ፡፡
❤ የንጉሡ ጭፍሮች ግን በጋለ ማረሻ ጀርባና ግንባራቸውን ደረታቸውንም ተኮሷቸው፡፡ ኃፍረታቸውንም እንዳይሸፍኑ እጆቻቸውን ወደ ኋላ አስረው ራቁታቸውንም በከተማው ሁሉ ሲያዞሯቸው ዋሉ፡፡ ማታም ንጉሡ "ታስረው ለኖሩ ኃይለኛ ውሾች ስጡት" ብሎ በማዘዝ ውሾቹ እንዲቦጫጭቋቸው ቢያደርጉም ውሾቹ ግን ከእግራቸው ስር ሰግደዋል፣ እርሳቸውም በእግራቸው ባረኳቸው፡፡ አማካሪዎቹም ንጉሡን "ከዚህ መነኩሴ ጋር ምን አጨቃጨቀህ በግዞት አርቀህ ስደደው ብለው" ብለው መክረውት "እስከ ቆርቆራ አገር አውጥታችሁ ወደ ትግሬ አገር ውሰዱት" ብሎ አዘዘ፡፡ እርሳቸውም ንጉሡን ከ3 ዓመት በኋላ ትሞታለህ ብለው ትንቢት ነገረውት በወታደሮች ተወሰዱ፡፡ በግርፋት ብዛት የተቆረሰ ሥጋቸው ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ደማቸውም አስረው የሚወስዷቸውን የአንዱን ወታደር አንድ ስውር ዐይኑን ፈወሰለትና ወታደሮቹም አምነው ከእርሳቸው ጋር በዚያው ተሰደው መከራን ተቀብለዋል፡፡ እሳቸው በትግራይ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ ሲያስተምሩ በትንቢታቸው መሠረትም ንጉሡ ከሦስት ዓመት በኋላ ሞተና ልጁ ነገሠ፡፡ ልጁም አባታችንን ከስደት መለሳቸውና ከተክለሃይማኖት መቃብር ደብረ አስቦ ገቡ፡፡
❤ የነገሠውንም ልጅ አንድ ክፉ ሰው "ከአንድ በላይ ማግባት ትችላለህ፣ በገና ወቅትም ረቡዕና አርብን መጾም ተገቢ አይደለም" ብሎ ስለመከረው ጳጳሱን ወደ ሀገራቸው ግብፅ እንዲሰደዱ ሲያደርግ አቡነ ፊሊጶስን ደግሞ "ረቡዕና አርብን በጠዋት ካልቀደስክ" ብሎ ወደ ደራ ተሰደው እንዲሄዱ አደረገ፡፡ አባታችን በአጠቃላይ አምስት ጊዜ ተሰደው በትግራይ፣ በደራ፣ በዝዋይ ባሕረ ደሴት፣ በዳሞት ገማስቄ እና በወለቃ በስደት ቆይተዋል፡፡ ጳጳሱን አባ ሰላማን በአቃሊት ቅበረኝ ብለዋቸው በቃሬዛ አድርጎ ከጌርጌሳ ወደ አቃሊት ወሰዷቸው፤ እዚያም ሐምሌ 28 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ አጽማቸውም ከተቀበረ ከ140 ዓመት በኋላ በመጋቢት 23 ቀን ወደ ደብረ ሊባኖስ በክብር መጥቶ ዐርፏል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰባት አክሊላት አቀዳጅቷቸዋል፡፡
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን ለነቢዩ ሕዝቅኤል ለራእዩ መታሰቢያ ቀን በዓል፣ ለአዳም ልጅ ለቅዱስ ሴት ለዕረፍት በዓል፣ ለወንጌላዊው ለቅዱስ ዮሐንስ በእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት በዓልና ተርኑጥ ከሚባል አገር ሰው ለሆነ ለቅዱስ አሞን ሰማዕትነት ለቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕቱ ቅዱስ አሞን ጋር ሰማትነት ከተቀበለች ከድንግል ቅድስት ትዮጲላ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትን በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለሴት ተክለ አቤል ርእሰ አበው። ተዘከረኒ እግዚኦ በምረትከ በእንተ ሴት ገብርከ ዘዓቀበ ትእዛዘከ ሕገከ ወሥርዓተከ፣ መሐረኒ በእንቲኣሁ ወአድኅነኒ እምሲኦል መሪር ለገብርከ አሜን"። ትርጉም፦ የአባቶች ራስ ለኾነ ለአቤል ምትክ ለሴት ሰላምታ ይገባል፤ አቤቱ ትእዛዝኽን ሕግኽንና ሥርዐትኽን የጠበቀ ስለኾነ ስለ አገልጋይኽ ስለ ሴት በምሕረትኽ ዐስበኝ፤ ስለ ርሱ ብለኽ ማረኝ፤ ከመሪር ሲኦል እኔን አገልጋይኽን አድነኝ፤ አሜን። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ የአዳም ልጅ ቅዱስ ሴት፦ ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ ሔኖስንም ወለደው። ሔኖስንም ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ዓመት ኖረ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። መላ እድሜውም ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ሆነ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ አሞን፦ ይህም ቅዱስ ተርኑጥ ከሚባል አገር ሰው የሆነ ነው። ወደ ላይኛው ግብጽ በሔደ ጊዜ የቅዱሳን ሰማዕታት ግፍ ተመለከተ ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስም ቀርቦ ክብር ይግባውና በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ታላቅ ስቃይ አሠቃየው ሥጋውን ሁሉ ሠነጣጠቀው እረጃጅም በሆኑ በተሳሉ በብረት ችንካሮች ቸነከሩት ጌታችንም ያጸናውና ያስታግሠው ያለ ጉዳትም በጤና ያስነሣው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ በዚያ ያሠቃዩት ዘንድ ወደ እስክንድርያ ከተማ ሰደደው ክብር ይግባውና ጌታችንም ለእርሱ ተገልጦ መታሰቢያው ለሚያደርግ፣ ገድሉንም ለሚጽፍ ስሙንም በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው። ይህን ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ አባ አሞንም ፈጽሞ ደስ አለው።
❤ ከዚህም በኋላ በዚያ ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሥቃዩ ሁሉ አዳነው ይህንንም ባዩ ጊዜ ብዙ ሕዝቦች ስለ ርሱ በጌታ አመነው በሰማዕትነት ሞቱ። ከውስጣቸው ቲዮጲላ የምትባል ድንግል ነበረች ወደ መኰንኑ ቀርባ ርሱንና የረከሱ አማልክቶቹን ረገመች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነች። በእሳት ውስጥ እንዲጥሏት አዘዘ እሳቱም አላቃጠላትም ከዚህም በኋላ ራሷን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊል ተቀበለች።
❤ ቅዱስ አሞንንም ብዙ ከአሠቃዩት አባላዘሩንም ቆረጡ ከዚያም እራሱን በሠይፍ ይቆርጡ ዘንድ መኰንኑ አዝዞ ቆረጡት ተጋድሎውንም ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን ፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አሞን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 27 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለአሞን አባላቲሁ ዘቊስላ። በቅንዋተ ኅፂን ዲቤሁ እለ ተተክላ። እስከ አስፈዎ አምላክ ኪዳነ መሐላ። ወሰላም ዓዲ ለድንግል ቲዮጲላ። እንተ ምስሌሁ በሠይፍ መኰንን አቅተላ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 27።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም። ወገብረ መድኃኒተ በማእከለ ምድር። አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ"። መዝ 73፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 18፥20-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወቅዱሰ እስራኤል ንጉሥነ። ውእቱ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ። ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል"። መዝ 88፥18-19። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 5፥7-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 5፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 4፥10-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ10፥30-43። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅድስት መስቀል ክብራ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ለታላቁ ለጻድቅ ንጉሥ ለላሊበላ ባለቤት (ሚስት) ለቅድስት መስቀል ክብራ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ቅድስት መስቀል ክብራ፡- የትውልድ ሀገሯ ትግራይ ሽሮ አካባቢ ነው፡፡ ይኽችም ቅድስት የታላቁ ጻጽቅ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ ባለቤት ስትሆን ሁለቱን ያጋባቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ዲዛኖችና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር ከመለሰው በኃላ ድጋሚ ተገልጦለት "...እንደ አንተ የተመረጠች ናት እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል፡፡
❤ ቅድስት መስቀል ክብራ ከቅዱስ ላሊበላ ይትባረክን የወለደች ሲሆን በ23 ዓመት ውስጥ ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት መስቀል ክብራን መንና ትግራይ ገባች። ወደ ትግራይ እየመራ የወሰዳት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ እርሷን በትግራይ ቅዱስ ሚካኤል እንዲጠብቃት ከተዋት በኃላ ቅዱስ ላሊበላን ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ መንግሥተ ሰማያት አውጥቶታል፡፡
❤ ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ሆና መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃት ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል፡፡ ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች፡፡ ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዲጠመቁ አድርጋለች፡፡
❤ ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ክልል ሽሬ አውራጃ መደባይ ታብር በተባለው ቦታ ላይ በስማ የተሰራ ትልቅ ገዳም አላት። እጅግ ውብ በሆኑ ሰንሰላታማ ትላላልቅ ድንጋዮች መካከል የሚገኝ አስደናቂና ጥንታዊ ገዳም ነው። ገዳሙ ከሽሬ ከተማ በእግር የ 7 ሰዓት መንገድ ያስኬዳል። የቅድስት መስቀል ክብራ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ እግዚአብሔር አምላክ ይማረን፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለአባ ሰላማ ውስተ ምድርነ ዘፈነወ ለብሔረ አግአዚ ጽድቅ ዘዜነወ ትእዛዛተ ሕይወት ዘመጠወ"። ትርጉም፦ የሕይወት ትእዛዛትን የሰጠ ነጻ አውጪ ለኾነች ሀገር ኢትዮጵያ ጽድቅን ያስተማረ፤ ወደ ምድራችን (ወደ ሀገራችን) የተላከ ለኾነ ለአባ ሰላማ ሰላምታ ይገባል"። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፡፡ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ። ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትጹሪዮ ይበኪ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፡፡ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይጸውር ስንቀኪ"። ትርጉም፦ ማርያም! አንድ ጊዜ በጀርባሽ፣ አንድ ጊዜ በጎንሽ ልጅን በማዘል በእጅጉ ደከምሽ በእግሩ በሚሄድበት ጊዜም ትሸከሚው ዘንድ ያለቅሳል ስንቅሽን ከሚሸከም ከሽማግሌው ዮሴፍና ከሰሎሜ በቀር አንችን የሚያስተጋግዝሽ የለም። በሰቆቃወ ድንግል ላይ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
