uz
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Kanalga Telegram’da o‘tish

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service

Ko'proq ko'rsatish
3 586
Obunachilar
-124 soatlar
-17 kunlar
+5430 kunlar
Postlar arxiv
«አንድ ተቋራጭ በመጀመሪያው ዉል (ጨረታ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ) Rebate ቢኖረው እና በዋጋ ንረት ምክንያት የዋጋ ማሻሸያ ቢሰራለት፤ አዲሱ ውል/ የተሻሻለው ውል REBATE ይደረጋል ወይስ አይደ
«አንድ ተቋራጭ በመጀመሪያው ዉል (ጨረታ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ) Rebate ቢኖረው እና በዋጋ ንረት ምክንያት የዋጋ ማሻሸያ ቢሰራለት፤ አዲሱ ውል/ የተሻሻለው ውል REBATE  ይደረጋል ወይስ አይደረግም?» 🏷አንድ የሥራ ተቋራጭ በመጀመሪያው ውል መጀመሪያ ላይ የዋጋ ቅናሽ አቅርቦ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና በኋላ ላይ የዋጋ ማስተካከያ (price adjustment) ከተደረገ በዋጋ ንረት ምክንያት የተሻሻለው ውል ባህሪ በአብዛኛው የሚመሰረተው በውሉ ላይ በተመለከተው «የዋጋ ማስተካከያን በሚመለከት በተቀመጡ ስምምነቶች (terms of price adjustment» ላይ ነው። ለምሳሌ የግንባታ ሥራው የሕንጻ ግንባታ ከሆነ በሀገሪቱ Public Procurement Agency (PPA) General Condition  of Contract, Clause 62 ሥር ባለው ዝርዝር መሰረት የሚዳኝ ይሆናል። ይህንን በሚመለከት ተዋዋዮች በልዩ ድንጋጌ (Special Conditions) ያስቀመጡት ስምምነት ካለ ገዢ ሆኖ ይቆጠራል። 💫ነገር ግን የተለመዱ አሠራሮችን እንደመነሻ ለማንየት ከፈለጉ፦ 1ኛ) በዋጋ ማስተካከያው (adjustment) የተጠየቀበት ምክንያት የዋጋ ንረትን ወይም የግንባታ ቁሳቁስ (Material Cost) ወይም የሰራተኛ ወጭ (Manpower cost) ወይም የማሺነሪና እቃዎች (Machineries anr tools cost) ለውጦችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሆኖ የተሰላ ከሆነ ይህ በአጠቃላይ የውል ዋጋ እንደጨመረ ይቆጠራል እንጂ የዋጋ ቅናሽ አይደለም። ተቋራጩ በዋጋ ንረት ምክንያት የጨመረውን ወጪ እንዲያስተላልፍ ሊፈቀድለት ይችላል፣ ይህም በመጀመሪያ ከተስማማበት ዋጋ በላይ ይሆናል። 2ኛ) የዋጋ ቅናሽ የሚለው ጽንሰሀሳብ በውል ትርጉም መሰረት ተጫራቹ በውድድር ሰዓት ያስገባው ዋጋ አሸናፊ እንዲያደርገው የሚያስገባው በጊዜው የሚተገበር የጠቅላላ ዋጋን (--%) የቅናሽ እድል እንጂ በየጊዜው ተግባራዊ እንዲደረግ የፈቀደው አይደለም። በኋላ ላይ የመጣው የዋጋ ማስተካከያ ተቀናሽን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ሆኖ ሊሰላ ይችላል። ይህም ማለት አዲስ የተሰራው ዋጋ የመጀመሪያውን የዋጋ ተቀናሽ (Rebate) ከግምት ውስጥ ሳያስገባ የተተከለ ዋጋ ሊሆን ይችላል። 3) አንድ ጊዜ አሸናፊ ሆኖ የተዋዋለ ተጫራች በኋላ ለሚመጣው የዋጋ ማሻሻያ ላይ ለሚገባው ውል “ቅናሽ የተደረገ” ተብሎ ሊቆጠር የሚችለበት አግባብ የለም። ምክንያቱም ቅናሹ በመጀመሪያ ስምምነት ላይ በተደረገው ዋጋ ላይ ነው አዲሱ ዋጋ (ከዋጋ ግሽበት በኋላ) ከመጀመሪያው ጨረታ የበለጠ ወጪን የሚያንፀባርቅ ሊሆን ይችላል እንጂ  ተቀናሽን ታሳቢ ማድረጉ ምንም አይነት ጥቅም የለውም። ስለሆነም ቀድሞ የነበረው (ዋናው) ተቀናሽ በዋጋ ግሽበት ምክንያት ተስተካክሎ ይቀራል ማለት ነው።

🔘የዲዛይን ለውጥ ሥራ የማን ኃላፊነት ነው?? በመጀመሪያ ስለዲዛይን ሥራ፦ በተለያዩ አካላት እና በተለያዩ መንገዶች ሊከናወን የሚችል ሲሆን የሚከተሉት መንገዶች ዋናዎቹ ናቸው። [1]. አንድ የፕሮጀ
🔘የዲዛይን ለውጥ ሥራ የማን ኃላፊነት ነው?? በመጀመሪያ ስለዲዛይን ሥራ፦  በተለያዩ አካላት እና በተለያዩ መንገዶች ሊከናወን የሚችል ሲሆን የሚከተሉት መንገዶች ዋናዎቹ ናቸው። [1]. አንድ የፕሮጀክት ባለቤት (client/owner/employer) በግለሰብ ባለሙያ ቢሆን ወይም በድርጅዉ ውስጥ  ድርጅቱ የዲዛይን ባለሙያዎች ያሉት ቢሆን እና ተያያዥ የዲዛይን አማካሪነት ንግድ ፍቃድ ያለው ከሆነ በራሱ ዲዛይን ሊሠራ ይችላል። በዚህ አግባብ የንባታ ባለቤቱም የዲዛይን አማካሪ ድርጅቱም ራሱ ይሆናል ማለት ነው። ተቋራጩ ግንባታ እያከናወነ ያለው ከዚህ አይነት ድርጅት ጋር ተዋውሎ ከሆነ ዲዛይኑን የማሻሻል ኃላፊነቱ ዲዛይኑን የሠራው /የግንባታ ባለቤቱ/ ነው።  [2] አንድ የግንባታ ባለቤት በዘርፉ ዕውቀት ባይኖረው ወይም ተያያዥ የዲዛይን ሥራን ለመሥራት ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ድርጅት ባይኖረው የዲዛይን ሥራውን ሕጋዊ ፍቃድ ላላቸው አማካሪ ድርጅት ሰጥቶ ያሠራል። ይህ በሆነ ጊዜ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር ሁለት አይነት ውል ሊኖራቸው ይችላል። ዲዛይኑን ሰርቶ እስከሚጸድቅ ድረስ በሚሰጡ ሙያዊ አስተያየቶች መሰረት እስከ ማስተካከል ወይም የግንባታ ሂደቱን እስከመቆጣጠር የሚደርስ ውል ሊይዙ ይችላሉ። ነገር ግን ዲዛይኑን የሠራው አማካሪ የተዋዋለው ውል ዲዛይኑ እስከሚጸድቅ ድረስ ብቻ ላለው ግድፈት የሌለበትና የተሟላ ሥራ እስከማስረከብ ከሆነ ግንባታው ከተጀመረ በኋላ በባለቤቱ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ መሐንዲስ በኩል የሚነሱ የዲዛይን ቅያሬ (ማሻሻያዎችን) የማስተካከል ግዴታ የለበትም። ተጨማሪ ውል ካልያዘ በቀር በሀሳብ ለውጥ መሰረት መጀመሪያ በተሰራበት ውል እና ዋጋ እንዲቀይር አይገደድም። ይህ በሚሆንበት ሰዓት ዲዛይን ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግ አዲስ ውል ተይዞ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር ወይም በኮንትራክተሩ በኩል ሊሆን ይችላል። በ'FIDIC MDB-Harmonized Edition sub clause 4.1 እና 13.2  መሰረት "የኮንትራት ውል ስምምነት ሰነዱ የዲዛይን ለውጥ ማሻሻያን ኮንትራክተሩ እንዲሠራ የሚገልጽ ከሆነ  ተቋራጩ አስፈላጊውን የማሻሻያ ንድፈ ሀሳብ (proposal) አቅርቦ በሁለቱም ወገን (both contractor & employer) ስምምነት ላይ ተደርሶ ከተፈረመበት ራሱ ተቋራጩ ሊሠራ ይችላል" ብሎ አስቀምጧል። [3] አንድ የሥራ ተቋራጭ ጎን ለጎን የዲዛይን ፍቃድ ያለው ድርጅት ያለው ከሆነ ዲዛይኑንም ግንባታውንም የሚሠራበት የውል ስምምነት (Contract agreement) መፈራረም የሚችልበት መንገድ ያለ ሲሆን ፕሮጀችት የማስተላለፍ ሂደቱ Design-Build (DB) project delivery method ተብሎ ይጠራል። (ዲዛይኑን የሠራው ይገነባዋል እንደማለት ነው)። በዚህ ሁኔታ ተቋራጩ ራሱ የሠራውን ዲዛይን እየገነባ ከሆነና የዲዛይን ለውጥ ከተፈለገ በአዲስ ውል ታስሮ የተቋራጩ ዲዛይን ቢሮ ተለዋጩን ዲዛይን ሊሠራ ይችላል። [4]... ይቀጥላል

በየቀኑ ለሚወጡ ነፃ ጨረታዎች/
🚧 እና ስራዎች የማቴሪያል/ማሽነሪ ግዥ እና ኪራይ ጨርታ እና ሌሎች ጠቃሚ ተያያዥ መረጃዎች ከስር ባለው ቴሌግራም ቻናል ዌብሳይታችን ላይ በቋሚነት ይለቀቃሉ/ይከታተሉ.. .
👇የቻናል ድህረ-ገፃችን🏗
http://t.me/Con_Site Official              መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ!

+2
Civil engineering objective questions.pdf10.27 MB

ፌሮ የአርማታ ብረት መግዛት ስትፈልጉ ጥሩ ደንበኞች አቅራቢዎች ስላሉን አድራሻቸውን ልንሰጣችሁ እችላለን 📞+251-908280208 | +251- 707999001 | +251-89999001 ለመልዕክት ይ
+2
ፌሮ የአርማታ ብረት መግዛት ስትፈልጉ ጥሩ ደንበኞች አቅራቢዎች ስላሉን አድራሻቸውን ልንሰጣችሁ እችላለን
📞+251-908280208 | +251- 707999001 | +251-89999001 ለመልዕክት ይጠቀሙ, ይደርሰናል
ቴሌግራም መልዕክት መስጫ ቦት
t.me/unitysupplydbot • ••☜|]
ፈጣን ምልሽ ያገኛሉ! ሰናይ ጊዜ🤚

⚠️ጥቆማ! ባንክ እና ሪልስቴት "የባንክ አማራጭ የተዘጋጀላቸው ሪል ኢስቴቶች ካሉ እንዳያመልጡዋችሁ። ካለ ለእኔም ጠቁሙኝ? የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያልቻለው፣ የመንግሥት የኮንስትራክሽን ባንክ ያቃተው፣ቤቶች ባንክ ተቋቁሞ ግራ የተጋባበት ዘርፍ ላይ የትኛው ባንክ ነው ላላለቀ ሪል ኢስቴት የሚመቻቸው? ያለቀውና እየተከራየ ላለው ቤት እንኳ ባንክ እሺ አይልህም:: ያንተ 40 ሺህ ብር ኪራይ ለባንኩ ምን ሊፈይድለት ነው? ቤቱም ካርታው ጥንቅቅ ያለ ከሆነ ለሌላ ቢዝነስ እንደ ማስያዣ ይሆናል እንጂ ባንክ እኮ ቤት ሻጭ አይደለም:: ለሚገነቡት ላይ ባንኩ የእናንተን ቅድመ ክፍያ ሊያመልጠው አይፈልግም:: ግን ቤቱን ስትፈልጉ አያስተናግዳችሁም:: ቅድመ ክፍያው ማለት ከወለድ ነጻ ቁጠባ በሉት:: መኪና ሻጭም ይሁን ሪል ኢስቴት ሻጭ "የባንክ ብድር የተመቻቸለት" ሲል ከየትኛው ባንክ? ብላችሁ ውልና ኮንትራታቸውን ሳታነቡና ባንኩ ጋር ሄዳችሁ ሳታረጋግጡ አትክፈሉ:: ከሀሰን ኢንጃሞ የፋይናንስ አዋቂ እና አማካሪ

🔺RISE Engineering Service አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ 🏗             - የስራው አይነት ኤስ ፒሲ መስራት የሚችል ባለሙያ - የስራ ልምድ ያለው - ብዛት 10 - ደሞዝ በስምምነት - የስራ ቦታ አንፎ አደባባይ
0911404617ወይም በቴሌግራም @RiseEngineering313

Share ታህሳስ ወር የኮንስትራክሽን ማተርያሎች ዋጋ.xlsx

🔺የሳይት መሐንዲስ🏗 የሳይት መሐንዲስ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ፣ በበጀት እና በጥራት ደረጃ መጠናቀቁን በማረጋገጥ በግንባታው ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። 🚧በግንባታ ላይ የሳይት መሐንዲስ
🔺የሳይት መሐንዲስ🏗  የሳይት መሐንዲስ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ፣ በበጀት እና በጥራት ደረጃ መጠናቀቁን በማረጋገጥ በግንባታው ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። 🚧በግንባታ ላይ የሳይት መሐንዲስ ዋና ዋና ኃላፊነቶች መካከል፡- 1. የግንባታ ሥራዎችን የመቆጣጠር፡ የሳይት መሐንዲስ በየእለቱ የሚከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን የመቆጣጠር፣ በፕሮጀክት መሥፈርቶችና በፕሮጀክት መሥፈርቶች መሠረት መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የጊዜ መስመር. 2. የጥራት ቁጥጥር፡- የሳይት መሐንዲሱ ሥራ በፕሮጀክት ዝርዝር መግለጫዎች እና በኢንዱስትሪ ደንቦች የተቀመጡ የጥራት ደረጃዎችን የማሟላቱን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። 🖱የፕሮጀክቱን ጥራት ለማረጋገጥ ሥራን መፈተሽ፣ ፈተናዎችን ማካሄድ እና ማንኛውንም ችግር መፍታት ይችላሉ። 3. ጤና እና ደህንነት፡- የሳይት መሐንዲሱ የጤና እና የደህንነት ደንቦች በቦታው ላይ መከበራቸውን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን የመለየት እና የመፍታት፣ የደህንነት እርምጃዎችን የመተግበር እና የደህንነት ፍተሻዎችን የማካሄድ ሃላፊነት አለባቸው። 4. ግብዓቶችን ማስተዳደር፡- የሳይት መሐንዲሱ ፕሮጀክቱ በተያዘለት መርሃ ግብር እና በበጀት ውስጥ እንዲቆይ ለማድረግ እንደ ቁሳቁስ፣ መሳሪያ እና ጉልበት ያሉ ሀብቶችን በብቃት የመምራት ሃላፊነት አለበት። 5. ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት፡ የሳይት መሐንዲሱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ማለትም ደንበኞችን፣ ተቋራጮችን፣ አቅራቢዎችን እና የቁጥጥር አካላትን ጨምሮ እንደ መገናኛ ነጥብ ሆኖ ያገለግላል። የፕሮጀክት ሂደትን የማሳወቅ፣ ጉዳዮችን የመፍታት እና የሚነሱ ችግሮችን የመፍታት ሃላፊነት አለባቸው። በአጠቃላይ የሳይት መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎችን በመከታተል፣የጥራትና የደኅንነት ደረጃዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ፣ሀብትን በመምራትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገናኘት የግንባታ ፕሮጀክቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል

Repost from Engineering Sound
+3
Building on a Strong Foundation-__.pdf.pdf2.07 KB

🤚ግልፅ ጨረታ ተመራጭ የሚሆኑባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች፡- . ለማንኛውም ህጋዊ ተጫራች (ግብር ከፋይ ) በህግ ልዩ አስተያየት ከተደረገባቸው በቀር እኩል እድል በመስጠቱ፣ . ከበርካታ ተጫራቾች የው
🤚ግልፅ ጨረታ ተመራጭ የሚሆኑባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች፡-   . ለማንኛውም ህጋዊ ተጫራች (ግብር ከፋይ ) በህግ ልዩ አስተያየት ከተደረገባቸው  በቀር እኩል እድል በመስጠቱ፣ . ከበርካታ ተጫራቾች የውድድር ተሳትፎ ከፍተኛ የዕቃ፣አገልግሎት ጥራት እና ያልተጋገነነ (ተመጣጣኝ) ዋጋ በማስገኘቱ፣ . ከሌሎች የግዥ ዘዴዎች በተሻለ የመንግስት ግዥ መሰረታዊ መርሆዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በማስቻሉ ናቸው

🟡የኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ.pdf በስራ ላይ ~ ሰናይ ቀን !🤚 ➡️https://t.me/con_site 🏗 ቻናሉን አጋሩ! Share➡️ይደረግ! @con_site 🏗

Share form all construction permit(Word).pdf