cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ከፍልስፍና ዓለም ™

" አዋቂ ሰው ማለት ፍላጎቱን የመግታት እውቀቱ ከፍተኛ የሆነ ማለት ነው በሕይወት ዝቅተኛው ደረጃ ራስን በፍላጎት አጥር ውስጥ ማስቀመጥ ነው አብዛኛው የሰው ልጅ በብዙ ፍላጎትና በጥቂት እውቀት የተሞላ ነው ፤ አዋቂነት ግን ብዙ እውቀትና ጥቂት ፍላጎት ብቻ ይበቃታል አርተር ሾፐንሀወር

Ko'proq ko'rsatish
Advertising posts
5 851Obunachilar
+624 soatlar
+1917 kunlar
+65530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Обуначиларнинг ўсиш даражаси

Ma'lumot yuklanmoqda...

ከበደ ሚካኤል ቀለል ባሉት ተራኪ ግጥሞቻቸው ከአገር በቀል እውቀት እስከ ፈረንጆቹ ፍልስፍና አንድም ሳይቀራቸው እውቀት ለማስተላለፍ ሞክረዋል። ‘ብርሃነ ሕሊና’ በሚል ርዕስ በ1933ዓም ከዛሬ ስምንት አስርት ዓመታት በፊት ባሳተሙት መጽሃፍ በአርስቶትል አንደበት እንዲህ ብለው ነበር፥ አሪስቶት አሪስቶት የሚባል ፈላስፋው መምህር ከሊቆች መካከል ቆሞ ሲያስተምር የወዳጅን ነገር ጠቅሶ ሲነግራቸው እንዲህ ሲል በምክሩ አስጠነቀቃቸው። ስሙኝ ልንገራችሁ ወዳጆቼ ሆይ ምንም ወዳጅ የለም በዚህ ዓለም ላይ። ለዚህ ላርስቶት ለትልቁ ሊቅ ወዳጆችህ ያንተን እውቀት በመናቅ ሲያሙህ ሰማናቸው ብለው ቢነግሩት እንኳን ማማት እና እሌለሁበት ቢደበድቡኝም አልቀየማቸው አሚታ አይጎዳኝም ሲል መለሰላቸው። እኛም እንደ አሪስቶት ምንም ባንሆን ሊቅ ይገባናል ዞትር አሚታን መናቅ አርስቶት= አርስቶትል ወይም ኤርስቶትል አሚታ= ሃሜት ስለሰው ክፉ ወሬ
Hammasini ko'rsatish...
8👍 1
For those interested
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
ከሀሳብ አይደለም ከስልቱ ነው
Hammasini ko'rsatish...
👍 7🥰 2
በአሉ ግርማን በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" በኩል እንደታዘብነው socialist realism:- እንደ አንድ የኪነት ስልት በ1932 አካባቢ ተጀመረ ይላሉ...ጥበብ ፤ ለሰውልጅ ነፃነትን ደስታንና ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚተጋውን የጭቁኑ ህዝብ ትግል ማገልገል መቻል አለበት ከሚል አዝማሚያ የተነሳ ይመስላል ...didactic use of literature, art, and music to develop social consciousness in an evolving socialist state.[1] socialist realism ጭቁኑን ትግል የሚያንፀባርቅ የጥበብ ስልት ተደርጎ ሊታይ ይችላል።The primary theme of Socialist Realism is the building of socialism and a classless society.In portraying this struggle, the writer could admit imperfections but was expected to take a positive and optimistic view of socialist society and to keep in mind its larger historical relevance.[2] በrealism እና በ socialist realism መካከል ያለው ልዩነት realism የህይወትን ነፀብራቅ ሊያሳየን ይሞክራል...ጥበብ የገሃዱ አለም ነፀብራቅ ነው በሚል መፈክር።"Realism is the attempt of art to capture life as realistically as possible."[3] በአንፃሩ ለsocialist realism ጥበብ የሰፊው ህዝብ ትግል ነፀብራቅ ነው።"Socialist realism differs from critical realism, not only in being based on a concrete socialist perspective, but also in using this perspective to describe the forces working towards socialism from the inside."[4] በዚህ መነሻነት ለኔ በአሉ ግርማ realist ደራሲ የሚለው ነገር አያስማማኝም socialist realismን የሚከተል ደራሲ ነው(ለኔ በአሉን ደራሲ ነው ብዬ ራሱ መጥራት ይቸግረኛል፤ በተለየ በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" ውስጥ እልም ያለ የደርግ ፕሮፓጋንዲስት ሆና እንታዘበዋለን) በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" ውስጥ የታዘብናቸው አብይ የስነፅሁፍ ህፀፆች 1 የጥበብ አረዳድ... በአሉ ስነፅሁፍን ለውበቱ ሳይሆን የራሱን ሀሳብና አመለካከለት ማንፀባረቂያ መንገድ አድርጎ ነው የተጠቀመው የራሱን ብቻ ሳይሆን በጊዜው ገዢ የነበረውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለመስበክም ይጋጋጣል...በመሰረቱ አንድ ጥበብ ውበት የሚኖረው ለጥበብነቱ የዋለ ጊዜ ነው ፤ ጥበብ የሆነ አይነት ዘርፍን ማገልገል ስትጀምር ጥበባዊ ለዛዋ ይሞታል....በአሉ በአተራረኩ የተወጣለት ቢሆንም አለማው ጥበባዊ ለዛ ሳይሆን የጭቁኑን ህዝብ ትግል ወይም የአብዮቱን "ቅዱሳዊነት" ማስተጋባት ነው። ጥበባዊ ለዛን ብለው ለሚመጡ አንባቢያን በጥበብ ስም ፖለቲካዊ ንትርክን ያጠጣ...አንዳንዴ የጥበባዊ ውበቱ አይሎብን ፖለቲካዊ ጥዝዛውን ችለን የምንቀበላቸው ስራዎች ይኖራሉ የበአሉ ግን ፅንፍ ይወጣል....በጣም ቋቅ ያለኝና በአሉ እልም ያለ ፕሮፓጋንዳስት ነው ያስባለኝ ..."ያብዮትና ያገር ፍቅር ከማንኛውም ፍቅር ይበልጥ ጠንካራ ነው። "(ገፅ-101)...ሚለው አባባል ነው፤ እንዴት አይተውት በአሉን የሚያንቆለጳጵሱት ስል ተገረምኩ 2 የንዑስ ታሪኮች ነገር በዚህ የቀይ ኮኮብ ጥሪ በሚለው ድርሰት ውስጥ ከዋናው ጭብጥ ጋር ፍፁም ግንኙነት የሌላቸው ሌሎች ንዑስ ታሪኮች እናነባለን... የድርሰቱ ዋና ጭብጥ በፍቅር ተጎዳ አሽከር እንዴት የአብዮቱን ጥሪ(የቀይ ኮኮብ ጥሪ) እንደተቀበለ ፤ እንዲሁም ይህ ሰው የአብዮቱን አደራ በመወጣትና የቀድሞ አሳዳሪዎቹ የዋሉለት ውለታ በፈጠረበት ስሜት መካከል የሚኖረው ጡዘት ነው....ነገር ግን በአሉ ትዝብቱን፣ ፖለቲካዊ አስተሳሰቡና ፕሮፖጋንዳውን ለማስተላለፍ ከዋናው የታሪክ ፍስት ጋር ትስስር የሌላቸው ሌሎች ተዳባይ ታሪኳችን ያስነበብናል...ይሄ የድርሰቱን ውበት ባያሌው አጉድፎታል ሲጀመርም ድርሰት ከተባለ ማለት ነው ከአላስፈላጊ ንዑስ ታሪኮች በተጨማሪ አላስፈላጊ ገፀባህርያትም ወዲያ ወዲህ ሲሉ ይታያሉ....ለምሳሌ ጌታቸው ሸዋሉል በድርሰቱ ውስጥ ተደጋግሞ ይነሳል ብዙ የገፅ ሽፋንም ተሰጥቶታል ነገር ግን ከዋናው የታሪክ ጭብጥ ጋራ ያለው ትስስር እጅግ የላላ ነው ለመፃፍ ባለኝ ስልቹነት የተነሳ ያልጠቀስኳቸው የበአሉ እልፍ ስህተቶች በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" መፅሐፍ ውስጥ ታዝቢያለው መፅሐፉን ጨርሼ ስከድን እዚህ መፅሐፍ ላይ ያባከንኩት ጊዜ ፀፀተኝ... የተሻለ እይታ አለኝ የሚለንን ለማድመጥ ዝግጁ እንደሆንን ይሰመርበትና... [1] [2] Encyclopedia Britannica [3] social realism literature: studysmarter.com.uk [4]critical realism and socialist realism: springer.com ✡אומנות
Hammasini ko'rsatish...
3😁 2👍 1
አያን ሂርሲ አሊ ትባላለች። ከአራቱ ሞገደኛ ኢአማንያን ከዶዊክንስ ከሂችንስ ካሃሪስ እና ዴኔት ጋር በአቻነት የምትወሳ ነበረች። ወዳጃችን ሂችንስ ነፍሱ በአፀደ ገነት ትረፍና በሞት ከተለየን ቆየ። አያን ደግሞ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ገደማ ጥላን ላሽ ብላለች። ከኢአማኝነት ወደ ሐይማኖተኝነት የተቀየሩ ምሁራኖች ጥቂት አይባሉም። ግን "ለምን? ለምን? ለምን?" አለ በስንቱ። እኔ ደግሞ እዚህ ተጎልቼ "እንዴት ነው አንድ የተማረ የተመራመረ የሚባል ሰው በአንድ ወቅት ያለምንም ጥርጣሬ ሽንጡን ገትሮ ሲሟገትለት የነበረን አመለካከት በአንዴ አሽቀንጥሮ በተቃራኒው ጎራ መሰለፍ የሚችለው?" እያልኩ እጠይቃለሁ። መጨረሻዬን አሳምርልኝ እንጂ ሌላ ምን ይባላል።
Hammasini ko'rsatish...
😁 7👍 5👌 2🙏 1
የዛሬውን አለምአቀፍ የመፅሀፍት ቀን በማስመልከት ማንኛውንም አይነት classic የልቦለድ፣የፍልስፍና፣የታሪክ ወይም የግጥም (ቧለቲካም ቢሆን)መፅሐፍት በስጦታ ልታበረክቱልኝ የምትሹ ካላችሁ አጋጣሚው እንዳያመልጣችሁ ስል በአክብሮት አሳስባለሁ። "10 መፅሃፍ ለሚሰጠኝ ሰው መንግስተ ሰማይ ስገባ ከሚኖረኝ የወይን እርሻ እኩሌታውን ልሰጠው ቃል እገባለሁ"ብሏል አንዱ😁..... #ማሳሰቢያ—self-help እና መሰል መፅሀፍትን አያካትትም።
Hammasini ko'rsatish...
😁 25👍 3
For those of you interested
Hammasini ko'rsatish...
Repost from AAU NEWS
ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት አርብ ይካሄዳል! ~   ~   ~   ~   ~   ~   ~   ~   ~ በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር የወሩን ድንቅ የኪነጥበብ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት አርብ ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም ያካሂዳል። በዕለቱም ደራሲና ገጣሚ በውቀቱ ስዩም የክብር እንግዳ ሆኖይገኛል። እንዲሁም በአራት ሳምንታት የኪነጥበብ ዝግጅቶች ቀርበው የተመረጡ ልዪ ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ። በተጨማሪም ባህል ማዕከሉ ከኢንፊኒክስ ሞባይል ጋር በመተባበር በቀኑ የታለንት ውድድር በማካሄድ አሸናፊዎችን አጓጊ ሽልማቶችን ይሸልማል። #ማስታወሻ :- ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 4 3🙏 1