cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethiopia Insider

Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
6 082
Obunachilar
+324 soatlar
+587 kunlar
+24930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
የተወካዮች ምክር ቤት ህወሓት ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን የአዋጅ ማሻሻያ አጸደቀ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድ አዋጅ አጸደቀ። በ2011 ዓ.ም. የወጣውን “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን” የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በሁለት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው። “በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ” የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ፤ “ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል” በሚል “ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ” የተደረገው ህወሓት በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል። “አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል” ሲል ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Hammasini ko'rsatish...
👍 11😁 4 3
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
“በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ” የፖለቲካ ፓርቲ፤ ማመልከቻው በ15 ቀናት ውስጥ ተቀባይነት የሚያደርግ አዋጅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው “በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ” የፖለቲካ ፓርቲ፤ “በልዩ ሁኔታ” ለመመዝገብ ማመልከቻ ባቀረበ “በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ምዝገባው እንዲፈጸም” የሚያደርግ አዋጅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ መልኩ የቀረበለትን ማመልከቻ ውድቅ የማድረግ አማራጭ በአዋጁ ባይሰጠውም፤ በፓርቲው ላይ ለሁለት ዓመታት “ክትትል እና ቁጥጥር” የማድረግ ስልጣንን ግን ያገኛል። ➡️ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩ ምዝገባ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ምርጫ ቦርድ የሚኖረውን ስልጣን የሚወስኑ ድንጋጌዎች የተካተቱት፤ ይህንኑ በተመለከተ በ2011 ዓ.ም የጸደቀን አዋጅ ለማሻሻል በቀረበ የህግ ረቂቅ ላይ ነው። ➡️ የተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ ግንቦት 26፤ 2016 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባው ከሚመለከታቸው ጉዳዮች አንዱ ይኸው የአዋጅ ማሻሻያ እንደሆነ፤ ፓርላማው ለመገናኛ ብዙሃን በሚልከው የስብሰባ አጀንዳ ማሳወቂያ መልዕክቱ ላይ አስፍሯል። ➡️ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የአዋጅ ረቂቅ፤ በነባሩ አዋጅ የተካተቱ 3 አንቀጾች ላይ ብቻ ማሻሻያ የሚያደርግ ነው። ከማሻሻያዎቹ መካከል፦ ⭕️ “አንድ የፖለቲካ ቡድን ሀይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል” የሚለው ይገኝበታል። 🔴 ለዝርዝሩ 👉 https://ethiopiainsider.com/2024/13159/ @EthiopiaInsiderNews
Hammasini ko'rsatish...
👍 8😁 6
Photo unavailableShow in Telegram
የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ፤ ስለ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ኃላፊነት ምን ይላል? በ1995 ዓ.ም. የወጣውን የኢሚግሬሽን አዋጅ የሚያሻሽል የህግ ረቂቅ በትላንትናው ዕለት ለፓርላማ ቀርቧል። አዋጁን ለማሻሻል ካስፈለገባቸው ምክንያቶች “አንዱ የተቀናጀ ድንበር ቁጥጥር አስተዳደርን” አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ተግባራዊ ካደረገው መመሪያ ጋር የኢትዮጵያን ስርዓት ማጣጣም በማስፈለጉ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። የዓለም አቀፉ ድርጅቱ ተግባራዊ ያደረገው መመሪያ፤ ሀገራት የመንገደኛ ቅደመ ጉዞ መረጃ እና ምዝገባ ስርዓትን እንዲዘረጉ የሚያስገድድ ነው። ኢትዮጵያ የዚህ መመሪያ ፈራሚ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ በመሆኗ፤ ይህንኑ ስርዓት በኢሚግሬሽን ማሻሻያ አዋጅ ላይ እንዲካተት መደረጉ በአዋጅ ማብራሪያው ላይ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት፦ ▶️ ማንኛውም አጓጓዥ መንገደኛን ወደ ሀገር ለማስገባት ወይም ከሀገር ለማስወጣት ከማጓጓዙ ከ3 ሰዓት በፊት፤ የመንገደኛውን ቅድመ ጉዞ መረጃ እና ስም ዝርዝር ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት የማሳወቅ ወይም የመላክ ግዴታ እንዲኖረው ተደርጓል። ▶️ ይህ መሆኑ “መረጃውን በመለዋወጥ የሚፈለጉ አደገኛ ወንጀለኞች በተለይም ሽብርተኞችን ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል” ተብሏል። ▶️ “ማንኛውም ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አጓጓዥ፤ በሀገራት መካከል በሚኖር በእንካ ለእንካ መርህ ወይም በሚደረግ ስምምነት መሰረት፤ የመንገደኞችን ቅድመ ጉዞ መረጃ እና ስም ዝርዝር ወደሚሄድበት አገር ከመውሰዱ በፊት እንዲያሳውቅ ግዴታ ተጥሎበታል። @EthiopiaInsiderNews
Hammasini ko'rsatish...
👍 11 1
Photo unavailableShow in Telegram
ባለፉት 9 ወራት ለዓለም ገበያ የቀረበው የማዕድን መጠን ምን ያህል ነው? ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለዓለም ገበያ ካቀረበቻቸው ማዕድናት ከ13.3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷን የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ሀብታሙ ተገኝ ትላንት አስታውቀዋል። ይህ የገንዘብ መጠን ከወርቅ ማዕድን የተገኘውን ገቢ አይጨምርም። ሀገሪቱ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያቀረበቻቸው ማዕድናት ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ ⭕️ ጌጣ ጌጥ - 79.55 ቶን ⭕️ ታንታለም ኦር - 69.8 ቶን - የኢንዱስትሪ ማዕድናት - 32,141 ቶን - ጥሬ እና እሴት የተጨመረበት ኦፓል - 19.9 ቶን - ሊቲየም - 11, 176.4 ቶን 🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13147/ @EthiopiaInsiderNews
Hammasini ko'rsatish...
👍 5 1
Photo unavailableShow in Telegram
ባለፉት 9 ወራት ከማዕድናት ሽያጭ ማሳካት የተቻለው ገቢ፤ ለበጀቱ ዓመቱ ከታቀደው 56 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለጸ ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከምታቀርባቸው ማዕድናት 514 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ብታቅድም፤ የበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ ሶስት ገደማ ወራት ብቻ በቀሩት በዚህ ጊዜ ማሳካት የቻለችው 56 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለጸ። ሀገሪቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወርቅ ያገኘችው የውጭ ምንዛሬ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ83 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ተነግሯል። የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ሀብታሙ ተገኝ የመስሪያ ቤታቸውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 22፤ 2016 ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት ከተናገሩት:- ➡️ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከቀረበ የወርቅ ምርት 274 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ➡️ በእነዚህ ወራት ለብሔራዊ ባንክ ከገባው 3.023 ቶን የወርቅ ምርት ውስጥ አብዛኛውን ያቀረቡት በወርቅ ማውጣት የተሰማሩ ኩባንያዎች ናቸው። ➡️ ባለፉት 9 ወራት የተመረተው የወርቅ መጠን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር “የ12.6 በመቶ ብልጫ ያሳየ ነው” ➡️ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ወርቅን ጨምሮ ከማዕድናት የተገኘው አጠቃላይ ገቢ 289 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንም ተናግረዋል። 🔴 ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13147/ @EthiopiaInsiderNews
Hammasini ko'rsatish...
👍 5😁 3 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዜጎች ከሀገር እንዳያወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ ማንኛውንም ሰው ከሀገር ውስጥ እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። የአዋጅ ማሻሻያው፤ በህገ ወጥ መንገድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎች “በጥቁር መዝገብ እንዲመዘግቡ እና ከሀገር እንዲወጡ” የሚያስችል “አስተዳደራዊ ቅጣት” የመጣል ስልጣንን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትም ሰጥቷል። ➡️ እነዚህን አዲስ ድንጋጌዎች ያካተተው የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ የተላለፈው፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ነው። ➡️ ሀገራት “ሉዓላዊ ስልጣንን” ተግባራዊ ከሚያደርጉባቸው ህጎች “በዋነኛነት” የሚጠቀስ ነው የሚባልለት የኢሚግሬሽን ህግ፤ “በህግ የተከለከሉ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡ እና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቁጥጥር የሚደረግበትን አግባብ” የሚደነግግ ነው። ➡️ በስራ ላይ ከዋለ 21 ዓመት የሞላው ነባሩ ህግ፤ “ማንኛውም ሰው ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት በፍርድ ቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው” ይላል። ➡️ ሬ ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ የተቀመጠውን የፍርድ ቤት “ብቸኛ ስልጣን” የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት ያጋራ ሆኗል። 🔴 ለዝርዝሩ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13135/ @EthiopiaInsiderNews
Hammasini ko'rsatish...
👍 5👎 4 2👏 1
02:21
Video unavailableShow in Telegram
ቪዲዮ፦ የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ገና ላልተወሰነለት ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ “ቁልፍ ሚና ይኖረዋል” የተባለለት የምክክር ምዕራፍ፤ ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 21፤ 2106 በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በይፋ ተጀምሯል። በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ በተካሄደው በዛሬው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ 119 ወረዳዎች በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ቁጥራቸው ከሁለት ሺህ በላይ የሚልቀው እነዚህ ተወካዮች፤ ለሀገር አቀፍ ጉባኤ የሚሆኑ የአጀንዳ ሀሳቦች ላይ ምክክር ያደርጋሉ። በዚህ ምክክር የሚለዩ አጀንዳዎችን፤ በቀጣይ በሚከናወነው የሀገር አቀፍ ጉባኤ “አጀንዳ ቀረጻ” ወቅት እንዲካተቱ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ነው። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ይህንኑ ኃላፊነቱን “በአግባቡ የሚወጣ መሆኑን” የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ፕሮፌሰር መስፍን በዛሬ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “አዲስ ውጤት ለማግኘት፣ በአዲስ መንገድ መሄድ አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ህዝቡ በተወካዮቹ አማካኝነት ትርጉም ያለው ተሳትፎ በማድረግ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ምንጭ ከመለየት ጀምሮ በምክክር ሂደቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት እኩል የምተሳተፉበት እና አሻራችሁን የምታሳርፉበት ታሪካዊ መድረክ እነሆ ተፈጥሯል” ብለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) 🔴 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ያደረጉትን ሙሉ ንግግር ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://youtu.be/Gij2BZV3xgM @EthiopiaInisderNews
Hammasini ko'rsatish...
prof mesfin final for X.mp4171.81 MB
😁 3🤬 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ በጎርፍ ሳቢያ የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛት ምን ያህል ነው? በኢትዮጵያ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ590 ሺህ በላይ ሰዎች መጠቃታቸው እና 95 ሺህ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት ተቋማት ባለፉት ቀናት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በጎርፍ የተጠቁት አካባቢዎች የሚገኙት በዘጠኝ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መሆናቸውንም የተቋማቱ ሪፖርት አመልክቷል። ከክልሎች መካከል በጎርፍ ብርቱ ጉዳት ያስተናገደው የሶማሌ ክልል መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (OCHA) አስታውቋል። በክልሉ በአፍዴር፣ ሊበን እና ሸበሌ ዞኖች የሚገኙ አካባቢዎች በጎርፍ በመጥለቅለቃቸው ከ247 ሺህ ሰዎች በላይ መጠቃታቸውን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በእነዚህ ዞኖች ቢያንስ 51 ሺህ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውንም ጽህፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል። በሶማሌ ክልል የሚገኙት የሸበሌ፣ ገናሌ እና ዌብ ወንዞች ከግንቦት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ መቀነስ ቢያሳዩም፤ በአካባቢው ሊጥል በሚችለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወንዞቹ ሊሞሉ ስለሚችሉ አሁንም ክትትል እንደሚያስፈልግ የመንግስታቱ ድርጅት ጽህፈት ቤት በሪፖርቱ አሳስቧል። በሶማሌ ክልል ባለፈው ጥቅምት እና ህዳር ወር በነበረው የዝናብ ወቅት፤ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጎርፍ ተጠቅተው እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የነበረው ጎርፍ በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በርካታ ከብቶችንም ለሞት ዳርጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @EthiopiaInsiderNews
Hammasini ko'rsatish...
👍 12