cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Sidaama Region Bureau of Justice

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
912
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+157 kunlar
+6530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሲብክመ የቤተሰብ ረቂቅ ህግ ላይ ውይይት ተደረገ ሀዋሳ፡ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም. የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ አመራሮችና አቃቢያነ ህግ የሲዳማ ክልል የቤተሰብ ረቂቅ ህግ ላይ ውይይት ተካሂዷል። የውይይት መድረኩ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የአስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ገነነ አበራ የከፈቱ ሲሆን፣ የፍትህ ቢሮ የክልሉ የቤተሰብ ረቂቅ ሕግ የክልሉን ህብረተሰብ የአኗኗር፣ ባህል እና ማህበራዊ መስተጋብር የኢፌዴሪ የቤተሰብ ህግ ማዕከል በማድረግ እንዲዘጋጅ በማሰብ ወደ ተግባር መገባቱን በመጥቀስ፣ በክልሉ በቤተሰብ ጉዳዮች ዙሪያ ምላሽ በሚሰጥ መልኩ ረቂቅ ህግ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል። አክለውም፣ ይህ ረቂቅ ህግ ለሚያጸድቅ አካል ዳብሮ መቅረብ ስላለበት ገንቢ ሀሳብ መስብሰብ በማስፈለጉ ለውይይት መቅረቡን አስገንዝበዋ። የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ትብብር ያደረጉትን ኤስ ኦ ኤስ ችልድረንስ ቪለጅ (SOS Childrens’ Village) አመስግነዋል። በረቂቅ ሕጉ ዉስጥ መካተት የሚገባቸዉ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ጋብቻ ለመመስረት አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች፣ ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ የሚኖራቸዉ መብትና ግዴታ እንዲሁም ንብረታቸዉን በተመለከተ ስለሚወስኑበት ሁኔታ፣ ቀለብ የመስጠት ግዴታ፣ የልጆች አያያዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጓል። በቀጣይም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት ተጨማሪ የግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ እንደሚዘጋጅ ተገልጾአል፡፡ ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...

"የተሻለ ፍትህ ለህዝባችን" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የፍትህ ትራንቅፎርሜሽን ስራዎች የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ። ሀዋሳ፦ ሰኔ 20/2016 ዓ.ም የፍትሕ መሻሻልና ተደራሽነት ለማስፈን ረዘም ላለ ጊዜ ስካሄድ የቆየው ፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች የማጠቃለያ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ሲሆኑ፣ በዓመቱ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን በማስመልከት በፍትህ ዘርፍና በጠቅላይ ፍርድ ቤት አማካይነት ግብ በማስቀመጥ፣ እስከ ታችኛው መዋቅር በቁርጠኝነት እንደተመራ አስታውቀዋል። ዋና አፈ ጉባዔዋ ቀጥለው የፍትሕ መሻሻል ተጨባጭ እንዲሆንና የህብረተሰቡን የፍትሕ ጥማት ለማርካት እንዲሁም ጥሩ የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ የዘርፉ አመራርና ባለሙያ ለመፍጠር በትኩረት እንደተሰራ በማውሳት፣ የፍትህ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች በየመዋቅሩ እንዲጠሩ መደረጉን ጠቁመዋል። በዚህም የሚታይ ለውጥ ሊመጣ ችሏል ብለዋል። የውይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ፕሬዚደንት የተከበሩ አቶ ደስታ ሌዳሞ ሲሆኑ፣ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራ እንዲሰራና ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊ ድጋፍ በማድረግ በምክር ቤት አማካይነት እንዲመራ በማድረግ በአጽንዖት ተሰርቷል ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ንግግራቸውን በመቀጠል፣ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራ የታቀደውን ግብ በመምታቱ ከማጠቃለያ ሪፖርት ባሻገር ህዝብን በወከሉ በምክር ቤት አባላት ውይይት ማረጋገጥ መቻሉን አስታውሰዋል። ህዝብን ያስመረሩ በየዘርፉ የተሰገሰጉ አካላትን ለማጥራት ከተሰሩ ስራዎች ባሻገር መረጃዎችን በማጠናቀር እርምጃ ለመውሰድ በህደት ላይ መሆኑን በመጥቀስ፤ በዚህ ብቻ ጨርሰናል ተብሎ መዘናጋት እንደማይኖር አረጋግጠዋል። የትራንስፎሜሽን አጠቃላይ ህደትና ክንውን የሚያሳይ ሰነድ በተመለከተ፣ ሰነዱን ያቀረቡት የክልሉ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ፣ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ማቶ ማሩ እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አለማየሁ ጢሞቴዎስ ስሆኑ ፣ በሰነዱ የፍትሕ መዘመንና ተደራሽነት  በየዘርፉ በሁሉም መዋቅር ክልላዊ የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ መሰረት ተፈጻሚነት የተደረጉ ቀርበዋል። የውይይት መድረኩን የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞና የምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ፋንታዬ ከበደ የመሩ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል። ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

ዜና ችሎት! የግል ተበዳይ የሆነችውን ፀጋ በላቸውን በመጥለፍ እና አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰ ሳጅን የኋላመብራቴ ወ/ማሪያም ላይ የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ሰሚ ችሎት የ14 ዓመት ጽኑ እስራት አስተላለፈ ሀዋሳ: ሴኔ 19/2016 ዓ.ም ሲብክመ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ያቀረበው የሳጅን የኋላመብራቴ ወ/ማሪያም መዝገብ እንደሚያስረዳው በቀን 12/02/2016 ዓ.ም የግል ተበዳይ የሆነችውን ፀጋ በላቸውን በመጥለፍና አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰበት መዝገብ የሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የበየነውን ተከሳሹ ያቀረበውን ይግባኝ በመስማት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ወደ 10 ዓመት ከ5 ወር በማድረግ ዝቅ ማድረጉን ዘግበን እንደነበር ይታወቃል። ይሁንና የክልሉ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የይግባኝ ጥያቄ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተከራከረ ሲሆን የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሲብክመ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ሁኔታዎችን በማየትና በማመዛዘን በዛሬው ዕለት ሰኔ 19/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሳጅን የኋላመብራቴ ወ/ማሪያምን በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት ወስኖበታል፡፡ ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የሲብክመ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በ.ዓ ዕቅድ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ገመገመ። ሀዋሳ፡ ሰኔ 15/2016 ዓ.ም በበጀት ዓመቱ በዘርፉ የፍትህ ስርዓቱን ማሸጋገር፣ ሕግ ማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ የዜጎችን መብት መጠበቅና ማስጠበቅ እንዲሁም የመንግስትና የሕዝብን ሀብትና ጥቅም ከማስከበር አንፃር በ12 ወራት ውስጥ በርካታ ተግባራት ስለመከናወኑ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ማዘጋጃ መድረክ ተካሂዷል፡፡ መድረኩን  የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ማቶ ማሩ የመክፈቻ ንግግር አድርገው የከፈቱ ሲሆን፣ እንደ ክልል በፍትህ ዘርፉ በዓመቱ ከታቀደው ዕቅድ አንጻር ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን የዕቅዱ አካል በማድረግ የፍትህ ስርዓትን ማዘመን፣ የህግ ግንዛቤ ማስረጽ፣ በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል ማጥራትና ማጠናከር፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር መቀናጀት፣ አማራጭ የፍትህ ስርዓትን ለማዳበር ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት በማጎልበት ፍትህን ወደ ተገልጋል ደጅ ማቅረብ፣ ተቋሙን በቴክኖሎጂ በማዘመንና የህዝብ ግንኙነት ስራ በማጠናከር ተገልጋይን ማዕከል ያደረገ የፍትህ ስርዓት ማበጀት በአመቱ የተከናወኑ ስራዎች መሆኑን ገልጸዋል። ኃላፊው በመጨረሻም፣ እንደ ክልል በዘርፉ ውጤታማ ስራ የተሰራ ብሆንም ሁሉም መዋቅሮች እኩል ውጤት አለማምጣታቸውን በመጥቀስ በቀጣይ ለማረም ጠንካራ አቋም እንደሚወሰድ አሳስበዋል። በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮምቴ አማላት፣ቢሮው አመራሮችና የየስራ ክፍሉ ዳይሬክተሮች፣ የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ የዞን የጸጥታና መልካም አስተዳደር ኃላፊዎች ፣ የሁሉም ዞንና የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ አቃቤ ህግ ኃላፊዎች፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የ12 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ተግምግሟል፡፡ የ12 ወር አፈፃፀም ሪፖርት በፍትሐ ብሔር ጉዳዮች፣ 79 ሚሊዬን የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ ማስመለስ የተቻለ ሲሆን 98 ሚሊዬን ማስቀረት ተችሏል። የሙስና ጉዳዮች በተመለከተ 68,214,143 ብር ማስመለስ ተችሏል። በንቃተ ህግ ከመፍጠር አኳያ፣ በሴቶች፣ ህጻናት ፣ በሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች የሰብአዊ መብት ማክበር እና ማስከበር፣ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነትን ማሻሻልል፣  ወንጀልን  መቀነስ፣  የምርመራ መዛግብትን የማጥራት ምጣኔ በሁሉም የወንጀል ዓይነቶች በአማካኝ 99% በላይ የማድረስ ስራዎች እንደተሰሩ በሪፖርቱ ተብራርቷል። በተጨማሪም በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች፣ በሴቶችና ህፃናት በሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ በምስክሮችና ተከሳሾች አለመቅረብ የሚቋረጡ መዛግብት መቀነስ፣ ከሙስና አኳያ የተሸለ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደተቻለ  ስለመሆኑ እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ ስለመቻሉ በሪፖርቱ ተጠቅሷ፡፡    በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ እንደቀረበው በአማራጭ ፍትህ ስርዓት ዙሪያ፣ የህግ ግንዛቤ በጥልቀት ማስገንዘብ፣ የወንጀል ጉዳዮችን ሳይንጠባጠቡ ውሳኔ ማሰጠት፣ የሰው ኃይል በስነ ምግባርና በክህሎት ማዳበር፣ ተቋሙን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የቅንጅት ስራዎች እና የኮሙንኬሽን ስራዎች ዙሪያ በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል። ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የሲብክመ ፍትህ ቢሮ በሲዳማ ክልል አፊን ባህላዊ ሶንጎ ለማቋቋምና እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ የተጀመረው የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ። ሀዋሳ፦ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም የሲብክመ ፍትህ ቢሮ በሲዳማ ክልል አፊን ባህላዊ ሶንጎ ለማቋቋምና እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከትናንት ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ  ስካሄድ የነበረው በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። በዛሬው ዕለት የአፊን ባህላዊ ስነስርዓት በተመለከተ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን፣ የማጠቃለያ መድረኩን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላ አቶ ገነነ አበራ መርተዋል። መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት ከትናንት ጀምሮ በተካሄደው ውይይት፣ ተሳታፊዎች በበቂ ሁኔታ በመወያየት የተፈለገውን ግብዓት እንድንሰበስብ አስችለውናል ብለዋል። አክለውም የህዝብ ባህል የሆነውን የአፊን ስርዓትን ለፍትህ መቀላጠፍ በሚመች መልኩ ለህዝብ መልሰን ለማቅረብ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል። በቀጣይ የተሰበሰበው ግብዓት ተጠናቅሮ አዋጁ በስሎ በቅርቡ ልክልሉ ምክር ቤት እንደምቀርብ ተጠቅሷል። ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Bero programe xa SMN la'e
Hammasini ko'rsatish...
''አፊን" በውስጡ በርካታ ትሩፋቶችን የያዘ ግዙፍ ባህል በመሆኑ ለፍትህ መሻሻል ከፍተኛ ሚና ስለሚኖረው ተቋማዊ አድርጎ ለህዝብ ማቅረብ የፍትህ ስርዓትን ያቀላጥፋል ተባለ። ሀዋሳ፦ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም የሲብክመ ፍትህ ቢሮ "ሴንተር ኦፍ ኮንሰርን" ከሚባል መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት በሲዳማ ክልል አፊን ባህላዊ ሶንጎ ለማቋቋምና እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ  አካሂዳል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ዋና አፈ-ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ክልል አፊን ባህላዊ ሶንጎ ለማቋቋምና እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ በማስመልከት ስናገሩ አፊን" በውስጡ በርካታ ትሩፋቶችን የያዘ ግዙፍ ባህል በመሆኑ ለፍትህ መሻሻል ከፍተኛ ሚና ስለሚኖረው ተቋማዊ አድርጎ ለህዝብ ማቅረብ የፍትህ ስርዓትን ያቀላጥፋል ብዬ አምናለሁ ብለዋል። ዋና አፈ-ጉባዔዋ አክለውም ባለፈው አንድ አመት ገደማ የፍትህ ሽግግር ለማቀላጠፍ ክልላዊ ኮሚቴ በማዋቀር በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ በማውሳት፣ በፍትህ ቢሮ በኩል አፊን ባህልን ተቋማዊ አድርጎ በመጠቀም ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን የፍትህ ፍላጎት ለማርካትና ከእንግልት ለማዳን ጥናት በማድረግ ለክልላዊ አብይ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል።  በመጠሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች አዋጁ በስሎ በምክር ቤት እንድፀርቅ የሚጠቅም ግብዓት አንድያክሉ አሳስበዋል። የሲብክመ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ማቶ ማሩ በመድረኩ  ስናገሩ፣ በሲዳማ ክልል አፊን ባህላዊ ሶንጎ ለማቋቋምና እውቅና ለመስጠት በቢሮ ደረጃ ስታሰብ የሲዳማ ህዝብ ለዘመናት በአፊን ስርዓት ባህላዊ ፍትህን መለማመዳቸውን በመጥቀስ ይህንን ስርዓት እውቅና በመስጠትና በአዋጅ በማስደገፍ ቀልጣፋ ፍትህ ማቅረብና ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል በማመን ወደ ተግባር መገባቱን አሳውቀዋል። የሲብክመ ባህል ቱሪዝምና እስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጀጎ አገኘሁ በመድረኩ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ አፊን ሰፊ ህዝባዊ ቅርስ በመሆኑ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ መጀመሩን በመጠቆም፣ ከዚህ ሰፊ ባህል ከሆነው አፊን ለፍትህ ቅልጥፍና በሚጠቅም መልኩ በፍትህ ቢሮ በኩል የተጀመሩ ስራዎች ቀደም ብለው እንደደረሷቸውና መመልከታቸውን በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል። ኃላፊው አክለውም እንደ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ለአፊን ሶንጎ መቋቋምና ተግባራዊነት የሚጠበቀውን ለማድረግ ቃል ገብተዋል። መድረኩን የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ የሲቪክ ማህበራት ተዎካዮና የሀገር ሽማግለዎች የተካፈሉ ሲሆን፣ የመቋቋሚያ አዋጅ እና የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ በቂ ግብዓት ተሰብስቦ መድረኩ የጠናቋል። ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Addi addi shilootu hoshsho!! Muishshu odoo gumulo!! Gubbo aate muishshu jaddonni qaxxaraminoha 4 aganinninna 1000 woxu qorichinni qorichiinshi. Sidaamu dagoomu qoqqowi mootimma Farcote Biiro seeru allaalaano shiqishshino qaxxaro xawissanno garinni Kalaa Daagimi Denneqe yinannihu Hookkote woradi Fayinansete borro mine baatooshshu ogeessa ikkinohu barra 15/2015 M.D SDQM Qara Odiite Biiro giddo B/ba Membere Mergia yaamantanno qara odiite loosaasinchora konni albaanni SDQM Qara Odiite Hookkote woradira 2012 M.D baajeette assitino odiitenni fultino odiitete afiro diwiisiisate hede 10,000 birra aleenni xawinsi loosaasinchora eena muishshu lallawi kiiro 881/2007 quwa 25(1) seerroonniha sae muishshu aate jaddonni qaxxarameena hundi hawaasi quchumi aliidi y/mini keerunni geeguse uyno gumulonni kado xa'mineenna kado haruunsanni keeshshinohu xaphoomu yoo mini barra 27/09/2016 M.D hosino shilootira 4 agani usurinninna mittu kumi birrinni qorichishino. Gubbo uyino 10,000 birrino mootimmate eo ikkanno gede gumulino. **** Muishu jaddonni huluullaammonni 2 qaxxaaramaano annu annunku 1 diri usurinninna 4000(shoolu kumi) woxu qorchinni qorichishantu SDQM Farcote Biiro seeru allaalaano shiqishshino qaxxaro xawissanno garinni: 1kihu Kalaa Harqa Leellisonna 2kihu Kalaa Mulaatu Saamueli Yaamantanno qaxxaramaano Hawassi Gaangaawi woradi Miinjunna Womaashshu borro mini uminna layinki sooreeyye ikkitinori SDQM Qara Odiite biironni 2015 M.D odiitete looso loosate borronsa minira martino sasu loosu ogeeyyeerra muishsha qixxeessite shiqishatenni Itoophiyu muishshu jaddo 881/2007 quwa 25(1) hunda seerroonniha sa’e jaddo loossinota xawissino. Aliyye Sidaamu zoone alliidi yoo mini mannunna sanadete farco yekkeersiisanni keeshshihu gedensaani barra 23/9/2016 M.D hosino jaddote shilootira qaxxaramaano anna annunku 1 diri usurinninna 4000(shoolu kumi) woxu qorichinni qorichishantanno gede yee gumulinoha ikkanna; qorichu jeefishsha lainohunni 2( lamu diri) kio ee gumulino. **** Muishshu jaddonni huluullammoonni qaxxaramaancho 22 (Lemiina lamu) diri usurunninna 45,000 (shooyillinna onte kume) woxu qorichinni qorichiinshi. **** Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Farcote Biiro Seeru Allaalaano qaxxaro xawissanno garinni qaxxaramaanchu Asheenafi Agenyowu SDQM Wayi Shiilotenna Inerjete biiro Baatooshshu gaamo massagaancho ikke loosi 18/01-5/2016 M.D yannara su'misinni Itophiyu daddalu baanke loosu hajora hosiisate fulo assino sase xiraaze cheeke eo assikkinni angasi keeshshiishe loosu soorreeyyyenna ogeeyye su'minni sanade qixxeesse 1,288,269.17 fulo asse muishshu jaddo jeefisate Muishshu Jadduwa Lallawi kiiro 881/2007 quwa 9(2) hunda qoromboonniha sa'e mootimmate biiloonye doogimale garinni horonsiratenna hattono layinki qaxxaronni kaphaancho taje biirote soorreeyyenna loosu ogeeyye su'minni lawise qixxeessatenni hasiissannokki horo umisiranna wolootaho afisiisate hedenna qixxaawe muishshu jaddo loosatenni aanasi shiqqino. Hajo yekkeersiisanni keeshshinohu Hawaasi Quchumi Aliidi Yoo Mini seeru allaalaano shiqishshino mannunna sanadete farco macciishshihu gedensaanni, hunaanchohoe yee barra Sadaasa 23/2016 M.D hosino shilootira qaxxaramaancho iso qorichishe woloota rosiisanno yee 22 diri kotottote usurinninna 45,000 (shoyillinna ontu kumi) qorichamanno gede yee gumulino. Seeraho, Farcotenna Tii"i-farcote Loonseemmo!!!! Teessonke Facebooke፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL Telegraame: https://t.me/sidamaattorney WhatsAppe: https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ አመራርና የማኔጅመንት አባላት በሲብክመ ፍትህ ቢሮ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደርጉ። ሀዋሳ፡ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ አመራርና የማኔጅመንት አባላት በቢሮው ኃላፊ በእስማኤል መሀመድ መሪነት በሲብክመ ፍትህ ቢሮ በመገኘት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን እና አጠቃላይ የተቋሙ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል። የሲብክመ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፍትሐብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መብራቴ መስፍን በክልሉ የፍትህ ዘርፉ ውጤታማ ለመሆን የተሰሩ ስራዎችን ከክልል ማዕከል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ያለውን ገለጻ አድርገዋል። ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የዓቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን በማስመልከት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ። ሀዋሳ:  ግንቦት 15/2016 ዓ.ም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የዓቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን በማስመልከት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፏል። በክልሉ የተጀመሩ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች በማስመልከት የተለያዩ ስራዎች በመሰራታቸው የመጡ አዎንታዊ ውጤቶችንና የተለያዩ በጉባዔው የተቀመጡ አቅጣጫዎች ተፈጻሚነት ጉባዔው በመገመገም  የተለያዩ ጉዳዮችና ሀሳቦች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል። የፍትህ ትራንስፎርሜሽን መነሻ በማድረግ በሁሉም መዋቅር ያሉ አመራሮችና አቃቢያነ ህጎች መገምገማቸው ይታወቃል።  በዚህም መሰረት 6 ወረዳዎች የጽህፈት ቤት አመራሮች እንዲመደቡ ተደርጓል። በተለያዩ መዋቅሮች ያሉትን 30 የስራ ሂዳት አስተባባሪዎችን ከቦታ የተነሱ ሲሆን፣ 142 አቃቢያነ ህግ የቦታ ዝውውር ተደርጓል። በቀጣይ በፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ በሁሉም መዋቅሮች  የሚከወን ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተነግሯል። ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!! ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.