አነባለሁ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🎷🎷🎷🎷❣️❣️💔💔🔊🔊💌💌🙆🤦በዚህ ቻይናላችን ፈታ ዘና እያልን እውቀት የምንቀስምበት ይሆናል 🎸🎸🎸🎷🎷ለስለስ የሉ ሙዚቃዎች ❣️❣️❣️💔❣️❣️💘ልብአንጠልጣይ ልቦለዶች 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🌍🌍የሚገርሙ ሀገራዊ ታሪኮች 💖💖💖💖❣️ዋናው love ነው ይመቻቹ ⌨️📞ሀሳብ አአስታየት @k5187852
Ko'proq ko'rsatish311
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
-1130 kunlar
- Kanalning o'sishi
- Post qamrovi
- ER - jalb qilish nisbati
Ma'lumot yuklanmoqda...
Obunachilar o'sish tezligi
Ma'lumot yuklanmoqda...
💔 አንድ አንዱ ህመም ሀዘንና
ድብርት ውስጥ እንድትገባ ያደርግሃል
አንድ አንዱ ደግሞ ነገራቶችን
እንድትረዳ እና እንድትቀየር ያደርግሃል ።
👨💻🧑💻🧑💻
ይከብዳል...
ኤርታሌ መሀል ላይ፥ገብቶ እንደመዋኘት፣
ለካንሰር መዳ'ኒት፥ፈልጎ እንደማግኘት፣
እንደ ክፍለ ዮሀንስ፥
ዘመን የሚራመድ፥ቅኔ እንደመቀኘት፣
ልክ እንደተዋነይ፥
ሞትን እንዳይገድል፥ቆሞ እንደመገዘት፣
ይከብዳል....
በሩጫ እንደመውጣት፥ሊማሊሞን ገደል፣
በድንጋይ ወርውሮ፥አንበሳ እንደመግደል፣
ፍየልን በጥበብ፥ቅኔ እንደማስተማር፣
በስነ ፈለክ ላይ፥እንደመመራመር፣
ነገን እንደማወቅ፥በአቡሻኽር ቀመር፣
ይከብዳል....
ከእይታ እንደመራቅ፥በመሰውረ እፅ፣
ተከበረ ድንጋይ፥ፅላት እንደመቅረፅ፣
የኢትዮጵያን ሚስጥር፥ፈልፍሎ እንደማወቅ፣
ታቦተ ፅዮንን፥አድኖ እንደመስረቅ፣
ሰይጣንን ከእግዜር ጋር፥ደግሞ እንደማስታረቅ፣
ይከብዳል...
ጣና ባህሩ ላይ፥ጎጆ እንደመቀለስ፣
በጥይት ተኩሶ፥ክር እንደመበጠስ፣
አክሱምን ከመሀል፥በእጅ እንደመቀንጠስ፣
የኢትዮጵያን እዳ፥ከፍሎ እንደመጨረስ፣
ይከብዳል...
ባህር እንደማድረግ፥መቅደላን አፍርሶ፣
መኖ እንደማበጀት፥አድዋን ደርምሶ፣
ድመትን ከውሻ፥ፈረስን ተግመል፣
ነብርን ታ'ንበሳ፥ችሎ እንደማዳቀል፣
ይከብዳል....
ገመድ እንደማቆም፥በአስማተ-ጥበብ፣
የዕፀ-ህይወት ፍሬን፥ቀጥፎ እንደመመገብ፣
የተራበ ጅብን፥አብልቶ እንደማጥገብ፣
በረዶ ክምር ውስጥ፥በራቁት እንደማደር፣
ይከብዳል አንቺዬ...
ይከብዳል እንደዚያ...
ፍቅርሽን መሰረዝ ከልቤ ማህደር።
Boshqa reja tanlang
Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.