cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ከመፃሕፍት ዓለም

መፅሐፍ የእውቀት ምንጭ ነው አንብቡ አንብቡ አንብቡ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
244
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
-430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

📚ርዕስ:- ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት 📝ደራሲ:- እንrሪ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ 📜ዘውግ:-.... 📅ዓ.ም:- 2005 📖የገፅ ብዛት:- 436 📌አዘጋጅ:- Emperor_Yothor 📌ማጋራት አይዘንጋ! @ETHIO_PDF_BOOKS1 @ETHIO_PDF_BOOKS @YETMHRTPDF @BHERE_TREKA
Hammasini ko'rsatish...
ቀድመህ ተገኝ! ፨፨፨///////፨፨፨ ወስጥህ እንዲቀር፣ ከልብህ እንዳይጠፋ፣ የእርጋታና የሰላምህ ምክንያት እንዲሆን የምትፈልገው አንዳች ነገር ቢኖር እርሱን ለሌሎች በማድረግ ቀዳሚ ሁን። በመልካም ስራህ ውስጥ ከምታገኘው ምስጋና ስሜቱን መካፈል ከፈለክ መልካም ላደረገ፣ በጎ ለሰራ ሁሉ ቀድመህ ምስጋና አቅርብ። በተግባሩ ትልቅነት ብቻ ሳይሆን በሃሳቡ ጠቃሚነትም ዋጋ ስጠው። ብትተዋወቀው ደስየሚልህን ሰው ብታገኝ የትውውቁን ጥያቄ ቀድመህ አቅርብ፤ ንግግር ለመጀመር በሚፈሩ ወዳጆችህ መሃል ብትሆን ለወረኝነት ሳይሆን በቅንነት ንግግሩን ጀምር። መደነቅና መሞገስ የሚያስደስትህ ከሆነ ቀድመህ ለማድነቅና ለማሞገስ ወደኋላ አትበል። አዎ! ጀግናዬ..! ቀድመህ ተገኝ! ለሰላምታ ቅደም፤ ለምስጋና ቅደም፤ ለእገዛ ቅደም፤ ለማበርታት፣ ለመደገፍና መልካም ለሚባሉ አስደሳች ተግባራት በሙሉ ቀድመህ ተገኝ። ፍቅርን ብትሻ ቀድመህ ፍቅርን የምትሰጠ፣ ክብርን ብትፈልግ ቀድመህ የምታከብር፣ እንክብካቤ ከተመኘህ ቀድመህ የምትንከባከብ ቀድሞ ሰጪ ድህረ ተቀባይ ሁን። የምትፈልገውን ብቻ ከሰዎች በጠበክ ቁጥር ለማግኘት ያለህ እድል እየቀዘቀዘና ስሜትህም እየተጎዳ ይመጣል። የፈለከውን ነገር በደፈናው ከመፈለግና ከማሰስ ደግሞ በተግባር እያሳዩ፣ በስሜት እየማረኩ፣ ደስታን እየለገሱ መቀበሉ እጅጉን የተሻለና ውጤታማ ነው። ከሌሎች የምትጠብቀው የስሜት ስጦታ ከሆነ የፈለከውን በመስጠት የስሜቱን ጥልቀት ቀድመህ አሳውቃቸው። አዎ! አንተ የፈለከውን ነገር ማድረግ ትችላለህ። ነገር ግን ሰዎች እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን ነገር ያለነሱ ፍቃድና ይሁንታ ማግኘትና ማድረግ አትችልም። ያንተ ንግስና በእራስህ ስሜት ላይ እንጂ በሌሎች ስሜት ላይ አይደለም። ለዚህም ነው እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን ነገር አንተ ቀድመህ አድርገህ መገኘት የሚኖርብህ። ሊያወሩህ ፈልገው ቀዳሚውን ንግግር ካንተ የሚጠብቁ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አስብ፤ ከሌላው በበለጠ ያንተ ሃሳብና አስተያየት ትርጉም የሚሰጣቸው ብዙ ሰዎች እንደሚኖሩ አስተውል፤ እንዳንተው የመመስገን ጠዓም የሚናፍቁ፣ ለመደነቅና ለመሞገስ የሚሽቆጠቁጡ ብዙ ነፍሳት ሊኖሩ እንደሚችል ገምት። በምታደርገው ነገር ቀድመህ ተገኘህ ማለት የሚሰጥህ ክብርና የምትዋሃደው ስሜት እጅግ ጥልቅ ይሆናል። መወደድ ብትፈልግ ቀድመህ ውደድ፣ ስሜቱንም ቀድመህ አስተዋውቅ፣ አለማምድ፤ በጎነትን ብትሻ ደግ መልካም ሰው ሆነህ አሳይ። የፈለከውን ሰተህ ተቀበል፤ እርካታውንም በዛው ልክ አጣጥም። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Hammasini ko'rsatish...
'ድንዛዜ' ድንዛዜ ከንቱ ወሬ ያለ ጥቅም ያለፍሬ ድንዛዜ በጭፈራ ያለአላማ ያለስራ ድንዛዜ በከተማ ሰው የሰው ብቻ እየሰማ ቴክኖሎጂ በላይ በላይ - ሰው ከራሱ እንዳይተያይ ድንዛዜ በቁሳቁስ- ደግሞ ፍቅር ወድቆ በሱስ ድንዛዜ በጫጫታ - በግርግር በሁካታ ስሜታችን አርቴፊሻል… ምኞታችን አርቴፊሻል… ውበታችን አርቴፊሻል… ህይወታችን አርቴፊሻል… ተፈጥሮን ማነው የሚያዳምጠው የሚያይ የሚመለከተው ተፈጥሮን ማነው የሚያገኘው የሚያሸት የሚዳስሰው ተፈጥሮን ማነው የሚኖረው????! 🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️ 🙏 Follow us on  Instagram ||  Facebook || Twitter join and follow our channel 👉 Share Share Share 👈 https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
Hammasini ko'rsatish...
ብዙ ታጣለህ! ፨፨፨////፨፨፨ አንዳንዶች ሁን ብለው አንዳንዶችም በልምድ ደጋግመው እራሳቸውን ይወቅሳሉ፣ ባላቸው ነገር ደስተኛ አይደሉም፣ እራሳቸው ላይ ህፀፅ ማውጣት ይወዳሉ፣ አብዝተው በበታችነት ስሜት ይዋጣሉ፣ ማንነታቸውን ለመቀበል አብዝተው ይቸገራሉ፣ በትንሹም በትልቁም በቀላሉ ይበሳጫሉ። ከእነዚህ አይነት ሰዎች ውስጥ አንደኛው ከሆንክ የእራስ ግንዛቤህን ደጋግመህ ማጤንና ለራስህ የምትሰጠውን ዋጋ መገንዘብ ይኖርብሃል። ሰዎች እንዲያዝኑልህ ምስኪን፣ ተጎጂ፣ ደካማና ብዙ ችግር የተደራረበበት ሰው መምሰል ትችላለህ ነገር ግን ከሰዎች ልታገኝ የምትችለው ከዘላቂው እርዳታ በላይ የአንድ ሰሞን ከንፈር መጠጣ ብቻ ይሆናል። ላንተ ለራስህ ካልሆነ ሁሌም ያንተ ዋጋቢስነትና ደካማነት ለማንም አጀንዳ እንደሆነ አይቀጥልም፣ ያንተ ደስታ ማጣት፣ ያንተ በአቃቂሮች መሞላት ለገዛ እራስህ እንጂ ለማንም የሚያስጨንቅ ጉዳይ አይሆንም። አዎ! ጀግናዬ..! የዋህ መስሎ ለመታየት፣ እንዲታዘንልህ፣ ተጨማሪ አገልግሎት ለማግኘት፣ ይበልጥ ለመወደድና እንክብካቤ ለማግኘት አስበህ ለራስህ የሆነውንከውንም ሆነ ያልሆንከውን የወረደ ስም እየሰጠህ ከቀጠልክ ብዙ ታጣለህ፣ ብዙ ዋጋም ትከፍላለህ። ውጪውን ታያለህ ከራስህ ህይወት ጋር ታነፃፅራለህ ለእራስህ ያነሰ ስፍራንም ትሰጣለህ፣ ድከመትህን ትቆጥራለህ፣ ካለህ በላይ የሌለህን ለሰዎችም ሆነ ለእራስህ ደጋግመህ ታወራለህ፣ የምትወደውን ነገር ስትጠየቅ የማትወደውን መዘርዘር ይቀናሃል፣ በተረጂነት ስሜት እራስህን የበታች ታደርጋለህ፣ ባለህ መርካትን አታውቅም፣ በትክክለኛው ማንነትህም ነገሮችን ማስተካከል እንደማትችል ታምናለህ። በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ እያለፍክ ከሆነ በእርግጠኝነት እውነተኛው ማንነትህን እየገደልከው ነው፤ ክብርህን እያወረድክ ነው፤ ደስትህን በፍቃድህ እያጣህ ነው፤ የህይወት አላማህን ከግብ ከማድረስ ወደኋላ እየቀረህ ነው። አዎ! ለእራስህ የምትሰጠውን ቦታ አስተካክል፣ እራስህን የምትመለከትበትን መነፅር ቀይር፣ ለእራስህ ማዘንህ እራስህን በእራስህ እንድትቀይር እንጂ በሰዎች ሃዘኔታ ለመቀየር እንድትጥር አያድርግህ፣ ስለእራስህ በሚገባ እወቅ፣ ባወከው ልክ እለት እለት እራስህ ላይ ስራ። ከራስ ጋር ድበብቆሽ አይሰራም፤ ራስን እያሳነሱ የሚገኝ ክብር የለም፤ ለራስ የወረደ ቦታ እየሰጡ የተሻለ ስፍራ መድረስ አይቻልም። የሁሉም ጅማሮ እራስን ከድክመትና ክፍተቱ ጋር መቀበል ነው፣ ህይወትን ቀለል አድርጎ ለመኖር ወሳኙ አማራጭ እራስን መውደድ፣ ከራስ ጋር በማይቋረጥ ፍቅር መውደቅ ነው። ማንም ያጠፋልና ታጠፋለህ፣ ማንም በሃጢአት ይወድቃልና በሃጢአት ትወድቃለህ፣ ማንም ይበድላልና ትበድላለህ። ነገር ግን እራስህን ነፃ ማውጣት ከፈለክ የሆነውን ተቀብለህ፣ እራስህን በይቅርታ አድሰህ፣ ለእራስህ ማዘንህን እራስህን በማሳደግ እየገለጥክ ወደፊት ተጓዝ። ስለራስህ የምታስበውን መጥፎ ሃሳብ ቀይር፣ ህይወትህም በሂደት ሲቀየር ተመልከት። ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Hammasini ko'rsatish...
ልብሽ ይማርካል! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ የምታሸንፊው በመልክሽ ሳይሆን በልብሽ ነው፤ የምትረቺው በገፅሽ ሳይሆን በስብዕናሽ ነው፤ እጅ የምታሰጪው በአቋምሽ ሳይሆን በማንነትሽ ነው፤ የምትገዢው በቃላቶችሽ ሳይሆን በምግባርሽ ነው። የማያልቅ ውስጣዊ ውበት እያለሽ ነገ በሚጠፋ መልክና ቁመና አትመኪ። ሰሪው በሚመሰገንበት ውበት፣ ፈጣሪውን በሚያስወድስ አቋም አትመፃደቂ። ማንም ቢሆን የአምላኩ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ተደናቂው፣ ተሞጋሹም፣ ተመስጋኙም ደግሞ እርሱ ነው። አንቺን ሳይሆን ያንቺን ነገር የፈለገ ሁሉ ሲያጣው ይሔዳል፤ በድምቀትሽ የተማረከ ሁሉ ሲደበዝዝ ይደነግጣል፤ መጥፋት ሲጀምር ጥሎ ይጠፋል። አንቺ መልክሽን፣ ገፅሽን፣ አቋምሽን እንዳልሆንሽ አስታውሺ። ውበትሽ ማንንም ሰው አብሮሽ ለማቆየት ዋስትና አይሆንሽም። ውስጥሽ አንቺን መግለፅ የምትችል ትክክለኛው አንቺ አለች። አዎ! ጀግኒት..! ልብሽ ይማርካል! መንፈስሽ ይስባል፤ ቀልብን ይሰርቃል፤ ውስጥን ያረጋጋል፤ መንፈስን ያድሳል። ነፍስሽ እንቁ ነች፤ ማንነትሽ ግሩም ነው፤ ስብዕናሽ ድንቅ ነው። በስብራት ውስጥ የተሰራ፣ ፈተናዎችን ያሸነፈ፣ እራሱን የመሰለ፣ እራሱን የሆነ ነው። መልካም ውብ ሴት መሆን፣ ማራኪ የተከበረች አክባሪ ሴት መሆን ክፍያው ብዙ አይደለም፤ ቅንነት፣ መልካምነት፣ ደግ አሳቢነትና በእራስ መተማመን ብቻ ነው። መንገስ ከፈለግሽ በቁመናሽ ሳይሆን በማንነትሽ ንገሺ፤ መወደድ ከፈለግሽ በገፅታሽ ሳይሆን በአንቺነትሽ ተወደጂ፤ እንዲቀበሉሽ፣ እንዲደመሙብሽ፣ እንዲደነቁብሽ ከፈለግሽ በተክለሰውነትሽ ሳይሆን በስብዕናሽ አስደምሚ፣ በቅንነትሽ አስደንቂ፣ በሰውነትሽ አስገርሚ። አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ነህ ገዢው፤ አንተ ነህ ተፈላጊው። ከንብረትህ፣ ከዝናህ፣ ከገንዘብህ የሚበልጥ ተፈላጊ ማንነት እንዳለህ አረጋግጥ። ከየትኛውም ቁስ ያንተ ሰውነት ይቀድማል፤ አንተ ስላለህ ሁሉን አምጥተሃልና። ወዳንተ የመጣው፣ የተወዳጀህ፣ የቀረበህ ሁሉ አንተን ብሎ እንጂ አንተ ያስገኘሀውን ቁስ ብሎ እንዳልመጣ እርግጠኛ ሁን። ስታጣ ሊሸሽህ ከሚንደረደር፣ ሲደክምህ ለመዝረፍ ከሚሯሯጥ፣ ሲታክትህ ለመውረስ ከሚንቀሳቀስ ወዳጅ፣ ወዳጅ ሳይሆን ንፁ ምስጋናውን የምታገኘው ተመፅዋች ይሻልሃል። በቁስ ሳይሆን በማንነትህ እራስህን አስከብር፤ በንብረት፣ በዝና ሳይሆን በአንተነትህ ግዛቸው፤ በተክለሰውነት፣ በቁመናህ ሳይሆን በስብዕናህ ማርካቸው። ልህቀትህ ከውስጣዊ መንፈስህ እንጂ ከውጫዊ ቁስንና ቁመና እንዳልሆነ አሳይ። እራስህን የምትወደው ባሳካሀው ስኬት መጠን፣ ባካበተው ሃብት ብዛት፣ በደረሰበት የከፍታ ደረጃ ሳይሆን በአንተነተቱና በማንነቱ እንደሆነ መስክርለት፣ አረጋግጥለት። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Hammasini ko'rsatish...
ለዛ ስጡት! ፨፨//////፨፨ የፍቅር ህይወት ውስጥ ለመግባት ካለህ ፍላጎት የተነሳ አንድ የተለመደ ነገር ታደርጋለህ። ያፈቀርካትን ሴት በእጅህ ለማስገባት ብዙ ትደክማለህ፣ ከፀባይህ ጀምሮ እስከ አቋምህ ብዙ ነገርህን ታስተካክላለህ። የእሷን ትኩረት ለመሳብ የማታደርገው ጥረት አይኖርም። ደጋግሞ መደወል፣ ከቀጠሮ ሰዓት ቀድሞ መገኘት፣ እራስን መጠበቅ፣ ወደእርሷ የሚያቀርብህን ማንኛውንም ነገር ማድረግ። ከዛስ እሺ ተብለህ የተመኘሀውን የፍቅር ህይወት ከጀመርክ ቦሃላ ያለው አቋምና ህይወትህ ምን ይመስላል? ፍቅርህን ምንያክል በጀመርከው ትገፋበታለህ? አንዴ እጄ አስገብቼያታለሁ ብለህ ትዘናጋለህ ወይስ ፍቅርህን ለማጠናከርና እርሷን ለማስደሰት የሚጠበቅብህን ትወጣለህ? አዎ! ጀግናዬ..! ከዛስ? እሺ መባልህንና መስማማቷን ብቻ አትመልከት። ፍቅር ከእሺታ የሚልቅ ሃላፊነት አለው፣ ፍቅር አብሮ ከመሆን በዘለለ የፍላጎትን መጣጣም ይፈልጋል፣ ፍቅር ከቃላት በላይ በተግባር ይገለጣል። የስቴንበርግ (Sternberg) የሶስት ማዕዘን የፍቅር ፅንሰ ሃሳብ ይህን ይላል፦ ፆታዊ ፍቅርን ሙሉ ሊያደርጉት የሚችሉት ወሳኝ መስፈርቶች መቀራረብ (intimacy)፣ ፍላጎት (passion) እና ቁርጠኝነት (commitment) ናቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ቀጠይነት ላለው ዘላቂ የፍቅር ህይወት ቁርጠኝነት (commitment) ትልቁን ሚና ይጫወታል። የምርም ወዳጅህን ለህይወት ዘመን አጋርነት ካሰብካት እነዚህን ሶስት መስፈርቶች በፍቅር ህይወትህ ውስጥ ማካተትህን አትርሳ። አዎ! ጀግኒት..! ፍቅሩን ከተቀበልሽ ቦሃላ ስለሚመጣው ህይወት በሚገባ አስቢበት። ከእሺታሽ ቦሃላ አንቺም ለግንኙነት የሚጠበቅብሽ ሃላፊነት እንደሚኖር አስታውሺ። አለመግባባት ሲፈጠር አስቀድሞ ወደ አዕምሮሽ የሚመጣው ሃሳብ ምንድነው? በቁርጠኝነት አለመግባባቱን መፍታት ወይስ ጉዳዩን ችላ በማለት ወደመለያየት መሔድ? ነገሮች ተደጋጋሚና አሰልቺ ሲሆኑብህ አስቀድመህ የምታደርገው ነገር ምንድነው? ነገሮችን በአዲስ መልክ ለማስኬድ መሞከር ወይስ ቶሎ ተስፋ መቁረጥ? ፍቅር ውስጥ መቀራረብ አለ፣ መፈላለግ ይኖራል፣ አብሮ እስከመጨረሻው ለመቆየት መከፈል ያለበትን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ቁርጠኝነት እጅግ ወሳኝ ነው። ቶሎ ከመለያየት በላይ ላለመለያየት መክፈል ያለባችሁን ዋጋ ክፈሉ፣ ፍቅራችሁን በቁርጠኝነት ምሩት፣ ቅርበታችሁን ቢደበዝዝም ዳግም መውዛት የሚችል ውበትና ለዛ ስጡት። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Hammasini ko'rsatish...
በትዕግስትህ ተማመን! ፨፨፨፨///////////፨፨፨፨ በአለም ላይ ምንም ጉዳት የሌለው ነገር ቢኖር ትዕግስት ነው። መታገስህ ከምን እንደሚያድንህ፣ ምን እንደሚያድልህ፣ የት እንደሚያደርስህ አታውቅም ግን ብቻ ታገስ። ከታገሱት ሁሉም ያልፋል፣ ከታገሱት በረዶም ውሃ ይሆናል፣ ከታገሱት ሰውም ይቀየራል። ትዕግስት የታላቅነት አስተሳሰብ ባለቤት ለሆኑ ሰዎች ዋና ስንቃቸው ነው። ለዘመናት ዋጋ ከፍለሃል፣ ለአመታት ያለማቋረጥ ጥረሃል፣ ሳትሰለች አንድን ነገር ደጋግመህ ሰርተሃል፣ በሰዎች ጫና ሳትሰበር፣ ለውጫዊ ግፊቶች ሳትበገር እስከ አሁን ታግለሃል። ማቆም ስትችል ሳታቆም እስካሁን መተሃል፣ መተው ስትችል ሳትተው በትዕግስት እስካሁን ዋጋ ከፍለሃል። በስተመጨረሻ ማቆም ብዙ እንደሚያሳጣህ ታውቃለህና ትዕግስትን ምርጫህ አድርገሃል፣ በመሃል ተስፋ መቁረት እንደሚፀፅትህ ገብቶሃልና በፅናት ተፋልመሃል። ታጋሾች እራሳቸውን ከቅጣት ያድናሉ፣ ታጋሾች እራሳቸውን ለላቀው ክብር ያበቃሉ። አዎ! ጀግናዬ..! በትዕግስትህ ተማመን! አንድ ቀን በብዙ እንደሚያኮራህ እመን። ዋጋ ቢያስከፍልህም በብዙ እንደሚያሸልምህ አስታውስ፣ ብዙ ቢያስጠብቅህም በስተመጨረሻ እንደሚክስህ አትርሳ። ስኬት የትዕግስተኞች እጣፋንታ ነው፤ ለውጥ፣ እድገት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የታጋሾች ሽልማት ነው። ብትታገስ ከፀፀት ትድናለህ፣ ብትታገስ ክብርህን ትጨምራለህ፣ ብትታገስ የተለየ ዋጋ ይኖርሃል፣ ብትታስ የአመታት ምኞትህን በእጅህ ማስገባት ትችላለህ። ቸኩሎ ከማትረፍ ጠብቆ ማጣት ትልቅ ትምህርት ነው። በጥበቃ ውስጥ የአላማ ፅናት ይፈተናል፣ በትዕግሥት ውስጥ ጠንካራ ማንነት ይገነባል። ሁለት ነገር እውነተኛውን አንተን ይገልፁሃል ይባላል፦ "አንድ ምንም በሌለህ ሰዓት ያለህ ትዕግስትህ፣ ሁለት ሁሉም ነገር ሲኖርህ አመለካከትህ።" አዎ! የሌለህን የምታገኘው በታገስከው ልክ ነው፤ የለፋህለት የሚከፍልህ በፅናትህ መጠን ነው። ትግስት ንዴትህን ያበርደዋል፣ ትዕግስት ስሜትህን ያስተካክለዋል። ብዙዎች የአንድ ደቂቃ ትዕግስት አጥተው እድሜ ዘመናቸውን በፀፀት ተቀጥተዋል፣ ብዙዎች ለደቂቃዎች ዝም ማለት አቅቷቸው የእራሳቸውንም የሰዎችንም ህይወት አመሰቃቅለዋል፣ ብዙዎች ባለመታገሳቸው  የሰው ነፍስ በእጃቸው ላይ ጠፍቷል። ህይወትህን ያለ ትዕግስት ለመምራት አትሞክር። የሆነው ሆኗል የሚሆነውም እስኪሆን ጠብቅ፣ በችኮላህ እራስህን አትስበር ለሌሎች ስብራትም መንስኤ አትሁን። ትዕግስት መራር ነች ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ነው፤ ትዕግስት ፈተናዋ ብዙ ነው ሽልማቷ ግን ከምንም በላይ ነው። ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Hammasini ko'rsatish...
ውብ ነሽ! ፨፨///፨፨ ከሰዎች ጠብቀሽ ላታገኚው ትችያለሽ፣ በወዳጆችሽ መባል ፈልገሽ አልተባልሽም ይሆናል፣ የተለየ ቦታ በሰጠሻቸው ሰዎች እንዲሁ የተለየ ስፍራ አልተሰጠሽም ይሆናል። ነገር ግን አንድ ነገር አስታውሺ የትም ሳትሔጂ፣ ማንንም ሳትመስዪ፣ ከማንም ሳትወዳጂ፣ ማንም ሳይኖርሽ፣ ምንም ሳትጨምሪ እንዲሁ ውብ ነሽ። ውበትሽም የግድ በሰዎች ሊነገርና ሊደነቅ አይገባም። ዛሬ ውብ እንደሆንሽ የነገረሽ ሰው ነገም ውብ ስለመሆንሽ እንደሚመሰክር እርግጠኛ መሆን አትችይም። አዳማቂ የማይፈልገው ውበትሽ ከትምህርት ደረጃሽ የመጣ አይደለም፣ ከስራሽ የመጣ አይደለም፣ ከቤተሰቦችሽ የመጣ አይደለም፣ ከጓደኞችሽ የመጣ አይደለም። የውበትሽ ምንጭ የአምላክሽ ልጅ መሆንሽ ነው፤ የውበትሽ መነሻ ሴትነትሽ፣ አንቺነትሽና ጥልቁ ማንነትሽ ነው። አዎ! ጀግኒት..! ውብ ነሽ! እስካከበርሽው ድረስ ሴት በመሆንሽ ብቻ ቆንጆ ነሽ፤ አሁን ያለሽበት ስፍራ በመገኘትሽ ብቻ ብርቱ ነሽ፣ እንዳቅምሽ ስለተንቀሳቀስሽ ብቻ ጠንካራ ሴት ነሽ። አለም የሚያደንቅልሽን ሳይሆን በአምላክሽ መንፈስ የተቃኘውን ውስጣዊ ውበትን የሚያዩ፣ የስብዕናሽን ጥልቀት የሚመረምሩ፣ እንዲሁ አይተው የሚማረኩብሽ ሰዎች እስኪከቡሽ ድረስ ውበትሽን ለእራስ ተናገሪ፣ ጥንካሬሽን ደጋግመሽ ለእራስሽ መስክሪ። የሚረዱሽን መምረጥ፣ የማይረዱሽንም የመተው ምርጫ አለሽ። ማንም እንዲያምንብሽ ዝቅ ብሎ የመለመን ግዴታ የለብሽም። አንደኛው ውበትሽ ክብርሽ እንደሆነ አስታውሺ። ለእራስሽ ብርታትና ሃይል መሆን ትችያለሽ፤ ለእራስሽ የሰጠሽውን ቦታ በመቀየር ብቻ አካባቢሽንና የተሰጠሽን ቦታ መቀየር ትችያለሽ። አዎ! ጀግናዬ..! ወንድነት በእራሱ ለፈተና የሚያዘጋጅህ ቢሆንም በጥንካሬህ ግን አትጠራጠር። በህይወት እስካለህ ቀላል ነገር አገኛለሁ ብለህ እንዳታስብ። ከምድር በላይ አንተ ዋጋህን ጨምረህ፣ ይበልጥ ጠንክረህና ተሻሽለህ እስካተገኘህ ድረስ ሁሉም ነገር ከባድ ነው። እራስህን ለመስራት አትስነፍ፣ አቅምህን ከማጎልበት ወደኋላ አትበል፣ ምንም ድጋፍ ባታገኝ ድጋፍህ ወንድነትህና ፈጣሪ እንደሆነ አስታውስ። ወንድነት በእራሱ የሃላፊነት መለኪያ ነው። አሁንም ሃላፊነት አለብህ፣ ወደፊትም እንዲሁ ሃላፊነትህ ይጨምራል። ምንም ባይኖርህ፣ ማንም ባይጠጋህ እግዚአብሔር አምላክህን ብቻ ስለያዝክና ወንድ ስለሆንክ ጠንካራ ነህ፣ ብርቱ ነህ። ለእራስህ አይደለም ለምትወዳቸውና ለሚወዱህ ሁሉ ዋጋ ከፍለህ ህይወታቸውን የመቀየር አቅሙ አለህ። እራስህን ጠበቅ፣ እራስህን ተንከባከብ፣ የወንድነትህን ልክ ለእራስህም አሳየው። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
Hammasini ko'rsatish...
ውሎህን መልካም ቦታና መልካም ሰው ጋር ይሁን!!! በመዳፍህ ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ ንፁህ ከመሆኑ የተነሳ ሊጠጣ ይችላል። በቆሻሻ ቦታ ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ እግርን እንኳ ለመታጠብ አይሆንም። በሞቃታማ ቦታ ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ መድረቁ አይቀርም። በቅጠል ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ እንደ እንቁ ያብረቀርቃል። የዝናቡ ጠብታ ተመሳሳይ ነው ነገርግን ቆይታውንና ጥቅሙን የሚወሰነው በሚያርፍበት ቦታ ነው። የምትውልበት ቦታና አብራኸው የምትውለው ሰው ልክ እንደ ዝናቡ ጠብታ ጠቃሚነትህንና ቆይታህን ልወስኑት ይችላሉ። አብረኸው የምትውለው ሰው ንፁህ ልብ ያለውና አላማውን ትልቅ ከሆነ የአንተም ስብዕና በበጎነት ይቀይረዋል። የምትውለው ሰው የወረደ ስብዕና ያለው ከሆነ የአንተም ስብዕና በመጥፎ ሊቀይረው ይችላልና ውሎህን መልካም ቦታና መልካም ሰው ጋር ይሁን። ✍ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተወሰደ 🌟 በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት መልካም ሰንበት ይሁንላችሁ  ❤️❤️❤️ 👉 Share Share Share 👈 @renewalofmind
Hammasini ko'rsatish...
ይቅርብህ! ፨፨////፨፨ ፍቅር ሰጪ እንጂ ተቀባይ አይደለም፤ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለም፤ ፍቅር ቀሪ እንጂ ተመላሽ አይደለም። እራስህን ጠይቅ፦ መቼ ነው የፍቅር ህይወት ሊኖረኝ የሚገባው? አሁን ለፍቅር ህይወት ብቁና ዝግጁ ነኝን? እንዴት ላስኬደው እችላለው? ከሁሉም በላይ ለሌላ ሰው የሚሆን፣ በደስታ የማካፍለው፣ በነፃነት የማጋራው የተሟላ ፍቅር ውስጤ አለን? ብለህ ጠይቅ። አዎ! ጀግናዬ..! የምትሰጠው ከሌለህ ይቅርብህ። ጠባቂነት ይጎዳሃል፤ ተቀባይነት ያሳምምሃል፤ ያሰቃይሃል። ከምንም በላይ የወደድከው ሰው መዓት ያወርድሃል፤ በመከራና ስቃይ ውስጥም ሆነህ በእልህ መውደድህን አንድታቆም አይፈቅድልህም፤ ባዶነትህን ከእርሱ ውጪ የሚሞላልህ ያለ አይመስልህም፤ በእራስህ ላይ ማዘዝ እስኪሳንህ እንደፈለገው እንዲጫወትብህ ፈልገህ ትፈቅዳለህ። በፍፁም በባዶነትና በተረጂነት ስሜት ሆነህ ፍቅርን አትጀምር። ይህን አደረክ ማለት ጉዳትህን ለማባባስ ቆርጠህ ተነስተሃል ማለት ነው። ከእራስህ አውጥተህ መስጠት ስትችል ብቻ ወደ ፍቅር ህይወት ግባ። ለእራስህ ያለህ ፍቅር ለሌላውም እንደሚገባው ስታምን ብቻ የፍቅር አጋር ይኑርህ። አዎ! ጀግኒት..! የምወደው ሰው ክፍተቴን ይሞላዋል፣ ባዶነቴን ያስረሳኛል ብለሽ ሳይሆን እኔ በፍቅሬ አክመዋለሁ፣ አበረታዋለሁ፣ እደግፈዋለሁ ብለሽ ፍቅርን ጀምሪ። ምንም እንኳን የጠበቅሽው ባይቀር በዘገየ ወቅት እንዳትጎጂ እራስሽን አቅቢ። ፍቅር ሙሉ ህይወት ነውና በእራስሽ ሙሉ ሳትሆኚ እንዳትገቢበት፣ ብቁነት ሳይሰማሽ ክፍተትሽን፣ ጉዳትሽን ይዘሽ እንዳትጀምሪው። ትኩረትሽን መስጠት ላይ እንጂ መቀበል ላይ አታድርጊ። እራስህን መውደድ፣ ማፍቀር፣ ማክበር፣ መንከባከብ፣ መጠበቅ፣ ማኩራት ስትጀምር፣ ይህን ማንነት የምታጋራው፣ የምታካፍለው ሰው ትፈልጋለህ፤ ካንተ ሙሉነት የምታቋድሰው፣ ለእራስህ የምታደርገውን በኩራት የምታደርግለት የእራስ ሰው የምትለውን ሰው ያኔ በልበሙሉነት ታገኘዋለህ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 JOIN FOR MORE: t.me/MentalCounsel 🔺🔻 SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ! https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Hammasini ko'rsatish...