cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ወሎ ሚዲያ ኔትወርክ Wollo Media Network

ወሎ ሚዲያ ኔትዎርክ የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፈጣን ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ መረጃዎችን ያደርሳል። ለአስተያየትና ጥቆማ ለመስጠት 👇

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
360
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
-830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በኢትዮጵያ ከ74ሺ በላይ ግለሰቦች የባንክ ሚስጥር ቁጥራቸው ተወስዶ ዘረፋ ተፋፅሞባቸዋል ተባለ:: በ2ዐ15 ዓ.ም ብቻ ከሞባይል ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ጋር ተያይዞ ከ74ሺ በላይ ግለሰቦችን የሚስጥር ቁጥር አጭበርብረው በመውሠድ ዘረፋ የሚፈፅሙ ሰዎች መበራከታቸውን የድርጊቱ ሠለባ የሆኑ ተጠቃሚዎች ተናግረዋል፡፡ አጭበርባሪዎቹ ከባንክ የደወሉ በማስመሠል የተለያዩ የተለያዩ የማሳመኛ መንገዶችን እንደሚጠቀሙ የወንጀሉ ሠለባ የሆኑ ደንበኞች ኤፍ.ኤም.አዲስ 97.1 ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዢ አቶ ሠለሞን ደስታ ከባልደረባችን ከታደሰ አለብኝ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ባደረጉት ቆይታ በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር እና ወንጀል እንደሚፈፅም ተናግረዋል፡፡ በብሄራዊ ባንክ በኩል ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የሚፈፅም ወንጀሎችን ለመከላከል የፋይናንስ ተቋማትን መከታተል የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱንም ተናግረዋል፡፡ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ሴኩሪቲ ባለሙያ አቶ ደሳለኝ ዳዋ በበኩላቸው በማጭበርበር ላይ የተሠማሩ ግለሰቦች የባንክ ደንበኞችን መረጃ በተለያየ መንገድ እንደሚያገኙ ገልፀዋል፡፡ ቁጥሮችን በመገመት፣ አንዱ መንገድ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የፌዴራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ መሲሳ አብዲሳ በዘርፉ እየተፈፀሙ ያሉ ወንጀሎች መበራከታቸውን ገልፀው ደንበኞች መሠል ድርጊቶች ሲፈፀሙባቸው በ15 ቀን ውስጥ ለፓሊስ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ዘግቦታል።
Hammasini ko'rsatish...
በጉራጌ ዞን በታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ፤ ሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እና ዕሁድ ሐምሌ 16/2015 የታጠቁ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። በወረዳው በቼ እና ዲዳ በተባሉ የቀበሌ ከተሞች፤ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ጥቃቱ እንደተሰነዘረ እና ግድያዎች እንደተፈጸሙ ምንጮች ከስፍራው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል፡፡ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከአካባቢው መሰወራቸው የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋለ አካል አለመኖሩ ተጠቅሷል። በተጠቀሰው ምሽት ላይ ሦሰት ሰዓት አካባቢ በቼ ቀበሌ ውስጥ በተሰነዘረ ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸው የታወቀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ዕሁድ ሐምሌ 17/2015 ምሽት ኹለት ሰዓት ገደማ አንድ አባውራ ከነባለቤታቸው እና ጎረቤታቸው ከሆኑ ግለሰብ ጋር መገደላቸውን አዲሰ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። በመስቃንና ማረቆ ብሔረሰብ መካከል ባለው የቆየ አለመግባባት በተደጋጋሚ የሚፈጸም ማንነት ተኮር ጥቃት መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ለአካባቢው ማህበረሰብ በነጻነት መንቀሳቀስ አስቸጋሪ መሆኑ ተመላክቷል። እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፤ በአካባቢው ባለው የሰላም እጦት ሳቢያ አብዛኛውየመንግሥት ሠራተኞች ለደኅንነታቸው በመስጋት በሥራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ እና ብዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ብሎም የተከፈቱትም አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ተነግሯል። የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ከሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እስከ ሐምሌ 17/2015 ድረስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት እንደደረሳቸው ጠቅሰው፤ “በቂ የጸጥታ አካላት ወደቦታው ልከናል” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም፤ ግድያውን በሚመለከት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው ወይም አይደለም? የሚለውን ጉዳይ በሚመለከት በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በጊዜው ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። በዞኑ ኹለቱ ወረዳዎች መካከል ዓመታትን ያስቆጠረው ግጭት ዕልባት ሳያገኝ የቀጠለ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ በርካታ አካላት ለችግሩ ዕልባት ለመስጠት ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት ከአራት ዓመታት በፊት ሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ሰፊ ሥራዎችን ይሰራ እንደነበር ነገር ግን ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ችግሮች ተባብሰው መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
Hammasini ko'rsatish...
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በትግራይ ክልል ኹሉም ትምህርት ቤቶች እንደማይሰጥ ተገለጸ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ከ2012 ጀምሮ ትምህርት ተቋርጦ በመቆየቱ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት ዘርፎችን እንዳይሰጡ መደረጉን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የትግራይ ሕጻናት ማግኘት የሚገባቸውን ትምህርት አላገኙም ያሉት ኃላፊው፣ ብዙዎች አምስተኛ ክፍል መሆን ሲገባቸው አንደኛ ክፍል እንደሚማሩ እንዲሁም የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት እየተማሩ ያሉት ዩኒቨርሲቲ መመረቅ የሚገባቸው ተማሪዎች ናቸው ብለዋል። ስለሆነም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ እና ለወደፊት ህይወታቸው ይጠቀማቸዋል ተብሎ የሚታሰቡትን የትምህርት ዘርፎችን ብቻ እንዲማሩ እያደረግን ነው ሲሉ ገልጸዋል። የአማርኛ ቋንቋ ጨምሮ የተወሰኑ የትምህርት ዘርፎች በትምህርት ቤቶች እንዳይሰጡ የተደረገውም፣ ተማሪዎች እድሜያቸው አስተምሯቸዋል ተብሎ ሰለሚታሰብ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኃላፊው አክለውም፣ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ አካባቢ ሳይንስ፣ ሙዚቃ፣ ስነጥበብ እና ሌሎች ትምህርቶች እንዳይሰጡ መደረጉን ገልጸው፣ ከ2012 እስከ 2015 ድረስ የተቋረጡትን ሰባት መንፈቀ ትምህርቶችን ለማካካስና ቶሎ ለመጨረስ ጠቃሚ ናቸው ተብሎ የሚታሰቡት የትምህርት ዘርፎችን ብቻ ለማስተማር ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡ የአማርኛ ቋንቋ በክልሉ ትምህርት ቤቶች አለመሰጠቱን በተመለከተ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው አንድ የተማሪ ወላጅ ‹‹አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ በመሆኑ ልጆቻችን ሊማሩት የሚገባ ነው፡፡ የትግራይ ልጆች ቋንቋውን መናገር፤ ማንበብ እና መጻፍ ካልቻሉ እንደሌላው የኢትዮጵያ ዜጋ በአገሪቱ ተዘዋውረው ሥራ መሥራት እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል›› ብለዋል፡፡ አክለውም፤ በክልሉ የአማርኛ ቋንቋ መሰጠት የሚጀመረው ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ኹሉም ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ እንዳይማሩ መደረጉ የትግራይ ተወላጆች ቋንቋውን እንዲረሱት ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል። ለአዲስ ማለዳ
Hammasini ko'rsatish...
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት ******************************* እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷል። የክብር ዶክተሬቱን በወላጅ እናቷ በወ/ሮ ተናኜ አማካኝነት ተቀብላልች። ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ፣ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬቱ የተበረከተላት። እንጅባራ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
Hammasini ko'rsatish...
01:24
Video unavailableShow in Telegram
የጎንደር ዙሪያ ፋኖዎች እና ወጣቶች ባደረጉት ብርቱ ተጋድሎ ታግቶ የነበረውን ፋኖ አደባባይ አበበ ከአፋኙ ኃይል ማስለቀቃቸውን አስመልክቶ ደስታቸውን አደባባይ በመውጣት ገልፀዋል
Hammasini ko'rsatish...
Sequence 67.mp4104.99 MB
Photo unavailableShow in Telegram
የሸዋሮቢት ከተማ የመንግሥት የሥራ አመራሮች ወደ ደብረብርሃን እና አዲሰ አበባ ሸሽተዋል ተባለ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አብዛኛው የመንግሥት የሥራ አመራሮች ወደ ደብረ ብርሃንና አዲስ አበባ መሸሻቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በዚህም የከተማዋን ከንቲባ ጨምሮ ሌሎችም የጸጥታ ተቋማት አመራሮች ከተማውን ለቀው ወደ ደብረብርሃንና አዲስ አበባ ከተሞች መሄዳቸው ነው የተነገረው። አመራሮቹ ከተማዋን ለቀው መውጣት የጀመሩት በዋናንት ሰኔ 27/2015 የከተማዋ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አብዱ ሁሴን ባለታወቁ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ መሆኑን ነዋሪዎች ጠቁመዋል። ይህን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች የቀበሌ መታወቂያ ማውጣትን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ከንቲባ ጽህፈት ቤት፣ ፖሊስ ጣቢያ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሲሄዱ፤ የሥራ ኃላፊዎች ባለመኖራቸው አገልግሎት ሳያገኙ እንደሚመለሱ ነው የገለጹት። ነዋሪዎቹ አክለውም፤ "በከተማው ከተወሰኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ውጭ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ሳይቀር የሉም፡፡ አብዛኞቹ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ሸሽተዋል፤ ያልሸሹትም በየቤታቸው ተቀምጠዋል።" ሲሉ ተናግረዋል። "በከተማዋ እና  ዙሪያው ጥይት ሲተኮስ ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ፖሊስ የለም፤ የሚዳኝ አካልም የለም።" ያሉት ነዋሪዎች፤ ነዋሪው የአካባቢውን ሰላም ለማስከበር በራሱ ጥረት እያደረግ መሆኑን ጠቅሰዋል። አዲስ ማለዳ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በጎንደር ከተማ ታግቷል የተባለዉ እስራኤላዊ አዛዉንት ቤተሰቦቹን ገንዘብ ለመቀበል አልሞ መሆኑን የእስራኤል መንግስት አሳወቀ በጎንደር ከተማ ታግቷል በተባለዉ የ 79 አመት አዛዉንት እስራኤላዊ ጉዳይ ዉዝግብ አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል። የእስራኤል ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢንተርፖልን አጋር በማድረግ ግለሰቡን በእገታ ለማስለቀቅ ጥረት እያደረኩ ነዉም ብሎ ነበር። ለህክምና እና ለቤተዘመድ ጥየቃ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል የተባለዉ አዛዉንቱ ግለሰብ ሳይታገት ታግቻለሁ ማለቱን የእስራኤል መንግስት አረጋግጫለሁ በማለቱ ጥረቱን እንዳቋረጠዉ ገልጿል። በሀገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲመራ የነበረዉም ግለሰቡን የማስለቀቅ ጥረት እንዳቆመዉ አሳዉቋል። ግለሰቡ በእስራኤል የሚኖሩ ቤተሰቦቹን እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር ድረስ ታግቻለሁ በሚል ሰበብ ሲጠይቅ እንደነበር የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን መዘገባቸዉን ብስራት ራዲዮ ተመልክቷል። ግለሰቡ ታግቷል በተባለበት ወቅትም የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምንም የቀረበለት አቤቱታ አለመኖሩን አሳዉቆ ነበር። አቪ የተሰኘዉ የግለሰቡ ወንድ ልጅ እገታዉ የዉሸት እንነበር እና ገንዘብ ፍለጋ መሆኑን አረጋግጧል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሳይታገቱ ታግቻለሁ በማለት ከቅርብ ቤተሰብ ፣ ከፍቅረኛ እና ከዘመድ አዝማድ ገንዘብ ለማግኘት የመሞከር ጥረት አሁን ድንበር ተሻጋሪ ሆኗል። በትናንትናው እለትም በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ወረዳ የሚኖር ወጣት ቤተሰቦቹን ሳይታገት ታገቻለሁ በሚል 500 ሺህ ብር የጠየቀ ቢሆንም በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
Hammasini ko'rsatish...
#ዲግሪና እና ወንበራቸውን እንዲሁም ገዋናቸውን አስቀምጠው ነፍጥ ያነሱ እንቁ የአማራ ልጆች‼ ድግሪያቸውን አስቀምጠው ነፍጥ ያነሱ፤ የህክምና ገዋናቸውን ይዘው ከነፃነት ተፋላሚዎቹ ጋር የተሰለፉ፤ ቢዝነሳቸውን ዘግተው የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ የሚመሩ፤ የዘመኔ ጣይቱዎች እነሱ ናቸው። ዛሬ ከአመራሮች ሙሉ ፈቃዳቸውን ወስጄ የማስተዋውቃችሁ የአማራ ህዝባዊ ሃይል ፋኖ የፊት ደጀን የሆኑ እንስቶችን ነው። እነዚህ እህቶቻችን ለአማራ ህዝብ ነፃነት እውን መሆን የበኩላቸውን ለማበርከት የህይወት ዋጋ የሚከፈልበትን ትግል ከተቀላቀሉ በርካታ ወራትን አስቆጥረዋል። መስዋዕትነት እየከፈሉም ይገኛሉ። ባለፈው ሳምንት በነበረ ውጊያ አንዷን አጥተናል። ለእኛ የሚከፈለው ህይወት ነው፤ እኛ ለእነሱ ማድረግ ያለብንስ? በእርግጥ ዛሬ ብዙዎች የነሱን ፈለግ እየተከተሉ ነው። ነፃነታችን እሩቅ አይሆንም። በተረፈ:- ትግሉ ሰፊ ሜዳ አለው፤ ሁላችንንም ባለንበት ማቀፍ የሚችል በርካታ ክፍት ቦታዎች አሉት። ተቀላቀሉ! ማስታወሻ ምስሉ ከAPF ፈቃድ የተሰጠበትና የሚያስከትለው ችግር እንደሌለ ታምኖበት ትግሉን መቀላቀል ለሚፈልጉ ሴት እህቶቻችንን ለማበረታታት የተለጠፈ ነው። ምስጋናው ዘ-ግዮን
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ውስጥ 40.65 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ አስመዘገቡ! ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ውስጥ 40 ነጥብ 65 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት መውጫ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ገልፀዋል። ለመውጫ ፈተና ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶ ከነበረው 240 ሺህ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን 194 ሺህ 239 ተማሪዎች ብቁ ሆነው ለፈተና መመዝገባቸውንም ነው የተናገሩት። ከዚህ ውስጥ ከ48 የመንግስት ተቋማት 84 ሺህ 627 ተማሪዎች እና ከ171 የግል ተቋማት 109 ሺህ 612 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውም ነው የገለጹት። የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ ከመንግስት ተቋማት 77 ሺህ 981 ተማሪዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት 72 ሺህ 203 ተማሪዎች በድምሩ 150 ሺህ 184 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 61 ሺህ 54 ተማሪዎች ወይም 40 ነጥብ 65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ አስመዝገበዋል ነው የተባለው፡፡ ለተቋማትም የተማሪዎቻቸውን ውጤት የመላክ ሥራ መጀመሩንም ጠቁመዋል። Via FBC
Hammasini ko'rsatish...