uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።

Ko'proq ko'rsatish
1 411
Obunachilar
+224 soatlar
+257 kun
+8530 kun
Postlar arxiv
«ባለሥልጣኑ የሥጋ ምርት ጥራቱን ጠብቆ በብዛት ለገበያ እንዲቀርብና በዓለም አቀፍ ገብያ ተወዳዳሪ ለመሆን የባለሙያዎች አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው!» ዶ/ር አያሌው ሹመት በባለሥልጣኑ የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሠርትፊኬሽን ዳይሬክተር ***** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በግብርና ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር በዓለምአቀፍ እና በአገርአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ጤና እንዲሁም በአካባቢ ላይ ጎጂ ተጽዕኖ እንዲቀንስ ወይም እንዲወገድ የማስቻል ዓላማ ይዞ በደንብ ቁጥር 509/2015 የተቋቋመ የፌደራል መ/ቤት ሲሆን ባለሥልጣኑ ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ የውጭ አገራት የሚላክ ሥጋና ተረፈ ስጋ ምርት አመራረት፣ አያያዝ እና አጓጓዝን በቅርብ በመከታተል እና የኢንስፔክሽን አገልግሎት በመስጠት የሚላከው ሥጋና ተረፈ ሥጋ ጤንነቱ፣ ደኅንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ የአገራችንን እና የተቀባይ አገሮችን መስፈርቶች ያሟላ ስለመሆኑ የጤና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በመስጠትና ብቁ የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎችን በማፍራት የአገሪቱን የሥጋና ተረፈ ሥጋ ምርት ኤክስፖርት ማሳደግ ነው፡፡ ይሄን ተግባርና ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት በባለሥልጣኑ የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሠርትፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አያሌው ሹመት በባለሥልጣኑ የ10 ዓመቱን መሪ እቅድ ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾችና ስትራቴጂያዊ ግቦች መሰረት በማድረግ ለመሥራት በሚያስችል ሁኔታ በተመረጡ የእንስሳት ምርቶች የደኅንነት ፕሮቶኮል (ጋይድ ላይን፣ የአሰራር ስርአት፣ ማኑዋል ወዘተ ...) ማዘጋጀት፣ እንዲሁም የቁጥጥር ሥትራቴጅ ለመቅረጽ፣ የተጀመሩትን ለማጠናቀቅ፣ ማስጸደቅና ለማስተግበር እና በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ባለሙያዎች የስጋ መመርመር ክህሎት ማሳደግ የሚያስችል ስልጠና በመስጠት በየጊዜው የባለሙያዎችን አቅም መገንባትን ጨምሮ በርካታ ሥራዎች እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ዶ/ር አያሌው አክለውም በአገራችን በሚገኙ 11 ኤክስፖርት ቄራዎች ውስጥ የሚካሄደውን አጠቃላይ የእንሰሳት እርድ ቅድመ ምርመራና ድህረ ምርመራ ሥራዎችን በመደገፍ እና በመከታተል እንድሁም ዓለምአቀፍ የምግብ ደኅንነት ሥርዓት መተግበሩን ኦዲት በማድረግ(በመቆጣጠር) እና በመጨረሻም ምርቱ ለኤክስፖርት ብቁ መሆኑን በምርመራ በማረጋገጥ ዓለምአቀፍ የጤና ሰርተፊኬት በመስጠት ለስጋ ተቀባይ አገራት እንዲላክ ለማድረግ ከ 70 በላይ የባለሥልጣኑ የቁጥጥር ባለሙያዎችን በሁሉም ቄራዎች በመመደብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የኤክስፖርት ቄራዎች ደረጃቸውን ጠብቀው በተገቢው ቦታ እንዲገነቡና የውስጥ አደረጃጀታቸውም ሆነ ግንባታቸው በመስፈርቱ መሰረት እንዲያሟሉ የቴክኒክ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ ግንባታቸው ሲያልቅም አገራዊ እውቅና የመስጠት፣ እንዲሁም በተቀባይ አገሮች በማስገምገም እውቅና እንዲያገኙ በማድረግ ምርታቸውን እንዲልኩ የማስቻል ሥራዎችን በባለሥልጣኑ በኩል እየተከናወነ መሆኑን ኃላፊው ያብራራሉ፡፡ በተመረጡ የእንስሳት ምርቶች የደኅንነት ፕሮቶኮል(ጋይድ ላይን፣ የአሰራር ስርአት፣ ማኑዋል ወዘተ ...) በማዘጋጀት የእንስሳት ውጤቶችን ደህንነት በመጠበቅ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በተመረጡ የእንስሳት ምርቶች ወይም ውጤቶች የደህንነት ፕሮቶኮል(የአሰራር ማኗል) በማዘጋጀትና በማስተግበር፤ ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር በማሳደግ፣ በክልሎች የቄራ ዲዛይኖችና በምግብ ደህንነትና ጥራት ዙሪያ ለክልሎች ክትትልና ድጋፍ በማድረግ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለይቶ በማስፋፋት የአገራችንንም ሆነ የዓለምአቀፉን ደንብና አሠራርን የተከተለ የሥጋ ምርመራ አገልግሎት በቄራዎች እንዲኖር ለክልል ባለሙዎች የተሀድሶና የአቅም ማሳደጊያ ስልጠና መስጠትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተግባራትን ባለሥልጣኑ እያከናወነ መሆኑን ዶ/ር አያሌው ገልጸዋል፡፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሠርትፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ሄርድ ከተባለ መንግስታዊ ኘሮጀክት ጋርበመተባበር ለሐላል፣ ለድርጅት የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎች እና በቄራዎች ለሚገኙ የባለሥልጣኑ ኢንስፔክተሮች ሞጆና ቢሾፍቱ በሚገኙ 5 የተመረጡ ቄራዎች የሥራ ላይ ሥልጠና እየሰጠ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር አያሌው የሥልጠናው ዓላማም የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ በመላ አገሪቱ ባሉት 11 የኤክስፖርት ቄራዎች የስጋ ምርት ተቀባይ አገራትን እና ዓለምአቀፍ የምግብ ደኅንነት ስርዓት መስፈርቶችን አሟልተው እንዲሰሩ በማድረግ የምግብ ደኅንነት የአሰራር ሥርዓቱን ቀጣይነት በማረጋገጥ የዓለም አቀፉን ገብያ ሰብሮ ለመግባት መሆኑንም አብራርተዋል። ሥልጠናው በስጋ ተቀባይ አገሮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና ከዘመኑ ጋር እያደገ የሚሄድ የምግብ ደህንነት አመራር ስርዓት በኤክስፖርት ቄራዎች ተፈጻሚነቱንና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ በቅድመ እርድና ድኅረ እርድ ምርመራ በማከናወን እና የቄራዎችን ሐይጅንና ሳኒቴሽን እንዲጠበቅ በመቆጣጠር ጤንነቱ፣ ደኅንነቱና ጥራቱን የተጠበቀ ለወጭ ገበያ የሚቀርብ እና ለሰው ምግብነት የሚውል የስጋ ምርት እንዲመረት በማስቻል በኩል ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ጠቃሚ መሆኑን የገለጹት የሥልጠናው ተሳታፊዎች ባለሥልጣኑ መሰል የሥራ ላይ ሥልጠናዎችን በመስጠት በኩል እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። ዶ/ር አያሌው ዘርፉ ልዩ ትኩረትና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ ከሐላል፣ ከድርጅት የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎች እና በቄራዎች ከሚገኙ የባለሥልጣኑ ኢንስፔክተሮች በተጨማሪ መሰል ሥልጠናዎች በቄራዎቹ ለሚሰሩ የተለያዩ ባለሙያዎች ለመሥጠት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ያብራራሉ፡፡ እስከአሁን አገሪቱ ባላት የእንስሳት ኃብት ልክ ከዘርፉ ተጠቃሚ ሳትሆን መቆየቷን የሚገልጹት ዶ/ር አያሌው አሁን ላይ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት፣ የሕግና የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ፣ ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከቄራዎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ከዘርፉ የሚገኜውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ባለሥልጣኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝና ይሄንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሥራ ያቆሙ ቄራዎችን በቅርበት ችግራቸውን በመፈተሸ፣ በማገዝና በማብቃት ሥራ የሚጀምሩበት ሁኔታን በማመቻቸት እና ሌሎች በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመፍታት አሁን አገሪቱ ባላት አቅም በየዓመቱ ከ200 ሺህ ቶን የሥጋ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚቻል የተናገሩት ዶ/ር አያሌው ይህንንም እውን ለማድረግ ባለሥልጣኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንና የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሥራ ላይ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ውጤታማ ሥራ እንደሚያከናውኑ ያለቸውን እምነት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 70.2 ሚሊየን የቀንድ ከብት፣ 42.9 ሚሊየን የበግ፣ 8 ሚሊየን የግመል እንዲሁም 52 ሚሊየን አካባቢ የፍየል ኃብት እንዳላት መረጃዎች ያመላክታሉ። ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

አግባባዊ የእንሰሳት መድኃኒት አጠቃቀም ስረዓት መዘርጋት ለእንሰሳት ጤንነት መጠበቅና ምርታማነት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፤ ***** የእንሰሳት መድሃኒትን በተመለከቱ መመሪያዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት ተካሄደ፤ የኢትዮጲያ ግብርና ባለስልጣን የእንሰሳት መድኃኒት ጥራት ደረጃ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ.ር ሰለሞን ከበደ በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የመድረኩ ዋና አላማ ለእንስሳት አርቢው ህብረተሰብ የሚቀርብ የእንስሳት መድኃኒት ጥራትና ፣ ፈዋሽነትና ደህንነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ለእንሰሳት አረቢው ማህበረሰብ የሚታደሉ መድኃኒትቶች በምን አግባብ መታዘዝና መሰራጨት እንዳለባቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ መድረስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ብለዋል፡፡ ይህ መድረክ ከዓለም የአርሻና ምግብ ድርጅት /FAO/ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በእንሰሳት መድኃኒት ማዘዣ አጠቃቀም ፣ ያለማዘዣ ወረቀት ሊታደሉ የሚችሉ የእንሰሳት መድኃኒቶች እና በእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ለመወሰን በተዘጋጁ መመሪያዎች ላይ ተገቢውን ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረስና ለተፈጻሚነቱ ጠንካራ እና ውጤታማ የቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት ፣ጥራቱ ፣ፈዋሽነቱና ደህንነቱ ባልተረጋገጠ በህገ-ወጥ መንገድ በሚታዘዝ የእንስሳት መድኃኒት ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የጤና ችግር ለመከላከል ፣ በእንስሳው፣ በህብረተሰቡ ፣ በአካባቢና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ከወድሁ መፍትሄ ለማስቀመጥ ፣ በአሁኑ ሰዓት በአለም ዙሪያ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለው የጸረ- ተህዋሲያን መድኃኒቶችን መላመድ ለመከላከል እና በረቂቅ መመሪያው ላይ የሚሻሻሉና ተጨማሪ ግብዓቶች ካሉ በዚህ ዉይይት የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ዶ.ር ሶሎሞን አክለውም ይህ መድረክ መዘጋጀቱ ለተዘጋጀው መመሪያ ግብዓት ለመውሰድና በዚህ መመሪያ ላይ የተቀመጡ መመሪያውን ለመተግበር ማነቆ የሚሆኑ ካሉ በባለሙያዎችና በባለድርሻ አካላት ታይተውና ተገምግመው ማሻሻያ ተደርጎባቸው መሪያው ከጸደቀ በኋላ እንድፈጸምና እንድተገበር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንድወጣ ያግዛል ብለዋል፡፡ የአለም እርሻና ምግብ ድርጅት ተወካይ የሆኑት አቶ ጤናው ታደግ በበኩላቸው የእንሰሳት ጤንነትን ለመጠበቅና ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚያስፈለጉ በአገርም ውስጥም ሆን በውጭ አገሮች ተመርተው በአገራችን ስራ ላይ የሚውሉ የእንሰሳት መድኃኒቶች ፣ የህክምና መገልገያዎችና ሌሎች ግብዓቶች የሚፈለገውን ጥራት አይነትና መጠን አሟልተው ለእንስሳት አርቢው ህብረተሰብ እንድደርሱ በማድረግ ሀገሪቱ በእንሰሳት ሀብት የበለጠ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያስችል ስረዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ መመሪያ ጸድቆ ስራ ላይ እንድውል የበኩላች ንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል፡፡ የእንሰሳት ሀኪሞች ፣ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች ፣ አጋር አካለት እና ከየኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በመድረኩ ላይ የተገኙ ሲሆን በተዘጋጀው የእንስሳት መድኃኒት ረቂቅ መመሪያ ላይ ተጨማሪ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች ተነስተዉ የቡድን ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ ተደርሶባቸዋል፡፡ በመጨረሻም ዶክተር ሰለሞን ለተነሱ ሀሳቦች ምላሽ በመስጠት እና በተዘጋጀው የእንሰሳት መድሃኒት የአሰተዛዘዝና አጠቃቀም ረቂቅ መመሪያ ላይ መካተት ያለባቸው ተጨማሪ ግብአቶች በመመሪያው እንደሚካተቱ ገልፀው መመሪያዎች ጸድቀዉ እንድተገበሩ በማድረግ የእንሰሳት መድኃኒት አጠቃቀም ስረዓት ለመዘርጋት ህገወጥ የእንሰሳት መደኃኒት ንግድንና አጠቃቀምን ለማሰቀረት እንድሁም አግባባዊ የእንሰሳት መድኃኒት አጠቃቀም እንድኖር ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለው የእለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡ @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

የሥጋ ምርት ጥራቱን ጠብቆ በብዛት ለገበያ እንዲቀርብና በዓለም አቀፍ ገብያ ተወዳዳሪ ለመሆን የባለሙያዎች አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤ ***** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሠርትፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ሄርድ ከተባለ መንግስታዊ ኘሮጀክት ጋር በመተባበር ለሐላል፣ ለድርጅት የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎች እና በቄራዎች ለሚገኙ የባለሥልጣኑ ኢንስፔክተሮች ሞጆና ቢሾፍቱ በሚገኙ 5 የተመረጡ ቄራዎች የሥራ ላይ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት አንዱ ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ የውጭ አገራት የሚላክ ሥጋና ተረፈ ስጋ ምርት አመራረት፣ አያያዝ እና አጓጓዝን በቅርብ በመከታተል እና የኢንስፔክሽን አገልግሎት በመስጠት የሚላከው ሥጋና ተረፈ ሥጋ ጤንነቱ፣ ደኅንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ የአገራችንን እና የተቀባይ አገሮችን መስፈርቶች ያሟላ ስለመሆኑ የጤና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በመስጠትና ብቁ የሥጋ ምርመራ ባለሙያዎችን በማፍራት የአገሪቱን የሥጋና ተረፈ ሥጋ ምርት ኤክስፖርት ማሳደግ መሆኑን የገለጹት በባለሥልጣኑ የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሠርትፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አያሌው ሹመት ባለሥልጣኑ የሥጋ ምርቱ ጥራቱን ጠብቆ በብዛት ለገበያ እንዲቀርብ በየጊዜው የባለሙያዎችን አቅም መገንባትን ጨምሮ በርካታ ሥራዎች እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሥልጠናው ዓላማም የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ በመላ አገሪቱ ባሉት 11 የኤክስፖርት ቄራዎች የስጋ ምርት ተቀባይ አገራትን እና ዓለምአቀፍ የምግብ ደኅንነት ስርዓት መስፈርቶችን አሟልተው እንዲሰሩ በማድረግ የምግብ ደኅንነት የአሰራር ሥርዓቱን ቀጣይነት በማረጋገጥ የዓለም አቀፉን ገብያ ሰብሮ ለመግባት መሆኑንም አብራርተዋል። የሥልጠናው ተሳታፊዎች ሥልጠናው በስጋ ተቀባይ አገሮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና ከዘመኑ ጋር እያደገ የሚሄድ የምግብ ደህንነት አመራር ስርዓት በኤክስፖርት ቄራዎች ተፈጻሚነቱንና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ በቅድመ እርድና ድኅረ እርድ ምርመራ በማከናወን እና የቄራዎችን ሐይጅንና ሳኒቴሽን እንዲጠበቅ በመቆጣጠር ጤንነቱ፣ ደኅንነቱና ጥራቱን የተጠበቀ ለወጭ ገበያ የሚቀርብ እና ለሰው ምግብነት የሚውል የስጋ ምርት እንዲመረት በማስቻል በኩል ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል። በሥልጠናዎቹ ላይ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የባለሥልጣኑ የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐሚድ ጀማል በበኩላቸው አገሪቱ ባላት የእንስሳት ኃብት ልክ ተጠቃሚ ሳትሆን መቆየቷን ገልጸው ለዚህም የሥጋ መርማሪና የባለሥልጣኑን ኢንስፔክተሮች በመሰል የሥራ ላይ ሥልጠናዎች በማብቃት ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ባለሥልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ሐሚድ አክለውም ዘርፉ ልዩ ትኩረትና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሥራ ላይ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ውጤታማ ሥራ እንደሚያከናውኑ ያለቸውን እምነት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 70.2 ሚሊየን የቀንድ ከብት፣ 42.9 ሚሊየን የበግ፣ 8 ሚሊየን የግመል እንዲሁም 52 ሚሊየን አካባቢ የፍየል ኃብት እንዳላት እና አሁን አገሪቱ ባላት አቅም በየዓመቱ ከ200 ሺህ ቶን የሥጋ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚቻል መረጃዎች ያመላክታሉ። @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

«ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ መኖ ለእንስሳት አርቢዎች ተደራሽ እንዲሆን ቁጥጥር እየተደረገ ነው!» ~አቶ ዘላለም አበበ በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የመኖ ጥራት ደረጃዎች ምዝገባና ፈቃድ ሥራ አሥፈጻሚ

የምግብ ደኅንነት ለምግብነት በሚወሉ ጥሬ የግብርና ምርቶች! **** በዘንድሮው ዓመት በዓለማቀፍ ደረጃ ለአምስተኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለአራተኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም የምግብ ደህንነት ቀን (World Food Safety Day) “የምግብ ደረጃዎች ህይወትን ያድናሉ” (Food Standards Save lives) በሚል መሪ ቃል እና የምግብ ደህንነት የሁሉም ኃላፊነት ነው (Food Safety is Everyone’s Business) የሚል መፈክርን በማንገብ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም (June 7 2023) በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህን በዓል በማስመልከት የምግብ ደህንነት ለምግብነት በሚውሉ ጥሬ የግብርና ምርቶች በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፅሁፍ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ለምግብነት የሚውሉ የግብርና ምርቶች (Primary Agricultural Products) ለሰው ልጆች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በማቅረብ የአመጋገብ ስርዓታችን የተሻለ እንዲሆን ያደርጋሉ። ይህ እንዲሆን ደግሞ ከእጽዋትና ለምግብነት ከሚውሉ እንስሳት የምናመርታቸው ምርቶች እና ተዋዕጽኦች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት። ነገርግን በአመራረት ሂደት ደህንነታቸው ካልተጠበቀ በበሽታ አምጪ ተህዋሰያንና በኬሚካል ሊበከሉ ወይም የሚጠበቅባቸውን የጥራት ደረጃ ላያሟሉ ይችላሉ፣ይህም ሰዎች ምርቶቹን ለምግብነት በሚጠቀሙብት ጊዜ ለተለየዩ በሽታዎች ሊዳርጋቸው ይችላል። ጤናማ ያልሆኑ የግብርና ምርቶችና ተዋዕጽኦች በሰዎች ጤና እና ደህንነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖን ብቻ ሳይሆን በኑሮ እና በኢኮኖሚው ላይ የማይፈለግ ተፅእኖ ያስከትላሉ። በመሆኑም አምራቾችና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ለምግብነት የሚውሉ ምርቶችን በሚያመርቱበት ወቅት ምርቶቹ በተዋህሲያን፣ በኬሚካልና በመድኃኒት ቅሪቶች ያልተበከሉ ሰለመሆናቸው ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። የምግብ ደህንነት ጠቀሜታ :- የምግብ ደህንነትን መጠበቅ የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል። ከአምራቹ  አንጻር የሚኖረው ጥቅም :- 1.  ድህንነቱ የተጠበቀ ምርት/ምግብ የአምራቾችን ምርታማነትንና የምርት ጥራትን ይጨምራል፣ 2.  የምግብ ብክነትን ይቀንሳል፣ 3.  የንግድ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ  የተመረተው ምርት/ምግብ የሚኖረው ዋጋ ይጨምራል፣ 4.  ሸማቹ ወይም ተጠቃሚው ማህበረሰብ ለምርቱ ያለው አመኔታ ይጨምራል፣ ከሸማቾች/ከተጠቃሚው ሕብረተሰብ አንጻር የሚኖረው ጥቅም :- 1. ጥራቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የግብርና ምርትና ተዋዕጾ ለሸማቹ ተደራሽ እንዲሆን ያግዛል። 2.  ሕበረተሰቡ የተሻለ ንጥረ-ምግብ እንዲያገኝ እና የምግብ ወለድ በሽታዎች እንዲቀንሱ ያደርጋል። 3.  የሸማቹ ማህበረሰብ ጤና እና የአኗኗር ዘይቤ የተሻለ እንዲሆን ያግዛል። የግብርና ምርትና ተዋዕጾ/የምግብ ደህንነትን እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? ከአምራቾች አንጻር:- አርሶአደሮች፣ አርብቶአደሮች እንዲሁም ባለሙያዎች ለምርት ሂደት የሚጠቀሙባቸው ግብዓቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ። ለምሳሌ ወተት በማምረት ሂደት ወስጥ ለወተት ላሞች የሚቀርበው መኖ የወተት ብክለትን ሊያስከትሉ ከሚችሉ እንደ አፍላቶክሲን፣ የኪሚካል ቅሪት፣ የእንስሳት መደኃኒት ቅሪት እና በሽታ አምጪ ተህዋስያን ለሆኑ በካዮች መግቢያ ሆኖ ወደ ወተት እንዳይመጣ ጥንቃቄ ማደረግ እና እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። ይህንን እና ሊሎች መሰረታዊ የሆኑ የንጽሕና አጠባበቅ ተግባራትን በማከናወን ለሰው ልጆች ምግብነት የሚቀርበው ወተት ያልተብከለና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል። ከአሰራር ወይም ከአመራረት ሂደት አንጻር:- የምግብ ደህንነትን ከእርሻ አሰከ ጉርሻ ባለው የምርት ሰንሰለት ወስጥ ለማስጠበቅ በአመራረት ሂደት ወቅት የሚከወኑ የተሻሻሉ አሰራሮች ወሳኝነት አላቸው። በመሆኑም በግብርና ምርቶች አመራረት ሂደት ወስጥ የተሻሻሉ አሰራሮችን ማለትም መልካም የግብርና አመራረት (Good Agricultural Practices)፣መልካም የንጽህና አጠባበቅ ዘዴን በመተግበር (Apply good hygiene Practice)፤ በእንስሳት እርባታው ሂደት ደግሞ መልካም የእንስሳት አረባብና አያያዝ ዘዴ (Good animal husbandry)፣ ክትባቶችን በመስጠትና እና ሌሎች በሽታ እንዳይከሰት የሚያስችሉ የቅድመ መከላከል ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲሁም በየእርባታ ጣቢያው ያሉትን እንስሣት አጠቃላይ ጤንነት (Biosecurity and herd health management on the farms) በመጠበቅ የምርቶችን ደህንነት ማረጋገጥ ይቻላል። በተጭማሪም ለምግብነት በሚውሉ እንስሳቶች ላይ አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር የሕክምና መድኃኒቶችን አለመጠቀም፣ የመድኃኒት ሕክምና ደግሞ የግድ ሆኖ ሲገኝ  መድኃኒቱ ከሰውነታቸው ውስጥ የሚፈጅበትን የማስወገጃ ጊዜ (withdrawal period) መጠበቅ እና በሕክምና ወቅት የሚመረቱ ምርቶችን ለሰው ምግብነት አለማዋል ሌሎች የምግብ ደህንነትን ማስጠበቂያ/ማረጋገጫ  ዘዴዎች ናቸው። ከምርት ተቆጣጣሪ አካላት አንጻር:- ከምርት ደህንነት እና ጥራት ቁጥጥር እና አንጻር ተቆጣጣሪ ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች ሊያከናውኗቸው የሚገቡ በርካታ ተግባራት አሉ። በተለይ ከምግብ ደህንንነት አንጻር የሚከተሉት ተግባራት በዋነኝነት መተግበር ይኖርባቸዋል:-   አምራቾች መልካም የአመራረት ዘዴዎችን [Good animal husbandry practices (GAHP) and good hygiene practices (GHP), Implementation of HACCP in abattoirs] እንዲከተሉ ማበረታታት፣ መደገፍ፣ ማስተግበር እና መቆጣጠር።   አርሶአደሮች የተሻሻሉ የግብርና ግብዓቶችንና ቴክኖሎጂዎችን፤ ከእንስሳት ወደ ሰው እና ከሰው ወደ እንስሳት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስቸሉ የእንስሳት ሕክምና እና የማማከር አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማመቻቸት።   የግብርና ምርትና ተዋዕዖ/ምግብ ደህንነትን የሚያስጠብቁ የሕግ ማዕቀፎችን ማለትም አሰራሮችን፣ ደንቦችን፣ አዋጆችን፣ ለምሳሌ እንደ የንፅህና አጠባበቅ ደንብ (Code of Hygienic Practice) ያሉትን ሰነዶች ማዘጋጀትና  ማስተዋወቅ።   የተዘጋጁ ደንቦችን ማስተግበር እና መደበኛ የክትትል እና የቁጥጥር ተግባራትን (Enforce regulations and undertake routine farm and other primary level production inspections) ማከናወን ይገባል፡፡ ‘’ያለምግብ ደህንነት የምግብ ዋሰትናን ማስጠበቅ አይቻለም’’ “There is no food security without food safety”

ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬ
ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

ባለሥልጣኑ በግብርው ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት ለመዘርጋትና ለመተግበር የእቅድ አፈጻጸሙን ማሻሻል ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፤ **** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የ2015 በጀት አመት የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ከተቋሙ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ/ም  በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ገምግሟል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውይይቱ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የእቅድ አፈጻጸሙ ግምገማ ዋና  ዓላማ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ካቀዳቸው ተግባራት ውስጥ በ9 ወራት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ምን እንደሚመስል በመገምገም እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን በመፈተሸ እንዲሁም ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበት በቀሪው በጀት ዓመት ውጤታማ ሥራ ለመስራት ነው ብለዋል፡፡ አምባሳደር ድሪባ አክለውም በግብርናው ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር በዓለም አቀፍ አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ሁሉም ሠራተኛ ተቅንጅቶና ተደምሮ በጊዜ የለንም መንፈስ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከታቀዱት የፊዚካል እቅዶች ማለትም የግብርና ቴክኖሎጂ ቁጥጥር፣ የግብርና አገልግሎት ቁጥጥር ፣ የግብርና ምርት ቁጥጥር፣ የግብርና ግብዓት ቁጥጥር እና ተቋማዊ የቁጥጥር አቅም ግንባታን  በተመለከተ የ9ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሰራተኛው በባለሥልጣኑ የፋይናንስ ፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አበባው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ አብዛኞቹ ተግባራት በእቅዳቸው መሰረት መከናወናቸውንና በበጀትና በትራንስፖርት እጥረት፣ በግዥ መጓተት አና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት አፈጻጸማቸው ዝቅ ያለ እና ያልተከናወኑ ተግባራት መኖራቸውን  በሪፖረቱ ተጠቅሰዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎችም ከትራንስፖርትና ከበጀት እጥረት ጋር በተያየዙ ያሉ ችግሮችን መፍታት፣ ከክልሎችና ከባለድርሻ አካለት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማሳደግ፣ የሚታዩ የመልካም አሥተዳደር ችግሮች በወቅቱ እንዲፈቱ እና ሌሎች ሪፖርቱን የተመለከቱ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው ሰፊ ውይይት ተደረጎበታል። በቀረበው ሪፖርትና በተነሱ ኃሳቦች ላይ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደር ድሪባ ተቋሙ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ብዙ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን ሁላችንም ህዝብን ለማገልገል እስከተቀመጥን ድረስ መልካም ስነ-ምግባር በመላበስ  ያሉብንን ችግሮች በመቋቋም ተቋማችን ከአለም አቀፍ የተቆጣጣሪ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን በቁርጠኝነት  መስራት አለብን ብለዋል፡፡ አምባሳደር ድሪባ አክለውም በዚህ ሪፖርት ላይ የተሻለ አፈጻጸም የታየባቸውን ተግባራት በማስቀጠልና ታቅደዉ ያልተከናወኑ ተግባራትን በመለየት ባሉት ቀሪ ጊዜያት ውስጥ አቅማችንን አሟጠን ለመፈጸምና እንደተቋም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ዝግጁ መሆን እንዳለበት አሳስበው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን አመራሮችና ሠራተኞች የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽንን ጎበኙ ************** የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን አመራሮችና ሠራተኞች “ከቤተ ሙከራ እስከ አዝመራ" በሚል መሪ ሀሳብ ለሕዝብ ይፋ ሆኖ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል፡፡ ግብርና የአገሪቱ የጀርባ አጥንት መሆኑንና ከእጅ ወደ አፍ የነበረው የግብርና ስራ በአሁን ወቅት ወደ ዘመናዊነት ለማሸጋገር መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኑነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ እጅጉ የጉብኝቱ ዋና አላማም አመራሩና ሠራተኛው ግብርናው ከነበረበት ኋላ-ቀር አሰራር ወጥቶ አሁን የደረሰበትን ደረጃ አውቆ ለበለጠ ውጤት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር አዘጋጅነት "ከቤተ ሙከራ እስከ አዝመራ" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም ይፋ የሆነው የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽን ከሳምንት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መከፈቱ ይታወሳል። ለበለጠ መረጃ፦ ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority ቴሌግራም፡- eaa_123 @የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤

ምክር ቤቱ የዕፅዋት ዘርን ለመደንገግ የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፤ * የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ17ኛ በመደበኛ ጉባዔው፤ የዕፅዋት ዘርን ለመደንገግ የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ፤ ረቂቅ አዋጁ የዕፅዋት ዝርያን በማዘመን ቴክኖሎጂ እና ኢንቨስትመንትን በመሳብ በዓለም አቀፍ ገበያው ተወዳደሪ እና ተሳታፊ ለማድረግ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከውጭ ሀገራት የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ወደ ውጭ ሀገር የሚላኩ ምርቶችን በማሳደግ እና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ረቂቅ አዋጁ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ሰብሳቢው አክለው አብራርተዋል፡፡ ከግብርና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና ከሚመለከታቻው አካላት ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለረቂቅ አዋጁ የሚሆኑ ግብአቶችን መሰብሰብ እንደተቻለ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ ለምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው፤ ለአርሶ አደሩ ጥራቱን የተበቀ ምርጥ ዘር በአይነት እና በመጠን በማቅረብ ለሀገር ዕድገት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የውጭ ሀገር ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚቀንስ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ለሀገር ኢኮኖሚ መነቃቃት ዘርፈ-ብዙ ጥቅም እንዳለው የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል፡፡ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1288/2015 አድረጎ በምሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ ©የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግብርና እና ሳይንስ አውደ ርዕይን መርቀው ከፈቱ ******* ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግብርና ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የግብርና እና ሳይንስ አውደ ርዕይን በሳይንስ ሙዚየም መርቀው ከፍተዋል። አውደ ርዕዩ የምርታማነት ቴክኖሎጂ ፣ የምርምርና ፈጠራ ስራዎች ፣ ዲጂታላይዜሽን ግብርና እና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮረ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ የሚቀርብበት ነው። በግብርና ሚኒስቴር ፣ በኢትዮ ቴሌኮም እና በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ''ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ '' በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ የጀመረው አውደ ርዕዩ 70 የውጭና የሀገር ውስጥ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ምርቶቻቸውን እና የግብርና ቴክኖሎጂዎቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም፣ አውደ ርዕዩ በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ዝግጅቶች የግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች የግብርና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይካሄዳል። በአውደ ርዕዩ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ተገኝተዋል። ©EBC