cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የኛ ሒ❤️ወ❤️ት

Hayku haykui

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
179
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ጓደኝነት ምንድነው ? ጓደኝነት ለኔ መውደቅ መነሳት ነው አልፎ ጥሎ መሄድ ሳይሆን በሚያደክም ረዥምና አታካች መንገድ ላይ እኩል መራመድ የደከመን ማጠንከር…… መብላት መጠጣት ማውራት ሳይሆን መኖር ፈቅዶ መሸነፍ ነው መሸነፍህን አይቶ ማውራት ለሚፈልግ ግን ገደብ ትሰጠዋለህ ጓደኛህ ሳይሆን የምታውቀው ሰው ብቻ ታደርገዋለህ…… አንተን ማወቅና መረዳት ካልቻለ አንተም ስለሱ ያሰብከው ስህተት ሆኖ ካገኘከው ቢያንስ ለነበራቹ ጊዜ ስትል ትሄዳለህ ስለማትወደው ሳይሆን እንዳይጎረብጠው ስለምትፈልግ ምቾቱ ስለሚያሳስብህ …… አንተ ላይ እንደደከመና ከዚ በላይ ሊቋቋምህ እንደማይችል እስኪነግርህ ድረስ አትጠብቅ የጓደኛም እጣ ክፍል ይኖረው ይሆናል …… ሳይሰለቹ . ኡፍ መጣ ደሞ ሳትባል ቀድመህ . ለራስህ ገደብን ፍጠር ነገሮች ሁሉ ጊዜ እስኪፈታቸው ጠብቅ…… ከሁሉም ግን ጉዞህ ጥሩ ጓደኛ ለማግኘት ሳይሆን ጥሩ ጓደኛ ለመሆን ይሁን ………
Hammasini ko'rsatish...
ሀይከል ነኝ አብቡልኝ ከተመቻችሁ ሸር ወዳጄ ጥሎህ በሔደ ሰዉ አትዘን አተን የማይፈልግህ ሰዉ ስለሔደ አተ አደለህም ማዘንና ማልቀስ ያለብህ እሱ እራሡ ነዉ ነገሩ እዲህ ነዉ 👇👇👇 አንዲት ወጣት አድ መልከ መልካም ልጂ ትወድና ፍቅሮን ለመግለፅ በጣም ትፈራለች ጎደኞቿም እድነግረዉ ያበረታቶን ነበር እሶ ግን ፍቃደኛ ልቶን አልቻለችም ፍራቻ ያዛት ግን ከግዜ ወደ ግዜ በትምህርቶም እየደከመች ሣቅ ጨዋታዋም እየጠፋ እና ሁሉም ነገር እያስጠላት ትመጣለች ከብዙ ሴቶችም ጋ ስታየዉ መቅናትና መናደድ ጀመረች ጎደኞቿም በስት መከራ አግባብተዉ እድነግረዉ ማድረግ ቻሉ እሶም እየፈራችና እየተርበተበተች በጣም እደምትወደዉ ትነግረዋለች እሱም በጣም ጉረኛና ቀብራራ ሰለ ነበር እዲህ አላት በጣም ይቅርታ እና እኮን የፍቅር ጥያቄሺን ልቀበል ይቅርና በዚህ ምድር ላይ ማንን ትጠላለህ ተብየኮ ብጠየቅ አንቺን ነዉ የምለዉ እና ይሄንን ጥያቄሺን ደግመሺ እዳጠይቂኝ አላት ልጂቱም ምንም እዳልተፈጠረ ተረጋግታና ፈገግ ብላ ወደ ጎደኞቿ ተመለሠች ። ጎደኞቿም ፈገግታዋን እያዩ ልጁ የፍቅር ጥያቄዋን እደተቀበላት አምነዉ በደስታ ተቀበሎት አዶም ጎደኛዋ እሺ አለሻ በጣም ደስ ይላል ስትላት ፈገግ ብላ አረ በፍፁም እደዉም በዚህ አለም ላይ እደንየ የሚጠላዉ ሰዉ እደለለ ነዉ የነገረኝ አለቻቸዉ ጎደኞቾም ታዳ እዴት አላዘሺም እዴ አልተከፋሺም አሎት እሶም ረጋ ብላ እዲህ አለቻቸዊ። ለምን እከፋለሁ ለምንስ አዝናለሁ እኔኮ ያጣሁት በዚህ ምድር ላይ በጣም የሚጠላኝን ሠዉ ነዉ እኮ ያጣሁት እሡ ግን በምድር ላይ ከምንም በላይ የሚወደዉን ሰዉ ነዉ ያጣዉስ ለዚህ እኔ ሳልሆን ማዘንና መከፋት ያለብኝ እሡ ነዉ አለቻቸዉ ይሄ ታሪክ የሁላችንም ነዉ አንድ የምንወደዉ ሰዉ ጥላቻዉን ሲያሣየን ወይም ሲርቀን እንከፋለን እናዝናለን እንከፋለን ግን ይሔ መሆን የለበትም ይሄንን ማረግ ያለበት ያ ትቶን የሔደዉ ሠዉ ነዉ እንጂ እኛ አልነበርንም።።።።።።። @haykuhaykuti ✍✍✍✍✍ haykel🙏🙏✍✍✍✍✍❤️❤️❤️🙏🙏 መልካም ምሺት
Hammasini ko'rsatish...
የሆነ የሚያናድድህ ነገር ስትሰማ ወዲያው መልስ አትስጥ ቀጣዮ ቀን እስኪመጣ ጠብቅ ምላሽህንም አዘግየው ከቀናት በውሀላ ጥበባዊ ምላሽ መስጠት የምትችል ሆነህ ራስህን ታገኘዋለህ ወይም ጉዳዮ መልስ የማይገባው እንደሆነ ትረዳለህ መልካም ምሽት 🙏✨✨ @fegegta_bcha
Hammasini ko'rsatish...
አስተዋይ ሰው ሁሉ ያንብብ አንዱ ለጓደኛው ስልክ ይደውልና እባክህ እናቴ በጣም ታማ ሆስፒታል ገብታለች እናም 3000 ሺ ብር ስለተባልኩኝ አሁኑኑ በፍጥነት እዚህ ሆስፒታል ድረስ ይዘህልኝ ና ይለዋል ። ጓደኛውም እሺ ግን 30 ደቂቃ ያህል ታገሰኝ አለው ። እሺ ብሎ ሲጠብቅ 30 ደቂቃ ብሎም አንድ ሰአት አለፈው ። ከዚያም ምነው ቆየ ብሎ ስልክ ሲደውልለት ስልኩ ጥሪ አይቀበልም ይላል ። ደጋግሞ ቢሞክርም ስልኩ ዝግ ነው ። በዚህም በጣም ይናደድና እንደውም በቃ ተወው ያንተን ገንዘብ አልፈልግም ፣ ድሮም እኔ ጓደኛ አይወጣልኝም ብሎ ሚሴጅ ላከለት ። ከጥቂት ደቂቃ በኃላ ጓደኛው ሆስፒታል መጣ ፣ ገና እንዳየውም ስማ ባይኖርህ እንኳን በቃ የለኝም ወይ ደግሞ አላገኘሁም አትልም እንዴ ? ለምን ስልክህን ትዘጋለህ ? ብሎ ጮኸበት ጓደኛውም እንዲህ ሲል መለሰለት ። ጓደኛዬ ስልኬን ዘግቼው አይደለም አጋጣሚ እጄ ላይ ብር አልነበረም ፣ በቅርበት የማውቃቸውን ሰዎች ሁሉ ብድር ስጠይቃቸው የለንም አሉኝ። ከዚያ ምንም አማራጭ ሳጣ ስልኬን ሽጬ ይኸው ያልከኝን 3000 ብር ይዤልህ መጣሁ ብሎ ሰጠው ። ከዚያም ጓደኛ አቅፎ ይቅርታ ጠየቀው ። አንዳንዴ ሰዎች ለእኛ ብለው ደፋ ቀና እያሉ እና ዋጋ እየከፈሉ ነገር ግን ያሉበትን ሁኔታ ሳንረዳ እንዲሁ ነገሮች በምንፈልገው ፍጥነት ስላልሆኑ ብቻ ለንግግር አንቸኩል !!!!!!!! አላህ በችግር ቀን ደርሰው እንዲህ ከጎን የሚሆኑ ፣ ሲኖረን አብረውን በልተው ሳይኖረን የማይርቁን ፣ በመልካም ቀን ፊት ሰጥተው በክፉ ቀን ጀርባ የማይሰጡን ፣ ሲሞላልን ቀርበውን ሲጎድልብን የማይሸሹን ፣ ደስታችንን ብቻ ሳይሆን ችግራችንንም አብረው የሚካፈሉ ፣ ቅን ወዳጆችን ያድለን ። አሚን ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ። በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ። : ስለዚህ አንተም ወዳጄ ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፉ ከተመቸህ ወዳጅ ዘመድዎም እንዲማርባቸው #ሼር አድርጉላቸው ።
Hammasini ko'rsatish...
በአንድ ወቅት ሁሉም ከጎንክ ይሆናሉ ከዛ አንድ ቀን ደሞ በድንገት ሁሉም ከጎንክ ይጠፋሉ ተመካክረው ይመስል 😢
Hammasini ko'rsatish...
​​አንድ ድሀ ሰው ነበረ.. ሶስት🍊🍊🍊 ብርቱካኖችን ይገዛል.. ጨለማ ስለነበር ማብራቱን ይዞ እያበራ ሊበላ አንደኛውን ብርቱካን ሲቆርጠው የተበላሸ ነው... ሁለተኛውንም ሲቆርጠው የተበላሸ ነው... ሶስተኛውን ከመቁረጡ በፊት ግን መብራቱን አጠፋና ቆርጦ በላው።.... አንዳዴ ለመኖር ሲባል አይተን👀 እንዳላየን ሰምተን👂 እንዳልሰማን መሆን አለብን !
Hammasini ko'rsatish...
እውነት Vs ውሸት..! "አንድ ቀን እውነት እና ውሸት ይገናኛሉ። ውሸት ለእውነት “ዛሬ አስደናቂ ቀን ነው” ትላታለች። እውነት ወደ ሰማይ ቀና ብላ ትመለከትና እውነትም ቀኑ እጅግ ውብ መሆኑን ታስተውላለች። ከዚያም ቀኑን ሙሉ አብረው ያሳልፉና በመጨረሻ በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ይደርሳሉ ። ውሸት እውነትን በድጋሚ “ውሃው በጣም ጥሩ ነው፤ አብረን እንታጠብ!” ትላታለች። እውነትም የጉድጓዱን ውሃ ባየች ጊዜ ጥሩ መሆኑን ተገነዘበች፡፡ በዚህም፣ እውነት የአብረን እንታጠብ ግብዣውን ተቀብላ ልብሳቸውን ከጉድጓዱ ዳር አስቀምጠው መታጠብ ይጀምራሉ። መታጠቢያ ጉድጓዱ ውስጥ እያሉ ውሸት ከውሃው በድንገት ትወጣለች፤ የእውነትንም ልብስ ትለብስና ትሸሻለች። በሁኔታው በጣም የከፋት እውነት ከጉድጓዱ ትወጣና ውሸትን ለማግኘት እና ልብሷን ለመቀበል በየቦታው ትሯሯጣለች። በየመንገዱ የምታገኛቸው ሰዎች እውነትን እርቃኗን በማየታቸው በንቀት እና በንዴት ይመለከቷታል። ውሸትን ሮጣ መያዝ ያልቻለችው ምስኪኗ እውነት ወደ ጉድጓዱ ተመልሳ የውሃው ጉድጓድ ውስጥ በመደበቅ ለዓለም ስትል እርቃኗን ለዘላለም ትሸፍናለች። እነሆ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ውሸት እንደ እውነት ለብሶ በዓለም ዙሪያ በመዘዋወር የኅብረተሰቡን ፍላጎቶች በማርካት ላይ ይገኛል፡፡ ዓለምም እውነትን የመፈለግ በጭራሽ ፍላጎት የለውምና የእውነት ለዘለዓለም በጉድጓዱ ውስጥ መቅረት አያስጨንቀውም። ዓለም፣ እውነት እርቃኗን ስትሆን የሚሸከምበት ሞራልም ስለሌለው በመደበቋ ደስተኛ ነው። ከውሸት የፀዳ፣ በእውኘት ያሸበረቀ ቀን ተመኘሁ! መልካም ውሎ ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ╔═══◈•🌺🌸•◈═══╗ @tibebislam_nw @tibebislam_nw ╚═══◈•🌺🌸•◈═══╝
Hammasini ko'rsatish...
ግርምም የሚለኝ እንደሚገባው
Hammasini ko'rsatish...
"ተሰጥኦ ስኬታማ አያደርግም! ይቺ ምድር በተሰጥኦ በታደሉ ግን ስኬታማ ባልሆኑ ሰዎች ተሞልታለች፤ ጂኒየስነትም አሸናፊ አያደርግም! ውጤት የሌለው ጉብዝና ስም ብቻ ነው፤ አሪፍ የትምህርት ደረጃም ስኬታማ አያደርግም! አለማችን ብዙ በተማሩና ዕውቀት ባላቸው ሰዎች ተጨናንቃለች፤ በዚህ ምድር የፅናትና የትዕግስትን ያህል አሸናፊ ሚያደርግ ነገር የለም!" ይለናል ካልቪን ኩሊጅ የተባለው የአሜሪካ ፕሬዘደንት። የምትረግጠውን መሬት ያህል ፈጣሪህን ካመንከው በከባዱ ጊዜም ትፀናለህ፤ ፈተናዎች የሚመጡት ሊያበረቱን እንጂ ሊሰብሩን አይደለም! ወዳጄ ፅናት ወሳኝ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
#የመፀፀት ህይወት መፀፀት ምንድነው ብለን ካየን ማድረግ ወይም አለማድረግ ብለን ልንፈታው እንችላለን ያ ማለት በተገቢው ቦታና ጊዜ የሆነ ነገርን አለማድረግ ወይም ደግሞ የማንፈልገውን ነገር ወይም ነገሮችንን ያለ ሰዓቱ ማድረግ እነዚህ ሁለት ነገሮች በአይምሯችን ወይም በትክክለኛው የህሊና ሸንጎ ላይ ወቀሳን ሲያስነሳ እኛም ክሱን ስንቀበል ፀፀት ተፈጠረ ማለት እንችላለን ታዲያ ፀፀት ወዴት ይመራናል የፀፀት መንገድ ሁለት ነው አንዱ ሞት ሌላኛው ህይወት አንዱ መታመም ሌላኛው መዳን ሁለት ተቃራኒ ሀይልና መንገዶች አሉት አንዱ ብርሀን ሌላው ጨለማ ታዲያ የጨለማውን መንገድ ስንይዝ ከተፈጠረብን በላይ ራስን መቅጣት ያንኑ የስህተት መንገድ ማጠናከር ይበልጡን ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይከተናል ሌላኛው መንገድ ብርሀን ነው ይህ ደሞ ለመመለስ ለእንደገና ከተጓዝንቀት የስህተት መንገድ በቆራጥነትና በእልህ በትግል እንድንወጣ ይረዳናል:: ለማነኘኛው እሄ የኔም እይታ ነው። መልካም ቀን🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.