uz
Feedback
Academic Education

Academic Education

Kanalga Telegram’da o‘tish

ለተማሪዎች ➤በተለያቱ ትምህርት ቤቶች የተዘጋጁ መልመጃዎችን ➤ በየ ጊዜው የሚወጡ ትኩስ መረጃዎች ➤ የአጠናን ስልትና የፈተና ጊዜ ሲቃረብ በአላህ እገዛ ጭንቀትን ለማስወገድ የሚረዱ ጥቆማዎችን ➤የ MSW-LOGO Programming Commands እንለቃለን

Ko'proq ko'rsatish
365
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-57 kun
-1530 kun
Postlar arxiv
📚 ቻናሉን ልሰርዘው ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የነበረው ግሩፕም አሁን የኔ አይደለም። ✅ በግሩፑም የሚለቀቁት ነገሮች እኔን አይወክሉኝም! ✅ ከይቅርታ ጋር

በዚህ ጊዜ ሰውን በነፃ የሚያግዝ ሰው አለ!? ካለም አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው። በነፃ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን የሚለቅ ቻናል። 📚 Halal Jobs 📚 ✅ ቻናሉን Join በማድረግ ለመልካም ስራቸው እናበረታታቸው። https://t.me/HalalJobsEth ════════════════ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎን በነፃ እንድንለቅልዎ በ @HalalJobsEthbot በኩል ይላኩልን ሐላል የሆኑ የስራ ማስታወቂያዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይወዳጁን! ይከታተሉን! ወዳጅዎንም ይጋብዙ! ያተርፉበታል!

በዚህ ጊዜ ሰውን በነፃ የሚያግዝ ሰው አለ!? ካለም አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው። በነፃ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን የሚለቅ ቻናል። 📚 Halal Jobs 📚 ✅ ቻናሉን Join በማድረግ ለመልካም ስራቸው እናበረታታቸው። ════════════════ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎን በነፃ እንድንለቅልዎ በ @HalalJobsEthbot በኩል ይላኩልን ሐላል የሆኑ የስራ ማስታወቂያዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይወዳጁን! ይከታተሉን! ወዳጅዎንም ይጋብዙ! ያተርፉበታል!

photo content

Grade 10 Info and Materials ምርጥ የቴሌግራም ቻናል Logo ስጠኝ። በቻናሉ ለተማሪዎች የምለቃቸው ነገሮች ➊ Worksheets ❷ Mid Exams ➌ Final Exams ❹ Videos
Grade 10 Info and Materials ምርጥ የቴሌግራም ቻናል Logo ስጠኝ። በቻናሉ ለተማሪዎች የምለቃቸው ነገሮች ➊ Worksheets ❷ Mid Exams ➌ Final Exams ❹ Videos ❺ Short notes ❻ Study Time Table ❼ Motivational texts for study ❽ Study Tips and Tricks .......✅ 💫 Hopes are the Wings of Dreams. Never stop hoping, never stop dreaming. ════════════════ 📚 ጠንካራ ተስፋዎች የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! 📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን ደግሞ የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ════════════════ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 https://t.me/Grade10Info

📚 ጠንካራ ተስፋዎች የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! ✅ ተስፋ የሰው ልብ ውስጥ ሲበቅል እንደ ትንንሽ ዘር ይጀምራል። ነገር ግን ይህ ትንንሽ ዘር እንዲበቅል በግንባር ጠንካራ እና በትክክል እንክብካቤ ያስፈልገዋል። ተስፋ ያለው ሰው ምን ያህል ችግር ቢያጋጥመው እንኳን በህልም መንገዱ አይቆምም። ✅ ተስፋ ህልምን ለማሳካት የሚረዳን ኃይል ነው፣ እና ያለ ተስፋ ህልም እንደ ቀላል ብናኝ በግድግዳ ላይ የተቀረ ነው፤ ያለ እንቅስቃሴ እና እድገት ደግሞ ዝም ብሎ በባድ መኖር በቁም መሞት ነው። ✅ ውድ ተማሪዎች ሆይ፣ ዛሬ ያላችሁን ትንሽ ህልም አትናቁት። ትንሹ ህልማችሁ በሰው ልብ ውስጥ ከተሰወረ፤ ትክክለኛ አቅጣጫ እምነት እና ትጋት በተሞላበት ሙከራ በጊዜ የማይታመን አስደናቂ ውጤት ያመጣል። 📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! እኛ በዛሬ የምናደርገው ነገር እንደ መጀመሪያ ዘር ነው። በሙሉ ልብ የምንተክለው "ዛሬ" ነገ ደግሞ ታላቅ ዛፍ ይሆናል። በዛሬ ላይ ያለን ጥረት (የምናደርገው ሙከራ) ለኛም ሆነ ለሌሎች ላይታይ ይችላል፣ ግን ጊዜው እየነጎደ ጥረታችንም እየፏፏ ይመጣና በቅፅበት የስኬታችን እርሻ ፍሬ ያፈራል፣ ያብባል። ✅ እናንተ ተማሪዎች፣ ዛሬ በትምህርታችሁ ላይ በምታደርጉት ጥረት በቀጣዩ ዓመት ከአምላካችሁ እርዳታ ጋር ምን ያህል ለውጥና ስኬት ሊያመጣ እንደሚችል አስቡ። የአሁኑን ጥረታችሁን አሁኑኑ አይታይም፣ እናንተም ጥረታችሁን አጧጡፉ እንጂ አትቸኩሉ። ነነገ የምታዩት ስኬት "ዛሬ" በትክክል የተወሰደ እርምጃ ነው (በአላህ እርዳታ ተስፋ-አለመቁረጥ የታከለበት የልፋታችሁ ውጤት ነው። ✨ እናም ውድ ወንድምና እህቶቼ (ተማሪዎቼ) ➊ ትኩረት አድርጉ:– በምትማሩት ትምህርት ላይ ትኩረታችሁ እየጨመረ ሲሄድ ወደ ስኬት ጉዞአችሁ መራመድ ትጀምራላችሁ። በዚህ ስኬት ጉዞ ሌሎችንም አብሯችሁ እንዲራመዱ እድሉን ታመቻቻላችሁ። ❷ ጊዜን በአግባቡ ተጠቀሙ – የዛሬውን ጊዜናችሁን ለነገ ስኬታችሁ ምክንያት እንዲሆን አድርጋችሁ ተጠቀሙበት። ➌ በትዕግሥት ጠብቁ:– ሁሉም ነገር በአላህ እርዳታ በጊዜው ይሆናል! የሆነ ዘርን ዘርተን እስከሚያፈራ ድረስ በትዕግስት እንደምንጠብቀው ሁሉ ዛሬ የምታደርጉት ጥረት ውጤቱ ለምን በቅፅበት አልታየንም አትበሉ። ❹ ተስፋን አትቁረጡ:– የምትችሉትን ከጣራችሁ በኋላም፣ ደጋግማችሁ ከሞከራችሁም በኋላ የሆነ ነገር ላይሳካ ይችላል ነገር ግን ተስፋ ፈፅሞ አትቁረጡ፤ ተስፋ ያለው ሰው መንገድ ያገኛል። "ህይወትህን እጣ እንጂ ተስፋ እንዳታጣ" ይላሉ ቱርኮች!! 📚 ደጋግሞ ወድቆ ደጋግሞ ሳይነሳ ከፍ ብሎ የሚበር የለም! 🌱 በመጨረሻም: በህይወት መንገድ ላይ የምንወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ለወደፊታችን መሠረት ናቸው። ዛሬ የምንተክለው ትንንሽ ዘሮች ትክክለኛውን እንክብካቤ ካገኙ በአላህ እርዳታ ነገ ብዙ ጣፋጭ ፍሬዎችን የያዘ ትልቅ የፍራፍሬ ዛፍ መሆናቸው አይቀሬ ነው። ህልምና ተስፋ እንዲሁም "በዛሬ" ላይ በምናደርገው ጥረት ነገ የምንፈልገውን ህልም ሁሉ ማሳካት እንችላለን። ⭕️ አዎ! ጠንካራ ተስፋዎች የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! የዛሬ እርምጃዎቻችን ደግሞ የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

photo content
+1

🎓 A Fearless Mind and Heart can Communicate Fearlessly! ════════════════ 🎓 ፍርሃት የሌለበት አዕምሮ እና ልብ ያለ ፍርሃት ይግባባሉ!! ══════════
+4
🎓 A Fearless Mind and Heart can Communicate Fearlessly! ════════════════ 🎓 ፍርሃት የሌለበት አዕምሮ እና ልብ ያለ ፍርሃት ይግባባሉ!! ════════════════ ⭕️ ለዚህ ደግሞ:- ሁሌም አዲስ ነገር መማር፣ ተስፋ አለመቁረጥ፤ ሁሌም መሞከር... በጣም አስፈላጊ ነው። ✍️ Reshad Ibnu Muzemil

📩 የጀግንነት ጉዟችሁ 📩 ✅ የእውቀት መንገድ፡ የዛሬው ጥረት የነገው ህይወት! 📚 ውድ ተማሪዎች፣ የትምህርት ጉዟችሁ በራሱ ትልቅ የጀግንነት ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ የእያንዳንዳችሁ ልዩ ልምድ፣ የእድገት እና የለውጥ ውብ ሂደት ነው። በእያንዳንዱ ምዕራፍ የምታገኙት እውቀት፣ የምትሰሩት ልምምድ እና የምትደርሱበት ደረጃ የወደፊት ህይወታችሁን የሚቀርጽ የጥንካሬ መሰረት ይጥላል። 📚 ይህ ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል፤ ፈተናዎች እና እንቅፋቶች ሊያጋጥሟችሁ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ከባድ መስለው ይታዩ ይሆናል፣ እናም ድካም ወይም ተስፋ መቁረጥ ሊሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን፣ አስታውሱ፣ እነዚህ ሁሉ የሂደቱ አካል ናቸው። እነዚህ መሰናክሎች እንድትጠነክሩ፣ እንድትማሩ እና ይበልጥ እንድታድጉ የሚረዷችሁ ናቸው። "ውድቀት" የስኬት አንዱ አካል ነው። 📚 በእያንዳንዱ ችግር ውስጥ የተደበቀ ትምህርት እንዳለ እወቁ። ዛሬ የምትዘሩት የትጋት ዘር ሁሉ ለነገው ስኬታችሁ ወሳኝ መሠረት ነውና! የትምህርት አጋጣሚያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ የትምህርት ቀን አዲስ ዕድል፣ አዲስ የመማሪያ እና የማደግ አጋጣሚ ነው። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የምትሄዱበት ቀን ለራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ እና ለአገራችሁ የምታደርጉት ኢንቨስትመንት ነው። ✅ ጥንካሬያችሁ፡ ተስፋን መቼም አለመቁረጥና መሰናክሎችን መግፋት! 📚 በውስጣችሁ ያለውን ታላቅ ጥንካሬ አውጡ! እያንዳንዱ ውድቀት የመማሪያ ትምህርት እንደሆነ አስቡት፣ እናም ወደፊት ለመራመድ የሚያስችል አዲስ መንገድ እንደሚያሳያችሁ እመኑ። ስህተት መስራት የሰውነት ባህሪ ቢሆንም ከስህተት መማር ግን ብልህነት ነው። ሁሌም ሞክሩ! ደጋግሞ መሞከር ለስኬት ወሳኝ ነው። ብዙ ታላላቅ ፈጠራዎች እና ግኝቶች የተገኙት ከተደጋጋሚ ሙከራዎች እና ውድቀቶች በኋላ ነው። ➡ አዎ! ደጋግሞ ወድቆ ደጋግሞ ሳይነሳ፤ ከፍ ብሎ የሚበር የለም!! 📚 ታዋቂው ሳይንቲስት ቶማስ ኤዲሰን የኤሌክትሪክ አምፖልን ከመፍጠሩ በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ጊዜያት ሳይሳካለት ቀርቷል፤ ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጡ፣ ዓለም የምታበራውን መብራት አበረከተላት። እናንተም እንደዛው ተስፋ የማትቆርጡ ከሆነ የሆነ ሙከራችሁ መሳካቱ አይቀሬ ነው!! ⭕️ አዎ! ተስፋ አትቁረጡ! በጽናት ከቀጠላችሁ፣ ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም የምትፈልጉትን ግብ ማሳካት እንደምትችሉ እወቁ። አስታውሱ፡ "ወንዝ የሚሻገረው በድፍረት እንጂ በመቆም አይሆንም!" ድፍረት ይኑራችሁ፣ ወደፊት ሂዱ! መሰናክሎች ሲያጋጥሟችሁ እንደ መጨረሻ አትዩዋቸው፤ ይልቁንም እንደ ፈተና እና ጥንካሬያችሁን የምታሳዩበት አጋጣሚ ተመልከቷቸው። ➡ ብሩህ ተስፋ፡ 📚 የእውቀት ኃይል ተጠቀሙበት እና የወደፊት ብሩህ ተስፋ ይኑራችሁ! በጥረታችሁ እና በትጋታችሁ ታላቅ ነገር መፍጠር እንደምትችሉ እመኑ። ✅ የዛሬው ጥረታችሁ የነገ ህይወታችሁን ይመሰርታል። ስለዚህ፣ በትጋት አጥኑ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ጓጉ፣ እና እርስ በርስ ተጋገዙ። የቡድን ስራ እና መረዳዳት የትምህርት ጉዞአችሁን የበለጠ ፍሬያማ ያደርገዋል። እርስ በርሳችሁ ተደጋገፉ፣ እውቀትን ተለዋወጡ፣ እና አብራችሁ ማደግን ተማሩ። እውቀት ሃይል ብቻ ሳይሆን መጨለማ ጉዞ መንገድን የሚያቅጣጭ ብርሃን ነውም ጭምር!፣ እናም በአላህ እርዳታ እናንተ የዚህ ሃይልና ብርሃን ባለቤቶች ናችሁ። ይህ ኃይልና ብርኃን የወደፊት ህይወታችሁን ብቻ ሳይሆን፣ ቤተሰባችሁን፣ ማኅበረሰባችሁን እና አገራችሁን የመለወጥ አቅም አለው። ✅ እውቀታችሁን ለበጎ ነገር ተጠቀሙበት። ዓለም የእናንተን አስተዋጽኦ ትፈልጋለች። እያንዳንዱ ያገኛችሁት ዕውቀት ለእናንተም ሆነ ለሌሎች በጎ ነገሮችን ለመፍጠር የሚያስችል ብርሃን ይሁን። በዓለም ላይ መልካም ለውጥ ለማምጣት የእናንተ ብቃት እና ትጋት ወሳኝ ነው። ✅ መትጋትና በራስ መተማመን፡ ገደብ የለሽ አቅም እና ታላቅነት 📚 ያለማቋረጥ በመትጋትና በራስ በመተማመን፣ ህልሞቻችሁን እውን ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ለአገራችሁ እና ለዓለም ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ትችላላችሁ። ስኬት የፅናት ውጤት ነው፤ ተስፋ እስካልቆረጣችሁ ድረስ መማር፣ ማደግ እና ማሸነፍ ትችላላችሁ። 📚 በራሳችሁ ተማመኑ፣ አቅማችሁን እወቁ። ወሰኖችን የሚያስቀምጠው የራሳችሁ አስተሳሰብ እንጂ ውጫዊ ሁኔታ አይደለም። ውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት። እያንዳንዳችሁ ልዩ የሆነ ተሰጥኦ እና አቅም አላችሁ። ያንን አቅም ለማውጣት አትፍሩ። 📚 ከዚህ በፊት ማንም ያላሰበውን ነገር ለማሰብ፣ ማንም ያልሰራውን ለመስራት ድፈሩ። የዓለምን ታሪክ የቀየሩ ታላላቅ ሰዎች የተለዩ ስላልሆኑ ሳይሆን፣ በራሳቸው ስላመኑ እና ተስፋ ስላልቆረጡ ነው። እናንተም ያን ማድረግ ትችላላችሁ። የዛሬው ጥረታችሁ፣ ትጋታችሁ እና ጽናታችሁ ለታላቅ የወደፊት ሕይወት መሠረት ይሆናል። ህልሞቻችሁን እውን ለማድረግ የማትታክቱ ከሆነ፣ ዓለም በእርምጃችሁ ወደ መልካም ትሸጋገራለች። ⭕️ አስታውሱ፣ የትምህርት ጉዞአችሁ የእድሜ ልክ የመማር ሂደት መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም። ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ዝግጁ ሁኑ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አትግደሉ። ራሳችሁን አዳዲስ ፈተናዎች ላይ ጣሉ፣ እና ከመጽናናት ፈጥናችሁ ለመውጣት አትፍሩ። ይህን ስታደርጉ፣ የምትችሉት ነገር ወሰን እንደሌለው ትገነዘባላችሁ። መልካም የትምህርት ጊዜ! በጉዟችሁ ሁሉ መልካም ዕድል እመኛለሁ። ════════════════ 📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! 📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! ════════════════ ቀን:- ሐምሌ 23/2017 ዓ.ል [ሰፈር 05/1447 አ.ሒ] ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

photo content

+1
Artificial Intelligence Fundamentals Video: Part 1 #Source: Udacity (Ethiocoders)

💬 Alhamdulillah 💫 Hopes are the Wings of Dreams. Never stop hoping, never stop dreaming. ════════════════ ✅ ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት። ✅ የላቀ የወደፊት ዕድል ለመፍጠር! እያንዳንዱ ጉዞ የሚጀምረው በአንድ እርምጃ ነው። በጋለ ስሜትና በትጋት ደግሞ ያ እርምጃ ታሪክ የሚሰራ ቅርስ ይሆናል። ይህ ሰርተፍኬት እናንተም ታላቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ማስታወሻ ይሁንልኝ! 📚 ስኬት የዕድል ጉዳይ አይደለም፤ የጥረትን፣ የመማርን እና በየቀኑ ጥረት የማድረግ ውጤት ነው። በጽናት ከሰሩ፣ የማይቻል ነገር የለም! 📚 Artificial Intelligence (AI) / (ሰው ሰራሽ አስተውሎት):  የወደፊት ብቻ አይደለም፤ የእናንተ የዛሬው ዕድል ነው። መማር ጀምሩ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አጧጥፉት፣ እና ለነገ ስኬትን የሙከራ እርምጃ ጀምሩ። ይህ ዘርፍ ገደብ የለሽ ዕድሎችን ይዟል፤ እናንተም የዚህ አካል መሆን ትችላላችሁ። ⭕️ ምናልባት አሁን በጥያቄዎችና በጥርጣሬዎች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በትኩረትና በእምነት እነዚያን ጥያቄዎች ወደ ብቃት መቀየር ይቻላል። አሁን የእናንተ ተራ ነው! እያንዳንዱ ጥረታችሁ ፍሬ ያፈራል። ኢንሻአላህ! ያለፈው ሁኔታችሁ ገደባችሁን አይወስንም፤ የአዕምሮአችሁ ሁኔታ ነው የሚወስነው። ወሰኖችን አፍርሷቸው፣ መሰናክሎችን ጣሷቸው (ሰባብሯቸው)፣ እና ብቃታችሁን ተጠቀሙበት! በውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት። 📚 እያንዳንዱን ትንሽ ድል አክብሩ። ይህ ሰርተፍኬት መጨረሻው አይደለም። በአላህ ፍቃድ ከእናንተ ጋር በፈጠራ እና በለውጥ ወደተሞላ የወደፊት ጊዜ የሚወስድ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ለበለጠ ስኬት መነሻ ይሁን። 📚 ዕድልን አትጠብቁ። ለዕድል ተዘጋጁ ። ተማሩ፣ እደጉ፣ አሁንም አድጉ! እናም በሩ ሲከፈት፣ በልበ-ሙሉነት ለመግባት ዝግጁ ትሆናላችሁ። የእውቀት ፍለጋችሁ መቼም አታቁሙ። ይህን አስደናቂ ትምህርት ለመማር እና ህይወታችሁን ለመለወጥ ይህ ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ምን ትጠብቃላችሁ ታዲያ⁉️ ════════════════ 📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! 📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! ቀን:- ሐምሌ 14/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 27/1447 አ.ሒ] ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

photo content
+2

💬 Alhamdulillah 💫 Hopes are the Wings of Dreams. Never stop hoping, never stop dreaming. ════════════════ ✅ ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት። ✅ የላቀ የወደፊት ዕድል ለመፍጠር! እያንዳንዱ ጉዞ የሚጀምረው በአንድ እርምጃ ነው። በጋለ ስሜትና በትጋት ደግሞ ያ እርምጃ ታሪክ የሚሰራ ቅርስ ይሆናል። ይህ ሰርተፍኬት እናንተም ታላቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ማስታወሻ ይሁንልኝ! 📚 ስኬት የዕድል ጉዳይ አይደለም፤ የጥረትን፣ የመማርን እና በየቀኑ ጥረት የማድረግ ውጤት ነው። በጽናት ከሰሩ፣ የማይቻል ነገር የለም! 📚 Artificial Intelligence (AI) / (ሰው ሰራሽ አስተውሎት):  የወደፊት ብቻ አይደለም፤ የእናንተ የዛሬው ዕድል ነው። መማር ጀምሩ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አጧጥፉት፣ እና ለነገ ስኬትን የሙከራ እርምጃ ጀምሩ። ይህ ዘርፍ ገደብ የለሽ ዕድሎችን ይዟል፤ እናንተም የዚህ አካል መሆን ትችላላችሁ። ⭕️ ምናልባት አሁን በጥያቄዎችና በጥርጣሬዎች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በትኩረትና በእምነት እነዚያን ጥያቄዎች ወደ ብቃት መቀየር ይቻላል። አሁን የእናንተ ተራ ነው! እያንዳንዱ ጥረታችሁ ፍሬ ያፈራል። ኢንሻአላህ! ያለፈው ሁኔታችሁ ገደባችሁን አይወስንም፤ የአዕምሮአችሁ ሁኔታ ነው የሚወስነው። ወሰኖችን አፍርሷቸው፣ መሰናክሎችን ጣሷቸው (ሰባብሯቸው)፣ እና ብቃታችሁን ተጠቀሙበት! በውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት። 📚 እያንዳንዱን ትንሽ ድል አክብሩ። ይህ ሰርተፍኬት መጨረሻው አይደለም። በአላህ ፍቃድ ከእናንተ ጋር በፈጠራ እና በለውጥ ወደተሞላ የወደፊት ጊዜ የሚወስድ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ለበለጠ ስኬት መነሻ ይሁን። 📚 ዕድልን አትጠብቁ። ለዕድል ተዘጋጁ ። ተማሩ፣ እደጉ፣ አሁንም አድጉ! እናም በሩ ሲከፈት፣ በልበ-ሙሉነት ለመግባት ዝግጁ ትሆናላችሁ። የእውቀት ፍለጋችሁ መቼም አታቁሙ። ይህን አስደናቂ ትምህርት ለመማር እና ህይወታችሁን ለመለወጥ ይህ ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ምን ትጠብቃላችሁ ታዲያ⁉️ ════════════════ 📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! 📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! ቀን:- ሐምሌ 14/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 27/1447 አ.ሒ] ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

photo content
+1

የላቀ የወደፊት ዕድል ለመፍጠር! እያንዳንዱ ጉዞ የሚጀምረው በአንድ እርምጃ ነው። በጋለ ስሜትና በትጋት ደግሞ ያ እርምጃ ታሪክ የሚሰራ ቅርስ ይሆናል። ይህ ሰርተፍኬት እናንተም ታላቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ማስታወሻ ይሁንልኝ! 📚 ስኬት የዕድል ጉዳይ አይደለም፤ የጥረትን፣ የመማርን እና በየቀኑ ጥረት የማድረግ ውጤት ነው። በጽናት ከሰሩ፣ የማይቻል ነገር የለም! 📚 Artificial Intelligence (AI) / (ሰው ሰራሽ አስተውሎት):  የወደፊት ብቻ አይደለም፤ የእናንተ የዛሬው ዕድል ነው። መማር ጀምሩ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አጧጥፉት፣ እና ለነገ ስኬትን የሙከራ እርምጃ ጀምሩ። ይህ ዘርፍ ገደብ የለሽ ዕድሎችን ይዟል፤ እናንተም የዚህ አካል መሆን ትችላላችሁ። ⭕️ ምናልባት አሁን በጥያቄዎችና በጥርጣሬዎች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በትኩረትና በእምነት እነዚያን ጥያቄዎች ወደ ብቃት መቀየር ይቻላል። አሁን የእናንተ ተራ ነው! እያንዳንዱ ጥረታችሁ ፍሬ ያፈራል። ኢንሻአላህ! ያለፈው ሁኔታችሁ ገደባችሁን አይወስንም፤ የአዕምሮአችሁ ሁኔታ ነው የሚወስነው። ወሰኖችን አፍርሷቸው፣ መሰናክሎችን ጣሷቸው (ሰባብሯቸው)፣ እና ብቃታችሁን ተጠቀሙበት! በውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት። 📚 እያንዳንዱን ትንሽ ድል አክብሩ። ይህ ሰርተፍኬት መጨረሻው አይደለም። በአላህ ፍቃድ ከእናንተ ጋር በፈጠራ እና በለውጥ ወደተሞላ የወደፊት ጊዜ የሚወስድ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ለበለጠ ስኬት መነሻ ይሁን። 📚 ዕድልን አትጠብቁ። ለዕድል ተዘጋጁ ። ተማሩ፣ እደጉ፣ አሁንም አድጉ! እናም በሩ ሲከፈት፣ በልበ-ሙሉነት ለመግባት ዝግጁ ትሆናላችሁ። የእውቀት ፍለጋችሁ መቼም አታቁሙ። ይህን አስደናቂ ትምህርት ለመማር እና ህይወታችሁን ለመለወጥ ይህ ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ምን ትጠብቃላችሁ ታዲያ⁉️ ════════════════ 📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! 📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! ቀን:- ሐምሌ 6/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 18/1447 አ.ሒ] ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

photo content

ነፃ የትምህርት እድል ውድድር ✅ ኮተቤ ሳይንስ ሸርድ
ነፃ የትምህርት እድል ውድድር ✅ ኮተቤ ሳይንስ ሸርድ

📚 የህልማችሁ ቁልፍ በእጃችሁ ነው! 📚 ውድ ተማሪዎች! በምስሉ ላይ የምታዩትን ልጅ ተመልከቱት እስኪ። ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብሎ በፈገግታ እየጻፈ ነው፤ በአዕምሮው ግን ወደፊት ምን መሆን እንደሚፈልግ እያሰበ ነው። ዶክተር ሆኖ ሰዎችን ሲያድን፣ ፓይለት ሆኖ አውሮፕላን ሲያበር፣ ወይም መሀንዲስ ሆኖ ትልልቅ ህንጻዎችን ሲገነባ ይታየዋል። እንዴት የሚያስደስት ህልም ነው! እናንተስ? ወደፊት ምን መሆን ትመኛላችሁ? ምናልባት ዶክተር፣ ፓይለት፣ መሀንዲስ፣ መምህር፣ ፕሮግራመር ወይም ዲዛይነር መሆን ትፈልጉ ይሆናል። እነዚህ ሁሉ በጣም ግሩም ህልሞች ናቸው። ✅ መልካም ነገር ማለም መልካም ነው፤ ነገር ግን የምናልመውን ህልም እውን ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብን። ታዲያ ይህንን ጣፋጭ ህልም እውን የምናደርገው እንዴት ነው? መልሱ በጣም ቀላል እና አሁን ባላችሁበት ቦታ ላይ የሚገኝ ነው፤ እርሱም ጠንክሮ መማርና ማንበብ ነው! ህልማችሁን የምትገነቡበት እውን የምታደርጉት በትምህርታችሁ ነው! ✅ ዶክተር መሆን ከፈለጋችሁ፣ ዛሬ በክፍል የምትማሩት የሳይንስ ትምህርት የሰውነትን አሰራር ለመረዳት የመጀመሪያው እርምጃችሁ ነው። ✅ ፓይለት የመሆን ህልም ካላችሁ፣ የሂሳብ ትምህርት አውሮፕላኑን ለማብረር እና አቅጣጫዎችን ለማወቅ ወሳኝ ነው። ✅ መሀንዲስ ሆናችሁ ድልድይና ህንጻ ለመስራት ስታስቡ፣ ዛሬ የምትሰሯቸው የስዕል እና የሂሳብ መልመጃዎች መሰረታችሁ ናቸው። 📚 ስለዚህ ዛሬ በክፍል ውስጥ የምትማሩት እያንዳንዱ ትምህርት፣ የምትጽፉት እያንዳንዱ አረፍተ ነገር እና የምትፈቱት እያንዳንዱ የቤት ስራ ወደ ህልማችሁ የሚወስዳችሁ አንድ መንገድ መሆኑን አስታውሱ። ⭕️ ተስፋ አትቁረጡ፣ ሁሌም ሞክሩ! አንዳንድ ጊዜ ትምህርት ከባድ ሊሆን ይችላል። አንድ የሂሳብ ቀመር ሊከብዳችሁ ወይም አንድ የእንግሊዝኛ ቃል ሊጠፋባችሁ ይችላል። ይህ ማለት ግን አትችሉም ማለት አይደለም። ተስፋ በፍጹም አትቁረጡ! ➊ ስትሳሳቱ አትፍሩ፦ ስህተት የትምህርት አንዱ አካል ነው። ከስህተታችሁ ትማራላችሁ። ❷ ጥያቄ ጠይቁ፦ ያልገባችሁ ነገር ሲኖር መምህራኖቻችሁን በድፍረት ጠይቁ። ➌ ደጋግማችሁ ሞክሩ፦ አንዴ ካልተሳካላችሁ፣ ደግማችሁ ሞክሩ። ጥረት ማድረግ ውጤት አለው! 📚 መጽሐፍትን ጓደኛችሁ አድርጉ! ከክፍል ትምህርታችሁ በተጨማሪ መጽሐፍትን ማንበብ አዲስ አለምን ያሳያችኋል። ታሪኮችን፣ ግጥሞችን እና የተለያዩ መረጃዎችን ስታነቡ አዕምሯችሁ ይዳብራል፣ የቃላት እውቀታችሁ ይጨምራል፣ ከሁሉም በላይ ለምህርታችሁ ቅርብ ትሆናላችሁ። ➡ አስታውሱ፣ የወደፊት ህይወታችሁ የሚቀረፀው በዛሬው ጥረታችሁ ነው። ስለዚህ በየቀኑ በደስታና በተነሳሽነት ተማሩ፣ አንብቡ፣ ጥረት አድርጉ። የዛሬው ትንሽ ጥረት የነገውን ትልቅ ህልም እውን ያደርጋል! በርቱ፣ ጎብዙ! ለሁላችሁም መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ! ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ════════════════ 📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! 📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው! ቀን:- ሐምሌ 6/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 18/1447 አ.ሒ]

photo content