cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethiopia Meteorology Institute

World-class meteorological services in Ethiopia.

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
444
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+277 kunlar
+6530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ 4ኛው የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ //////////////////////// 4ኛው በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ተካሄደ፡፡ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጀት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ ኢትዮጵያን ለስብሰባቸው በመምረጣቸው በማመስገን አዲስ አበባ ሁለተኛ ቤታቸው እንደሆነና የሚያደርጉት ቆይታም የተሳካ እንዲሆን በመመኘት የአየር ንብረትና ጠባይ ድንበር የማይገድበው መሆኑን በመግለፅ ሁሉም በሳይንሱ ዙሪያ ያሉ ተመራማሪዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር አንድሬ ካምጋ የአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልእክት የአየር ንብረት ለውጥን መዋጋት በአለም አቀፍ፣ በአህጉር፣ በብሔራዊ እና በአካባቢያዊ ደረጃ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የገለፁ ሲሆን አያይዘውም ተቋማቸው የአየር ንብረት መረጃን ለግብርና፣ ለውሃ፣ ለጤና እንዲሁም ለአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፅ/ቤት የዳይሬክተሯ ተወካይ ዶ/ር ማሪያ የአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ከአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ ጋር በመሆን የማህበረሰቡን ህይወትና ንብረትን ከአደጋ ለመታደግ በጋራ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል፡፡ የእለቱም ስብሰባ በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ/ACMAD/ እና በአጋር ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ ያለውን ሂደት እና ስኬቶችን በመገምገም፣ የማእከሉን የሚቀጥለውን ዓመት የሥራ ዕቅድ እና በጀት ገምግሞ በማጽደቅ እንዲሁም ከሌሎች ፕሮጀክቶች እና አጋሮች ጋር በሚኖረው ትብብር ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጀንዳዎቹንም በጋራ በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በአፍሪካ ሚቲዎሮሎጂ ልማትና ትግበራ /ACMAD/ 4ኛው የአየር ንብረት አገልግሎቶችና ተዛማጅ መተግበሪያዎች ፕሮግራም /ClimSA/ አህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል-አሶሳ ያስገነባው የG+2 ህንፃ አስመረቀ። ////////////////////////////////////// ኢንስቲትዩቱ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል-አሶሳ ከተማ ላይ ያስገነባውን የG+2 ህንፃ የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር የሚንስትሩ አማካሪ፣ የክልሉ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም አስመረቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኢንስቲትዩቱ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በሰፊው እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የእለቱ የክብር እንግዳ በውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር በሚንስትር ድኤታ ማእረግ የሚንስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኢንስቲትዩቱ በአሶሳ ከተማ ላይ ካስገነባው ህንፃ በተጨማሪ የሚሰጠው መረጃ ከእውነታው ጋር የተቀራረበ እንዲሆን በሰራተኛ አቅም ግንባታ ላይ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀዋል። በኢንስቲትዩቱ የመሰረታዊ የሚቲዎሮሎጂ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም ስለ ህንፃው አጠቃላይ ማብራሪያ በመስጠት የምረቃ ፕሮግራሙ ተካሂዷል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
ኢንስቲትዩቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ክረምት 2016/7 ዓ.ም ወቅት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ትንበያ ሰጠ /////////////////////////////// የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በቀጣዩ የክረምት ወቅት ክልሉን ጨምሮ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖራቸው ክልላዊ የበልግ 2016 አመት የአየር ሁኔታ ግምገማና የቀጣይ የክረምት 2016/17 ወቅት የአየር ሁኔታ ትንበያ ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ አስታውቋል። በመድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ ኢንስቲትዩቱ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አስራ አንድ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስጫ ማእከሎች በማደራጀት በእነርሱ አማካኝነት የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን በመስጠት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃ በድንበር እንደማይሰወሰንና ተቋሙ ለትንበያው ዓለም አቀፍ መረጃዎችንም ጭምር እንደሚጠቀም በመግለፅ የኢንስቲትዩቱን መረጃዎች በአግባቡ በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር በህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ እንደሚያስችልም አብራርተዋል። በመድረኩ አጠቃላይ አገራዊ ትንበያ በኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በዶ/ር አሳምነው ተሾመ፣ ክልላዊ የበልግ ወቅት ትንበያ ግምገማና ቀጣይ ክረምት ወቅት ትንበያ በአቶ ደጀኔ አያና እንዲሁም የዘርፍ ተኮሩን በአቶ ወንድም አዱኛው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በቤንሻንጉል ጉምዝ የሚቲዎሮሎጂ  አገልግሎት ማእከል ውስጥ ያስገነባውን የG+2 ህንፃ ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2016 በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚንስትሩ አማካሪ በአቶ ሞቱማ መቃሳ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ፈጠነ ተሾመ ተመረቀ።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከል ክልላዊ የበልግ 2016ዓ.ም የአየር ሁኔታ ግምገማና የክረምት 2016/17 ወቅት  የአየር ሁኔታ ትንበያ መድረክ ተጀመረ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
04:24
Video unavailableShow in Telegram
ESAT
Hammasini ko'rsatish...
06:14
Video unavailableShow in Telegram
H.E. Mr. Fetene Teshome Director of Ethiopian Meteorology Institute and WMO Regional Association I /Africa/ President about the meeting of RA-I 19th Session
Hammasini ko'rsatish...
02:09
Video unavailableShow in Telegram
አሻም ቲቪ
Hammasini ko'rsatish...