cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ምስለ ኦርቶዶክስ በNTG

የህ ቻናል የተከከፈተበት ዋና አላማ የስልክ መጥሪያዎች,ምስሎችን,መዝሙሮችን እንዲሁም የእለቱን በአላት በተሻለ መልኩ ለማግኘት እንዲያመች ሲባል ነው ዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዩሀንስለ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
758
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
-530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

9eoaltu4pfhfvg9n1wj9.m4a2.96 MB
#ሀይሌ_ብርታቴ ሀይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ(2) የዘላለሙ የአብርሀሙ ስላሴ(2) አዝ ተመረጠች ነፍሴ አንተን ለማወደስ ከላይ ከአርያም ከስላሴ መቅደስ በአንድነት ሶስትነትበዙፋኑ ሞልቶ የሚሳነው የለም ለስላሴ ከቶ አዝ ከመንገድ ዳር ልቁም የወደቀ ላንሳ የተራበ ላብላ የታመመ አልርሳ እንደ አብርሀም አድርገኝ እንደ ደጉ አባት ቤቴ እንዲሞላ ያንተ በረከት አዝ ጠፈሩን በውሀ በጥበብ የሰራህ እኔስ ይገርመኛል የስላሴ ስራ ኑና ተመልከቱት ታምራት ሲሰራ ሰዎች እልል በሉ ወላድ ሆነች ሳራ አዝ አብ አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ወዶናል ወልድ በተዋህዶ እኛኑ መስሎናል ሀይሉ ተገለጠ የመንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን አድሮ ሲያድን ሲፈውስ @NEY_NEY_EMYE_MARYAM @NEY_NEY_EMYE_MARYAM @NEY_NEY_EMYE_MARYAM
Hammasini ko'rsatish...
ሀይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ.mp37.17 KB
👍 2
v3kjlzvuvm103q46nqds.m4a5.48 MB
👍 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
🛑 ጉባኤ አቅሌሲያ ⛪️ ''በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ'' አኩፋዳው ቢጓደል የማይጎድል ጥበብ የያዘ ፣ እልፍኝ ቢዘጋበት የዕውቀት ገጿ ያልጠፋው የዛሬ የየኔታ እሸት የነገ የቤተክርስቲያን ፍሬ የአብነት ተማሪ! የጥበብ ምንጯ እግዚአብሔር ፤ ሐገሯ ከየኔታ ብራና ሆና ሚስጥራትን በመጋረጃዋ ጋርዳ ለዘመናት ለሚፈልጓት ብቻ እየተገለጠች ፍሬ አፍርታ ጥበበኞችን አፍልቃለች። ''በእንተ ስማ ለማርያም'' ስንል ጉባኤ ዘርግተን የየኔታን ደጅ በጥቂት ልናሳይ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ሰባኪያነ ወንጌል ፣ ካህናት ዘማሪያን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በተገኙበት መንፈሳዊ ኦርቶዶክሳዊ የወንጌልን ገበታ ዘርግተን ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7:00) ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ 4ተኛ ፎቅ የሚገኘው አዳራሽ እንጠብቃችኋለን። መግቢያ ፦ በነጻ ነው! ለበለጠ መረጃ:- በነጻ አጭር የስልክ መስመር 9066 ወይም 0938944444 አዘጋጅ:- ማህበረ ቁስቋም
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ሰኔ 21 በሆሳዕና ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ። ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀላሉ ለመቀላቀል▻ @m_ezmur21                 ▻ @m_ezmur21 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የዐይነ ሥውሩ ፋኖስ አንድ ዓይነ ሥውር በእጁ ደማቅ ብርሃን ያለው ፋኖስ ይዞ በጨለማ በመንደር ውስጥ እየሔደ ነው:: አንድ ሰው ድንገት ሲያልፍ አየውና ፋኖሱን ሲያይ ተገርሞ ጠየቀው:: "ይቅርታ ወንድሜ:: በእጅህ ፋኖስ አብርተህ ይዘሃል:: እንዳትደናቀፍ ነው እንዳልል እንደማይህ ዓይነ ሥውር ነህ:: የማታይ ከሆነ የፋኖሱ ብርሃን ምን ይጠቅምሃል?" አለው:: "ልክ ነህ የፋኖሱን ብርሃን አላይም:: የምይዘው እኔ በጨለማ ውስጥ ስሔድ እንዳልደናቀፍ አይደለም:: ሆኖም በጨለማ ውስጥ ብርሃን ሳልይዝ ከሔድኩ ሰዎች እኔን ስለማያዩኝ ከእኔ ጋር እንዳይጋጩ ወይንም እንዳይደናቀፉ ነው:: ፋኖሴንን  ከያዝሁ በብርሃኑ እኔን ያዩኛል" ብሎ መለሰለት:: ወዳጄ በዚህች ጨለማ ዓለም ስትሔድ የልብህ ዓይን በመታወሩ ምክንያት የማታያቸው ብዙ እንቅፋቶች አሉ:: ''ኸረ እኔ ዕውር አይደለሁም" ካልክ "ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፡ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ ነው:: (ራእ 3:17) በጨለማው ዓለም ስትሔድ ለራስህ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ማሰብ ትገደዳለህ:: እውነተኛውን ፋና ክርስቶስን በጉያህ ከያዝክ ሰዎች እሱን አይተው በአንተ ከመሰናከል ይድናሉ:: አለዚያ ግን በአንተ ምክንያት የሚደናቀፈው ሰው ብዙ ነው:: #ከተመረጡ_ገፆች ምንጭ :- ከሞት ባሻገር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሼር//SHARE#በማድረግ_ያሳውቁ         21 መዝሙር @m_ezmur21 @m_ezmur21
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
688h2vu42n9m0cdenqjd.m4a5.34 MB
ዘፀአት ነው ለህዝቡ      ዘጸአት ነው ለህዝቡ      በደም ታስሯል ወጀቡ      ጽኑ ክብርን ያየነው      ኢየሱስን ይዘን ነው      ክርስቶስን ለብሰን ነው የግብጹ ፈርኦን በግፍ ሲያስጨንቀን ክቡደ መዝርዕት ሙሴ ተነሳና ከራምሴ መንጋውን ይዞ ወጣ እያቀና በሀቅለ ቃዴስ በሲና ያ መንፈሳዊ መጣን ያ መንፈሳዊ መበል ክርስቶስ ነበረ እኛን የሚከተል      አዝማች በረፍድም እንዳንቀር ተወልን ምስክር በእያሱ ወልደ ነዌ እያዳነን ከአርዌ ከነአን ሄደ ከፊት እየመራን ስሙ መድሃኒት ሆነን እስራኤል ዘነፍስ ነን ድል ባደረገው ጌታ እያሪኮ ሲኦል ፈርሷል በእልልታ ተጨማሪ  ለማግኘት ይቀላቀሉ  ➟ @m_ezmur21 ለሌሎች ያጋሩ  ➟@m_ezmur21
Hammasini ko'rsatish...
06. 6 ዘጸአት ነው ለሕዝቡ.mp35.11 MB
በምስጋና_ዘማሪ_ገብረዮሐንስ_ገብረፃድቅ.mp35.94 MB
👍 3
Blog - Latest News You are here:Home/ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር/ጾመ ሐዋርያት ጾመ ሐዋርያት በተክለሐዋርያት ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን ይዟቸው ከቤት በመውጣት መንገድ ጀመረ፡፡ እርሱ ከፊት እየመራቸው እነርሱ እየተከተሉት ወደ ረጅሙና በረጃጅም ዛፎች ወደ ተሞላው ደብረ ዘይት ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡ ይህንንም እየነገራቸው ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ፤ከፍ አለ፡፡ ነጭ የሆነች ብሩህ ደመናም አምላካችንን ተቀበለችው፡፡ከዓይናቸውም እየራቀ፤ከእይታቸው በርቀት ሳይሆን በርኅቀት ተሰወረባቸው፡፡ሐዋርያትም ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ይወዱት ስለነበር ሲለያቸው አዝነው አተኩረው ሰማዩን ለረጅም ሰዓት ተመለከቱ፡፡ ድንገትቸከቸኸ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡መላእክትም ሐዋርያትን እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን  ቆማችኋል፡፡ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል›› አሏቸው፤ (ሐዋ. ፩፥፰-፲፩)፡፡ ሐዋርያትም የመላእክትን ማረጋጊያ ቃል ከሰሙ በኋላ  በኢየሩሳሌም ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ በመሄድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸው እስኪፈጸም ድረስ ቀን ከሌሊት በአንድነት ሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከመካከላቸው አድርገው በጾምና በጸሎት እየተጉ ቆዩ፡፡ የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት›› (ማቴ.፱፥፲፬)።  ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው  ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ያንጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፭)፡፡ እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማጸን ነው፡፡ ይህን ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አብዛኛው ምእመን ‹‹የቄስ ጾም›› ነው በማለት ከጾሙ ሽሽት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተክርስትያንን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ መስተካከል ይገባዋል፡፡ ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ጾመን በረከትን ልናተርፍ ይገባናል፡፡ የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት እና ምልጃ አይለየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.