cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Tesfaye Menberu

I prefer issue based politics

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
196
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Hammasini ko'rsatish...
አዲስአበባን ምን በጃት? የጨዋታው የመጨረሻ ምእራፍ? 12/22/22

Reyot አዲስአበባን ምን በጃት? የጨዋታው የመጨረሻ ምእራፍ? 12/22/22 #ReyotMedia #LidetuAyalew #ErmiasLegese #EthiopiaNews #AbiyAhmed #AdanechAbebe #Oromia #EritreaNews #IsayasAfewerki #BirhanuNega #TPLF #PP #TewodrosTsegaye

Hammasini ko'rsatish...
''የትግራይ ሕዝብ አገር የመሆን ጉዞ''የልደቱ አያሌው ልብ የሚነካ ይቅርታ

Please support Reyot Media. Go Fund Me:

https://gofund.me/afe7b8cb

2.3. በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የተፈጠረው ችግር በዚህ መጠን ተባብሶ አሁን የሚገኝበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ አክራሪ የአማራና የትግራይ ብሔርተኞች የተጫወቱት አሉታዊ ሚና መኖሩ እንደተጠቀ ሆኖ፣ የ27 ዓመቱ ሕወሓት መራሽ መንግሥት ሕዝቡ የሚያቀርበውን የመብት ጥያቄ ከጅምሩ በተገቢው ጊዜና ሁኔታ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ጥያቄውን ያለአግባብ ለማፈን በመሞከሩ ምክንያት ወደዚህ የተወሳሰወበ ደረጃ እንደደረሰ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ችግሩ አሁን ላይ በደረሰበት ደረጃ መፍትሄ እንዲያገኝ ሲፈለግ መፍትሄው የአማራውንም ሕዝብ ፍላጎትና ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሆን የማድረግ የሞራልና የፖለቲካ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሕወሓትና የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም መፍትሄው ዐውደ-ሰፊና ዘላቂ እንዲሆን የሁለቱም ክልል የፖለቲካ ልኂቃን የጋራ ተነሳሽነትና አስተዋፅዖ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 2.4. በማንኛውም ሀገር የሚካሄድ የእርስ-በርስ ጦርነት ሲጠናቀቅ የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ ይዞ መምጣቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ የወቅቱን ጦርነት መጠናቀቅ ተከትሎ በሀገራችን በሚመጣው የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ ለየራሳቸውም ሆነ ለጋራ የሀገሪቱ ጥቅም ሲሉ የአማራና የትግራይ ሕዝቦች ግንኙነታቸውን ወደ በጎ አቅጣጫ መቀየርና ማጠናከር ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም የአማራና የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች የወቅቱን የሰላም ስምምነት ከዚህ ወቅታዊና ስትራቴጂክ ዓላማ ጋር በጥንቃቄ አያይዘው ሊያዩትና ሊቋጩት ይገባል፡፡ በዚህ የሰላም ስምምነት ውጤት ምክንያት የሁለቱ ሕዝቦች ግንኙነት መሻከር በዘላቂነት እንዲቀጥል የሚፈልጉ ሻዕቢያን የመሰሉ የፖለቲካ ኃይሎች ምቹ ሁኔታ እንዳያገኙ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የሚታየው የተካረረ ቅራኔ በዘላቂነት እንዲፈታም ሆነ ለአጠቃላዩ የሀገራችን ሰላምና ደህንነት አዎንታዊ ፋይዳ እንዲኖረው ከተፈለገ በትግራይና በአማራ ክልል መካከል አወዛጋቢ የሆኑ ቦታዎች ጉዳይ በሕገ-መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን ከሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌዎች በተለየና (Extraconstitutional) ዐውደ-ሰፊ በሆኑ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲፈቱ መስማማት ያስፈልጋል፡፡ 3. ከናይሮቢው ስምምነት ጋር በተያያዘ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ “ስምምነቱ በፌደራሉ መንግሥትና በሕወሓት ወታደራዊ አዛዦች መካከል የተካሄደ ነው” መባሉን በአፅንዖት ተቃውሟል፡፡ ወደ ፕሪቶሪያው ድርድርም ሕዋሓትን የወከሉ ተደራዳሪዎችን ያልላከ ስለመሆኑም ገልጿል፡፡ በእኔ በኩል የፕሪቶሪያው ስምምነት ይፋ እንደተደረገ በፃፍኩት ፅሁፍ ‘የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ በኩል ከሕወሓት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረምኩ እያለ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ አይወክልም የሚል አቋም መያዙ ከመርህ አኳያ እርስ-በርሱ የሚጋጭ ከመሆኑም በተጨማሪ የሰላም ስምምነቱን በተግባር ለማዋል ሲሞከርም እንቅፋት ሊፈጥር የሚችል ክፍተት እንደሚሆን’ ስጋቴን መግለፄ ይታወቃል፡፡ አሁን በተግባር እየሆነ ያለውም ይኸው ይመስላል። ይህ ተስፋ-ሰጪ የሰላም ስምምነት አሁንም የአፈፃፀም ችግር እንዳይገጥመው ከተፈለገ ሁለቱም ተደራዳሪ ወገኖች የሕጋዊነትንና የእውቅናን ጉዳይ ሰበብ አድርገው እያነሱት ያለው አላስፈላጊ ውዝግብ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፡፡ ለኢትዮጵያ ሰላም ማግኘት የግድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው እንጂ የውክልናና የሕጋዊነት ጉዳይ በሃቅ ይነሳ ከተባለ ግን ሁለቱም ተደራዳሪ ኃይሎች ዛሬ ላይ በፍርድ አደባባይ እንጂ በተደራዳሪነት ሚና ላይ መገኘት የሚገባቸው አልነበሩም፡፡ አሁንም በጦርነቱ መቀጠል ከማንም በላይ ዋና ተጎጂ የሚሆነው ሕዝብ በተደራዳሪዎቹ ላይ “አትወክሉኝም” የሚል ጥያቄ እስካላነሳ ድረስ ሁለቱም ኃይሎች ልባዊ እውቅናን አንዳቸው ለሌላቸው በመስጠት የሰላም ስምምነቱን ውጤታማ ሊያደርጉት ይገባል፡፡ እንወክለዋለን የሚሉት ሕዝብ ከእነርሱ የሕጋዊነትና የውክልና ጥያቄ በላይ የሚያሳስበው የሰላም እጦት ስለሆነ እንዲህ ዓይነቱን የእርስ-በርስ መካሰስ በአስቸኳይ ማቆምና የፈረሙትን የሰላም ስምምነት ዘላቂና የሰመረ በማድረግ ተግባር ላይ ማተኮር ይገባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ - በናይሮቢ የተፈረመው የወቅቱ ስምምነት በብዙ እጅ በጎ ጥረት የታየበት አበረታች ስምምነት ነው፡፡ ወደፊትም የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ መሬት ላይ በተግባር እስከሚፈፀም ድረስ በስምምነቱ የአፈፃፀም ሂደት ላይ የሚገጥሙ ችግሮች በቂ ግምገማና ውይይት ሊደረግባቸውና ተመሳሳይ የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚካሄደውን የወቅቱን አውዳሚ ጦርነት ማስቆም መቻል በራሱ ፋይዳው እጅግ ከፍተኛ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሀገራዊ የሰላም ችግራችን በዘላቂነት መፍትሄ ሊያገኝ የሚችለው በሀገር ደረጃ ወደ ሃቀኛና ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ የውይይትና የድርድር ሂደት ውስጥ በአስቸኳይ በመግባትና በሀገር ደረጃ ላሉብን መዋቅራዊ ችግሮች መዋቅራዊ መፍትሄ ለማግኘት ስንችል ነው፡፡ ከሕገ-መንግሥቱ፣ በልዩ ኃይል ስም ከተቋቋሙ ሕገ-ወጥ የብሔር የጦር ሰራዊቶች፣ ከሽግግር ጊዜ ፍትህ፣ ከብሔራዊ መግባባትና ከእርቀ-ሰላም ጋር የተያያዙ ሀገራዊ ጉዳዮቻችን ሁሉ በፍጥነት መፍትሄ ማግኘት አለባቸው፡፡ ስለሆነም የጉዳዩ ዋና ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብና በሀገሪቱ ፖለቲካ ባለድርሻ የሆኑ ወገኖች በሙሉ መንግሥት ሃቀኛና ሁሉን-አቀፍ የሆነ ሀገራዊ የውይይትና የድርድር ሂደት በአስቸኳይ እንዲጀምር አስፈላጊውን ትግልና ጫና ሊያደርጉ ይገባል እላለሁ፡፡ ልደቱ አያሌው ህዳር 04 ቀን 2015 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
የናይሮቢው የጦር መሪዎች “ቃል-ኪዳን” በቅርቡ በፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰበትን ስምምነት ተከትሎ ሰሞኑን በናይሮቢ በሁለቱ ተፋፈላሚ ወገኖች ወታደራዊ መሪዎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ቀጣይ ድርድር በጎ እና አበረታች ዜና ይዞ መጥቷል፡፡ በእኔ እምነት ይህ የናይሮቢ ስምምነት “የአፈፃፀም ድርድር ውጤት ነው” ቢባልም በዋናው የፕሪቶሪያ ስምምነት ዙሪያ የታዩ የአፈፃፀም ችግሮችን እንደገና ለማስተካከልና የአፈፃፀም ሂደቱን ቅደም-ተከተል በዝርዝር ለመወሰን የተሞከረበት ስምምነት ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጥረት የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ በመሬት ላይ ተፈፃሚ እስከሚሆን ድረስ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት አበረታች ጅምር ነው፡፡ በዚህ ስምምነት የተፈጠሩ የሰላም ተስፋዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ፣ በስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የሚታዩ ተግዳሮቶችም መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ የሚቻለው እንዲህ ዓይነት ግምገማዎችንና የእርምት እርምጃዎችን በተከታታይ በማካሄድ ስለሆነ ጅምሩን የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ይህንን የናይሮቢ ስምምነት በበጎ ጅምርነት እንድናይ የሚያደርጉን ዋና ዋና ተስፋ ሰጪ የስምምነት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. በዋናው የስምምነት ሰነድ ላይ ለአፈፃፀሙ ሂደት እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮች ያሉ መሆናቸውን አምኖ በመቀበል እንዲህ ዓይነት የማሻሻያ እርምጃ ለመውሰድ መሞከሩ በራሱ አበረታች ጥረት ነው፡፡ ምክንያቱም የናይሮቢው ድርድር “በአፈፃፀም ላይ የተካሄደ ድርድር ነው” ቢባልም በይዘት ግን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ጭምር በተወሰነ ደረጃ ያሻሻለ ድርድር በመሆኑ ነው፡፡ ይህ የናይሮቢ የወታደራዊ አዛዦች ስምምነት ፖለቲከኛና ዲፕሎማት በሆኑ ሰዎች ከተካሄደው የፕሪቶሪያው ስምምነት የተሻለ መሆኑም የሚገርም ነው፡፡ 2. የናይሮቢው ስምምነት ለፈጣን ሰብዓዊ እርዳታ፣ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦትና ለሲቪል ዜጎች ደህንነት ቀዳሚ ትኩረት የሰጠ በመሆኑና እነዚህ ጉዳዮች በሕዝቡ ውስጥ የመተማመን ስሜት ለመፍጠር የሚያስችሉ አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎች በመሆናቸው እጅግ ጠቃሚ እርምጃዎች ናቸው፡፡ 3. የትግራይ ኃይሎችን ከባድ መሳሪያ የማስፈታቱ እርምጃ በትግራይ ክልል የሚገኙ “የውጪ ኃይሎችን” እና “ከማዕከላዊ መንግሥቱ ሰራዊት ውጪ ያሉ ሌሎች ታጣቂ ኃይሎችን” ከማስወጣት እርምጃ ጋር ተጣምሮ እንዲፈፀም፣ አጠቃላይ ትጥቅ የማስፈታቱ እርምጃ ደግሞ ወደፊት የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝርዝር የአፈፃፀም ሂደት እንዲኖረውና እንዲፈፀም ስምምነት ላይ መደረሱ በራሱ ተስፋ ሰጪ እርምጃ ነው፡፡ 4. በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ይዞታ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን የሰላም ስምምነቱን የሚያደናቅፍ አፍራሽ ሚና ከመጫወት እንዲቆጠቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ በስምምነቱ ላይ መቀመጡም ሌላው የስምምነቱ በጎ ጎን ነው፡፡ እነዚህ አራት ነጥቦች የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል እጅግ ጠቃሚ፣ አበረታችና አጋዥ ጉዳዮች ሲሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ደግሞ አሁንም ተጨማሪ ማሻሻያ ሊደረግባቸው የሚገቡና የሰላም ስምምነቱን በዘላቂነት ለመተግበር እንዲቻል ልዩ ትኩረት የሚያሻቸው ናቸው፡፡ 1. የኤርትራን መንግሥት ጣልቃ-ገብነትና ወረራ በተመከለተ አሁንም በተድበሰበሰ ሁኔታ “የውጪ ኃይሎች” በሚል እየጠሩ መቀጠል ተገቢ አይደለም፡፡ ለተደራዳሪ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ደህንነትና ሉዓላዊነት መከበር የሚበልጥ ሌላ ጉዳይ ሊኖር ስለማይገባና የተጀመረው የሰላም ስምምነት በሙሉ ልብ በሃቅና በግልፅነት ተግባራዊ እንዲሆን ከተፈለገ የኤርትራ መንግሥት በእውነተኛ ስሙና ግብሩ ሊጠራ ይገባል፡፡ የኤርትራ መንግሥት የጦርነቱ ተባባሪ ሳይሆን የጦርነቱ ዋና ተሳታፊ በመሆኑ በስም ከመጠራትም አልፎ የተደራዳሪ ወገኖች የውይይትና የድርድር አጀንዳ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህ መሆን እንዳይችል የሚያደርግ ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያትም የለም፡፡ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውና ለረዥም ጊዜ ሲንከባለል የመጣው የባድመ ጉዳይም መቋጫ ሊያገኝ የሚገባው በሁለቱ ሉዓላዊ ሀገራት ስምምነት ቢሆንም ጉዳዩ ከዚህ ጦርነት አንፃር እንዴት በሰላማዊ መንገድና በዘላቂነት ሊፈታ እንደሚችል በዚህኛው ስምምነት ላይም ግልፅ አቅጣጫ ሊቀመጥለት ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ጉዳዩ ለወቅቱ ስምምነት አደናቃፊ ምክንያት ሆኖ ብቅ እንደሚል ከወዲሁ መገመት ቀላል ነው፡፡ 2. በዚህ የናይሮቢ ስምምነት - “ከማዕከላዊ መንግሥቱ ሰራዊት ውጪ ያሉ ሌሎች ታጣቂ ኃይሎች” በሚል የተዘዋዋሪ አገላለፅ “የአማራ ኃይሎችም” ከትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ አንዳንድ የአማራ ብሔርተኞች ይህ አባባል ወልቃይትንና ራያን እንደማይመለከት አድርገው በማቅረብ ራሳቸውን ሊያታልሉና እውነቱን ሊደብቁ ሲሞክሩ ቢታይም “ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓትን ወደ ቦታው መመለስ” የሚለው የስምምነቱ ዋና ድንጋጌ የአማራ ኃይሎች ከወልቃይትና ከራያ መውጣትን ጭምር የሚመለከት ስለመሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ ነገር ግን በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረውን ይህንን የማንነት ወይም የአከላለል ጥያቄ “በሕገ-መንግሥቱ ብቻ ይፈታል” የሚለው የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዳለ በቀጠለበት ሁኔታ የአማራ ኃይሎችን ከትግራይ ክልል የማስወጣቱ ስምምነት ብቻውን ስምምነቱ መሬት ላይ በሰላም እንዲፈፀም የሚያስችል አይሆንም፡፡ ይህ ጉዳይ ከወዲሁ የተሻለ መፍትሄ ካልተሰጠው የሰላም ስምምነቱን በማደናቀፍ ረገድ አንድ የጎላ ተግዳሮት ሆኖ ብቅ ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ይህ እንደሚሆን በቂ ምልክቶችን ከሰሞኑንም እያየን ነው፡፡ ከሩቅ ጊዜ ግብም አኳያ እንዲህ ዓይነቱ ስምምነት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በአካባቢውም ሆነ በሀገሪቱ ሊያመጣ አይችልም፡፡ በዚህ ረገድ በአማራና በትግራይ መካከል ያለውን ቅራኔ በዘላቂነትና ሁሉንም ወገን የጋራ አሸናፊ በሚያደርግ አግባብ ለመፍታት ከተፈለገም የወቅቱ የሰላም ስምምነት ተደራዳሪዎች ለሚከተሉት አራት ምክረ-ሃሳቦች የተለየ ትኩረት መስጠት ይገባቸዋል፡፡ 2.1. በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የአከላለልና የማንነት ጥያቄ የተነሳው በዋናነት ከሕገመንግሥቱ የአፈፃፀም ችግር ጋር ተያይዞ መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ከወቅቱ ሕገመንግሥት በስራ ላይ መዋል በፊት በሁለቱ ሕዝቦች መካከል እንዲህ ዓይነት “ከማንነትናከድንበር ጋር የተያያዘ” ግጭት በታሪካችን አይተን አናውቅም፡፡ የተፈጠረውን ችግር - ችግሩን በፈጠረው ሕግ እንደገና መፍታት የሚቻልበት ዕድል እንደማይኖር በመገንዘብም - ይህንን ችግር በሕገ-መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን ዐውደ-ሰፊ በሆነ የመፍትሄ አማራጭ መፍታት ያስፈልጋል፡፡ 2.2. ለችግሩ የሚሰጠው መፍትሄ ችግሩ ዳግም እንዳያመረቅዝ በሚያደርግና በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን የወቅቱን “ድንበር” ከተራ የአስተዳደር ወሰን ምልክትነት ያለፈ ፋይዳና ትርጉም እንዳይኖረው በሚያደርግ አግባብ መፍታት ያስፈልጋል፡፡ ችግሩ በዚህ አግባብ ከተፈታ መፍትሄውን ዘላቂ እንዲሆን ከማድረግም በላይ በሌሎች የሀገሪቱ ተጎራባች ክልሎች ያሉና ወደፊትም ሊኖሩ የሚችሉ ተመሳሳይ ችግሮች አስተማማኝ መፍትሄ እንዲኖራቸው የአርዓያነት ሚና የሚኖረው ስምምነት ይሆናል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
በዘላቂነት ውጤታማ ሊሆን የሚችለው በዋናነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ሲኖረው እንደሆነ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለየ ሁኔታም የሰሜኑ ጦርነት ሕዝባዊ ጦርነት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ 2. የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም በአፍሪካ ህብረት መሪነት መካሄዱ እንደተጠበቀ ሆኖ የአሜሪካ፣ የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በአፈፃፀም ሂደቱ ላይ ቢያንስ የታዛቢነት ሚና እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 3. አንድን የሰላም ስምምነት የፀና ማድረግ የሚቻለው ‘የጠብመንጃ አፈ-ሙዞችን’ ብቻ እንዲዘጉ በማድረግ አይደለም፡፡ ይልቁንም የሰላም ስምምነቱ በዘላቂነት የሚፀናው ጥላቻን የሚያስፋፉ ‘የሰው ላንቃዎች’ ሲዘጉ ስለሆነ የስምምነቱ አፈፃፀም በዚህ ረገድ ጥብቅ የሆነ ግዴታ በተፋላሚ ወገን መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው ላይ መጣል ይኖርበታል፡፡ 4. የወቅቱ ጦርነት እንዲነሳም ሆነ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር በማድረግ ረገድ የኤርትራ መንግሥት ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የተፈረመው የሰላም ስምምነት ሳይደናቀፍ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ከተፈለገም በአንድ በኩል የኤርትራ መንግሥት ሙሉ በሙሉ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ላይ ያለው ጣልቃ-ገብነት እንዴት እንደሚቆም፣ በሌላ ኩል ደግሞ ባድመን በሚመለከት በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው አለመግባባት እንዴት መፈታት እንዳለበት የስምምነቱ አፈፃፀም ባልተደባበሰ ሁኔታ ግልፅ መፍትሄ ማስቀመጥ አለበት፡፡ የኤርትራ መንግሥት ጣልቃ-ገብነት በእርግጠኛነት ከሀገሪቱ ባልተወገደበት ሁኔታ እንኳንስ የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች ሌሎች ኢትዮጵያውያንም አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ሊኖረን አይችልም፡፡ 5. ክልሎች የሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ከሚፈቅደው ውጪ “ልዩ-ኃይል” የሚባል ታጣቂ ኃይል እስካላቸው ድረስ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ሊኖር አይችልም፡፡ “በአንድ ሀገር ሁለት ሰራዊት አይኖርም” የሚለው መርህ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ ከመደበኛ ፖሊስ ኃይል ውጪ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ያሉ ልዩ-ኃይሎችና ሌሎች ህጋዊ መሰረት የሌላቸው ታጣቂ ኃይሎች በሙሉ እንዲፈርሱ መደረግ አለበት፡፡ 6. የወቅቱ ጦርነት ወደ አስከፊ ደረጃ እንዲሸጋገር የተደረገው በአማራና በትግራይ ሕዝብ መካከል ስር የሰደደ ግጭት እንዲፈጠር በመደረጉ ነው፡፡ ወደፊትም በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ በአግባቡ ካልተፈታ በስተቀር ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን ስለማይችል የሁለቱ ሕዝቦች ግንኙነት ወደ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲቀየርና በመካከላቸው ያለው ቅራኔም ዐውደ-ሰፊ በሆነና ዘላቂነት ባለው መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል፡፡ 7. የሰሜኑ ጦርነት ዋናው አውዳሚ ጦርነት ቢሆንም በሀገሪቱ ያለ ብቸኛ ጦርነት ግን አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲኖራት ከተፈለገ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ ከፋኖ እና ከሌሎችም ታጣቂ ኃይሎች ጋር ያለው ግጭት ወይም ጦርነት በተመሳሳይ ሁኔታ በአስቸኳይ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 8. የወቅቱ ጦርነት በሆነ ቅፅበታዊ ምክንያት የተፈጠረ ሳይሆን ሀገሪቱ ለአለፉት ሰላሳ ዓመታት ከተከተለችው የልዩነትና የብሔር ፖለቲካ መዋቅራዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ የተከሰተ ጦርነት ነው፡፡ ጦርነቱ በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ከተፈለገ የብሔር ፖለቲካን ገዢ ካደረገው ሕገ-መንግሥት ጀምሮ ያሉ ሌሎች መዋቅራዊ ችግሮችም መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 9. የወቅቱ የሰላም ስምምነት ሰነድ በትግራይ ክልል ከሁለት ዓመት በፊት የተካሄደው ምርጫ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አማካኝነት ያልተካሄደ ከመሆኑ አኳያ “ሕገ-ወጥ ነው” ተብሎ መፈረጁና በትግራይ ክልል አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑ ተገቢ ነው፡፡ ሆኖም በሀገር ደረጃ በስልጣን ላይ የሚገኘው ብልጽግና ፓርቲም ከሕግ ውጪ የስልጣን ዕድሜውን ያራዘመ፣ የፓርቲ ጉባዔ ሳያካሄድና የምርጫ ሕጉን መስፈርት ሳያሟላ ለምርጫ የተወዳደረ፣ በተካሄደው ምርጫም ተቀናቃኞቹን በማሰርና በሕገ-ወጥ መንገድ የፓርቲዎችን ሕጋዊ እውቅና በመሰረዝ የተመረጠ፣ አመራሮቹን በጠቅላላ ጉባዔ ሳያስመርጥ ጠቅላይ ሚኒስትር የሾመና መንግሥት ያቋቋመ ፓርቲ በመሆኑ ከሕወሓት እኩል ሳይሆን በበለጠ መጠን በሕገ-ወጥ መንገድ ለስልጣን የበቃ ፓርቲ ነው፡፡ ስለሆነም ድጋሜ ምርጫ የማካሄዱ ስምምነት በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃም ተፈፃሚ ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነና ‘የሕገወጥነቱ ጉዳይ ሕወሓትን ብቻ የሚመለከት ነው’ ከተባለ ግን የወቅቱ ድርድር የተካሄደው ‘የሕዝብ ውክልና ከሌለው ሕገ- ወጥ ድርጅት ጋር ነው’ የሚልና ራሱን የስምምነቱን ሕጋዊነትም ጭምር ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የመርህ ግጭት ይፈጥራል፡፡ 10.በአጠቃላይ የወቅቱ የሰላም ስምምነት የሰሜኑን ጦርነት በማስቆም ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሀገሪቱን ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በፊት ወደነበረችበት ሁኔታ የሚመልስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት የነበረችበት ሁኔታ ደግሞ ምን ያህል የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ፍፁማዊ አምባ-ገነንነት የሰፈነበት ኢ- ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ ወደ ወቅቱ አውዳሚ ጦርነት የገባነውም ያ አምባገነናዊ ስርዓት በተከተለው የተሳሳተ መንገድ ነው፡፡ የወቅቱ የሰላም ስምምነት አጠቃላይ ውጤት ጦርነቱን ከማስቆም አልፎ ‘የቀድሞውን ኢሕአዴግ በስልጣን ላይ እንደገና ለረዥም ጊዜ የማስቀጠል የማይገባ ውጤት’ እንዳያመጣ ከተፈለገ በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በሀገር ደረጃ እውነተኛ ሽግግር ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን-አቀፍና ሃቀኛ ሀገራዊ የውይይትና የድርድር ሂደት በአስቸኳይ ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡ ለሰላሳ ዓመታት ተፈትኖ የወደቀውና የሀገሪቱ የወቅቱ መሰረታዊ ችግሮች ዋና ምንጭ የሆነው ኢሕአዴግ ለሁለት ተከፍሎም ሆነ እንደገና አንድ ሆኖ የኢትዮጵያን መዋቅራዊ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ፍላጎትም ሆነ ብቃት ስለሌለው “በአዲስ የሽግግር ሂደት” ከማለፍ ያነሰ ማንኛውም “አካባቢያዊም ሆነ ጥገናዊ ለውጥ” ሀገሪቱን ወደሚፈለገው ዘላቂ ሰላም ሊያሸጋግራት አይችልም፡፡ ስለሆነም እነዚህ ኢትዮጵያን ወደ ዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ብልጽግና ማሸጋገር የሚያስችሉ አስር መሰረታዊ ጉዳዮች ተፈፃሚ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚመለከቷቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላትና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚሹ የውጪ መንግሥታትና ተቋማት አስፈላጊውን ጥረትና ድጋፍ ሁሉ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ሰላም የፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ሳይሆን ስትራቴጂክ ግብ ይሁን…! ልደቱ አያሌው ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
የሰላም ስምምነቱ - ያሳዝናል… ያስደስታል… ያሳስባል. 2 1.ለምን ያሳዝናል…? ለአለፉት ሁለት ዓመታት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲካሄድ የቆየውን አውዳሚ ጦርነት በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ብቻ ለመፍታት ያስችላል የተባለ ስምምነት በፕሪቶሪያ ተፈርሟል፡፡ የስምምነቱ አጠቃላይ ይዘት በአጭሩ ሁኔታዎችን ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በፊት ወደነበሩበት መመለስ ነው፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ከሁለት ዓመታት በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ ከመመለስ ውጪ ያገኙትም ሆነ ያሳኩት የተለየ ጥቅምና ግብ የለም፡፡ የዚህ ጦርነት ቀስቃሾችና ፈፃሚዎች በዚህ ስምምነት መሰረት ወደነበሩበት ሁኔታ መመለስና ስልጣናቸውን ማስቀጠል ቢችሉም፤ አውዳሚው ጦርነት በዜጎች፣ በማህበረሰቦችና በሀገር ላይ ያስከተለው ጉዳት ግን እንዲሁ በቀላሉ ወደነበረበት አይመለስም፡፡ የዚህ አውዳሚ ጦርነት ዳፋ እና ጠባሳ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ለረዥም ዓመታት አብሮን ይኖራል፤ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ወደኋላ በማይመለስና በማይጠገን መጠን ጎድቶን አልፏል፡፡ ታዲያ - በዚህ የሁለት ዓመት አውዳሚ ጦርነት በመቶ-ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ውድ ህይወታቸውን ያጡት፣ በብዙ አስር-ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን አካል ጉዳተኛ የሆኑት፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ እህቶቻችን የተደፈሩት፣ ብዙ ሺህ ህፃናት ወላጅ-አልባ የሆኑት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን መኖሪያ ቀዬአቸውን ጥለው የተሰደዱት፣ ብዙ ትዳሮች የፈረሱትና ማህበራዊ ግንኙነቶች የተበጣጠሱት፣ ምናልባትም አራት የአባይ ግድቦችን ለመገንባት የሚያስችል የሀገርና የሕዝብ ሃብት ያጣነው፣ ገፅታችንን በዓለም ሕዝብ ፊት ያጠለሸነው - እንደዚህ ወደነበርንበት ለመመለስ ከሆነ የሕግ ተጠያቂነትን ጉዳይ ለጊዜው እንተወውና ቢያንስ በሞራልና በታሪክ ለዚህ ሁሉ እልቂትና ውድመት ተጠያቂው ማን ነው? ያሳዝናል…! ጦርነትና ጦረኝነት ለዘለዓለም ይውደም…!!! 2.ለምን ያስደስታል…? የሰሞኑ የሰላም ስምምነት እንዲህ በቀላሉ ይሳካል ተብሎ የማይገመት እጅግ አስገራሚና አስደሳች የሆነ ድንገተኛ ክስተት ነው፡፡ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሂደት በቅርበት የምንከታተል ሰዎች ከዚህ የመጀመሪያ ዙር ድርድር ይገኛል ብለን የገመትነው ከፍተኛ ውጤት - ‘ጦርነቱን በሰላማዊ ድርድር ለመፍታት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ጊዜያዊ የግጭት ማስወገድ ስምምነት (Cessation of Hostilities)’ ላይ ሊደረስ ይችላል ብለን ነበር፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች በዚህ የመጀመሪያ ድርድር ከጊዜያዊ የተኩስ ስምምነት አልፈው ‘አጠቃላይና ቋሚ የተኩስ ማቆም ስምምነት (Negotiated Ceasefire)’ ላይ መድረስ ችለዋል፡፡ ‘ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?’ የሚል ከባድ ጥያቄ መኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ተፋላሚ ወገኖች በዚህ የመጀመሪያ ግንኙነት ለዚህ ዓይነት ፈጣንና ሁለንተናዊ የሆነ ስምምነት መብቃታቸው ሊታመን በማይችል ደረጃ እጅግ አስደሳች ዜና ነው፡፡ እንደኔ አመለካከት ሁለቱም ወገኖች ይህንን ስምምነት በዚህ መጠንና ፍጥነት መቀበላቸው ከፖለቲካ ግምት ውጪ የሆነና “እንደ ተዓምር” የሚቆጠር ነው፡፡ ይህ ስምምነት ሳይደናቀፍ ወደ ተግባር መቀየር የሚችል ከሆነ - ተጨማሪ ዜጎቻችን ውድ ህይወታቸውንና አካላቸውን ከማጣት ይድናሉ፣ የሀገሪቱና የሕዝቡ አጠቃላይ ትኩረት ከጦርነት ይልቅ ወደ ልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ይሸጋገራል፣ በመፍረስ ሂደት ላይ የሚገኘው የሀገሪቱ ህልውናም ከጥፋት የመዳን ዕድል ይኖረዋል፡፡ በአጠቃላይ - ስለ ህዝቡ ደህንነትና ስለ ሀገሪቱ ህልውና በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ለምንገኝ ዜጎች የሰሞኑ የሰላም ስምምነት ‘በረዥሙ የጨለማ ዋሻ ጫፍ ላይ የምትገኝ የብርሃን ፍንጣቂ’ እንድናይ አድርጎናል፡፡ እንኳን ደስ አለን…! ሰላምና ሰላማዊነት በኢትዮጵያ ላይ ዘላለማዊ አሸናፊ ይሁን…! 3.ለምን ያሳስባል…? ከፍ ሲል ለመግለፅ እንደተሞከረው የሰሞኑ የሰላም ስምምነት ፈፅሞ በማይጠበቅ ሁኔታና ፍጥነት አስደሳች ውጤት ይዞ የመጣ ክስተት ነው፡፡ ሆኖም እንደ እኔ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሂደት በቅርበት ለሚከታተልና ተፋላሚ ወገኖች በምን ዓይነት የጥላቻ፣ ያለመተማመንና የመጠፋፋት ስሜት ውስጥ እንደሚገኙ ለሚገነዘብ ሰው ይህ የሰላም ስምምነት በስምምነት ሰነዱ ላይ በሰፈረው ሁኔታና ፍጥነት ተግባራዊ ይሆናል ብሎ ለማመን አይችልም፡፡ ስምምነቱ በአንድ በኩል ራሱ የጦርነቱ ሂደት በተፋላሚ ወገኖች ህልውና ላይ በፈጠረው ጫና፤ በሌላ በኩል ደግሞ የውጪ መንግሥታትና ተቋማት ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ባሳደሩት ከባድ ተፅዕኖ ምክንያት እንጂ በተፋላሚ ወገኖች ልባዊ ፍላጎትና የአስተሳሰብ ለውጥ ምክንያት እንዳልመጣ ብዙም አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ ራሳችንን ለማታለል ካልፈለግን በስተቀር እርስ-በርስ መጠፋፋትን የመጨረሻ ዓላማና ግብ አድርገው በከፍተኛ ጭካኔ እየተገዳደሉ (በዋናነት እያገዳደሉ) የሚገኙ ተፋላሚ ወገኖች በድንገትና በዚህ መጠን የጠላትነትና ያለመተማመን ባህርያቸው ተወግዶ ወደ አጠቃላይ የሰላም ስምምነት ሊደርሱ ይችላሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ ይህ ስምምነት ለአውዳሚው ጦርነት መቆም ካለው ከፍተኛ ጠቀሜታ አንጻር ፈፅሞ መሰናከል የሌለበት ቢሆንም ‘የሰላም ስምምነቱ በሰነዱ ላይ በሰፈረው ሁኔታና ፍጥነት በተግባር ሊፈፀም ይችላል ወይ?’ የሚለው ጥያቄ ግን እጅግ አሳሳቢ ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ በአጭሩ የዚህ የሰላም ስምምነት የአፈፃፀም ሂደት ተገቢ ያልሆነ ብቻም ሳይሆን በቀላሉ በተግባር ሊተረጎም የማይችልም ነው፡፡ በተግባር መፈፀም ከቻለም ሌላ ተጨማሪ “ተዓምራዊ ክስተት” ይሆናል፡፡ በእኔ አመለካከት ይህ ስምምነት በሰነዱ ላይ በተቀመጠው የአፈፃፀም ሂደት መሰረት መፈፀም ቢችል ደስተኛ የምሆን ቢሆንም ስምምነቱ ለረዥም ጊዜ ፀንቶ ይቆያል የሚል ግምት ግን የለኝም፡፡ ይህ ስምምነት ሊቀለበስ በማይችልበት ሁኔታ በተግባር እንዲፈፀምና ለአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አዎንታዊ ፋይዳ እንዲኖረው ከተፈለገ የሚከተሉትን አስር መሰረታዊ ጉዳዮች ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 1. ዘላቂ ሰላም በተፋላሚ ወገኖች ልባዊ ፍላጎትና መተማመን ላይ ተመስርቶ እንጂ በውስጣዊም ሆነ በውጫዊ ጫና እና ተፅዕኖ በሚፈፀም የፊርማ ስምምነት ብቻ ሊገኝ አይችልም፡፡ ስለሆነም - በሰላም ስምምነቱ ላይ የሚታየው እጅግ የታጨቀና የተቻኮለ የአፈፃፀም ሂደት በተፋላሚ ወገኖች ዘንድ ልባዊ መተማመንና መግባባትን መፍጠር በሚያስችል ስክነትና በመሬት ላይ ያለውን እጅግ ውስብስብ ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ አግባብ በአስቸኳይ እንዲሻሻል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የስምምነቱ የአፈፃፀም የጊዜ ገደብ የስምምነቱ ፍሬ ሃሳቦች በፖለቲካ አመራሮች ደረጃ ብቻ ሳይሆን በበታች መዋቅራቸውና በሚወክሉት ሕዝብ ውስጥም የሚኖርን የመተማመንና የመግባባት አስፈላጊነት ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ አንድ የሰላም ስምምነት
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ወርዶ በሚለው አልስማማም ተሜ! በእርግጥ ክርክሩን የልደቱና የመስከረም ብቻ አድርገን ካየነው ሊያስብል ይችላል። እውነታው ግን በአንድ በኩል እሱም አስቀድሞ እንደገለፀው እሷ ያራመደችውን የተሳሳተ ሀሳብ የሚጋሩ ብዙ የዋህ ኢትዮጵያዊ ስላሉ ነገሩን ግልፅ ማድረጉ ስለሚጠቅም ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአማራው ህዝብ የህልውና ትግል ከተነሱለት ዓላማ ይልቅ ለሆዳቸው በተንበረከኩ አድርባዮችና እንጭጭ ፖለቲከኞች እጅ ወድቆ ተስፋ ወደሚያስቆርጥ ቁልቁለት ስለወረደ በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችን በማጋጨት ትግሉ የሚጠይቀውን የአስተሳሰብና የአመለካከት ጥራት እንዲላበስ የሚያስችል አዲስ ጅምርና ፍንጭ ለመስጠት ነው። በተጨማሪም በውይይቱ ላይ እንደተናገረው ትግሉ ከፍረጃና ስም ማጥፋት ወጥቶ ወደ ውስጥ በማየት የአማራ ህዝብ ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ በሚወጣበት ሁኔታና ከሌሎች ኢትዮያውያን ወገኖቹ ጋር በሰላም አብሮ ለመኖር በሚያስችለው ጠላትን እየቀነሱ ወዳጅ የማብዛት የትግል ስልት የበኩሉን አስተዋጽኦ የማበርከት ፍላጎት እንዳለው ለማሳየትም ጭምር ነው። ሌላው ይቆየን።
Hammasini ko'rsatish...
የሚስቁብንን የሚሳለቁብንን አንገት እናስደፋ፡፡ ችግሮቻችንን በሰላም መፍታት የምንችል ጠንካራ ህዝቦች መሆናችንን ለዓለም እናሳይ፡፡ በዓለም ፊት ዕፍረት ውስጥ የከተተንን የራሳችንን ጉዳይ በጓዳችን፣ በቤታችን የመፍታት አቅም እንዳለን እናሳይ፡፡ ተደራዳሪዎቻችን ድርድሩን ግዜ መግዣ አድርጋችሁ፣ ጠላት የምትሉትን አድብቶ መምቻ ዘዴ አድርጋችሁ በማሰብ የምታስመስሉ ከሆነ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ ይሄ ከዚህ በፊት የነበረ በአባቶቻችን ተደጋግሞ የተሞከረ፣ ማንንም ያልጠቀመ፣ እስካሁንም ዋጋ እያስከፈለን ያለ የከሸፈ መንገድ ነው፡፡ ህዝባችሁን አገራችሁን አስቡ፡፡ የህዝቡን ስቃይ፣ መከራ፣ ሞት፣ ስደት እምባና ስቃይ አስቡ፡፡ ስልጣን፣ አገር መምራት እና ምቾት የምትመሩት አገርና ህዝብ ሲኖር ነው፡፡ እነሱ በሌሉበት ሁሉም ነገር ምንም ነው፡፡ የድርድሩ የመጨረሻ ውጤት ስልጣናችሁን የሚያሳጣ ቢሆን እንኳ ለአገርና ለህዝብ ስትሉ ለመቀበል ተዘጋጁ፡፡ የኛን ስቃይና ሀዘን ወደ ደስታ፣ የኛን እንባና ለቅሶ ወደ ሳቅ፣ የኛን ርሃብ እና ጠኔ ወደ ጥጋብ፣ የኛን የህልውና ስጋት ወደ ተስፋ፣ የኛን የረከሰ ሞት ወደ ክብር የመመለስ ታሪካዊ ሃላፊነት በእጃችሁ አለ፡፡ የብዙ ኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ በድረድሩ መጀመር ላይ ነው፡፡ የብዙ መከራ እና ስቃይ ውስጥ ያሉ እናቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ተስፋ በእናንተ እጅ ነው፡፡ የግል የቡድን የስልጣን ፍላጎታችሁን፣ የግል እና የቡድን ቂምና በቀላችሁን ወደ ጎን በማድረግ የህዝባችሁን እና የአገራችሁን ጥቅም አስቀድሙ፡፡ ከአጉል የብልጣብልጥነትና የሴራ ፖለቲካ ራሳችሁን አጽዱ፡፡ ከውጭ ሃይል ጣልቃ ገብነት ለአገራችሁና ለህዝባችሁ ስትሉ ራቁ፡፡ የአገራችን የቀደሙ መንግስታት ባልሄዱበት አዲስ የፖለቲካ ባህል ውስጥ አልፋችሁ አዲስ ታሪክ በመፃፍ ከታሪክ ተወቃሽነት ራሳችሁን አድኑ፡፡ ታሪክ ለመሰራት ተዘጋጁ፡፡ ይሄን ስታደርጉ የምንግዜም የአገራችን ጀግኖች ትሆናላችሁ፡፡ ለእስከዛሬውም ይቅር እንላችኋለን፡፡ የመጭው ትውልድ እና ታሪክም በውርደታችሁ ሳይሆን በክብር ያስታውሳችኋል፡፡ በጥላቻ እና በበቀል ለታወሩ ድምፆች ጆሮ አትስጡ፡፡ የነገዋን ኢትዮጵያ እያሰባችሁ ጦርነቱን አቁማችሁ ለድርድር እና ለውይይት ተዘጋጁ፡፡ ስለ ሰላም እና ስለ ዕርቅ ስንወተውት የነበርን ቀላል የማንባል ማህበረሰብ ክፍሎች ከጎናችሁ ነን፡፡ ቀላል የማይባሉ እናቶች እና አባቶች ክርስቲያኑ በፀሎት፣ ሙስሊሙ በዱዓ ከጎናችሁ ነው፡፡ ለኛ ሌላው ሁሉ ለጊዜው ቅንጦት ነው፡፡ ይቅርብን፡፡ አገራዊ ህልውናችንን፣ ነጋችንን ግን አደራ፣ ተስፋችንን እና ህልማችንን ግን አደራ፡፡ አገራችን ከመፍረስ ህዝባችን ከአገር አልባነት የሚተርፈው በድርድር እና በሰላማዊ ውይይት ብቻ ነው፡፡ ጦርነት፣ ሞት፣ ስደት፣ ረሃብ፣ እርዛት ይብቃን! ፍቅር፣ ሰላም ያሸንፋል! ቸር ወሬ ያሰማን! አመሰግናለሁ! ቀን- መስከረም 30/2015 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
ይድረስ የአገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ የህዝባችንን የነገ ተስፋ ለተሸከማችሁ ተደራዳሪዎች! ከአዳነ ታደሰ የቀድሞ የኢዴፓ ፕሬዝደንት የጦርነት የመጨረሻው መቋጫ ድርድር ነው ያልነው ድሮ ነበር፡፡ መጨረሻው ይሄ መሆኑ ካልቀረ ደግሞ የሰው ህይወት ሳይጠፋ፣ ብዙ መስራት፣ ማድረግ የሚችሉ ወጣቶች አካል ሳይጎድል፣ ተጨማሪ ቁርሾ እና ቂም በህበረተሰቡ መካከል ሳይፈጠር፣ አብሮነታችን ሳይላላ፣ ጥላቻ ሳይነግስ፣ ማህበራዊ ትስስራችን ሳይበጠስና ኢኮኖሚው እንዲህ ሳይንኮታኮት ማድረግ የምንችለው የበሰለ መንገድ በሆነ ነበር፡፡ ብዙ ነገሮችንም ባስቀረን ነበር፡፡ ግን ለሱ አልታደልንም፡፡ ነገር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ ብዙ ዋጋ ካስከፈለንም በኋላ ቢሆን ይሄ የድርድር እና የውይይት እድል ሳንወድ በግዳችን ከፊታችን ተደቅኗል፡፡ ይሄ መልካም የታሪክ አጋጣሚ ደግሞ የ4 ዓመቱን ቂምና ቁርሾ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት የተከማቸውንም መከራችንን ለማቃለል ይጠቅማል ብዬ እንደ አንድ ዜጋ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ መቼም ከቀደመ የተደራዳሪዎቹ የፖለቲካ ባህል እና ከገነገነው የግራ ፖለቲካ አስተሳሰብ አንፃር የድርድሩ መሳካት እድል የመነመነ እንደሆነ ብረዳም ተስፋ ካለማድረግ ተስፋ ማድረግ ይሻላል፡፡ ከባይሆንስ ይሆናል ቢባል ይመረጣል በሚል እንጥፍጣፊ ተስፋዬን ይዤ መልዕክቴን መከተቡን መርጫለሁ፡፡ ለዚህም ነው ድርድሩ እንደማይሰናከል ተስፋ በማድረግ ይድረስ ለተደራዳሪዎች በሚል መልዕክቴን ለወገኖቼ ማድረስ የፈለኩት፡፡ ወገኖቼ ይሄ የድርድር እና ጉዳዩን በሰላም የመቋጨት እድል ካመለጠን እንደ አገር መፍረስ ይሆናል እጣ ፈንታችን፡፡ እንደ ህዝብ ስደት፣ መከራ፣ ሞትና ረሃብ ነው ከፊታችን የሚጠብቀን፡፡ እድሉን በሃላፊነት ስሜት፣ በአስተዋይነትና በአርቆ አሳቢነት የምንጠቀምበት ከሆነ ግን አዲስ የድል ታሪክ የምናስመዘግብበት ወሳኝ ምዕራፍ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ያለፈውን ረስተን፣ የምንማርበትን ተምረንበት፣ ስለ ወደፊቱ እጣ ፈንታችን የምናስብ ከሆነ እንደ ሰው፣ እንደ ህዝብ እና እንደ አገር እናተርፋለን፡፡ ይሄንን እድል የምናባክን ከሆነ በታሪክ፣ በትውልድ ተወቃሽ እንሆናለን፡፡ አዳፋ ታሪካችንንም ተሸክመን እንኖራለን፡፡ የቂምና ቁርሾ፣ የጥላቻና የበቀል ሂሳብ ለማወራረድ ጉርጓድ የምንቆፍር ከሆነ በቆፈርነው ጉድጓድ ሁላችንም እንቀበራለን፡፡ ዘላቂ አሸናፊነት የሚመነጨው በበቀል ሳይሆን በይቅር ባይነት ነው፡፡በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር ነው፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ለዘመናት ስናከባልል እዚህ ያደረሰንቸው፤ ለአብሮ መኖር እንቅፋት የሆኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉብን፡፡ እነዚህን የከረሙና አላስኬድ ያሉ እንቅፋቶቻችንን አፍረጥርጠን በመነጋገር፣ በመደማመጥ፣ በመከባበር እና በመቻቻል ለመፍታት የመጨረሻ እድላችን ይሄ ነው፡፡ ድርድር እና ውይይት ብቻ፡፡ መፍትሄ ያመጣል ያልነው ጦርነት አዳዲስ ዘመን ተሻጋሪ ቅራኔዎችን ቆሰቆሰብን እንጂ የጠቀመን አንዳችም ነገር የለም፡፡ የሚለያየንን እና የሚያቃቅረንን ጉዳያችንን በሰለጠነ መንገድ ፈተን፤ እጅ ለእጅ የሚያያይዘን፣ አንድ የሚያደርገን ላይ አተኩረን፤ የጥላቻን ግንብ አፍርሰን የይቅርታ እና የፍቅር ሐውልት የምንገነባበት አዲስ መንገድ እንጀምር፡፡ ስለ ሰላም ሲወራ የሚጨንቃቸው፣ ስለ ዕርቅ ሲወራ የሚያንገፈግፋቸው ጥላቻ የገቢ ምንጫቸው፣ ጦርነት የዕለት ገቢ ማግኛቸው፣ ሰበር ዜና ሆዳቸው፣ ከተማ ተያዘ፣ ጠላት ተደመሰሰ ሃሴታቸው የሆኑ አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች፣ ዩቲበሮች በድርድር አይጠቀሙም፡፡ በጥላቻ ንግግራቸውና በሰሩት ወንጀል ነገ ተጠያቂነት ይመጣል ብለው የሚሰጉ የፖለቲካ መሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች ድርድሩ እንዳይሳካ ጉድጓድ መቆፈራቸው የማይቀር ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ምልክቶችም የድርድሩ ዜና ከተሰማበት ቀን ጀምሮ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በግልፅ እና በአደባባይ ሲቀነቀኑ እያስተዋልን ነው፡፡ እነዚህ አካላት በህዝብ ውስጥ የጥላቻ፣ የመጠራጠር፣ ተስፋን የማጨለም መርዛቸውን አዛኝ እና ተቆርቋሪ መስለው መርጨት ጀምረዋል፡፡ እነዚህ አካለት በግለሰቦች እና በቡድኖች ላይ ያላቸው ጥላቻ ከአገራቸው ጥቅም ሲበልጥ እያስተዋልን ነው፡፡ በኔ እምነት በግለሰብ እና በቡድን ላይ ያለን ጥላቻ ከአገር እና ከህዝብ ጥቅም በፍፁም የማይነፃፀር የኮፍያና ካልሲ ያህል ልዩነት ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ድርጊታቸው ለአገርና ለህዝባቸው ሲሉ ቢቆጠቡ መልካም ነው እላለሁ፡፡ ህብረተሰቡም እነዚህ ሃይሎች በሚቆሰቁሱት እሳት የሚሞቁ እንጂ የማይቃጠሉ የእሳት ዳር ፖለቲከኞች መሆናቸውን በመረዳት በቃችሁ ሊላቸው፣ ሊታገላቸው ይገባል፡፡ ወገኖቼ የሚያስብ አዕምሮ፣ የሚስተውል ልቦና ካለን እኮ ያሳለፍነው ሁለት ዓመት በቂ ትምህርት በሆነን ነበር፡፡ አሸናፊ እና ተሸናፊ በሌለው የወንድማማች ጦርነት ውስጥ ምን አተረፍን? ብለን ከደረሰብን እና ካለፍንበት ተነስተን ሂሳቡን ብናሰላ መልሱ ምንም ነው፡፡ ኪሳራ ብቻ! ጦርነቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት በብዙዎች ዘንድ እንደሚታመነው በአገራችን ዘመናዊ የመንግስትነት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የብዙ ዜጎቻችንን ህይወት የቀጠፈ፣ የብዙ ዜጎቻችንን አካል በማጉደል ነጋቸውን የነጠቀ፣ የአገራችንን ኢኮኖሚ ቢያንስ ለ20 እና ለ30 ዓመት ወደ ኋላ የመለሰ፣ ዜጎችን ለስደት፣ ለርሃብ፣ ለእርዛት ያጋለጠ፣ ማህበራዊ ትስስሮቻችንን ያላላ፣ አንድነታችንን አደጋ ውስጥ የከተተ፣ የሞራል ልዕልናችንን ገደል የከተተ፣ ሃይማኖታዊ እሴቶቻችንን ያሳጣ፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት፣ የመቻቻል አኩሪ ባህላችንን ያቀጨጨ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ያተረፈልን አንዳችም ነገር የለም፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው አገራችንን ከፍተኛ የህልውና ስጋት ውስጥ ከቷታል፡፡ ወገኖቼ ከዚህ በላይ ኪሳራ፣ ከዚህ በላይ መዓት፣ ከዚህ በላይ አገራዊ ውርደት ምን ይምጣብን? ዜጎች ነጋቸውን እንዲፈሩ፣ አገር እያላቸው በአገራቸው ተስፋ እንዲቆርጡ ሆነዋል፡፡ ወጥቶ መግባት፣ ሰርቶ ማትረፍ፣ ስለ ነገ ማሰብ የማንችልበት ሁኔታ ውስጥ ገብተናል፡፡ ለቅሶ፣ ዋይታ፣ ሰቆቃ መስማት የዕለት ተዕለት ምሳችን ሆኗል፡፡ በክብር ሞቶ በክብር መቀበር ብርቅ ሆኗል፡፡ ገዳዮቹን ከማውገዝ ይልቅ በሟቾቹ ቁጥር እና ብሄራቸው ላይ መወዛገብ እና መጨቃጨቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባራችን ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ግፍን፣ በደልን፣ ፍትህ መጓደልን በጋራ ከማውገዝ ይልቅ ጎራ ለይተን መነታረክ ስራችን ሆኗል፡፡ ወገኖቼ ይሄ የደረስንበት የሞራል ዝቅጠት ማብቃት አለበት፡፡ እንደታሪካችን፣ እንደቀደመ ክብራችን፣ እንደሚመጥነን እንኑር፡፡ ወደ ክብራችን እና ወደ ከፍታችን እንመለስ፡፡ ይሄን ማድረግ የምንችለው ደግሞ እንደ ሰለጠነ ህዝብ እና እንደ ኩሩ ህዝብ ማሰብ ስንችል ነው፡፡እንደለመድነው የሚገጥሙንን ፈተናዎች በጉልበት እና በጦርነት ለመፍታት በመሞከር ሳይሆን በድርድር እና በውይይት መፍታት ስንጀምር ነው፡፡ አሁን አዲስ ችግርን በድርድር እና በውይይት የመፍታት የፖለቲካ ባህል እንጀምር፡፡ ሄደንበት በማናውቀው የለውጥ መንገድ ውስጥ እንግባ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
"እስከማውቀው ድረስ የሕወሓት ወዳጅ ብቻ ሳይሆን አሽከርና ተላላኪ ሆነው የኖሩት የወቅቱ የብልጽግና ፓርቲ መሪዎች ናቸው ዛሬም የሻዕቢያ አሽከር ለመሆን የበቁት በዚያው ልማዳቸው ነው፡፡ ልደቱ አያሌው --- ከሁለት ቀን በፊት ያሰራጨሁትን መጣጥፍ በተመለከተ በተለምዶ “ማህበራዊ አንቂዎች” ተብለው የሚጠሩ፣ እኔ ግን “ማህበራዊ አደንቋሪዎች” ብዬ የምጠራቸው የብሌጽግና ፓርቲ ካድሬዎች የፈጠራ አሉባልታ ዘመቻ ከፍተውብኛል፡፡ እነዚህን ሆን-ብለው የሚያጠፉ ማህበራዊ አደንቋሪዎች ምንም ዓይነት መልስም ሆነ ማስተባበያ በመስጠት ማስረዳትም ሆነ ማሳመን እንደማይቻል ባውቅም እነርሱን በማድመጥ አንዳንድ የዋህ ዜጎች ሊወናበዱ ይችላሉ ብዬ በመገመት ይህንን አጭር ማስተባበያ ለመስጠት እፈልጋለሁ፡፡ በመጣጥፌ ላይ ያስተላለፍኳቸው መልዕክቶች በዋናነት ሶስት ናቸው፡፡ እነርሱም - 1. “ችግራችን በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንጂ በጦርነት ሊፈታ ስለማይችል በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን ህይወት እያሳጣን ያለው የወቅቱ አውዳሚ ጦርነት ተገዳድለን ከማለቃችን በፊት በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ 2. “በጦርነቱ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላትና የውጪ ኃይል የሆነው የሻዕቢያ ሰራዊት ቀጥተኛ ጣልቃ-ገብነትና ወረራ በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ 3. “በጉርብትና፣ በባህል፣ በታሪክና በማንነት ተጋምዶ የኖረው የአማራና የትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ከጦርነትና ከፍጥጫ ወጥቶ ወደ ሰላማዊ ግንኙነት መሸጋገር አለበት” የሚሉ ናቸው፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ካድሬዎች የሆኑ የማህበራዊ አደንቋሪዎች ለእነዚህ የእኔ ግልፅ አመለካከቶችና አቋሞች ምክንያታዊ የሆነ ትችት የማቅረብ አቅም ስላላገኙ ያልተባለን ጉዳይ እንደተባለ አድርገው በማቅረብ በእኔ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድን መርጠዋል፡፡ ብዙውን እንቶ-ፈንቶ ወደጎን ትቼ ዋና መልዕክታቸውን ለመረዳት እንደሞከርኩት ማህበራዊ አድንቋሪዎቹ በጥቅሉ ሊያሰራጩት የፈለጉት አሉባልታ “ልደቱ ሕወሓትን እንደግፍ አለ” የሚል ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ሆኖም በሰሞኑ ፅሁፌም ሆነ በማንኛውም ሌላ ጊዜ “ሕወሓትን እንደግፍ” የሚል ሃሳብ በእኔ በኩል ቀርቦ አያውቅም፡፡ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት የማልደግፍ እስከሆነ ድረስም በዚህ ጦርነት ሕወሓትንም ሆነ ብልጽግና ፓርቲን ለይቼ ልደግፍ እንደማልችል ግልፅ ነው፡፡ ስለሆነም የአሉባልታ ዘመቻ ከማካሄድ ይልቅ ከእኔ አቋም በተጻራሪ “የወቅቱ አውዳሚ ጦርነት መቀጠል አለበት”፣ “የሻዕቢያ ሰራዊት ቀጥተኛ ድጋፍና ጣልቃ-ገብነትም ሕጋዊና ጠቃሚ ነው”፣ “የአማራና የትግራይ ሕዝብም ሰላማዊ ግንኙነት መፍጠር አያስፈልጋቸውም” ብሎ በድፍረት ለመከራከር የሚፈልግ የመንግሥት ወይም የፓርቲ አመራር ካለ በእኔ በኩል በግልፅ መድረክ ተገኝቸ ለማስረዳትም ሆነ ለመረዳት ወይም ለማሳመንም ሆነ ለማመን ፍላጎት ያለኝ መሆኑን እየገለፅኩ በዚህ አጋጣሚም ግብዣዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሊሰራጭ የተሞከረው አሉባልታ “ልደቱ ይህንን ሃሳብ ያቀረበው ሕወሓት ሊሸነፍ ስለሆነ ነው” የሚል ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እንደዚህ ዓይነት ትችት በእኔ ላይ እያቀረቡ ከሚገኙት የብልጽግና ካድሬዎች በላይ ለ28 ዓመታት ሕወሓትን በምክንያትና በሰላማዊ መንገድ ስታገል የኖርኩ ሰው በመሆኔ ማንም እኔን በሕወሓት ወዳጅነት የመክሰስ የሞራል ብቃት የለውም፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ የሕወሓት ወዳጅ ብቻ ሳይሆን አሽከርና ተላላኪ ሆነው የኖሩት የወቅቱ የብልጽግና ፓርቲ መሪዎች ናቸው፡፡ ዛሬም የሻዕቢያ አሽከር ለመሆን የበቁት በዚያው ልማዳቸው ነው፡፡ ሲቀጥልም እኔ ስለሰላም ያለኝ ሃሳብ ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረ ነው፡፡ የወቅቱ ጦርነት ከተጀመረ በኋላም “ጦርነት መቆም አለበት” የሚለውን አቋሜን ሕወሓት ተንቤንም፣ መቀሌም፣ ጣርማ-በርም በነበረበት ወቅት ሳራምደው የነበረ ነው፡፡ እንዲያውም የእኔን አቋም በአግባቡ የሚከታተል ሰው ሊረዳው እንደሚችለው ከዓመት በፊት ያልተናገርኩትና በአሁኑ ፅሁፌ ላይ የተገለፀ ምንም ዓይነት አዲስ ሃሳብ የለም፡፡ የወቅቱን ጦርነትም የትኛውም አካል በዘላቂነት ሊያሸንፍ ይችላል የሚል እምነት ስለሌለኝ “ጦርነት ይቁም” የሚል አቋም የማራምደው የወታደራዊ የኃይል ሚዛን አይቼ እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የእኔ ወገንተኝነትም ለጦረኛ ፓርቲዎች ሳይሆን በጦርነቱ ምክንያት ያለ-አበሳው እያለቀ ላለው ወጣት ትውልድ፣ እየተፈናቀለና በየዕለቱ በድህነት አረንቋ ውስጥ እየተዘፈቀ ላለው ሕዝብ እና በግልብ ፖለቲከኞች የአመራር ድክመት ህልውናዋን እያጣች ላለቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ ነው፡፡ ችግሩ የብልጽግና ካድሬዎች በጥላቻና በመርህ መካከል ያለውን መሰረታዊ ልዩነት ስለማይረዱት ምክንያታዊ ፖለቲካ ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዱት መሞከር ከንቱ ድካም ነው፡፡ በአጠቃላይ - ‘ለትግራይ ሕዝብ’ የተቆረቆረ ሁሉ ‘ሕወሓት’ በሚመስላቸው ዘረኛ የብልጽግና ፓርቲ ካድሬዎች እየተሰራጨ ያለው አሉባልታ እንደተለመደው ከእውነት የራቀ የስም ማጥፋት ዘመቻ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ በሀገራችን የጥላቻ ፖለቲካ እንዲነግሥና ወደዚህ ዓይነቱ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ እንድንገባ ካደረጉን ምክንያቶች ውስጥም እነዚህ ማህበራዊ አደንቋሪዎች አንዳንድ ጊዜ እየፈጠሩ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እያጋነኑ ወይም እያዛቡ የሚያሰራጩት ሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ ስለሆነ ህብረተሰቡ የዚህ እኩይ ተግባር ሰለባ ከመሆን እንዲቆጠብ፣ ኃላፊነት የሚሰማችሁ መገናኛ ብዙኀንም የጥላቻና የሀሰት መረጃ ለሕዝብ የሚያሰራጩ አካላትን በማጋለጥ ሞያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ ልደቱ አያሌው መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...