cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የኢትዮጰያ ታሪክ

ኢትዮጵያ ባለብዙ ጥበቦች፣ ባህሎችና ቋንቋዎች ባለቤት ህዝብ መገኛ ስትሆን ፤ ታሪኳ በሳይንሱ ከሚሊዮን ዓመታት በፊት ከሉሲ ሲጀምር በሀይማኖቱ ደሞ ከ7ሺ ዓመታት በፊት ከአዳም ከዛም ከጥፋት ውሃ በኋላ ደሞ ከ5ሺ ዓመታት በፊት ከኖህ እንደምትጀምር ተጨባጭ ማስረጃዎች ያትታሉ። ይህ የቴሌግራም ቻናል የሀገራችንን ታሪክ፣ ባህልና ጥንታዊ ጥበቦች ለናንተ ያካፍላል።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
660
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+137 kunlar
+4230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

⛰አለም ላይ ካሉ ሚስጥራዊ ቦታወች አንዱ እና ዋናው ኤረር(የረር)። ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል እንደሚገኝ የሚነገረው እጅግ ሚስጥራዊው ኤረር ተራራ በጥቅሉ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ቦታ እንደሆነ ድርሳናት ይናገራሉ። በእርግጥ ከዚህ ከፍ ብሎም ኤረር ተራራ የአዳም ርስት ሀገር ማዕከላዊ ቦታም እንደሆነ ይነገርለታል። ኢትዮጵያ የአዳም ርስት ሀገር በምንለው ምድር ወስጥ የምትገኝ እንደመሆኗ በአዳም ርስት ሀገር አሉ ተብለው ከሚነሱ ሰባት ታላላቅ ስፍራዎች መካካል ሶስቱ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። እነዚህ ስፍራዎች የጥንታዊ ኢትዮጵያ ስልጣኔ መውጫ ለሆነው መንፈሳዊ ክፍል እንደ ማዕከል የሚያገለግሉ ነበሩ። ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች መካካል የመጀመሪያው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲገኝ ሁለተኛው ምስራቁ የሀገራችን ክፍል ላይ የሚገኝ ሆኖ ሶስተኛው በመካከለኛው ኢትዮጵያ ላይ የሚገኝ መለኮታው ሃይል ያላቸው ቦታቸወች ናቸው ። እንግዲህ ኤረር ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች አንዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የሁሉም ማዕከላዊ ቦታ ነው። ስለ ኤረር ተራራ በርካታ ንግርቶች (Myths) ይነገራሉ። ሆኖም ከእነዚህ ንግርቶች መካካል ትልቁን ስፍራ የሚይዘው አዳም ከገነት ሲመለስ ስድስቱን የክብር ዕቃዎች ከኤረር ማዕከላዊ ስፍራ አስቀምጦታል የሚለው ነው። ይህ በኤረር ተራራ ላይ የምናገኘው ማእከላዊ ስፍራ በተራራው መካካል ላይ የጉልላት ቅርጽ ይዞ ይታያል። ከዚህም ስፍራ አሁንም በርካታ መንፋሳዊ ሰዎች በስውር ይኖራሉ ። በዚህ ስፍራ እንዚህን በርካታ የሆኑ መንፈሳዊ ሰዎችን ያሰባሰባቸው ይህ ማዕከላዊ የሆነው ስፍራ ነው። በዚህ ስፍራ ላይ በግልጽ እንዲሁም በስውር ኢትዮጵያኖች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ መንፋሳዊ ሰዎች ከአለም ዳርቻ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተሰባስበው ይገኛሉ። ንግርቱ(Myth) እንደሚለው እውነት አዳም ይዟቸው የመጣው ስድስቱ የክብር ዕቃዎች እዚህ ይሆን የሚገኙት? ይህንን ጥያቄ ይህ ትውልድ ሊጠይቀው እና እውነቱን አነፍንፎ ሊያገኝ የሚጋባ ነው። የዚህ ሚስጥራዊ ኤረር ተራሮችን ለማወቅ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ህንጻ አሰራር ማወቅ የግድ ይላል፤ በዚህም መሰረት የህንጻ ቤተክርስቲያናችንን ተምሳሌታዊ አወቃቀር ይዘን ኤረር ተራሮች ላይ ስንሄድ ተራራው ሁለት ክፍሎችን ይዞ እናገኘዋለን፤ የመጀመሪያው ክፍል ከተራራው በላይ የሚገኘውና በአይን ሊታይ የሚችለው በሥጋ ባህሪ የሚመሰለው ክፍል ነው፤ ሁለተኛው የተራራው ክፍል የውስጠኛው ስውር ከተማ ሲሆን ይሄውም በነፍስ ባህሪ የሚወከልው ነው፤ ወደዚህ ወደ ሁለተኛው ወይንም ወደ ውስጠኛው የተራራው ክፍል ለመግባትም ልክ እንደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ ሦስት በሮችን ይዟል፤ የመጀመሪያው በር በምስራቁ አቅጣጫ የሚገኘውና ከተራራው በላይም የቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን የሚገኝበት በር ነው፤ ሁለተኛው በሰሜናዊው የተራራው አቅጣጫ የሚገኘውና ከበላዩም በደን የተሸፈነው እንዲሁም የባህታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሚገኝበት ሲሆን ሦስተኛውና የመጨረሻው በር በደቡባዊው አቅጣጫ በኮራ ማርያም ቤተክርስቲያን በኩል ይገኛል። ወደዚህ ስውር ከተማ በምስራቁ በር ከብሔረ ህያዋን ብሎም በምድር የበቁ ታላላቅ አባቶቻችን የሚጠቀሙበት በር ሲሆን የሰሜናዊውን በር ወንድ ነገስታት እስከ አሥራ ሦስተኛው ክ/ዘመን ድረስ ሲጠቀሙበት ኖረዋል፤ ይህንን በር ለዘመናት ሲናፈቅ የኖረውና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀውና የገዢነት ክብሩን ይዞ የተወለደው ካህኑ ንጉሥ ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ዳግም ይጠቀምበታል ተብሎም ይነገራል ፤ ሦስተኛውን በር እና በደቡባዊው አቅጣጫ በኩል የሚገኘውን በር ሴት ነገስታት ሲጠቀሙበት እንደኖሩ ። ይሄንን አቀማመጥ ወደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን ስናመጣውም በምስራቁ በር ካህናት በሰሜኑ በር ወንድ ምዕመናን እንዲሁም በደቡቡ በር ሴት እና እናት ምዕመናን እንደሚጠቀሙበት ያሳያል። በዚህ ታምረኛ ኤረር ተራራ ውስጥ ከ 300 በላይ የሚሆኑ ዋሻወች እንዳሉና ከመላው አለም የመጡ ቅዱሳን መነኮሳት እግዚአብሄርን እያመሰገኑ እንደሚኖሩበት ይታመናል፡፡ በአለም ካሉት 7 ቱ ሚስጥራዊ ቦታወች 3 ቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እነደሚገኙ ከሶስቱ አነዱም ኤረር ተራራ እንደሆን አየን፡፡ በሰሜን እና በምስራቅ የኢትዮጵያ ክፋል የሚገኙት የፈጣሪ ሚስጥራዊ ከተሞች እነማን ይሆኑ ?? በውስጣቸውስ ምን ምን የረቀቁ ሚስጥራትን ተሸክመው ይሆን? ... @felegetibebat
Hammasini ko'rsatish...
የጥንት ኢትዮጵያያ x-ray ህክምና በጨለማ የሚያበሩ ኪነ - ህንፃ ግንባታ 🦆 ስለ ምታበራዋ ሙሴ ወፍ 💎ስለ ብርቁ የከበረ መዓድን መድኃኒትነት ✦የጥንት ኢትዮጵያያን አምፖል(ዲም ላይት) መብራት ከመሰራቱ አስቀድሞ አብያተ ክርስቲያናን እንዲሁም ቤተ መንግስት ሲገነቡ ብርቁ ወይም ብርቅርቅ የሚባል የብርሀን ሀይል ማመንጨት ድንጋይ ይጠቀሙ ነበር።ይህ የከበረ መዓድን ሌሊት አአንዳንድ ግዜ የሚያበራ ደግሞም የሚጠፋ ድንጋይ ነው።ከዋሻ ውስጥ ወይም ከባሐር ዳር ላይ ይገኛል።እሱ በአለበት ዋሻ ውስጥ እንደ እሳት ላንቃ የመሰለ ብርሀን ይታያል።መልኩም በመዓልት ቢጫ አረንጓዴ ነው።ተወቅሮ ኪነ - ህንፃ ከተሰራበት ደግሞ ሌሊት ላይ ህንፃው ያበራል። ✦ መብረቅ ብዙ ጊዜ ይመታዋል ፣ ይሰነጥቀዋል ፣ ጭራ የመሰለ ይታይበታል።ብርቅ የምትባል አውሬ ተጠግታ ልጅ ትወልድበታለች።ማነኛውም አውሬ መጥቶ ልጅዋን አይበላውም : ልጁም እስኪያድግ ከድንጋዮ ስር አይጠፋም።አንዳንድ ጊዜም ውስጡ የተከፈተ ይገኛል።አንድ ሰው በውስጡ ገብቶ ቢተኛበት መብራቱ ሲበራ ማነኛውም የውስጥ የሰውነት ክፍሎችን(የሆድ እቃ) በሙሉ ማየት ያስችላል።ልክ በመስታውት ፊት ቁመን ከራስ ፀጉራችን እስከ እግር ጥፍራችን እንደምናየው ሁሉን አጥርቶ ያሳያል።ከደዌ ከህመምም ይፈውሳል።አራዊትም ሲታመሙ ከስሩ ሂደው ይተኛሉ ፣ ይድናሉ።በአሁን ጊዜ X- ray ብለን የምንጠቀመው ቴክኖሎጅ የጥንት አባቶቻችን በዚህ መንገድ ይገለገሉበት ነበር። ✦ እንደ ሰጎን ቁመታም የሆነች ሙሴ (thunderbird) የምትባል ወፍ አንዳንድ ጊዜ እንቁላል ትጥልበታለች።ድንጋዮን እየወቀረች በእንቁላሉ ላይ ትረጭበታለች : የታቀፈችበት እግሩዋ ፍህም ይመስላል: ከእርሱ ስር የተፈለፈለ ጫጩት ሆዱ እግሩ ያበራል።"በሊሃልም በናትሲ ሱሲ ተቀናሂም ሮሜማላ ቦሃቢ ባህፍዊ በሐተዊ መብራቂል መብረቅ ዝውእቱ ማህረጽየ ወመሐሯልየ " ብለህ እየፀለይህ የመታኸው እንደሆነ ይሰበራል፣ ይደቃልም። ✦ እኒህን እና ስለ ሌሎች የከበሩ መዓድናት የሚያብራሩ 'ኁልቆ አእባን፣መጽሐፈ አዕባን ፣ ምስጢረ አዕባን...' የተሰኙ የብራና መፃሕፍ በማህፀነ ለምለሟ የኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥ ይገኛሉ።ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እፁብ ድንቅ የከበሩ መዓድናት ባህሪያቸውን ፣ መገኛ ቦታቸውን ፣ እንዲሁም ጠቀሜታቸውን የሚያስረዳ መፃሕፍ መሪ ራስ አማን በላይ <ጥበበ ዕንቆ አእባን> በሚል ርዕስ 'ዜና አበውና ኁልቆ አእባን' ተርጉመውታል። #ደሸት
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
መርበብት_compressed.pdf52.14 MB
ስለ ኢትዮጵያ ጠበብት አባቶችና ድንቅ ድንቅ ገዳማት እውቀቶን ማስፋት ከፈለጉ እኒህን ሶስት የዶክተር አለማየሁ ዋሴ መፅሐፍት ያንብቧቸው። መሳጭና አጓጊ በሆነ አቀራረብ የተፃፉ ድንቅ ቅርሶች ናቸው
Hammasini ko'rsatish...
እመጓ ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ 2007 ዓ.ም.pdf56.70 MB
ዝጎራ.pdf31.91 MB
🇪🇹ጦርነትን ሳይሆን የፍቅርን አስፈላጊነት በተግባር ያስተማረ ኢትዮጵያዊው ንጉስ ሐንዲው አብራ ንጉስ ሐንዲው አብራ (532-521 ቅ.ል.ክ) ኢትዮጵያን በሚአስተዳድርበት ወቅት 31 ግዛቶችን ያስገበሩት ሃያላኑ ፋርሶች በኢትዮጵያ ግዛት ስር የምትገኝውን 'ፊላዬ' የተባለች ወርቅና መዕድን የሚገኝባት ከተማ በእጃቸው አስገብተው ነበርና ኢትዮጵያዊው ንጉስ የፋርስ ወታደሮችን አባሮ ከተማዋን አስለቀቀ። በፋርስ የተሾመው የግብፅ ንጉስ አርአንዲስም ይህን ሲሰማ በፋርስ ስር ካሉ ሀገራት(ግብፅ፣ ሜዶን፣ ሊቢያና ሌሎች) የተወጣጡ ሃያል ወታደሮቹን ይዞ ከቴብ ከተማ ተነስቶ መጣ። ኢትየጵያውያኑም ወደዚያ ሂደው ከፍተኛና እልህ አስጨራሽ በብልሃት የተሞላ ፍልሚያ በማድረግ ሃያላኑን ፋርሶች ድል አርገው ንጉስ አርአንዴስን ማረኩ። ኢትዮጲያዊው ንጉሥ ሐንዲው አብራምም የተማረከውን ንጉስ ቁስል እንዲታከማ ካረገ በኋላ እንዲህ አለው "እኔ በአባይ የተከለለው የጥንቱ ሀገሬ ይበቃኛል፤ ፍርድንና ህግንም ለማክበር ስል አንተንም በነፃነት ለቅቄሀለሁ። ነገር ግን ለወደፊቱ ከወሰንህ አትለፍ። ለፋርሱ ንጉስም እንዲህ ብለህ ፃፍለት፤ ንጉስ ሐንዲው ድል አርጎኛል ነገር ግን የራስህን አገር መልሶ ለቆለሃል። ይህንንም ማድረጉ ወዳጅነትህን ፈልጎ ነው። ምክንያቱም ፍቅር ለሠው ልጅ ከእንቁ የበለጠ ነገር ነውና። ይሁን እንጂ በጦር ከመጣህ ለመዋጋት ወደኋላ አልልም።" 👉 እንግዲህ ንጉስ ሐንዲው አብራ በዘመኑ በቅን ፍርድ የሚታወቅና የጦርነትን ሳይሆን የፍቅርን አስፈላጊነት ያስተማረ ታላቅ ኢትዮጵያዊ መሪ ነበር።
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 2
🙏 ዓለም ዛሬ ድረስ ለመስራት አደለም የጥበብ ሚስጥሩን መርምራ ልትደርስበት ያልቻለችው የላሊበላ ፍልፍል፤ በኢትዮጵያ እጆች በኛ ዘመን ዳግም ተገነቡ!! “ጥበቡ የፈጣሪ ነው፤እኔ የእርሱ መሣሪያ ነኝ”       ሐናፂው አባ ገ/መስቀል ተሰማ። 11ዱ ፍልፍል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ ጎልተው ይታወቃሉ፡፡ አብያተ ክርስቲያኑ፣ በጠቢባን እጆች የተሠሩት በ12ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ የእኒያ ጠቢባን እጆች ሥራቸውን ቀጥለውበታል፤ ዛሬም ዐዲስ አብያተ ክርስቲያን በሀገራችን ጠቢባን እጅ እየተፈለፈሉ ናቸው፡፡ በምስሉ ላይ የሚታዩት አባ ገብረ መስቀል ተሰማ ይባላሉ፤ ዐዲስ ሕንፃ አብያተ ክርስቲያን ከወጥ አለት በመፈልፈል ላይ ይገኛሉ። ዓለም አቀፍ ሚዲያ የኾነው ቢቢሲ፣ “በዩኔስኮ የተመዘገቡ የቅርስ ሥፍራዎችና የብዙኃን ጎብኚዎች መዳረሻ የኾኑት ኢትዮጵያውያን፣ ከ800 ዓመት በፊት የሠሩትን ታሪክ በራሳቸው እጅ ደግመውታል፤” የሚል ሐሳብ ያለውን ዘገባ አውጥቷል፡ “ዳግማዊ ላሊበላ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው አብያተ ክርስቲያኑ፣ በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ከጋሸና ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ለላሊበላ ከተማ ቀረብ ባለ ሥፍራ ነው እየታነፁ ያሉት፡፡ አባ ገብረ መስቀል እስከ አኹን፣ አራት ፍልፍል አብያተ መቅደስን ከወጥ አለት አንፀው ጨርሰዋል፤ ሌሎችንም በማነፅ ላይ ናቸው፡፡ በሥራቸው ግን፣ ዘመናዊ መሣሪያን አይጠቀሙም፤ የምሕንድስና ትምህርትም አያውቁም፤ ግን ሠርተውታል፡፡ አይታችሁ ተገረሙ!! 👉 ትላንት "ላሊበላን ፖርቹጋላዊያን ነው ያነፁት" ፣ "ላሊበላ በህዳውያን እጅ ነው የተገነባ" ፣ "ግብፃውያኑ የሰሩት ነው" ...እያሉ ታሪክን ሲመርዙ የኖሩ ምላሶች ዛሬ ምን ይሉ ይሆን? 🙏 ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን ማለት ይሄ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
#ፈጠራና_ለዉጥ_በኢትዮጵያ_ከጥንት_ጀምሮ_እስከ_1930ዎቹ በኢትዮጵያ ከጥንት እስከዛሬ የተለያዩ የፈጠራ ሥራ ሙከራዎችና የሥልጣኔ አሻራዎች ታይተዋል። የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት እኝህን የለውጥና የሥልጣኔ ጮራዎች፣ በተለይም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ 1930ዎቹ የታዩትን በታሪክ መዝገብ ሰንደው አኑረውልናል። እኛም ለናንተ ለተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን በሚመች መልኩ እንዲህ ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰን አሰናድተናል። መልካም ንባብ! የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ መልክዓ-ምድር እና በተራሮች የተከበበች አገር መሆኗ አውሮፓዊያን አፍሪካን በተቀራመቱበት ዘመን (scramble for Africa) ነጻነቷን ጠብቃ ለረዥም ዘመናት እንድትኖር ረድቷታል። የዚህች አገር በቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንቆቅልሽ የሆነበት Daniel Thwaite የተባለ ጸሀፊ The Seething African Pot: A Study of Black Nationalism, 1882-1935 በተሰኘ መጽሀፉ ስለኢትዮጵያ ክብር እንዲህ ይላል፤ ይች የአፍሪካ ትንሳኤ ተምሳሌት ፣ የጥቁር ትግል አይበገሬነት ህያው ማሳያ ሲል ይህ ደራሲ የገለጻት አገራችን ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የሄደችበት የታሪክ መንገድ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የተለየ ነው። ይህም መሆኑ አገሪቱ በታሪኳ ያለፈችበት የፈጠራና ለውጥ (innovation and change) ሂደት የራሱ የሆነ አሉታዊም አውንታዊም ገጽታ እንዲኖረው አድርጎታል። #ጥንታዊ_አክሱም ይህ ዘመን በኢትዮጵያ የፈጠራና ለውጥ ታሪክ ውስጥ ወርቃማው ዘመን ነበር ሊባል ይችላል። በስነ-ህንጻው ዘርፍ የአክሱም ሀውልት በዘመኑ ኢትዮጵያዊያን የነበሩበትን የስነ-ህንጻ ደረጃ ሲያመላክት፣ በዘመኑ የነበረው የጽሁፍና የቋንቋ እድገት፣ በገንዘብ የመገበያየት ሥልጣኔ፣ ወዘተ የዘመኑን የእድገት ደረጃ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያ ለውጭው ዓለም እውቀትና ጥበብ በሯን የዘጋች አልነበረችም። ለዚህ እንደማሳያ በክብረ ነገሥት ላይ የሰፈረውን የንግሥት ሳባንና የንጉሥ ሰለሞንን ታሪክ ማንሳት ይቻላል። በዚህ ታሪክ ውስጥ ንግሥተ ሳባ ስለ ሰለሞን ጥበብ ሰምታ ለጥበብ ካላት ታላቅ ፍላጎት የተነሳ እየሩሳሌም ድረስ ተጉዛ ከንጉሥ ሰለሞን መገናኘቷን እናያለን። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ዞስካለስ ዓይነቱ የአክሱም ነገሥታት የግሪክን ስነ-ጽሁፍ ጠንቅቀው ያውቁ እንደነበር በታሪክ ድርሳናት ተጽፎ እናገኛለን። ከዚህም በተጨማሪ የግሪክ ፊደላት በአክሱማዊያን ሳንቲሞች ላይ ታትመው ይታዩ ነበር። በአክሱማዊያን ኪነ-ህንጻ ላይም የግሪክ አማልክት የሆኑት ዜዉስ፣አሬስ እና ፖሴይዶን ተቀርጸው ይታያሉ። በሀይማኖቱ ረገድ በአክሱም ዘመነ መንግሥት የታዩትን ለውጦች ስንመለከት፣ የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያዊያን በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንጉሥ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ክርስትናን መቀበላቸውን በኋላም ከአረቡ አለም ለተሰደዱ መስሊሞች አምባ መጠጊያ መሆናቸውን ታሪክ ይነግረናል። በዚህ ጊዜ የአክሱም ንጉሥ የነበረው ንጉሥ አርማህ፣ እሱን ተማምነው የመጡትን የነብዪ መሐመድ ተከታዮች ከሳሾቻቸው አሳልፎ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁት…..” የወርቅ ተራራ ብትሰጡኝ እንኳን እንኚህን ሰዎች አሳልፌ አልሰጣችሁም”። ነበር ያላቸው። ንጉሥ አርማህ …..”የወርቅ ተራራ ብትሰጡኝ እንኳን እንኚህን ሰዎች አሳልፌ አልሰጣችሁም”። #የአክሱማዊያን_የንግድ_ግንኙነት የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ አገራት መካከል ግንባር ቀደም ነበረች። ለጊዜውም ቢሆን ደቡብ አረቢያን ተቆጣጥረው የነበሩት አክሱማዊያን በታላላቆቹ ኢምፓየሮች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጥያቄዎችን ያስተናግዱ ነበር። በዚህም ምክንያት በንግዱ ዘርፍ ከግብጽ፣ኑቢያ፣አረቢያ፣ ፐርሺያና ህንድ ግንኙነት የነበራቸው አክሱማዊያን መርከቦቻቸው ቀይ ባህርን እና የህንድ ውቂያኖስን አቋርጠው ሩቅ ተጓዦች ነበሩ። በቀጣይ ክፍል የመካከለኛውን ዘመን ኢትዮጵያ የፈጠራና የለውጥ ታሪክ እንቃኛለን።
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.