cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የብዕር ወዳጆች✍✍✍

በዚህ channel ላይ ግጥም ልብ ወለድ አስገራሚ እዉነታወች ፍልስፍናና ወጎች እንዲሁም አባባሎችን ያገኙበታል ሀሳብና አስተያየት @Jemal15219ላይ ይላኩልን @jemthelast

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
189
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
#የምስራች #እንኳን_ደስ_አለን የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ተኛ ዙር ሙሌት ተጠናቆ ውሀው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል። ግድቡ ራሱን አስታጥቆ ለወዳጅ የምስራች ለጠላትም መርዶን አሰምቷል። #GERD #Ethiopia 💚💛❤️ @yegtm @yegtm
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
መለየት አቃተን - ብስሉን ከጥሬ ያንድነት ቅኝቱ - ጠፍቶባት ሀገሬ እንብላው... እንብላው... ሆኖ በየፊናው፥ እየተቧደኑ በጎራው፣ በደኑ ጊዜ የጣለውና - ጊዜ ያነሳው ሁሉ እምዬን ኢትዮጵያን - ያምሷታል አሉ፤ አንተ እንዲህ - እኛ እንዲህ ሂድ ወዲያ - ልሂድ ወዲህ አንደራረስም - አበቃ ከ'ንግዲህ፥ እየተባባሉ... እየተማማሉ... ፍቅርን እየጣሉ ለጠብ የቸኮሉ ስንቱን አንገት ቀሉ ሥጋና ነብስ በሉ መለየት አቃተን - መጥፎውን ከጥሩ የአንድነት ቅኝቱ - ጠፍቶብን ባገሩ! ከ-አለመኖር/አለማወቅ ሐምሌ-26/2014
Hammasini ko'rsatish...
📢 ይድረስ ለግሬዶች 😂 📚 A የሩቅ ሀገር ሰው ነሽ እንዴት ነሽ ዘመዴ፤ ኧረ ተይ ጠይቂኝ ብቅ ብለሽ አንዳንዴ። አንቺ ኩሩ ዘመድ የኔ ዘመናይ፤ እንደ እንደ አደይ አበባ በአመት አንድ ጊዜ ብቅ አትይም ወይ። ሀገርሽ ሩቅ ነው መንገዱ ጉራጉር በቶሎ አይደረስ፤ እድሌ ተሳክቶ ምነው አንድጊዜ አይቼሽ ብመለስ። ወይልብሽ አይራራ አንድ ቀን እንደሰው፤ ይብላኝልሽ ላንቺ ስፈልግሽ ኑሬ አንዴም ሳላገኝሽ እኔስ መሄዴ ነው። 📚 B የኔዋ ሽቅርቅር የኔዋ ፈልሳሳ፤ ብቅ ጥልቅ እያልሽ ጎበኘሽኝ እሳ። ወይ በብዙ መጥተሽ ቤቴን አልሞላሽው ፤ ሄድ መጣ እያልሽ ልቤን አሳሳሽው፤ ጉልበቴን አድክመሽ ውስጤን አሳመምሽው። 📚 C የመኖሬ ሚስጥር ልዩ ስጦታዬ ፤ እጥፍ ድርብ ሁነሽ ነይልኝ ሽታዬ ፤ አንቺ ብቻ እኮነሽ የኔ መከታዬ። በትንሽ ተፍተፍ በትንሽ ፉጨራ፤ ደከመብኝ ብለሽ ሆድሽ እየራራ። የኔ ምስኪን አዛኝ ትመጫለሽ ቢሉኝ፤ አንድም ቀን ሳላስብ ሁልጊዜ ተኛሁኝ። ጊዜም አትሻሚ እንቅልፍም አትነሺ ሁሉን አስከባሪ፤ እኔን እንዳይከፋኝ ሺህ ሁነሽ ነይና ደስታን አብስሪ። የኔ ዲሞክራቲክ የኔ ሚዛናዊ ሁልጊዘም ነይልኝ፤ እኔስ መሄዴ ነው አንቺን እንዳይከፋሽ ዘላለም ኑሪልኝ። 📚 D ከተቀመጥኩበት ፈልገህ አታጣኝ ፤ ምናለ አንዳንዴ እንኳን ፊትህን ብትነሳኝ። አንተ የኔ ጀግና የኔ ልበ-ሙሉ፤ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ነህ አሉ። 📚 F የኔ አዶልፍ ሒትለር የኔ ሙሶሎኒ ምንኛ አስመረርከኝ፤ እኔ ምን አልኩና ሕይወቴን ለማጥፋት ቁማር ቆመርክብኝ። ስራህ እንደ ሒትለር አንጀትህ አይራራ፤ ከመጣህ ላትሄድ ቢወድቁ ቢነሱ ቢያለቅሱ በተራ። እንዳንተ አይነት ጨካኝ እንዳንተ አይነት ክፉ፤ ከየትም አይገኝ ቢለፉ ቢለፉ። አንተም እኔን ሰደህ ደስታን ካገኘህ፤ ይብላኝ ለከራሚ እኔስ ሄድኩልህ። @resinhun @Jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
"እውነቱን ተናገር" "ሁል ጊዜም እውነትን ከተናገርክ ከሦሥት ወር በፊት ምን ነበር ያልኩት ብለህ ሌላ ሦስት ወር አትጨነቅም። ምክኒያቱም አውነት ምንጊዜም እውነት ነው። ለመሸፋፈን በመሞከከር ህይወትህን አታወሳስብም።" @Jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
አንዴ ከሄዱ ብትለምኗቸው የማይመለሱ አራት ነገሮች! ምንጩ ያልታወቀ አንድ ማስታወሻ፡- በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯችሁ አራት ነገሮች፡- “እድል” - አንዴ ካመለጣችሁ በኋላ! “ቃል” - አንዴ ከአንደበታችሁ ከወጣ በኋላ! “ጊዜ” - አንዴ ሳትጠቀሙበት ካለፈ በኋላ! “አመኔታ” አንዴ ከጎደለ በኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡ 1. “እድል” - በአጋጣሚም ሆነ ጠንክራችሁ በመስራታችሁ የመጣን እድል መለየት፣ ማክበርና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም፡፡ 2. “ቃል” - ሁኔታዎች ሲገፋፏችሁም ሆነ እንዲሁ ስለለመደባችሁ በቀላሉ የምትናገሯቸውን ሰው ጎጂ ንግግሮች በሚገባ ማሰብና ራስን መግታት፡፡ 3. “ጊዜ” - በሆነ ባልሆነ የምታባክኑትና አሁን ባላችሁ እድሜ ማድረግ የሚገባችሁን ነገር ባለማድረግ የምታባክኑትን ጊዜ በጥንቃቄ መያዝ 4. “አመኔታ” - ሰዎች ሲያምኗችሁና ራሳቸውንም ሆነ ነገሮቻቸው በእናንተ ላይ ሲጥሉ እምነት ከማጉደል መጠበቅ፡፡ Dr-Eyob-Mamo- @Jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
ጥበብ የሌለበት እውቀት ! ~ ጥበብ የሌለበት እውቀት ለብስጭት እንጂ ለእረፍት አይሆንም ፤ ጥበብ የሌለበት እውቀት ስድብ እንጂ ትምህርት አይቀናውም ፤ ጥበብ የሌለበት እውቀት የት ቦታ ምን እንደሚናገር አያውቅም ፤ ጥበብ የሌለበት እውቀት አታውቅም ለማለት እንጂ ለማሳወቅ አይተጋም ፡፡ ~ እውቀት የግንዛቤ ክምችት ነው ፣ ጥበብ ደግሞ እውቀትን በመልክ በመልኩ ማስቀመጥ መቻል ነው ፡፡ @Jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
👆አገጋገር ቀርቶ ማሰስ አይችሉበት የወጣ እንጀራ ላይ ሀሳብ አስተያየት @jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ስዕል ለምትወዱ @jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ስዕል ለምትወዱ @jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ስዕል ለምትወዱ @jemthelast
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.