cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኢትዮ ሙስሊም ተማሪዎች ማህበር 🇪🇹

🇪🇹Ethiopian Muslim Students Union 🇪🇹 "አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ♥ ይህ ትክክለኛው የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች ማህበር የቴሌግራም ቻናል ነው። "ባረከላሁ ፊኩም ተማሪዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!👇 Telegram👇 https://t.me/EthiopianMuslimStudentsUnion

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 036
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-67 kunlar
-3430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

01:04
Video unavailable
የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የጦርነት አውድማዎች መስለዋል ! በተማሪዎች የፍልስጤም የድጋፍ ሰልፍ እየተናጡ ነው ! አሜሪካ የተማሪዎቹን አመፅና ሰልፍ ለመበተን የፀጥታ ሀይሏን ብታሰማራም ሊሳካላት አልቻለም ! ተቃውሞና ቁጣው ተጠናክሮ እንደ ሰደድ እሳት ተባብሶ ቀጥሏል ! አሜሪካን በውጥረት እስራኤልን በጭንቀት ሰቅዞ የያዘው የተማሪዎቹ የፍትህ ድምፅ ከአለም ጫፍ እስከ ጫፍ እያስተጋባ ነው ! Seid social ይህ ከስር የምትመለከቱት የዛሬው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ውሎ ነው !
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailable
እናቴ ልጅ እያለው የትምህርት ቤት ካርዴ ላይ እንዲህ ብላ ፃፈችልኝ "አንተ ፓይለት ስትሆን ወደ መካ 🕋 ትወስደኛለህ በአንተ ፕሌን" ዛሬ እናቴ ከተሳፋሪዎቹ መካከል ነች ወደ መካ ከሚጓዙት 🕋 እኔ ደግሞ የበረራው ፓይለት ነኝ 💖
Hammasini ko'rsatish...
🥰 6
ሒጃብ የለበሰች ፌሚኒስት ካገባህ፤ ሚስት ሳይሆን ተጋጣሚህን ነው ያገባኸው። አንድ ስትል ሁለት ትልሃለች። ብትቀርብህ ይሻልሃል። ስንት አደብ ያላቸው ሸሪዓውን ያከበሩ እህቶች ሞልተውን፤ ከርሷ ጋር ምን አጋተረህ። ደሞ ኮሜንት ላይ ተሳደቡ አሏችሁ:: copy past የተደረገ ፅሑፍ ነው:: ግን ደሞ እውነት ነው
Hammasini ko'rsatish...
👌 2
ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው "በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነበረው ተቃውሞ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ተማሪዎች በ10 ቀናት ውስጥ 900 ተማሪዎች ታስረዋል:: ግን ተቃውሞው አሁንም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል:: From the river to the sea Palestine will be free!
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
"ተማሪዎች እናመሰግናለን:: ከጋዛውያን ጎን ቁሙ:: ሰው ሁኑ::" - (ከጋዛ ወጥተው በካምፕ ውስጥ ያሉ ህፃናት መልዕክት) ስለ እነርሱ ድምፅ ለመሆን እየታተሩ ያሉትን የምዕራቡን አለም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አመሰገኑ:: የአለም ህዝብ ሰው ሆኖ ሰብዓዊነት እንዲገደው ጠየቁ:: ተማሪዎቹ ተቃውሟቸው እንደ ሰደድ እሳት ከሀገር ሀገር ከዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ እየተዛመተ ነው:: በምላሳቸው ሰብዓዊነትን እየሰበኩ በጠመንጃቸው ጄኖሳይድን የሚናገሩ የአውሮፓ ዲሞክራቶችም የተማሪዎችን ድምፅ ለማፈን የቻሉትን እየሞከሩ ነው :: እስሩ ቀጥሏል:: አፈናው ቀጥሏል:: ተቃውሞውም ቀጥሏል:: የጋዛ ፍሬዎችም ስለነሱ የቆሙትን አመስግነዋል:: ስለኛስ ምን ይሉ ይሆን? አይጠይቁን ይሆን? ቢላህ ይጠይቁናል! ዛሬ ባይሆን ነገ በአኼራ! ከመኽሉቅ ፊት ባይሆን ከኻሊቁ ፊት ይጠይቁናል! በትንሹ ህመማቸው ይሰማን! በዱዓችን እናስታውሳቸው! ስለነሱ እናንብብ! እንፃፍ! ነፃነታቸው የመላው ሙስሊም ነፃነት ነው! ነፃ ፍልስጤም ስንል ነፃ የአለም ሙስሊምን እየጠየቅን ነው! ፍልስጤም ከትናንሽ ወንዞቿ ጀምራ ነፃነትን ትቀዳጃለች ሰንል የአለም ሙስሊም ነፃነቱን እስከ ውቅያኖሶቹ ያገኛል ማለታችን ነው:: አሁንም እንደ ትላንቱ Free Free Palestine! From the river to the sea Palestine will be free!
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
ጥቆማ‼ ======= (የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ልጅ ላላችሁ ወላጆች በሙሉ!) || ✍ እኔ በዚህ ጉዳይ የምነግራችሁን ነገር ጆሯችሁን አቁማችሁ ማዳመጥ፣ ዓይናችሁን ከፍታችሁ ማየት ግደታ አለባችሁ። ልጆቻችሁን ፍጠኑን ለቀጣይ ክረምት ለዚህ ትሬይኒንግ አሁኑኑ መዝግቧቸው። የሚቀበሉት 200 ሰው ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የለቀቁት ገና አሁን ነው። ልጆቻችሁ ገና ከወዲሁ ለቀጣዩ ጊዜም ተራማጅ የሆኑ መስኮችን በማወቅ ዓይን እንዲከፍቱና ፍላጎቱ እንዲያድርባቸው ያደርጋቸዋል። ተናግሪያለሁ! «ማስታወቂያ ለኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2024 የክረምት ስልጠና ፈላጊ ታዳጊዎች በሙሉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወራት የሚቆይ የኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2024 የስልጠና መርሓ ግብር በአዲስ አበባ አዘጋጅቷል፡፡ ስልጠናዉ በ 🎯AI basics 🎯Robotics 🎯Programming 🎯Machine learning 🎯Internet of Things (IoT) ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡ የመመዝገቢያ መስፈርቶች 👉🏼የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆነ/ የሆነች 👉🏼ስልጠናውን በሳምንት 4ቀን መከታተል የሚችል/ የምትችል የምዝገባ ቀናት 👉🏼ከሚያዝያ 17 - ግንቦት 07፣ 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት አመልካቾች ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 👉🏼 https://forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8 👉🏼 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ በተጨማሪም እውቀት እና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ተከታዮቹን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ 👉🏼 https://www.aii.et/ethiopian-ai-summer-camp-2024-application-form-trainer-for-summer-camp/ 👉🏼 https://forms.gle/P2vAoZuWT7JgYQtT6 ለበለጠ መረጃ [email protected] ይጠቀሙ ወይም ድረ ገጻችንን www.aii.et ይጎብኙ፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሁሉም!» ልብ በሉ! በነፃ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
00:20
Video unavailable
ኒውዮርክ ፣ ፈረንሳይ ፓሪስ ፣ ካናዳ ቶሮንቶ ፣ ኮሎምቢያ ፣ ዋሽንግተን ፣ አውስትራሊያ ወዘተ የተማሪዎች የፍልስጤም አብዮት ተቀጣጥሎ ቀጥሏል ! አረቦች ሲቀሩ ሁሉም ነፃ ህዝብ የፍልስጤምም ትግል ይቀላቀላል
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በፍልስጤማውያን ድጋፍ እየተናጡ ነው ። የዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ላይ ሲሆኑ አሜሪካ ጉዳዩን ማረጋጋት ተቸግራለች ። ታላላቆቹ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ እና ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ ተመራማሪዎቹና የዩኒቨርስቲዎቹ ፕሮፌሰሮች ሳይቀሩ ስለፍልስጤም ሰላማዊ ትግል በመጀመራቸው አሜሪካ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል ። የአሜሪካ መንግስት ለዩኒቨርስቲ ሀላፊዎቹ ጉዳዩን እንዲያረጋግጉና ተቃውሞውን የሚመሩት ተማሪዎችና ፕሮፌሰሮች እንዲታሰሩ ቢያዙም የተቃውሞ ትግሉን ማስቆምም ማረጋጋትም አልቻሉም ። የዩኒቨርስቲዎቹ ፕሬዚዳንቶችም ለአሜሪካ ምክርቤት ቀርበው እንዲያብራሩ ተጠርተው ቀርበዋል። ተቃውሞውን ለማቆም በመቶ የሚቆጠሩ ተማሪዎች የታሰሩ ቢሆንም ትግሉ ግን ተባብሶ ቀጥሏል። እናም በአሁኑ ሰአት ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እና ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ለማቆም ተገደዋል። ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ወደ ቨርቹዋል ትምህርት የቀየረ ሲሆን በአካል ማስተማር የማይቻል ሆኗል። ከፍተኛ እስራኤል ጠል ትውልድ በምእራባውያን ሀገራት እየተፈጠረ ነው ። በተለይም ይህ ትውልድ የታላላቆቹ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የሚመሩት መሆኑ ለእስራኤል አደገኛ ምልክት ነው ። ቀጣዩ የአሜሪካ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እስራኤልን የሚፀየፍ ትውልድ እየሆነ መምጣቱ የአሜሪካን እና የእስራኤልን መንግስታት ክፉኛ አሳስቧቸዋል።
Hammasini ko'rsatish...
🥰 3
እስኪ ዛሬ ለኔም ለእናንተም ኻሰተን ለእህቶቻችን ማነቀቃያ ትሆን ዘንድ በዘመናችን ካሉ ድንቅ የሴት ሸይኻህ በወፍ በረር አንዷን ልጠቁማቹ ስሟ ሸይኻህ ዱክቱራህ ካሚለህ ቢንት መሃመድ ቢን ጃሲም ቢን ዐሊይ አል ጁሃሪል ከዋሪ ትባላለች ዱክቱራህ ካሚለቱል ከዋሪ በሚባለው በስፋት ትታወቃለች ኳታራዊ ነች እጅግ ድንቅ የሆነች የእውቀት ባለቤት ነች ፊቂህ ነህው ኡሱሉል ፊቂህ ተፍሲር እና ሌሎችም ፈኖች ላይ ያላት ተመኩን ዐጂብ ነው የተለያዩ 17 በዑሉሙ ተፍሲር ፣ ዐቂዳህ ፣ ፊቂህ ፣ ኡሱሉል ፊቂህ ፣ ቀዋኢዱል ፊቂሂያህ ፣ ሲራህ ፣ ሉገህ ፣ መንጢቅ ፣ በላጋህ በመሳሰሉት ፈኖች ላይ ወሳኝ ኪታቦች ተእሊቃቶች እና ኢኽቲሳራቶች አሉዋት ከነሱም ውስጥ በከፊሉ 1ኛ፦ አል ሙኽተሰሩ ሚን ሸርሂል ሙምቲዕ፦ ይህ ኪታብ የኢብኑ ዑሰይሚኑን የዘመኑ የፊቂህ ኢንሳይክሎፒድያ ሚባለውን ግዙፉን ሸርህ አል ሙምቲዕን ያሰጠረችበት ኪታብ ነው የተለያዩ ፈዋኢዶችንም ጨምራበታለች በጃሚአዎች ውስጥ እንደ ዋና ማስተያያ ይወሰዳል ሸይኹ ከመዝሃባቸው ሃናቢላ ወጥተው ተርጂህ ሲያረጉ እሷ የተለያዩ ከመዝሃቡ ፈዋኢዶች ትጨምራለች 2፦  ተፍሲሩ ገሪቢል ቁርአን 3፦ አል ፈዋኢዱል መስጡራህ ፊ ሀሊ አልፋዚ ኪታቢ ኢዕላሚ ሱነቲል መንሹራህ(2 ሙጀለድ) 4፦  አልወሲጥ ፊ ነህው 5፦ አተጥቢቁል ኢዕራቢይ 6፦  አፍናኑ ሲያገቲ ፊ ሀሊ አልፋዚ ዱሩሱል በላገቲ 7፦ አደውኡል ባሂር ፊ ሀሊ አልፋዚ ረውደቱ ናዚር ወጀነቱል ሙናዚር 8፦ አል ዐዝቡል መዒን ፊ ሃሊ አልፋዚ ሚንሃጁ ሳሊኪን 9፦ ሸርህ ኪታቡ ተህቢሪ ፊ ዒልሚ ተፍሲር(2 ሙጀለድ) 10፦ ሸርህ ቀዋኢዱል ፊቂሂያህ 11፦ ቀድሙል ዐሊም ወተሰልሱሉል ሃዋዲስ በይነ ሸይኺል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ወልፈላሲፋህ መዐ በያኒ መን አኽጠአ ፊል መስአለቲ ሚነ ሳቢቂን ወልሙዐሲሪን 12፦ አል ተስሂሉል ሙቅኒዕ ፊ ሃሊ አልፋዚ ረውዲል ሙረቢዕ (4 ሙጀለድ) 14፦ አል ኹላሰቱ ፊ ኡሱሉል ፊቂህ 15፦ አል ሙጅላ ፊ ሸርሂ ቀዋኢዱል ሙስላ ፊ አስማኢላሁል ሁስና 16፦ ሸርሁ ኑኒየቲ ሸይኽ ዐኢድ ዐዒድአል ቀርኒ 17፦ አህካሙ ሰላቲል ኹሱፍ ቡግየቱል ሙቅተሲዲ ሸርህ ቢዳየቱል ሙጅተሂድን ተዕሊቅ እና ተህቂቅ አርጋዋለች አትደነቁምን? አትገረሙምን ? ©Abdulhafiz_Mitiku መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ! የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
Hammasini ko'rsatish...
🥰 2 1
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable