uz
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Kanalga Telegram’da o‘tish

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

Ko'proq ko'rsatish
1 868
Obunachilar
-324 soatlar
-87 kun
-5730 kun
Postlar arxiv
The Prophet (saw) emphasized fasting on the day of Ashura (the 10th day in the month of Muharram), which falls on Friday, Jul
+1
The Prophet (saw) emphasized fasting on the day of Ashura (the 10th day in the month of Muharram), which falls on Friday, July 28th inshAllah. It is highly recommended to fast both the 9th day and the 10th day (Thurs, Jul 27th and Fri, Jul 28th). If that is not possible, scholars have noted that one can fast on the 10th and 11th day (Fri, Jul 28, and Sat, Jul 29th). Nonetheless, it is still commendable to just fast on the 10th day. We ask Allah most High to accept our fasting, and to grant us His mercies and guidance. t.me/Secrets_of_Truth

ማህበራዊ ገጾች 100 ሚሊየን ተጠቃሚ ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ወሰደባቸው? ሜታ በቅርቡ ያስተዋወቀው ትሪድስ በቀናት ውስጥ ከ100 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አግኝቷል። t.me/TechnologyMast
ማህበራዊ ገጾች 100 ሚሊየን ተጠቃሚ ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ወሰደባቸው? ሜታ በቅርቡ ያስተዋወቀው ትሪድስ በቀናት ውስጥ ከ100 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አግኝቷል። t.me/TechnologyMasterPage Fb.com/TechnologyMasterPage

ሞባይል  ባትሪና  ቻርጀር ስንገዛ ኦርጅናልና ፌክ ኮፒ መሆኑን እንዴት ማወቅ (መለየት) እንደምንችል እነሆ... ✔️ከሌሎች በይበልጥ ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችም📱 በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡ ሳምሰንግ የጉግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይጠቃማል፣ የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል ፍቃድ ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች ከኦርጂናሉ ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡ ⚠️ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን እነዚህን 👇 መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ... ✅ የስልኩን  ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም 👇 ፌክ ሳምሰንግ ስልክ፡ 1⃣. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም‼️ 2⃣. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል‼️ 3⃣. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል‼️ 4⃣. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል‼️ 5⃣. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ❌ መሆናቸዉን ይመለከታሉ‼️ ✅የስልኩን ፍጥነት እና የትእዞች አፈጻፀም በመገምገም * 1⃣. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል 2⃣. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡ 3⃣. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም ✅የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም * 1⃣. ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps) የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ... 2⃣. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ Settings የሚለዉን ይጫኑ... 3⃣. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ 4⃣. እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡ ✅የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም * ወደ ስልክ📱 መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል ✔️ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡ 1⃣. *#0*# 👉 አጠቃላይ መገምገሚያ 2⃣. *#1234# or *#9999# 👉 ስልኩ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ 3⃣. *#12580*369# 👉 ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ 4⃣. *#06# 👉 የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር ማወቂያ 5⃣. *#9998*246# 👉 የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ ✅ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም * ከላይ 👆 በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡ 1⃣. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት💻 ላይ ይጫኑት... 2⃣. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት 3⃣. ሶፍትዌሩ ስልኩን 📱ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ      ❖ Contact      ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።               ━━━━━━━━━━━━━━━ http://t.me/TechnologyMasterPage http://Fb.com/TechnologyMasterPage ▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬

ሰበር መረጃ ⭕️ ያለ VPN ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች መስራት ጀምረዋል።
ሰበር መረጃ ⭕️ ያለ VPN ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች መስራት ጀምረዋል።

👉ዛሬ አንድ የይለፍ ቃል ( Password ) ጠንካራ ለመባል ምን ምን ማሟላት እንዳለበት አሳያችኋለሁ። ጠንካራ የይለፍ-ቃል password እንዴት መፍጠር እንችላለን? የመረጃ መዝባሪዎችን ለመከላከል ጠንካራ የይለፍ-ቃል መጠቀም ቀዳሚው መሣሪያ ነው፡፡ 👉 አንድ የይለፍ ቃል ( Password ) ጠንካራ ነው የሚባለው የይለፍ-ቃሉ የፊደላት ብዛት ቢያንስ 12 ፊደላትን የያዘ ሊሆን ይገባል እንዲሁም የተለያዩ ፊደላት /Characters/ ቁጥሮችን እና የምልክቶችን ስብጥር መጠቀም ስንችል ነው። ✔️ የይለፍ ቃል ስንፈጥር ትኩረት ማድረግ ያለብን ነገሮች ▶️ ጠንካራና ረጅም የይለፍ ቃል መጠቀም ▶️ የግል መረጃዎችን አለመጠቀም:- ስልክ የልደት ቀን ወ.ዘ.ተ ▶️ የይለፍ ቃለዎን ለማንኛውም ሰው ከመስጠት ይቆጠቡ ▶️ ለተለያዩ Online Account የተለያዩ የይለፍ ቃል መጠቀም ▶️ የተለመዱ ቃላቶችን አለመጠቀም መረጃው ለሌሎች እንድደርስ Share አድርጉ አመሰግናለሁ‼️ t.me/TechnologyMasterPage

How can students check their ministry exam registration information ተማሪዎች እንዴት የሚኒስትሪ ምዝገባ መረጃ ያያሉ⁉️ t.me/TechnologyMasterPage

አላስፈላጊ ወጪ ላለማውጣት 🔥 የሞባይል ስልኮ ላይ Email አካውንት ወይም play store አካውንት የሞላችሁ እና እየተጠቀማችሁ ያላችሁ ስልካችሁን ድንገት Reset ብታደርጉት የግድ Email ይ
አላስፈላጊ ወጪ ላለማውጣት 🔥 የሞባይል ስልኮ ላይ Email አካውንት ወይም play store አካውንት የሞላችሁ እና እየተጠቀማችሁ ያላችሁ ስልካችሁን ድንገት Reset ብታደርጉት የግድ Email ይጠይቃል ለመክፈት ካወቃችሁት በመሙላት ይከፈታል። ነገር ግን በተለይ ከሠው ስልክ ገዝታችሁ ድንገት የሆነ ጊዜ Reset ብታደርጉት ስልኩን የተጠቀመውን ሠው Email መጀመርያ የገባውን ይጠይቃችዋል። ታድያ ይህን ስልክ በPattern /password ምክንያት ሊሆን ይችላል Reset ያደረጋችሁት ስለሆነም ካልሞላችሁ የመጀመርያውን Email ስልካችሁን መክፈት አትችሉም። ለማስከፈት የግድ ሞባይል ቤት መሄድ አለባችሁ ----- ⛔️መፍትሄው ማንኛውንም ስልክ Email ከተሞላበት በዋላ Reset ለማድረግ ከፈለጋችሁ ድንገት የረሳችሁትን የናንተን Email ወይም ስልኩን መጀመርያ የተጠቀመበትን ሠው Email እንዳይጠይቃችሁ ይህንን መንገድ ተጠቀሙ 🔥 በመጀመርያ Setting ላይ ከዛን About phone የሚለውን ከመረጣችሁ በዋላ ከታች Build Number የሚል አለ እሱን 5x ትጫናላችሁ የዛኔ Developer option enabled ወይም You are in developer option ይላችዋል ከዛን ወደ ዋላ back በማድረግ Developer Option የሚል አዲስ ይመጣል እሱ ላይ በመግባት OME UNLOCK የሚለውን ታበራላችሁ በቃ ከዛ በዋላ Reset ብታደርጉ ስልኩን ምንም Email ሳይጠይቃችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። t.me/TechnologyMasterPage

የእኔን የፌስቡክ የይለፍ ቃል እንዴት መለወጥ ወይም ማስተካከል እችላለሁ? ⓵ የይለፍ ቃልዎን ለመቀየር አስቀድመው ገብተው ከሆነ ፌስቡክ ላይ የይለፍ ቃልዎን ለመለወጥ- 1. Settings & Privacy የሚለውን ይጫኑ። 2. Security and Login የሚለውን ይጫኑ፡፡ 3. Change Password የሚለውን ይጫኑ ። 4. Type your current ከሚለው ሳጥን አሁን የምንጠቀምበትን ፓስዎርድ ያስገቡ ከዛም new password ከሚለው ሳጥን አዲስ መቀየር የፈለጋችሁትን ፓስዎርድ ያስገቡ ከዛም አሁንም ደግማችሁ ከሶስተኛው ሳጥን አዲስ መቀየር የፈለጋችሁትን ፓስዎርድ ያስገቡ ከዛም, Save Changes የሚለውን ይጫኑ። ⓶ ፓስዎርዳችሁ ቢጠፋባችሁ እንዴት ፌስቡካችንን መክፈት እንችላለን? ወደ ፌስቡክ ካልገቡ የይለፍ ቃልዎን እንደገና ለማስጀመር: 1. Click Forgot Password? የሚለውን ይጫኑ . 2. የርስዎን ኢሜል ፣ የሞባይል ስልክ ቁጥር ፣ ሙሉ ስም ወይም የተጠቃሚ ስም ይተይቡ ፣ ከዚያ search የሚለውን ይጫኑ ይፈልጉ 3. ከዛም የርስዎን የስልክ ቁጥርና ኢሜይል ያሳይዎታል ከፈለጉ በስልክ ቁጥርዎ ወይም በኢሜይል የምስጢር ቁጥር ይላክልዎታል ከዛም ተላከለዎትን የምስጢር ቁጥሩ ያስገቡ። ትክክለኛውን ካስገቡ አዲስ ፓስዎርድ እንድናስገባ ይጋብዘናል ስህተት ካስገባን ግን ትክክል አለመሆኑንና አዲስ ፓስዎርድ እንድናስገባ አይጋብዘንም። ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት... ⭕️ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ 〽️ t.me/TechnologyMasterPage Facebook 〽️ Fb.com/TechnologyMasterPage

የሞባይል ስልካችን ዳታ ኮኔክሽን እየጠፋ ወይም ሲግናሉ ደካማ እየሆነ ሲያስቸግረን ምን ማድረግ ይኖርብናል!!! ኢንተርኔት እየተጠቀምን የሞባይል ዳታ ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ እንቸገራለን፡፡አንዳንዴ አስቸካይ ስራ ለምስራት ፈልገን የኢንተርኔት ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ ወይም ጭራሽ እየጠፋ መስራት የምንፈልገውን ስራ ለመስራት እንቸገራለን፡፡ የዳታ ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ ወይም እየጠፋ በሚያስቸግረን ሰዓት ኮኔክሽናችን እንዲሻሻል(BOOST) ለማድረግ የሚያስችሉ 3 ቲፖችን ላካፍላችሁ፦ 1ኛ፡- የሞባይላችሁ Airplane Modeን “ON” ማድረግና “OFF” ማድረግ፦ Airplane Modeን “OFF” ካደረጋችሁ በሃላ ቢያንስ 30 ሰከንድ ጠብቃችሁ Airplane Modeን “ON” አድርጉት፡፡አሁን ዳታ ኮኔክሽናችሁ የተሻለ ይሆናል፡፡ 2ኛ፡- ሞባይል ስልካችንን (Restart) ማድረግ፦ ሞባይል ስልኮች miniature computers በመሆናቸው ማለትም ባህሪያቸው እንደኮምፒውተር በመሆኑ አንዳንድ ችግሮች ሲገጥሙን ስልካችንን አጥፍተን ስናበራ የገጠሙን ችግሮች ይስተካከላሉ፡፡ የኮኔክሽን ችግር ሲገጥመንም ስልካችንን ሪስታርት ስናረገው ኮኔክሽናችን ይሻሻላል፡፡ 3ኛ፡- ሲም ካርዳችን ከስልካችን ማውጣት(Remove your SIM card)፡ ሞባይል ስልካችንን ሳናጠፋ ሲምካርዳችን አውጥተን መልሰን ማስገባት፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን በማድረግ ኮኔክሽንናችን እንዲሻሻል ማድረግ እንችላለን። ▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ      ❖ Contact      ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።              ━━━━━━━━━━━━━━━ t.me/TechnologyMasyerPage ━━━━━━━━━━━━━━━ ▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬

ይመልከቱ ይለማመዱ ይዘጋጁ የመውጫ ፈተና ኦንላይን አገባብ፣ አጠቃቀም እና አፈታተኑን የሚያሳይ አጋዥ ቪዲዮ 📼 3.2 MB መልካም እድል ተመኘን ▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ      ❖ Contact      ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።                ━━━━━━━━━━━━━━━ t.me/TechnologyMasterPage ━━━━━━━━━━━━━━━ ▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬

+1
Grade 6 Regional Exam Schedule.pdf5.21 KB

⭕️ ውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ይህ ማስታወሻ በፈተና ወቅት ይጠቅማችኋል በትኩረት ይነበብ። ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▬▭▬▭▬▭▬▭ 🛑 ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች! ➤ በፈተና ወቅት በተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ውጥረት እና መጨናነቅ ለመቀነስ ይህንን ምክር በማስገንዘብ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን። 🎯 በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች:- 📙 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው። ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት። ♻️ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች ◆ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ◆ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ◆ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አለመሆኑን መረዳት።  ◆ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጁ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ◆ ከጓደኞቻችን ወይም ከወላጆቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ እርማት እንድናረግም ያግዘናል። ◆ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።  ◉ ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ ◉ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። ◉ አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 🔰 ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ  እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። ◉ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር:: ◉ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ ◉ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። ◉ ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። ◉ በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ➚ ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆንና ፈተና ማለት ለጀነትና ለጀኃነም ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን። ▮ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ ሌላውን ለአላህ መተው ነው‼️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ◉ ወቅቱ የፈተና ወቅት በመሆኑ ተማሪዎች እንዳየ እድሜያቸው እና የክፍል ደረጃቸው ይህን ማስታወሻ እንዲጠቀሙበት  አሳስባለሁ። 🎯 አላህ ይርዳችሁ‼️

🌙🌙🌙 🌺 عيدكم مبارك 🌺 🔶 🌸Eid Mubarak 🌸 🔶 🌹 ዒድ ሙባረክ 🌹 تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 💎ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን
                  🌙🌙🌙 🌺 عيدكم مبارك 🌺 🔶 🌸Eid Mubarak 🌸 🔶 🌹 ዒድ ሙባረክ 🌹 تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 💎ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን💎 ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል        

☑️ Reminder ➚ Tomorrow is the day of ARAFAH (9th Dhul-Hijjah) ◆ Tuesday 27th June, 2023 #FAST if you are able. ▮Please share
+1
☑️ Reminder ➚ Tomorrow is the day of ARAFAH (9th Dhul-Hijjah) ◆ Tuesday 27th June, 2023 #FAST if you are able. ▮Please share to get the blessing Insha'Allah. t.me/ReshadIbnuMuzemil