cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Journalist-at-large

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
100 707
Obunachilar
+524 soatlar
+2507 kunlar
+8 43630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! መልካም በዓል። @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
742🙏 307👍 104😁 15🕊 13🤔 5
100,000 followers on #Telegram አመሰግናለሁ! Galatoomaa! የቐንየለይ! @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
1777👍 925🙏 106😁 76🕊 44🤔 20😱 17😢 2
አስተያየት እና ጥቆማ ለምታደርሱኝ፣ አካውንቶቼ ለተወሰኑ ሳምንታት ዝግ ሆነው ይቆያሉ፣ ሁሉንም መልእክቶቻችሁን ላልመለከት ስለምችል አቆዩልኝ። መልካም ግዜ 👋👋 @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 782😢 138 71😁 52🤔 25😱 18🙏 15
#Update የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ዙርያ ባቀረብኩት መረጃ ላይ ያደረሰኝ መረጃ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ ከሚገኝ የምግብ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ለተራቡ ዜጎች ተብለው የሚወጡትን የምግብ አይነቶች እዛው የንግድ ቀጠና ውስጥ ፓኬጁ ላይ ባንዲራ በመጨመር እየታሸጉ እንደሆነ አንድ መረጃ አቅርቤ ነበር። በዚህ ዙርያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ይህን መረጃ አድርሶኛል: "WFP procured 50,000 MT of wheat on behalf of the EDRMC from WFP’s Global Commodity Management Facility (GCMF) - WFP's regional storage facility for purchased commodities - for EDRMC’s humanitarian support to communities affected by drought, floods, and conflict in Ethiopia. The wheat purchased from WFP by EDRMC is being collected from WFP’s warehouses in Dire Dawa after it has been transferred from UN bags to those provided by the government, ready for distribution. WFP occasionally leverages its extensive procurement expertise and networks to provide food procurement services to partners allowing them to respond to food needs in a timely manner." ለመረጃው የአለም ምግብ ፕሮግራምን እያመሰገንኩ ከለጋሽ ድርጅቶች የሚለገሱ የምግብ አይነቶችን 'በኢትዮጵያ የተመረተ' በሚል ማሸግያ ቀይሮ ማውጣት ለምን እንዳስፈለገ የሚመለከተው የመንግስት አካል አስተያየት ቢሰጥበት መልካም ነው እላለሁ። በቅርብ ወራት የእርዳታ ምግብ ምን ሲደረግ እንደነበር የሰማን/የምናውቅ እና እርዳታው ለተጠቃሚው ህዝብ እንዲደርስ የምንፈልግ ሁሉ ይህን መጠየቅ አለብን። @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 623 67😢 60😁 15🕊 14🤔 10😱 3
👍 34 4
👌👌 @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 1323 386🙏 42🕊 19😁 15🤔 7😱 5😢 2
የትብብር ጥያቄ! ዶ/ር እደግልኝ ሀይሉ ፓስፖርታቸው ትናንት (ቅዳሜ) አዲስ አበባ ብሔራዊ አካባቢ ጠፍቶባቸዋል። ፓስፖርቱን ያገኘ ሰው ቢተባበራቸው ውለታውን ይከፍላሉ። ስልክ ቁጥራቸው: 0936454509
Hammasini ko'rsatish...
👍 232 14😢 12😁 10🕊 3
የዛሬ 50 አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከካናዳ፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከቱርክ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጣልያን... ወዘተ ይበልጣል? አንዳንድ 'ተቀፅላዎች' ይህን ስክሪንሾት በስፋት ሲያጋሩ እንደነበር ጥቆማዎች ደርሰውኝ ነበር፣ እንዲጣራም የጠየቁ አሉ። ነገሩ እንዲህ ነው፣ መረጃው በ Goldman Sachs የ 2022 ሪፖርት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እ.አ.አ በ 2075 ወይም የዛሬ 50 አመት 6.2 ትሪሊየን ዶላር የማደግ እድል እንዳለው ይጠቁማል። በዚህ መረጃ ላይ ታድያ እነ ከካናዳ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ቱርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን ከኢትዮጵያ በታች የተቀመጡ ሲሆን ቻይና፣ ህንድ እና አሜሪካ ከ 1-3 ያለውን ቦታ ይዘዋል። እውነታው ግን ወዲህ ነው፣ እንዲህ አይነት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያዎች በአብዛኛው የወደፊት የማደግ አቅምን የሚያሳዩ ሲሆን በርካታ አሁናዊ እና የወደፊት እድሎችን እና መሰናክሎችን አያካትትም። በተጨማሪም ይህ አሀዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚንተራሰው የህዝብ ብዛት ቁጥር ላይ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት በ2075 አካባቢ 281 ሚልዮን ዶላር ይገመታል፣ ይህም ለከፍተኛ ምርታማነት እና የኢኮኖሚ እድገት መሰረት የመሆን እድል አለው። ሪፖርቱ የጠቀሰውም ይህን ነው። ይሁንና ተቀፅላዎቹ ሊያቀርቡት እንደፈለጉት ይህ ብቻውን የሀብት ወይም እድገት መለኪያ እንዳልሆነ አለም ተግባብቷል። ትክክለኛ እድገት መለኪያው ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣ የኑሮ ደረጃ መሻሻል፣ እንደ ውሀ፣ መኖርያ ቤት እና ኤሌክትሪክ ላሉ አገልግሎቶች ያለ ተደራሽነት... ወዘተ መሆናቸውን ራሱ Goldman Sachs ይጠቅሳል። - የጋሪ እና ፈረስ ትራንስፖርት እናመጣለን እየተባለ ወደ ቀደመው ክፍለ ዘመን ወደኋላ ለመሄድ እየተንደረደርን - በአለም ትላልቅ የሚባሉ ግጭቶች፣ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እና ስደቶች እያስተናገድን - የህዝብ የመኖር፣ የቤት ባለቤትነት፣ የስራ እና ተንቀሳቅሶ የማምረት አቅም እየተፈተነ... ወዘተ ባለበት ወቅት ይህን ትንበያ ይዞ ከካናዳ እና አውስትራልያ ልንበልጥ ነው ማለት ማደንዘዣ እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም። ብቻ መልካሙን ለሀገራችን እንመኛለን። @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 868😁 194 81🙏 12🤔 9🕊 9😱 8😢 2
😁 157👍 35 13🤔 8😱 5🙏 4
ለእርሻ፣ ለኮንስትራክሽን እና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚውሉ ትራክተሮች እና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስገቡ እንደተከለከሉ አስመጪዎች መናገራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነበበን ይህም የሆነው ካለምንም መመርያ ሲሆን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያለ ምንም በቂ ምክንያት "የመኪና ማስገቢያ ፈቃድ አልሰጣችሁም" እንዳላቸው ገልጸዋል። ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃም የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ጠይቁ መባላቸውን አመልክተዋል። ከሁሉም ግር የሚለው ደግሞ በቅርቡ በከተሞች በእንስሳት የታገዘ ትራንስፖርት እንዲኖር ስራ እየሰራ እንደሆነ የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከባድ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ እንዲሰሩ መጠበቁ ነው። በኤሌክትሪክ የሚሰራ ትራክተር? ገልባጭ መኪና? ግሬደር? ቡልዶዘር? ታድያ ይህ እየሆነ ያለው በቢልዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ለጫካ ፕሮጀክት እየፈሰሰ፣ ተጨማሪ በመቶ ሚልዮን ዶላሮች የሚቆጠር ደግሞ ለከተማ ማስዋብ እና ለቱሪዝም ስፍራዎች ግንባታ እየዋለ ባለበት ወቅት ነው። ነዳጅ ለማስገባት የዶላር በእጅጉ መመናመን እንዳለ እንረዳለን፣ ግን በአንድ በኩል ለወደፊት ሊቆዩ የሚችሉ የከተማ ማስዋብ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘብ እየፈሰሰ፣ በዚህ በኩል ደግሞ ያውም ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ የሆኑትን ግብርናን እና ግንባታን የሚያከናውኑ ቅንጡ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ምን ያህል misplaced priorities እንዳሉብን ማሳያ ነው። @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 584😢 90 47🤔 30😁 8😱 4🙏 4