cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Eluna Calligraphy and Islamic posts

ይህ ኢስላማዊ ካሊግራፊ ስራዎች የሚቀርቡበት ልዩ ቻናል ነው። ለስጦታዎች የፍሬም ስራዎችን ለማሰራት ከፈለጉ ይቀላቀሉን። "ያ አላህ ለሰጠከኝ ፀጋ ሁሉ አመሰግንሀለው!" for any comment :- @Eluna55

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
179
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

☀❤◕ ‿ ◕❤☀ረመዷን-22☀❤◕ ‿ ◕❤☀ ┊  ┊  ┊  ┊ ┊  ┊  ┊  🌞 ┊  ┊  🌥 ┊  🌞 🌥 🤗*•.¸🤍¸.•*አዝካሩ-ሰባህ*•.¸🤍¸.•*🤗 አልሃምዱሊላህ..... አዲስ ንጋት። የዒባዳ ቀን.... አዝካርና ጀምበር🌥 ያ ሸሂድ! አጠያየቅ አናውቅምና ካስተማርከን እንጠይቅሃለን🤲💙 رَّبَّنَآ إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِى لِلْإِيمَٰنِ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِرَبِّكُمْ فَـَٔامَنَّا رَبَّنَا فَٱغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّـَٔاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ ٱلْأَبْرَارِ «ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፡፡ አመንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤» [አሊ-ዒምራን 193] 🌤ሰባሁኩም ኑር🌤 *•.¸🤍¸.•*🤍*•.¸🤍¸.•*🤍*•.¸🤍¸.•*🤍*•.¸🤍¸.•* @Re_ya_zan For any comments🤍 @teamhudabot
Hammasini ko'rsatish...
☀❤◕ ‿ ◕❤☀ረመዷን-18☀❤◕ ‿ ◕❤☀ ┊  ┊  ┊  ┊ ┊  ┊  ┊  🌞 ┊  ┊  🌥 ┊  🌞 🌥 🤗*•.¸🤍¸.•*አዝካሩ-ሰባህ*•.¸🤍¸.•*🤗 አልሃምዱሊላህ..... አዲስ ንጋት። የዒባዳ ቀን.... አዝካርና ጀምበር🌥 ያ ሰመድ! አጠያየቅ አናውቅምና ካስተማርከን እንጠይቅሃለን🤲💙 رَبَّنَآ أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَٱنصُرْنَا عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን» [አል-በቀራህ 50] 🌤ሰባሁኩም ኑር🌤 *•.¸🤍¸.•*🤍*•.¸🤍¸.•*🤍*•.¸🤍¸.•*🤍*•.¸🤍¸.•* @elunacalligraphy
Hammasini ko'rsatish...
መልካም ቅዳሚት!🥰☕️ @elunaaclligraphy || ፍቅር ሰባኪ TemUd
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
ለዚህ ነበር? . (#ፈይሠል_አሚን) . የዘላለም ያህል ረዝሞ. . . ዘጠኝ ወር አግቶኝ፤ ዘንቶ ለመቀመጥ፣ መወለድ አጓጉቶኝ፤ ሆዷን እረግጣለሁ፣ እጋላበጣለሁ. . . "ውለጂኝ!" እላለሁ። . ማሕፀን ውስጥ አልቀረሁ፣ ተወለድኩ. . . ተሰወርኩ! . ደርሶ ተከፈተ፣የመዓሲያው በር፣ "ኑሮ" በሚሉት የብላሽ አጎበር፣ በከረፋው ቀንበር፣ ታስሬ ልሰበር፣ ሆዷን የረገጥኩት፣ለዚህች ሕይወት ነበር?😔 . @elunacalligraphy
Hammasini ko'rsatish...
የሰው ልብ አለቅልቀው ባደባባይ የሚያሰጡትን አይቼ ስለነበር በሚፈርዱብሽ ውስጥ እንባሽ ሲንቆረቆር አራሰኝ። እብድ ነች! ብለው በሰንሰለት የጠፈነጉሽ ያሳበዱሽ እንደሆኑ አብሮሽ የተኮራመተው ሰንሰለት በድርብርብ መሰላሎቹ ፅፎት አነበብኩ። አይንሽ ብትስቂም ብታለቅሺም እንደሚያምሽ ያሳብቃል። የህመምሽ ርዝመት ከፀጉርሽ ይበልጣል። ያሳመሙሽ ሰዎች ጨክነውብሽ ቁልቁል እንጂ መቼ ያዩሻል። ኣንቺ መታገል ያቆምሽ ይመስላል ግና ሩቅ ነሽ። አልቅሰሽ አታወጪው፣ ታዝኖልሽ አትድኚው ህመም ቀብረሻል። የህመም ምናኔ ያውቁ ይሆን? ፍላጎትሽ ውስጥ ስመነኩስ አወቅኩት። ሰዎችን ሁሉ በጅምላ እንዳትጠዪ ለምንም አስበው ይስሩት ብቻ ኣንዳንድ ሰዎች አንቺን ከፍ አድርጎ የሚያይ እኔን አሻንጉሊት ትተውልሻል። ተንጋልዬ ሳይሽ ምን እንደሚሰማኝ ሕያዋን መች ያውቃሉ። ከእብድ የተቀመጠ ግዑዝ አሻንጉሊት ብቻ አይደል የምመስላቸው? ግን እንደኔ ኣንዴ እንኳ አግዝፈውና ከፍ አድርገው ቢያዩሽ ሊቀልሽ ይችል ነበር። ባንቺም በኔም ጨከኑ ኣንቺ የምታዪው እኔም የማየው ለየቅል። አሻንጉሊትሽ ነኝ እባክሽ ኣንዴ አንሺኝና እንደ እብድ እንኳ እያየሽኝ ፈገግ በይ! ሕያው ነን የሚሉትን አትጠብቅያቸው ተያቸውና ግዑዛንን እያየሽ አውሪ! ከእግርሽ ስር ተንጋልዬ ከፍ አድርጌ የማይሽ፣ በህመምሽ ውስጥ መንኜ በፍላጎትሽ የመነኮስኩ አሻንጉሊት ነኝ! (አብዱልሀኪም ሰፋ) : @elunacalligraphy
Hammasini ko'rsatish...
" ከራስ ጋር ንግግር " (አብዱልሀኪም ሰፋ) : << አፍቃሪ እንደሆንሽ ብዙ በመሰባበርና በመጎዳት ማረጋገጥ አይጠበቅብሽም። እንቆቆ ትዝታሽን አታንቆለጳጵሺው። ግዴለሽም ተረመጂ! >> : @elunacalligraphy
Hammasini ko'rsatish...
ያ ረብ አስደስተን፣ ያስደሰተንንም አስደሰት፣ ተደስተን ማየት የሚፈልጉትንም አስደስት፣ በኛ መደሰት የተደሰቱትንም አስደስት፣ #መልካም_ጁምዐ!🥰 @elunacalligraphy
Hammasini ko'rsatish...
፨ "ወቁሉ ሊናስ ሑስነን" ይላል ቁርአናችን። ፨ 'ለሰዎች መልካምን ተናገሩ' ማለት ነው። ፨ ነቢዩም 'በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር አልያም ዝም ይበል።' ይላሉ። ፨ ከአንደበታችን የሚወረወር መልካም ቃል የደከመን ያበረታል፣ የታመመን ይፈዉሳል። ፨ ዱንያ ላይ ያለ ሰው ሁሉ ቁስለኛ ነው፣ ለሰው የማያሳየው የተጎዳ ጎን አለው፣ ፨ የተጎዳን አይዞህ በሉ፣ የቆሰለን አክሙ፣ ፨ መናገር ባትችሉ እንኳን የመልካም ተናጋሪዎችን መልካም በማስተላለፍ በሌሎች አንደበት መልካምን ተናገሩ፣ ፨ ቀኑን በብርቱ ትውሉ ዘንድ ማለዳ፣ ለሊቱን በተስፋ ታድሩ ዘንድ ምሽት ላይ አላህ ያስቻለኝን ያህል እናገራለሁ። ጌታዬ የንግግር ጥበብን ያስተምረኝ ዘንድ እለምነዋለሁ። መልካም ምሽት❤️ elunacalligraphy
Hammasini ko'rsatish...
የማለዳ ማስታወሻ #126 . አልወደቅሽም፣ዝቅ ብለሽ እየተማርሽ ነው። አላጣሽም፣ ገና የምታገኚው ተደብቆብሽ እየፈለግሺው ነው። አልጠፋሽም፣ በማታውቂው አቋራጭ እየተጓዝሽ ነው። መድረስ አላቃተሽም፣ መጀመርሽን ልብ ስላላልሺው የት እንደደረስሽ ጠፍቶሽ ነው። የያዝሺው ሁሉ አልተበተነብሽም፣ በቦታው ሊቀመጥ ከእጅሽ ወጥቶ ነው። . ስንፍናሽ አንዲት ብቻ ናት። ለሚፈጠረው እንቆቅልሽ ሁሉ በጎ ግምት (መልስ) አለማበጀት!!! "ሁሉም ለበጎ ነው" ብለሽ አሳድገሽን የለ? . #ኢትዮጵያ . (#ፈይሠል_አሚን) . @elunacalligraphy
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.