cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Amhara Jobs

በአማራ ክልል ከሚገኙ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመተባበር ፡ ማንኛውም ስራ ነክ መረጃዎችን እንዲሁም ወቅታዊ የስራ ማስታወቂያዎችን በልዩ ሁኔታ በነፃ የሚተላለፍበት ምርጥ የመረጃ ምንጭ እንሆ በእጅዎ ፦ በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የማማከር አገልግሎት 👉የፅሁፍ እና የቃል ፈተና ዝግጅት 👉 Curriculum Vitae (CV) & Application letter መስጠት ጀምረናል።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
6 814
Obunachilar
-124 soatlar
-57 kunlar
-330 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
👍 4 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ዳሽን_ከፍታ: በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው "ዳሽን ከፍታ" የሥራ ፈጠራ ውድድር ሶስተኛ ምዕራፍ ሊጀመር ነው፡፡ በዳሸን ከፍታ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድሮች ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሸልማትና የፋይናስ ድጋፍ አግኝተው በተለያዩ የስራ ዘርፎች ስኬታማ እየሆኑ ነው፡፡ ለሌሎችም የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት? ዳሽን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምዕራፍ ሶስት የቅድመ ውድድር ጅማሬ ስልጠና ለመስጠት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ይንቀሳቀሳል! የስልጠና ቦታዎች ፡ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ አዳማ ፣ መቀሌ ፣ ድሬዳዋ ፣ ሀዋሳ ፣ ወላይታ ፣ ጅማ እና ደሴ ምዝገባ እስከ #ሰኔ_22/2016 ዓ.ም. ድረስ በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ወደ 6333 ይደውሉ ወይም የባንኩን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይጎብኙ፡፡ ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!
Hammasini ko'rsatish...
👍 13
👍 2 1
One app for all your Word, Excel, PowerPoint and PDF needs. Get the Microsoft 365 app: https://aka.ms/GetM365
Hammasini ko'rsatish...
d226b674-eb1b-4a91-96cc-e9995fde4325.pdf3.89 KB
Photo unavailableShow in Telegram
8👍 1
የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ እንዴት ይፈፀማል፤ የመደበኛ የስራ ሰዓት በቀን 8 ሰዓት እና በሳምንት 48 ሰዓት ነው፡፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ <<መደበኛ የስራ ሰዓት›› ማለት ሰራተኛው በትክክል ስራውን የሚሰራበት ወይም እራሱን ለስራ ዝግጁ አድርጎ በህጉ፣ በህብረት ስምምነት ወይም በስራ ደንቦች መሰረት በስራ ቦታ የሚገኝበት ሰዓት ማለት እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በሚኒስቴሩ መመሪያ መሰረት ለኢኮኖሚ ዘርፎች፣ ለኢንዱስትሪዎች ወይም ልዩ የስራ ሁኔታዎች ባሉባቸው ስራዎች የሰራተኛው ደመወዝ ሳይቀነስ በሰራተኛው የስራ ሰዓት ሊቀነስ ይችላል፡፡ የስራ ሰዓቶች ለሳምንቱ የስራ ቀናት እኩል ይደለደላሉ፡፡ ነገር ግን የስራው ባህሪይ ቢያስገድድ በማናቸውም የሣምንቱ የስራ ቀኖች ሰአቶችን ማሣጠርና ልዩነቱን ለተቀሩት ቀኖች ማደላደል ይቻላል፡፡ የስራ ሰዓታት በቀን እስከ 10 ሰዓታት ማራዘም ይቻላል:: ከመደበኛ የሥራ ሰዓት በላይ የሚሠራ ሥራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ነው፡፡ በአደጋ ጊዜ (አደጋ ሲደርስ ወይም የሚደርስ መሆኑ ሲያሰጋ) ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም፤ በአስቸኳይ መሰራት ያለበት ሥራ ሲያጋጥም እና በማያቋርጥና ተከታታይ ሥራ ላይ ከሥራ የቀሩ ሠራተኞችን ለመተካት ካልሆነ በስተቀር አንድ ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ አይገደድም፡፡ የትርፍ ሰዓት ሥራ በቀን ከ4 ሰዓት ወይም በሣምንት ከ12 ሰዓት ላይበልጥ ይችላል፡፡ አንድ ሰራተኛ በስራ ቀናት እነዲሰራ ከተወሰነው መደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ቢሰራ ማለትም በቀን 8 ሰዓት እና በሣምንት 48 ሰዓት ቢሰራ ከመደበኛ ደመወዙ በተጨማሪ ቀጥሎ በተመለከተው አኳኋን ይከፈለዋል፡፡ ❤ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በ150 % ተባዝቶ ይከፈላል፤ ❤ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ለሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራው በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በ175 % ተባዝቶ ይከፈላል፤ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ ተመን 200% በሳምንቱ የዕረፍት ቀን ስራ እና ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ ተመን 250% በህዝባዊ በዓላት ቀን ለሰራ እንደሚከፈል የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 ከአንቀጽ 61-68 ድረስ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የምሽት ስራ ክፍያ፤ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት የምሽት ስራ ከምሽት 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት የሚሠራ ሥራ ማለት ነው፡፡ በሥራ ህጉ ላይ አሰሪዎቹ ለምሽት ሠራተኞች ክፍያ እንዲፈፅሙ የሚያደርግ አንቀፅ የለም፡፡ ከፍተኛ ክፍያዎች የሚፈፀሙት የቀን ሠራተኞች ሆነው በምሸት ትርፍ ስራ ለሚሰሩ ማካካሻ ክፍያዎችን ለመክፈል የሚያስገድድ የተለየ ድንጋጌ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ውስጥ የለም፡፡ የምሽት ሰዓታት ትርፍ ሰዓታት ከሆኑ ለሠራተኛው የመደበኛውን ክፍያ 175% ማግኘት እንዳለበት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 68 ተቀምጧል። ❤ በምትክ የሚሰጥ ዕረፍት፤ ሰራተኞች በአደጋ(አደጋ ሲኖር ወይም ይደርሳል ተብሎ ሲገመት) ምክንያት የተከሰተ ከባድ ችግር ለማስወገድ ወይም ከአቅም በላይ በሆነ አደጋ ወይም አስቸኳይ ስራ ሲኖር በሳምንት የእረፍት ቀን ወይም በህዝባዊ በዓል ቀን ስራ እንዲሰሩ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ አንድ ሰራተኛ ማካካሻ የሚያገኝበት የበዓል ቀን ከመድረሱ በፊት የስራ ውሉ/ሏ ቢቋረጥ ማካካሻ የሚያገኝ/ታገኝ ይሆናል፡፡ በህዝባዊ በዓላት ቀናት ለሚሰሩ ሰራተኞች የሚሰጥ የምትክ ዕረፍት ጊዜን የተመለከተ ድንጋጌ ግን የለም፡፡ለዚህ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 75 መመልከት:: በህዝባዊ በዓላት ቀናት ለሚሰሩ ሰራተኞች የሚሰጥ የምትክ ዕረፍት ጊዜን የተመለከተ ድንጋጌ ግን የለም፡፡ለዚህ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 75 መመልከት ይቻላል። ❤ የሳምንት መጨረሻ / የህዝባዊ በዓላት ስራ ክፍያ፤ ሰራተኞች በሳምንት የእረፍት ቀናት ወይም ህዝባዊ በዓል ቀናት እንዲሰሩ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሲኖር ሰራተኞቹ በህጋዊ ህዝባዊ በዓል ቀናት እንዲሰሩ ከተፈለገ መደበኛ የሰዓት ክፍያ ተመን 200% በማካካሻ ክፍያ የመቀበል መብት እንዳላቸው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 75 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ለብዙዎች ይደርስ ዘንድ፤https://t.me/JobsinAmharaRegion
Hammasini ko'rsatish...
Amhara Jobs

በአማራ ክልል ከሚገኙ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመተባበር ፡ ማንኛውም ስራ ነክ መረጃዎችን እንዲሁም ወቅታዊ የስራ ማስታወቂያዎችን በልዩ ሁኔታ በነፃ የሚተላለፍበት ምርጥ የመረጃ ምንጭ እንሆ በእጅዎ ፦ በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የማማከር አገልግሎት 👉የፅሁፍ እና የቃል ፈተና ዝግጅት 👉 Curriculum Vitae (CV) & Application letter መስጠት ጀምረናል።

👍 10 3
Photo unavailableShow in Telegram
የሰራተኛ ደሞዝ ቅነሳ Legal tips/h۸ ! ስለሰራተኛ ደመወዝ ቅነሳ ህጉ ምን ይላል፤ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 53 እና ተከታዮቹን ድንጋጌ ስንመለከት ደመወዝ አንድ ሰራተኛ በስራ ውሉ መሰረት ለሚያከናውነው ስራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ሲሆን አሰሪው ለሰራተኛው የሚከፍለው የትርፍ ሰአት ክፍያ፣ የተለያዩ አበሎች፣ ጉርሻ( ቦነስ)፣ ኮሚሽን፣ የማትጊያ ክፍያዎች እና ከደንበኛ የሚሰበሰቡ የአገልግሎት ክፍያዎች እንደ ደመወዝ እንደማይቆጠሩ ይደነግጋል፡፡ የሰራተኛ ደመወዝ በምን አግባብ መቀነስ ይቻላል የሚለውን በአዋጁ አንቀፅ 59 ስር የተቀመጠ ሲሆን ይህም በህግ፣ በህብረት ስምምነት ወይም በስራ ደንብ በተወሰነ ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፤ መሰረት ካልሆነ ወይም ሰራተኛው በፅሁፍ ካልተስማማ በስተቀር አሰሪው ከሰራተኛው ደመወዝ ሊቀንስ እንደማይችል ወይም በእዳ ሊይዝ ወይም ሊያቻችል አይችልም በማለት፤ በግልፅ የሚደነግግ በመሆኑ ይህንን በመተላለፍ የሚደረጉ የደመወዝ ቅነሳዎች ህግን መሰረት ያደረጉ አይደሉም፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 59666 ላይ ከደመወዝም በተጨማሪ አሰሪ፤ ለሰራተኛው ለትምህርት ቤት የከፈልኩት ክፍያ ነው በማለት ሰራተኛው ስራ በሚለቅበት ጊዜ ከሚያገኘው የአገልግሎት ካሳም ላይ ቢሆን እንኳን አሰሪ በራሱ ውሳኔ ሊቀንስ ወይም ሊይዝ ወይም ለእዳ እንዲቻቻል ማድረግ እንደማይችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ አሰሪው ከሰራተኛ እዳ እንዳለበት ካመነ እዳውን ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ማስመለስ ይችላል እንጂ ሰራተኛው ሳይፈቅድ በራሱ ተነሳሽነት የሰራተኛውን ደመወዝ ወይም ሌሎች ጥቅሞቹን መቁረጥ አይችልም፡፡ በተጨማሪነትም በሰራተኛው ፈቃድ፣ በህብረት ስምምነት፣ በስራ ደንብ ወይም በህግ በተቀመጠው አግባብ የሚቀነሰውን የደመወዝ መጠን፤ በተመለከተ በአዋጁ አንቀፅ 59(2) ላይ የተገለፀ ሲሆን ሰራተኛው በፅሁፍ ስምምነቱን ካልገለፀ በቀር በአንድ ጊዜ ከሰራተኛው ደመወዝ ላይ በአጠቃላይ ሊቆረጥ የሚችለው የገንዘብ መጠን በምንም አኳኃን ከወር ደመወዙ አንድ ሶስተኛ( 1/3) መብለጥ እንዳሌለበት አስገዳጅ ህግ ተቀምጧል፡፡ በመሆኑም አሰሪዎች ከሰራተኛው ላይ ደመወዝ ሲቀንሱ ወይም ሲቆርጡ ይህንኑ ታሳቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ለብዙዎች ይደርስ ዘንድ፤https://t.me/JobsinAmharaRegion
Hammasini ko'rsatish...
Amhara Jobs

በአማራ ክልል ከሚገኙ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመተባበር ፡ ማንኛውም ስራ ነክ መረጃዎችን እንዲሁም ወቅታዊ የስራ ማስታወቂያዎችን በልዩ ሁኔታ በነፃ የሚተላለፍበት ምርጥ የመረጃ ምንጭ እንሆ በእጅዎ ፦ በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የማማከር አገልግሎት 👉የፅሁፍ እና የቃል ፈተና ዝግጅት 👉 Curriculum Vitae (CV) & Application letter መስጠት ጀምረናል።

👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
10
Photo unavailableShow in Telegram
👍 4 3
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.