cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

✞ ፀሐየ ጽድቅ ✞

👉ፀሐየ ጽድቅ የሕይወት መብራት የጽድቅ ብርሃን በዚህ channel ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ቅዱሳንን እንዘክራለን ስለቅዱሳን እንማማራለን ዕለታዊ ዜና ቤተ-ክርስቲያ ስንክሳር ግጻዌ ጥያቄና መልስ እንዲሁም በየእለቱ አጥንትን የሚያጠነክሩ መንፈስን የሚያለመልሙ ጽሁፎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡ ቻናሉን ይቀላቀሉ @Tsehaye_Tsidk ሼር ያርጉ!!

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 092
Obunachilar
-124 soatlar
-57 kunlar
-3430 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
"ትልቁን በትንሹ አትጋርድ!" በእውቀታቸው የተከበሩትና በትህትናቸው የሚወደዱት መንፈሳዊው መምህር የማለዳውን ትምህርት ለተማሪዎቻቸው ሰጥተው እንደጨረሱ ተማሪዎቻቸውን አሰናብተው በጥሞና ቆመው አድማሱን አሻግረው በሃሳብ እያስተዋሉ ሳለ ከተማሪዎቻቸው አንዱ "መምህር አንድ ጉዳይ አስጨንቆኝ ልጠይቅ ነው የመጣሁ" በማለት ከሄዱበት የሃሳብ አለም መለሳቸው መምህሩም ወደ ተማሪያቸው ዞር ብለው እያዩት "ጉዳዩ አስጨንቆህ ሳይሆን በጉዳዩ አንተ ተጨንቀህ ነው ፡፡ የሆነስ ሆነና ምን እንደሆነ ንገረኝ" ተማሪውም "እንዴት መሰሎዎ መምህር የቅዱስ ቃሉ ምስጢር እንዲገለጥልኝ እሻለሁ ይሁን እንጂ እለት በእለት እንዳላጠና እንቅፋት ገጥሞኛል ..." መንፈሳዊው መምህር በጣቶቻቸው ጢማቸውን ሳብ ሳብ እያደረጉ "እንቅፋት እንደገጠመህ አመንክ ፡፡መልካም እንቅፋቱ ምንድነው? " ተማሪው ቀጠለ "የምኖረው ከወንድም እህቶቼ ጋር እናትና አባቴን ጨምሮ በአንድ ትንሽ ጎጆ ቤት ውስጥ ነው እናም ቃሉን ለማጥናት ጥሞናና ጸጥታ የማገኝበት የአፍታ ጊዜ ስለሌለ ተቸግሬያለሁ ፡፡ ምን ባደርግ ይሻላል?" ችግሩን በደንብ አድምጠው የተረዱት መምህርም የተማሪያቸውን ትከሻ በፍቅር አሸት አሸት እያደረጉ "እስቲ አንድ አፍታ ወደጉዋሮ ዞር ዞር እንበል ምናልባት አንዳች ነገር ይገለጥልን ይሆናል" ብለው ወደ ውጭ አብረው ወጡ፡፡ "እስቲ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት" አሉት "ምን ይታይሃል? " "ወሰን የሌለው ሰፊ ሰማይ" ተማሪው መለሰ "አሁን ደሞ እጅህን አይኖችህ ፊት ጋርደህ ወደላይ ተመልከት፡፡ ምንድነው የሚታይህ?" "እጄ ብቻ" "በደንብ አይተህ ንገረኝ" ብለው በቆመበት ትተውት ጥቂት እርምጃ እንደተራመዱ "መምህር ከእጄ መዳፍ እና ጣት ውጭ ምንም አይታየኝም" እርምጃቸውን ሳያቋርጡ "አየህ ልጄ ወሰን አልባውን ትልቁን ሰማይ ማየት ያልቻልከው በትንሿ እጅህ አይንህን ስለሸፈንክ ነው ልክ እንደዚሁ ከቤተሰቦችህ ጋር በትንሽ ጎጆ መኖርህን መንፈሳዊውን እውቀት ልብህ እንዳትረዳ ጋረድክ ፥ በነሱ ጨዋታና አንድ ላይ አብሮ በመኖር ፍቅር ውስጥ የቅዱስ ቃሉን ፍቺ መገለጥ ፈልግ . . ."ትልቁን በትንሹ አትጋርድ" እኔም አልኩኝ « …ወሰን አልባውን የልባችን ቁልፍ ያላገኘነው የሌሎችን በመናፈቅ ነው» (ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተገኘ)
993Loading...
02
#ዕርገት #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡ ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡     እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡ ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡ ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡ (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
1645Loading...
03
#የንጉሥ_ግብዣ_አለ_ተጠርተሃል_እንዳትቀር ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትራችሁ የምትመጡ ይህን ልመናዬን ስሙ፤ ሰነፍ የኾኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድን አስፈላጊነት አስተምሯቸው፡፡ የትምህርቷን ውበት ቀምሳችኋልና እናንተ ያወቃችሁትን ሳያውቁ እንዳይቀሩ፡፡ ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ የነፍስ ፍርድ ቤት አይደለችም። የኃጢአትን ስርዬት ትሰጣለች እንጂ ኃጢአትን አትፈርድም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደምናገኘው ምስጋና በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ደስተኞች ደስታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ የሚጨነቁት፤ ያዘኑት፣ ሰላምን ያገኛሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፤ የተቸገሩ ሰዎች እፎይታ ያገኛሉ፤ ኹሉም ከተሸከሙት ያርፋሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ኹሉን ታቅፋለች፡፡ ውስጥ ከሆንክ ተኩላው አይገባም፣ ብትሄድ ግን አራዊቶች ይይዙሃል፡፡ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፣ ከቤተክርስቲያን የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን መዳንህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከድንጋይ ትከብዳለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከአለም ትስፋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አታረጅም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እራሷን ታድሳለች፡፡ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ በመከራና በኃጢአታችሁ የከበደ ኹሉ' ወደ እኔ ኑ" ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡" (ማቴ ፲፩፥፳፰) ይህንን ድምጽ ከመስማት የበለጠ ምን ደስታን ሊሰጠን ይችላል? ከዚህ ግብዣ የበለጠ ጣፋጭ ምንድነው? ጌታ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጠራችሁ ለታላቅ ግብዣ ነው፡፡ ከትግል ወደ እረፍት፣ ከስቃይ ወደ እፎይታ ያሸጋግራችኋል፡፡ ከኃጢአታችሁ ሸክም ያገላግላችኋል፡፡ ጭንቀትን በምስጋና፣ ሀዘንንም በደስታ ይፈውሳል፡፡ ለክርስቶስ ከሚኖረው በቀር በእውነት ነጻ፣ በእውነት ደስተኛ የሆነ ማን ነው? እንዲህ ያለው ሰው ክፋትን ኹሉ ያሸንፋል ምንም አይፈራም! ቤተ ክርስቲያን ለኹሉም መጠጊያ ሆና ቆማለች፡፡ የአምላክን ትዕዛዝ የምትፈጽም መልካም ሰው ከሆንክ ቅድስናህን ለመጠበቅ ግባ፤ ኃጢአተኛ ከሆንህ መዳንን ለማግኘት እርምጃህን ፈጠን አድርገው:: የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይሰሙስ እንዴት ነፍስን ወደ መልካም መንገድ መምራት ይቻላል? የእግዚአብሔር ቃል 'ብርሃን' በመባል ይጠራል፤ ፀሐይ ከምታፈልቀውና እኛም ከምናየው ብርሃን፣ እጅግ በጣም የከበረ ብርሃን፣ የነፍሳችንን ጥልቀት የሚያበራ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ እውነት እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው::" ከእናንተ መካከል በታማኝነት ቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉ፤ 'ስራ በዛብኝ፣ ልመጣ አልችልም' እንዳይሉ ሌሎቹን ምከሩ፡፡ ወደ ንጉሱ ግብዣ የተጋበዙ ግን መምጣት ያልቻሉትን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ አንደኛው አምስት ጥማድ በሬዎችን ሊገዛ እንደሄደ ተናገረ፣ ሌላው አዲስ መሬትን ሊገዛ እንደሄደ ሲናገር ሌላው ደግሞ ሚስት ማግባቱን ተናገረ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ንጉሡ ግብዣውን ንቀው ስለቀሩ የሚታገሳቸው ይመስልሃል? እናም ንጉሡን በሰበብ አስባቡ አታናዱት፡፡ ከጊዜህ ላይ አንድ ሰዓት ያህል እንኳን መቆጠብ ያቅትሃል? ቤተክርስቲያንን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሥራ መሄድ በእውነት ይህን ያህል ከባድ ነውን? አንድ ሰው ወርቅ፣ ብር፣ ማር ወይም ወይን በነጻ እየሰጠ ነው ቢባል፤ ማንም ሳይቀድማችሁ ለመድረስ አትቸኩልም? ነገር ግን፣ ከወርቅ የሚበልጥ፣ ከማርም ከወተትም የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማድመጥ ወደ ቤተክርስቲያን የምትመጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡ ስለዚህም፣ ይህን ችላ ማለታችሁን አውግዣለሁ፤ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ያላችሁን ግድየለሽነት እቃወማለሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቶቿ በመራቃችሁ፣ በውስጣችሁ የእግዚአብሔር ፍራቻ የለም፤ እግዚአብሔርን የማትፈራ ነፍስም ለኃጢአት የተገዛች ትሆናለችና ነፍሳችንን እንጠብቃት፡፡ (#የነፍስ_ምግብ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው - ገጽ 105-107) #ይቀላቀሉን!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
2734Loading...
04
#ህዳር_26 ዝ ክ ረ - ቅ ዱ ሳ ን በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 እንኳን ለታላቁ ጻድቅ አቡነ ሃብተ ማርያም አመታዊ ክበረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ✞ አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ ✞ እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው። "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው። ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል። ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች። በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች። እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር። ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች። ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች። ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ። ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር። የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል። ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ። ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል። የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል። ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል። በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም። ➠ ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ። ➠ በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ። (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው) ➠ በ40 ቀናት : ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ። ➠ ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው። ➠ በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ። (ካህን ናቸውና) ➠ ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ። ➠ በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም። በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር። ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው። "1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: 2.ስለ ምናኔሕ: 3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: 4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: 5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: 6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: 7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ።" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ። በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው። ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው። ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው። ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች። በዝማሬም ወሰዷት። {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት።} አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን። --------------------------------------------- "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና። ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና። ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ። በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል። አንደበቱም ፍርድን ይናገራል። የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው። በእርምጃውም አይሰናከልም።" (መዝ. 36:28-31) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> #ስንክሳር_ዘወርሃ_ህዳር ለወዳጅዎ ያካፍሉ!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
2504Loading...
05
Media files
1671Loading...
06
ተወዳጆች ሆይ አንድ የልብ ምክር አለኝና አድምጡኝ፦ ወዳጄ የቤተሰብ ሓላፊ ከሆንህ፡- እኔ ለቤተሰቤ እንደ ኢዮብ ካህን ነኝ ስለዚህ በመንፈስ ሁል ጊዜ፤ በአካል ደግሞ እንደ ችሎታዬ መጠን ስለራሴ ምክንያቱም በመልካም ማስተዋል ቤተሰቤን እመራ ዘንድ ስለቤተሰቤ ምክንያቱም ቤተሰቤ በኃጢአት ምክንያት አእምሮው እንዳይቆሽሽ በራስ መተማመን እንዳያጣ በማስተዋልና እግዚአብሔርን በመፍራት እንዲመላለሱ ስለሀገሬ ሰዎች ደግሞ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ማስተዋልንና እርስ በእርስ መግባባትን እንዲሰጣቸው ፍቅር እንድትነግሥ ስለዓለሙ ሁሉ ደግሞ “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” እንድንል ጌታ እንዳስተማረን የምንኖርባት ዓለም ፈቃዱን ለማድረግ እንደሚተጉ መላእክት ለመልካም ሥራ እንዲበረቱ በጸሎት መትጋት አለብኝ ብለህ ለልብህ ንገረው፡፡ ለቤተሰባቸው እማወራ ለሆኑ እናቶችና ሚስቶች ደግሞ ለልባቸው እንዲህ ብለው ይንገሩ፡- እኔ ለቤተሰቤ አካሉ ነኝ፡፡ በእርግጥም ባለቤቴ ራሴ ነው እኔም አካሉ ነኝ ልጆቼም ከእኔ የወጡ የአካሌ ክፋዮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሳራን “ካንቺ ሕዝብና አሕዛብ ይወጣሉ” እንደተባለች ከእኔ ማኅበረሱ ተገኝቶአል ይገኛልም፡፡ እኔ ለማኅበረሰቡ ፣ እንደ ሀገር ለሚቆጠረው ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ እንደ መሠረት ነኝ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ቡሆው ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ይሆናል” እንዲል የእኔ ቅድስና ለእነርሱ ቅድስና መሠረት ነው፡፡ ይህን ሁሌም ላስበው ይገባል ትበል፡፡ ሁሌም ይህን አስቤ እንደ ተምሳሌቴ እንደ ቤተ ክርስቲያን ማስተዋልን ያድለኝ ዘንድ ስለሀገሬ ስለ ዓለሙ ሁሉ ሰላም በመንፈስ ሁልጊዜ ፤ በአካል እንደ ችሎታዬ መጠን በጸሎትና ራሴን በማስተዋል ለማነጽ ልተጋ ይገባኛል ትበል፡፡ ልጅም እንደ ክርስቶስ በመንፈስም በአካልም በጥበብም በእግዚአብሔርም በሰው ፊት ሊያድግ እንዲገባው ዘወትር ያስብ የእርሱ ወጣትነት ዘመን ክርስቶስ ዓለምን ለማስተማር በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተመላለሰበት ዘመን እንደሆነ ያስብ፡፡ ስለዚህም ሰውነቱን በኃጢአት ሳይተደደፍ ወጣትነቱን በንጽሕና ይጠብቃት ዘንድ ክርስቶስን ማወቅ ከቅዱሳን ጋር ማኅበርተኛ መሆንን ሊለማመድ እንደሚገባው ቆጥሮ በጸሎትም በምንባብም በተመስጦም ሊተጋ እንዲገባው ለልቡ ይንገረው፡፡ ሁሉ ነገር ከራስ ሲጀመር እጅግ መልካም ነው፡፡ የቅድስና መንገዱም ይህ ነው፡፡ ጌታስ ቢሆን ያስተማረው ይሄንኑ አይደለምን? አንተ ግብዝ አስቀድመህ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ በኋላ የወንድምህን ጉድፍ ማየት ይቻልሃል” ብሎ አላስተማረንምን? ወገኖቼ በጸሎት አንዳችንለአንዳችን እንትጋ፡፡ (ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ) @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
2500Loading...
07
#ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡ እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን? ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
3475Loading...
08
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡" ቅዱስ ፓትርያርኩ በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተናገሩት ግንቦት 21/2016 ዓም
2452Loading...
09
አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡"
3474Loading...
10
ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡ ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡ አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡ የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡ እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡ በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳  እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡ ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡ የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡ ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’ ብዬ ላመስግነው፡፡ ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡ የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ” Deacon Henok Haile #የብርሃን_እናት - ገፅ 305-308
3262Loading...
11
#ግንቦት_21 ዝ    ክ    ረ   -   ቅ    ዱ    ሳ     ን 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺    አ  ን  ኳ  ን  -   አ  ደ  ረ  ሳ  ች  ሁ!!! 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺            ✞ ደብረ ምጥማቅ ✞ ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ። እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል። አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ። ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል። ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ። ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር። እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል። እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። --------------------------------------------- ልብሷ የወርቅ መጎናጸፊያ ነው፤ በኋላዋ ደናግልን ለንጉሥ ይወስዳሉ። በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ። በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድረገሽ ትሾማቺዋልሽ። ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ። (መዝ 44፥12-16) #ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት ለሌሎች ያካፍሉ!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
6356Loading...
12
Media files
2352Loading...
13
"#እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ"    አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው። ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡ ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡ ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡ በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን! (ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን) #ይቀላቀሉን!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
2664Loading...
14
"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡ እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡" (ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)
3396Loading...
15
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡ በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
3884Loading...
16
Media files
2530Loading...
17

10Loading...
18
የከበረ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እንዲህ አትበል እንዲህ አንተ እንደምትለው አይደለም የከበረች ድንግል እመቤታችንስ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆድዋ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእርሱ ኅብረ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋር መልኳ ይለወዋወጥ ነበር። በንጹሕ ብርሌ ውስጥ ውኃ በጨመሩ ጊዜ ውኃ መስሎ እንደሚታይ ወይን ጠጅም ቢጨምሩ ያንኑ መስሎ እንደሚታይ ወይም ከውስጡ በተጨመረው ቀይም ቢሆን ቀልቶ እንደሚታይ ቅጠልያም ቢገባበት ቅጠልያ መስሎ እንደሚታይ። ድንግልም በሆድዋ ውስጥ የልጅዋ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን አበባ የምትቀላበት ጊዜ አለ እንደናርዶስም የምታብለጨልጭበት ጊዜ አለ የለመለመ ቅጠል የምትመስልበትም ጊዜ አለ ከወለደች በኋላ ግን አልተለወጠችምና ዮሴፍ በአንድ በቀድሞው ኅብረ መልኳ ተወስናለት መልኳን ተረዳ ማለት ነው አለው። በዚያን ጊዜ በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ከወርቅ የተሠራ የእመቤታችን አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ሥዕል ነበረችና አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት ዮሐንስ መልካም ተናገርክ የሚል ቃል ከእርሷ ወጣ። ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት በዚያን ጊዜ ንጉሥ አዝዞ ወርቅ ሠሪ አስመጥቶ ለከበረ ዮሐንስ የወርቅ ልሳን አሠርቶ ለሚያየው ሁሉ መታሰቢያ ምልክት ሊሆን አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥዕል ዘንድ ሰቀለው። ቅዱስ ዮሐንስንም ከዚያች ቀን ወዲህ ልሳነ ወርቅ ብሎ ጠራው አፈ ወርቅም ተብሎ እስከዛሬ ተጠራ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
2473Loading...
19
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ በዚህችም ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ አረፈ፡፡ ይህም አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናሲያ ነው እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሒዶ በመምህራን ቤት ተቀምጦ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና። ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተውለት ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ። በዚያም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ዮሐንስን አያቸው ወደ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታለቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደ አንተ ተልከናልና ዕወቅ እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ። ሁለተኛውም እኔም በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል። ጻድቅ ሲሲኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንደሚሾም ዐወቀ። ከዚህም በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጐመ። በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ አለው የቅዱስ ዮሐንስም ልቡ ተጽናንቶ ጌታዬ አንተ ማነህ ግርማህ አስፈርቶኛልና አለው የእግዚአብሔር መልአክም ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ። አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በየማዕረጋቸው የሚያዝህንም አድርግ የእግዚአብሐር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም አለው። ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው በማግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው። የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቍስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚአደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኤጲስቆጶሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፉትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም። የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት አውዶክስያም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የደኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት። ቍጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንደሚገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፉ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሀድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አስተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው። የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም። መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቍስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ። ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልእክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት። ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደአረፈና ሥጋውንም ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ እንደአመጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት። ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውድክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት። ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታአምራትን ገለጠ። ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።
2182Loading...
20
ያሬድ ነጎድጓድን ..ከደመናት ተውሶ ዜማን ....ከመላዕክቱ ማዕድ ቆርሶ ብስራትን ...ከገብርኤል ቀንሶ የሚካኤልን ሰይፍ... ተንተርሶ ያሬድ በልሳኑ እያዜመ ...በልቡ እየተቀኘ የድጓውን ባህር ቀዝፎ...በቅኔው ማዕበል እየዋኘ ከላይ....ከመላዕክቱ ነጥቆ ምድርን ..በዜማ ሰንጥቆ በመወድሱ ጎርፍ ...አጥለቅልቆ በዝማሬው ሰረገላ ...አምጥቆ መሬት ላይ አንስቶ...ከሰማይ ያደረሰን ከመላዕክቱ ጋር አቁሙ...ግዕዝና ዕዝል ያዘመረን አራራይ ብሎ በርህራሔ...በዝማሬ ሲቃ ያስለቀሰን ያሬድ ዋይ ዜማ እያለ....ዋይታን አጥፍቶ ዋይታ ልቅሶአችን ቀይሮ...ዋይ ዜማ ዝማሬን ተክቶ እንደ መላእክቱ አርቅቆ እንደ ሰውም አድምቆ ሰማይና መሬት አስተባብሮ ከመላእክቱ ጋር ደምሮ "ሃሌ ሉያ" ብሎ አዘምሮ በዜማ ቁልፉ ከፍቶ...በቅኔው በትር ገልጦ አሳየን ከላይ እግዜርን...ከዜማ ወንበር ላይ አስቀምጦ ያሬድ ኢትዮጵያ ላይ... የቆመ የዜማ ብርሃን ሻማ ጥበብን ያገኘንበት ...የመስፈሪያው አውድማ ይህ ነው ብርሃን የአለሙ...ኢትዮጵያዊ ነው ቀለሙ ከያሬድ በተጨማሪ..."ምድራዊ መልአክ" ነው ስሙ Moges Hunyalew #ሼር @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
3052Loading...
21
ሰባኬ ወንጌል መጋቤ ሃይማኖት ለቤተ ክርስቲያን ዘይደምፅ ቀርን ነባቤ ለቤተ ክርስቲያን፡፡ ያሬድ ፀሐያ ለኢትዮዽያ ዓምደ ብርሃን ለቤተ ክርስቲያን መልአክ ዘበምድር፡፡                     ትርጉም፡- ቅዱስ ያሬድ ሰባኬ ወንጌል መጋቤ ሃይማኖት ለቤተ ክርስቲያንም የሚመሰክር መለከት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፀሐይ የብርሃንም ምሰሶ በምድር ላይ ያለ መልአክ ነው፡፡
2901Loading...
22
Media files
3041Loading...
23
#ግንቦት_11 #ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅድስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት። ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ። ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው። ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ። በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ። ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ። ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ። ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው። የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም። በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም። ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው። ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ። ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
2202Loading...
24
#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል። እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል። የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና። በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል። ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።” ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ። የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ። በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)። በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል። አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163) @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
3113Loading...
"ትልቁን በትንሹ አትጋርድ!" በእውቀታቸው የተከበሩትና በትህትናቸው የሚወደዱት መንፈሳዊው መምህር የማለዳውን ትምህርት ለተማሪዎቻቸው ሰጥተው እንደጨረሱ ተማሪዎቻቸውን አሰናብተው በጥሞና ቆመው አድማሱን አሻግረው በሃሳብ እያስተዋሉ ሳለ ከተማሪዎቻቸው አንዱ "መምህር አንድ ጉዳይ አስጨንቆኝ ልጠይቅ ነው የመጣሁ" በማለት ከሄዱበት የሃሳብ አለም መለሳቸው መምህሩም ወደ ተማሪያቸው ዞር ብለው እያዩት "ጉዳዩ አስጨንቆህ ሳይሆን በጉዳዩ አንተ ተጨንቀህ ነው ፡፡ የሆነስ ሆነና ምን እንደሆነ ንገረኝ" ተማሪውም "እንዴት መሰሎዎ መምህር የቅዱስ ቃሉ ምስጢር እንዲገለጥልኝ እሻለሁ ይሁን እንጂ እለት በእለት እንዳላጠና እንቅፋት ገጥሞኛል ..." መንፈሳዊው መምህር በጣቶቻቸው ጢማቸውን ሳብ ሳብ እያደረጉ "እንቅፋት እንደገጠመህ አመንክ ፡፡መልካም እንቅፋቱ ምንድነው? " ተማሪው ቀጠለ "የምኖረው ከወንድም እህቶቼ ጋር እናትና አባቴን ጨምሮ በአንድ ትንሽ ጎጆ ቤት ውስጥ ነው እናም ቃሉን ለማጥናት ጥሞናና ጸጥታ የማገኝበት የአፍታ ጊዜ ስለሌለ ተቸግሬያለሁ ፡፡ ምን ባደርግ ይሻላል?" ችግሩን በደንብ አድምጠው የተረዱት መምህርም የተማሪያቸውን ትከሻ በፍቅር አሸት አሸት እያደረጉ "እስቲ አንድ አፍታ ወደጉዋሮ ዞር ዞር እንበል ምናልባት አንዳች ነገር ይገለጥልን ይሆናል" ብለው ወደ ውጭ አብረው ወጡ፡፡ "እስቲ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት" አሉት "ምን ይታይሃል? " "ወሰን የሌለው ሰፊ ሰማይ" ተማሪው መለሰ "አሁን ደሞ እጅህን አይኖችህ ፊት ጋርደህ ወደላይ ተመልከት፡፡ ምንድነው የሚታይህ?" "እጄ ብቻ" "በደንብ አይተህ ንገረኝ" ብለው በቆመበት ትተውት ጥቂት እርምጃ እንደተራመዱ "መምህር ከእጄ መዳፍ እና ጣት ውጭ ምንም አይታየኝም" እርምጃቸውን ሳያቋርጡ "አየህ ልጄ ወሰን አልባውን ትልቁን ሰማይ ማየት ያልቻልከው በትንሿ እጅህ አይንህን ስለሸፈንክ ነው ልክ እንደዚሁ ከቤተሰቦችህ ጋር በትንሽ ጎጆ መኖርህን መንፈሳዊውን እውቀት ልብህ እንዳትረዳ ጋረድክ ፥ በነሱ ጨዋታና አንድ ላይ አብሮ በመኖር ፍቅር ውስጥ የቅዱስ ቃሉን ፍቺ መገለጥ ፈልግ . . ."ትልቁን በትንሹ አትጋርድ" እኔም አልኩኝ « …ወሰን አልባውን የልባችን ቁልፍ ያላገኘነው የሌሎችን በመናፈቅ ነው» (ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተገኘ)
Hammasini ko'rsatish...
1
#ዕርገት #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡ ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡     እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡ ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡ ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡ (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
Hammasini ko'rsatish...
3👍 2
#የንጉሥ_ግብዣ_አለ_ተጠርተሃል_እንዳትቀር ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትራችሁ የምትመጡ ይህን ልመናዬን ስሙ፤ ሰነፍ የኾኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድን አስፈላጊነት አስተምሯቸው፡፡ የትምህርቷን ውበት ቀምሳችኋልና እናንተ ያወቃችሁትን ሳያውቁ እንዳይቀሩ፡፡ ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ የነፍስ ፍርድ ቤት አይደለችም። የኃጢአትን ስርዬት ትሰጣለች እንጂ ኃጢአትን አትፈርድም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደምናገኘው ምስጋና በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ደስተኞች ደስታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ የሚጨነቁት፤ ያዘኑት፣ ሰላምን ያገኛሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፤ የተቸገሩ ሰዎች እፎይታ ያገኛሉ፤ ኹሉም ከተሸከሙት ያርፋሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ኹሉን ታቅፋለች፡፡ ውስጥ ከሆንክ ተኩላው አይገባም፣ ብትሄድ ግን አራዊቶች ይይዙሃል፡፡ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፣ ከቤተክርስቲያን የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን መዳንህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከድንጋይ ትከብዳለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከአለም ትስፋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አታረጅም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እራሷን ታድሳለች፡፡ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ በመከራና በኃጢአታችሁ የከበደ ኹሉ' ወደ እኔ ኑ" ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡" (ማቴ ፲፩፥፳፰) ይህንን ድምጽ ከመስማት የበለጠ ምን ደስታን ሊሰጠን ይችላል? ከዚህ ግብዣ የበለጠ ጣፋጭ ምንድነው? ጌታ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጠራችሁ ለታላቅ ግብዣ ነው፡፡ ከትግል ወደ እረፍት፣ ከስቃይ ወደ እፎይታ ያሸጋግራችኋል፡፡ ከኃጢአታችሁ ሸክም ያገላግላችኋል፡፡ ጭንቀትን በምስጋና፣ ሀዘንንም በደስታ ይፈውሳል፡፡ ለክርስቶስ ከሚኖረው በቀር በእውነት ነጻ፣ በእውነት ደስተኛ የሆነ ማን ነው? እንዲህ ያለው ሰው ክፋትን ኹሉ ያሸንፋል ምንም አይፈራም! ቤተ ክርስቲያን ለኹሉም መጠጊያ ሆና ቆማለች፡፡ የአምላክን ትዕዛዝ የምትፈጽም መልካም ሰው ከሆንክ ቅድስናህን ለመጠበቅ ግባ፤ ኃጢአተኛ ከሆንህ መዳንን ለማግኘት እርምጃህን ፈጠን አድርገው:: የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይሰሙስ እንዴት ነፍስን ወደ መልካም መንገድ መምራት ይቻላል? የእግዚአብሔር ቃል 'ብርሃን' በመባል ይጠራል፤ ፀሐይ ከምታፈልቀውና እኛም ከምናየው ብርሃን፣ እጅግ በጣም የከበረ ብርሃን፣ የነፍሳችንን ጥልቀት የሚያበራ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ እውነት እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው::" ከእናንተ መካከል በታማኝነት ቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉ፤ 'ስራ በዛብኝ፣ ልመጣ አልችልም' እንዳይሉ ሌሎቹን ምከሩ፡፡ ወደ ንጉሱ ግብዣ የተጋበዙ ግን መምጣት ያልቻሉትን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ አንደኛው አምስት ጥማድ በሬዎችን ሊገዛ እንደሄደ ተናገረ፣ ሌላው አዲስ መሬትን ሊገዛ እንደሄደ ሲናገር ሌላው ደግሞ ሚስት ማግባቱን ተናገረ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ንጉሡ ግብዣውን ንቀው ስለቀሩ የሚታገሳቸው ይመስልሃል? እናም ንጉሡን በሰበብ አስባቡ አታናዱት፡፡ ከጊዜህ ላይ አንድ ሰዓት ያህል እንኳን መቆጠብ ያቅትሃል? ቤተክርስቲያንን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሥራ መሄድ በእውነት ይህን ያህል ከባድ ነውን? አንድ ሰው ወርቅ፣ ብር፣ ማር ወይም ወይን በነጻ እየሰጠ ነው ቢባል፤ ማንም ሳይቀድማችሁ ለመድረስ አትቸኩልም? ነገር ግን፣ ከወርቅ የሚበልጥ፣ ከማርም ከወተትም የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማድመጥ ወደ ቤተክርስቲያን የምትመጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡ ስለዚህም፣ ይህን ችላ ማለታችሁን አውግዣለሁ፤ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ያላችሁን ግድየለሽነት እቃወማለሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቶቿ በመራቃችሁ፣ በውስጣችሁ የእግዚአብሔር ፍራቻ የለም፤ እግዚአብሔርን የማትፈራ ነፍስም ለኃጢአት የተገዛች ትሆናለችና ነፍሳችንን እንጠብቃት፡፡ (#የነፍስ_ምግብ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው - ገጽ 105-107) #ይቀላቀሉን!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Hammasini ko'rsatish...
4👍 1
#ህዳር_26 ዝ ክ ረ - ቅ ዱ ሳ ን በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 እንኳን ለታላቁ ጻድቅ አቡነ ሃብተ ማርያም አመታዊ ክበረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ✞ አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ ✞ እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው። "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው። ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል። ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች። በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች። እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር። ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች። ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች። ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ። ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር። የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል። ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ። ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል። የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል። ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል። በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም። ➠ ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ። ➠ በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ። (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው) ➠ በ40 ቀናት : ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ። ➠ ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው። ➠ በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ። (ካህን ናቸውና) ➠ ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ። ➠ በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም። በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር። ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው። "1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: 2.ስለ ምናኔሕ: 3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: 4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: 5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: 6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: 7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ።" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ። በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው። ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው። ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው። ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች። በዝማሬም ወሰዷት። {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት።} አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን። --------------------------------------------- "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና። ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና። ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ። በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል። አንደበቱም ፍርድን ይናገራል። የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው። በእርምጃውም አይሰናከልም።" (መዝ. 36:28-31) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> #ስንክሳር_ዘወርሃ_ህዳር ለወዳጅዎ ያካፍሉ!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 2👏 1
ተወዳጆች ሆይ አንድ የልብ ምክር አለኝና አድምጡኝ፦
ወዳጄ የቤተሰብ ሓላፊ ከሆንህ፡- እኔ ለቤተሰቤ እንደ ኢዮብ ካህን ነኝ ስለዚህ በመንፈስ ሁል ጊዜ፤ በአካል ደግሞ እንደ ችሎታዬ መጠን ስለራሴ ምክንያቱም በመልካም ማስተዋል ቤተሰቤን እመራ ዘንድ ስለቤተሰቤ ምክንያቱም ቤተሰቤ በኃጢአት ምክንያት አእምሮው እንዳይቆሽሽ በራስ መተማመን እንዳያጣ በማስተዋልና እግዚአብሔርን በመፍራት እንዲመላለሱ ስለሀገሬ ሰዎች ደግሞ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ማስተዋልንና እርስ በእርስ መግባባትን እንዲሰጣቸው ፍቅር እንድትነግሥ ስለዓለሙ ሁሉ ደግሞ “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” እንድንል ጌታ እንዳስተማረን የምንኖርባት ዓለም ፈቃዱን ለማድረግ እንደሚተጉ መላእክት ለመልካም ሥራ እንዲበረቱ በጸሎት መትጋት አለብኝ ብለህ ለልብህ ንገረው፡፡ ለቤተሰባቸው እማወራ ለሆኑ እናቶችና ሚስቶች ደግሞ ለልባቸው እንዲህ ብለው ይንገሩ፡- እኔ ለቤተሰቤ አካሉ ነኝ፡፡ በእርግጥም ባለቤቴ ራሴ ነው እኔም አካሉ ነኝ ልጆቼም ከእኔ የወጡ የአካሌ ክፋዮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሳራን “ካንቺ ሕዝብና አሕዛብ ይወጣሉ” እንደተባለች ከእኔ ማኅበረሱ ተገኝቶአል ይገኛልም፡፡ እኔ ለማኅበረሰቡ ፣ እንደ ሀገር ለሚቆጠረው ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ እንደ መሠረት ነኝ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ቡሆው ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ይሆናል” እንዲል የእኔ ቅድስና ለእነርሱ ቅድስና መሠረት ነው፡፡ ይህን ሁሌም ላስበው ይገባል ትበል፡፡ ሁሌም ይህን አስቤ እንደ ተምሳሌቴ እንደ ቤተ ክርስቲያን ማስተዋልን ያድለኝ ዘንድ ስለሀገሬ ስለ ዓለሙ ሁሉ ሰላም በመንፈስ ሁልጊዜ ፤ በአካል እንደ ችሎታዬ መጠን በጸሎትና ራሴን በማስተዋል ለማነጽ ልተጋ ይገባኛል ትበል፡፡ ልጅም እንደ ክርስቶስ በመንፈስም በአካልም በጥበብም በእግዚአብሔርም በሰው ፊት ሊያድግ እንዲገባው ዘወትር ያስብ የእርሱ ወጣትነት ዘመን ክርስቶስ ዓለምን ለማስተማር በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተመላለሰበት ዘመን እንደሆነ ያስብ፡፡ ስለዚህም ሰውነቱን በኃጢአት ሳይተደደፍ ወጣትነቱን በንጽሕና ይጠብቃት ዘንድ ክርስቶስን ማወቅ ከቅዱሳን ጋር ማኅበርተኛ መሆንን ሊለማመድ እንደሚገባው ቆጥሮ በጸሎትም በምንባብም በተመስጦም ሊተጋ እንዲገባው ለልቡ ይንገረው፡፡ ሁሉ ነገር ከራስ ሲጀመር እጅግ መልካም ነው፡፡ የቅድስና መንገዱም ይህ ነው፡፡ ጌታስ ቢሆን ያስተማረው ይሄንኑ አይደለምን? አንተ ግብዝ አስቀድመህ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ በኋላ የወንድምህን ጉድፍ ማየት ይቻልሃል” ብሎ አላስተማረንምን? ወገኖቼ በጸሎት አንዳችንለአንዳችን እንትጋ፡፡ (ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ) @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Hammasini ko'rsatish...
👍 2🥰 2
#ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡ እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን? ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡" ቅዱስ ፓትርያርኩ በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተናገሩት ግንቦት 21/2016 ዓም
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡"
Hammasini ko'rsatish...
👍 4🥰 1

3👍 1