cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ቤተ- ተክለ ሃይማኖት"ወኢያኅጥኦሙ አምዘ ፈቀዱ።"

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
868
Obunachilar
+124 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከግንቦት 20-25 በነዚህ ቀናት በደብረ ምጥማቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰራው ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው የነበሩ ምእመናን በመንፈስ ቅዱስ ተመልተው አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በታላቅ ቃል አመሰገኗት:: በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአርያም ንግሥት የሰማይና የምድር እመቤት የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ከእኛም ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር አሜን! 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 በሰሚዐ ዜናሆሙ ለፃድቃን ይትፌሥሑ አሕዛብ በሰሚዐ ዜናሆሙ ለቅዱሳን ይትፌሥሑ ኃጥኣን በሰሚዐ ዜናሆሙ ለፍሡሓን አንፈርአፁ ኅዙናን በሰሚዐ ዜናሆሙ ለትጉኃን ይነቅሁ ሐካያን 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 ❖ ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን ➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ❖ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ ➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን) ❖ አሠሮ ለሰይጣን ➠(ሰይንን አሠረው) ❖ አግዓዞ ለአዳም ➠(አዳምን ነጻ አወጣው) ❖ ሰላም ➠(ፍቅር አንድነት ሆነ) ❖ እምይእዜሰ ➠(ከእንግዲህስ) ❖ ኮነ ➠(ሆነ) ❖ ፍሥሐ ወሰላም። ➠(ደስታ እና ሰላም) 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 ዕለት ዕለት የሚደርሶትን መአድ ለብቻ መመገብ በእውነት ክርስትና አይደለምና ሌሎችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች በመላክ ወደዚህ ቤተ ተክለ ሃይማኖት የቴሌግራም ገጽ ይጋብዙ (አድ) በማድረግ ቤተሰብ ያድርጓቸው። 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...
🔹ዜና ልደተ ሀብተ ማርያም🔹 🌸🌸ክፍል አንድ🌸🌸 🔹አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከግንቦት ሃያ እስከ ሃያ ስድስት በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ለአንድ ሱባዔ የሚነበበውና የሚተረጓመው የኢትዮጵያዊው ኮከብ አቡነ ሀብተ ማርያም ገድል ይኽ ነው። 🔹ዛሬ የምንነግራችሁ የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያምን ዜና ልደት ነውና በዚህ ኢትዮጵያዊ መወለድ ዜና ደስ ይበላችሁ። 🔹የዚህን ኢትዮጵያዊ ዜና በማንበባችን፣ በመናገራችንና በማስተማራችን የምናገኘው ጥቅም ብዙ ነውና፡፡ 🔹የአባታችንን ነገር የሚናገረውን ገድል ለማንበብና ለመስማት በመውደድንና በመፋጠናችን የሚገኘው ርዳታ በእውነት ያለ ሐሰት እጅግ ታላቅ ነው፡፡ 🔹ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፡- “ወኵሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ ተጽሕፈ - የተጻፈው ኹሉ ለእኛ ምክር ለእኛ እዝናት ሊኾን ተጽፏል” አለ (ሮሜ.15፡4)፤ “ዝንቱ ኵሉ ዘረከቦሙ ለእልክቱ ምሳሌ ተጽሕፈ ለአእምሮ ወለተግሣጽ ዚአነ እለ በድኅረ መዋእል - እነዚያን ያገኛቸው መከራ ኹሉ በኋላ ዘመን ለምንነሣ ለእኛ ምክር እዝናት ሊኾን ተጽፏል” (1ኛ ቆሮ.10፡11)፡፡ 🔹በእውነቱ ከሆነ የአባታችንን አብነ ሀብተ ማርያም ዜና የኹሉም ዓይነት መድኃኒቶች ግምጃ ቤት ነው፡፡ 🔹በዓለም ያሉ የመቅሰፍታትን፣ የወረርሽኝና ተሰቦ በሽታ በተለይ በዚህ ዘመን ያለውን መቅሰፍት ይሽርለት ዘንድ የሚሻ ሰው በዚህ ጻድቅ ግምጃ ቤት ውስጥ ፈጣሪ ከሰጠው ቃል ኪዳን ብቻ አምኖ ጽኑ መድኃኒትን ያገኛል፡፡ 🔹የጻድቁን ዜና የምትሰማ ነፍስ በዓለም ያለ ደዌ ሥጋና ነፍስ አያስፈራትም፣ በማዕጠንቱ ዕጣን ሽታ ፍርሃቱን ያርቃል፣ ጠብሉን ጠጥቶ ከደዌ ሥጋ ነፍስ ይፈወሳል፣ ገድሉን አንብቦ አጋንንትን ለመጣል፣ መከራን ለመታገስ፣ ጽናትን ለመማር፣ ከጻድቁ ቃል ኪዳን የሚገኘውን መድኃኒቱን ከዚህ ጻድቅ ያገኛል፡፡ 🔹በከፍተኛ ጽኑ ደዌ ውስጥ ያለ፣ በጽኑ ሥጋዊ ሕመምም የተሠቃየ የጻድቁን ዜና ሲሰማ ይፈወሳል። 🔹ማነው ታዲያ ይኽን በረከት ለማግኘት ዜናውን ለመስማትና ለማሰማት የሚፋጠንና የሚተጋ? አንሆ መፈውሰ ነፍስ ወመፈውሰ ሥጋ የሆነ ዜና ልደተ አቡነ ሀብተ ማርያምን ስሙ፣ ላልሰሙም አሰሙ። የጻድቁ ልጆች ይኽን ገጽ ለ26 ሰው ሼር ያደርጋሉ....... 🔹አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ትውልድ ሀገር የራውእይ የምትባል ምስራቃዊት ሀገር ውስጥ ሲሆን የኢትዮጵያ ንጉስ እስክንድር በነገሠ በሺ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት ዓመተ ምህረት ነው። በዚህችም ሀገር ፍሬ ብሩክ የሚባል አንድ ደግ፣ ርሕሩና ቸር ሰው ነበር፡፡ ይኸውም ከከበሩም ሰዎች ተለይቶ ብዙ ገንዘብ ያለው ባለ ጸጋ ነበር፡፡ 🔹ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር ምንም ምድራዊ ጸጋ በዝቶለት ሀብታም ቢባልም መንፈሳዊ ሥራ ካልሰራበት ነፍሳዊ ደሀ ይሆንበታል፣ ፍሬ ብሩክ ግን በገንዘቡ የሚመጸውት፣ ደሀ የሚያበላ፣ የሚያጠጣ፣ የታረዘ የሚያለብስ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዳ በሁሉ ነገር ፈጥኖ የሚደርስ ቸር ነበር። 🔹በህጋዊ ጋብቻ ስሟ ዮስቴና የምትባል እጅግ ደመ ግቡ፣ ምጽዋትን ወዳጅ፣ ቡርክት ሴት አገባ ይህችውም ሴት በደግ ሥራ ሁሉ የተሸለመች ያጌጠች ነበረች፡፡ 🔹ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ባለው ቃል መሠረት በቃለ እግዚአብሔር የተጋች ከከንቱ ነገር የራቀች ለቃለ እግዚአብሔር የተጋች ሌት ተቀን ከቤተ ክርስቲያን የማትጠፋ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን የምትካፈል ደግ ሴት ነበረች። 🔹እነዲህ ባለ ደግ ሥራ ሳለች መንፈሳዊ ሀሳብ እንዲህ ሲል ተነሳባት። መንፈሳዊ ሀሳብ ስናስብ ከፊታችን መንፈሳዊ ነገር ነው የሚገጥመንና ይኽችም ቅድስት እግዚአብሔር መልካም ነገር ሊነግራት አስቦ መንፈሳዊ ነገር አሳሰበት። 🔹ሃሳቧም "ለአንቺ በዚህ ዓለም መኖር ምን ይረባሻል ዛሬ የሚያልፍ የሚጠፋ ነውና የሚመሰገንበት ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ሌላ ዓለም ይገለጣልና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢነዳ በነፍሱ ከተጎዳ ምን ይጠቅመዋል እንዳለ” ማቴ. 16÷26፣ ማር. 10÷36፡፡ ለአንቺ ግን በሰማይ ጸንቶ መኖርን ሁለተኛዋን ሀገር መያዝ ይሻላል" የሚል ሃሳብ መጣባት፡፡ 🔹ይህን ካሰበች በኋላ ፈጥና ተነስታ በሌሊት ከቤት በመውጣት በሀገሯ አንፃር ትይዩ ወደ ሆነው ከጅቦች፣ ከነብሮች፣ ከዓሳማዎች፣ ከጦጦችና ከዝንጀሮዎች በስተቀር ምንም ምን ወደ ማይኖርበት በረሀ ደረሰች፡፡ 🔹በዚያም ደጃፏ ያልተዘጋ ትንሽ ዋሻ አገኘች፡፡ በዋሻው ውስጥም መዝሙረ ዳዊትን በአንክሮ የሚደግም ክቡር ባህታዊ አየች ባየችውም ጊዜ ደነገጠች እርሱም ሴቲቱን ባያት ጊዜ ፍርሀት መንቀጥቀጥ በላዩ ላይ ወረደበት፡፡ 🔹መጀመሪያ ስትገባ የጋኔን ምትሀት መስላው ነበርና ሰው መሆኗን ባወቀና በተረዳ ጊዜ ተቆጣት፡፡ 🔹እሷም ቤቴን ንብረቴን ያለኝን ሁሉ ትቼ መጥቻለሁ በዓለም ውስጥ ያለውን ሁሉ ንቄ እመንን ዘንድ እወዳለሁና ስለዚህም ወደዚህ ምድረ በዳ መጣሁ አለችው፡፡ 🔹ይህም ባህታዊ በትህትናና በፈሪሀ እግዚአብሔር ይህን የሚያስደንቅ መልካም መልስ በመለሰችለት ጊዜ አንድ ሰዓት ያህል በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት መንፈሳዊ ሃሰበ አሰበ። 🔹እንዲህም አላት ምንኩስናስ የለሽም ነገር ግን በፍቅር በአንድነት ወደ ቤትሽ ወደ ህጋዊ ባልሽ በሰላም ተመለሽ አላት። ለዛሬ ይቆየን ...ተከታዩን በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁ። የጻድቁ ወዳጅ ለ26 ሰው ሼር ያደርጋል! 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 ዕለት ዕለት የሚደርሶትን መአድ ለብቻ መመገብ በእውነት ክርስትና አይደለምና ሌሎችን የጻድቁ ልጆች በመላክ ወደዚህ ቤተ ተክለ ሃይማኖት የቴሌግራም ገጽ ይጋብዙ (አድ) በማድረግ ቤተሰብ ያድርጓቸው። 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለጻዱቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የልደት በዓል አደረሳችሁ! የፊታችን ግንቦት 26 የሚከበረውን የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም የልደታቸውን በዓል በማስመልከት ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ7 ቀን አንድ ሱባዔ ገድላቸውን በማንበብና በመተርጎም በገድል ቤት ሰፊ አገልግሎት ይሰጣል። የአባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ዐጽም ባረፈት ደብረ ሊባኖስ ገዳም ላይ የአባታችን ገድል በሚነበብተ ጊዜ ታላላቅ ተአምራት ይደረጋል። አጋንንት ይወጣሉ፣ ደዌያት ይርቃሉ፣ እውራን ይፈወሳሉ፣ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፣ ሙታን ይነሣሉ። በተለይ በተለይ አባታችን ሀብተ ማርያም በደብረ ሊባኖስ ለመቀበራቸው ምክንያት በደብረ ሊባኖስም ሆነ በሀገራችን ለሚነሱ አምስቱ መቅሰፍታት መድኃኒት መሆናቸው ነው። የቤተ ተክለ ሃይማኖት ቻናል ተከታታዮችም ይህ በረከት እንዳይቀርባቸው በተከታታይ ለአንድ ሱባዔ የአባታችንን ገድል ይቀርባልና ይከታተሉ። ታዲያ እርሶም ይህን የጻድቁን መአድ ለብቻ መመገብ በእውነቱ ክርስትናም አይደለምና ለሌሎች በመላክና አድ በማድረግ ቤተሰብ ያድርጓቸው። 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከግንቦት 20-25 በነዚህ ቀናት በደብረ ምጥማቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰራው ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው የነበሩ ምእመናን በመንፈስ ቅዱስ ተመልተው አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በታላቅ ቃል አመሰገኗት:: በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስመታየቱ የክርስቲያ ወገኖች ሁሉም በታላቅ በዓልን ያደርጋሉ። እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕርጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥናዋ ገናናነት ይሰግዳሉ ስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል "አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ"። ሁለተኛም ሰማዕታትም በየማረጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል። ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጠው ይህ ቅዱስ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋና ያቀርብላታል። ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ። ኄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመታቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰብትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር። እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልጀራው "ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል። እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም አምላክ በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 እርሷ እመ ብርሃን ፦ ዓለማትን ሁሉ በመዳፉ የያዘውን ንጉሥ በእጆቿ አቅፋ – በክርኖቿ ደግፋ የያዘች ፣ ሁሉን በመግቦቱ የሚያስተዳድረውን አባት ከደረቷ አስጠግታ – ጡቶቿን አጥብታ ያኖረች፣ ፍጥረትን ሁሉ በመንገድ የሚመራ እረኛ በጀርባዋ አዝላ – ከኋላዋ አስከትላ የታየች፣ ፈጣሪዋን የወለደች ፡ አምላኳን ያሳደገች፡ ጌታዋን ያዘዘች ናት፤ ስለዚህ ብቻዋን እመአምላክ ፣ብቻዋን ወላዲተ ቃል፣ ብቻዋን ማኅደረ መለኮት በመሆኗ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ብርህት ከመፀሓይ እያልን፣ በሁሉ እንደተቀደሰች እየመሰከርን "ንጽሕት ወብርህት ወቅድስት በኲሉ" እንበላት! 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 በሰሚዐ ዜናሆሙ ለፃድቃን ይትፌሥሑ አሕዛብ በሰሚዐ ዜናሆሙ ለቅዱሳን ይትፌሥሑ ኃጥኣን በሰሚዐ ዜናሆሙ ለፍሡሓን አንፈርአፁ ኅዙናን በሰሚዐ ዜናሆሙ ለትጉኃን ይነቅሁ ሐካያን 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 ❖ ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን ➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ❖ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ ➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን) ❖ አሠሮ ለሰይጣን ➠(ሰይንን አሠረው) ❖ አግዓዞ ለአዳም ➠(አዳምን ነጻ አወጣው) ❖ ሰላም ➠(ፍቅር አንድነት ሆነ) ❖ እምይእዜሰ ➠(ከእንግዲህስ) ❖ ኮነ ➠(ሆነ) ❖ ፍሥሐ ወሰላም። ➠(ደስታ እና ሰላም) 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 ዕለት ዕለት የሚደርሶትን መአድ ለብቻ መመገብ በእውነት ክርስትና አይደለምና ሌሎችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች በመላክ ወደዚህ ቤተ ተክለ ሃይማኖት የቴሌግራም ገጽ ይጋብዙ (አድ) በማድረግ ቤተሰብ ያድርጓቸው። 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አምላክ በሚሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከግንቦት 21 እስከ 25 የእመቤታችንን በዓል (ምሰሶ አቁመው፥ አጎበር ጥለው፥ ድንኳን ተክለው፥ ድባብ ዘርግተው ያከብራሉ፤ እመቤታችንም ከቅዱሳን ጋር በመገኘት ትባርካቸዋለች፡፡ ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ቀን ግንቦት 21 ና 22 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡ በሦስተኛው ቀን ግንቦት 23 ቀን ደብረ ምጥማቅ በተባለች ቦታ የታየችበት ነው፡፡ በአራተኛው ቀን ግንቦት 24 ተሰዳ ግብጽ የገባችበት ቀን ነው፤ /ኢሣ.1 9፥11፣ ማቴ.2፥13-15/ በአምስተኛው ቀን ግንቦት 25 ልጇ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የደረቁ በትሮችን ተክሎ ያለመለመበት በዓል ነው፡፡ እነዚህም ከላይ ያየናቸውን የደብረ ምጥማቅ በዓላት (ከግንቦት 21-25) በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በግብፅ ተነሥቶ የነበረው ንጉሥ የግብጽ ክርስቲያኖች በዓሉን እንዳያከብሩ ይከለክላቸው እንደነበረ ይነገራል። ኢትዮጵያውያንም ይህንን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ወደ ግብፅ ይሄዱ ነበር ፤ በዚሁ ዘመን የነበረው ንጉሥም አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለመጽናኛ እንዲሆን በሃገራችን እንዲከበር ታላቅ ፍላጎት ነበረው። በዚህም የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያምን በዚህ አገር ተክሎ በዓሏን ማክበር ጀመረ፤ እመቤታችንም ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጠችው፤ ይኸው ቃል ኪዳኗ ሳይታጠፍ በጻድቃኔ ማርያም እስከ ዛሬ ድረስ ስፍር ቊጥር የሌለው ብዙ ተዓምራትና የምሕረት ሥራ የሚፈጸምባት ቅዱስ ቦታ ኾና ይገኛል፡፡ ዛሬም ቡዙ ምእመናን ወደዛ በመጎዝ ታላቅ በዓል ያደርጋሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ያሳትፈን ለዘለዓለሙ አሜን። እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ! ❖ ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን ➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ❖ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ ➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን) ❖ አሠሮ ለሰይጣን ➠(ሰይጣንን አሠረው) ❖ አግዓዞ ለአዳም ➠(አዳምን ነጻ አወጣው) ❖ ሰላም ➠(ፍቅር አንድነት ሆነ) ❖ እምይእዜሰ ➠(ከእንግዲህስ) ❖ ኮነ ➠(ሆነ) ❖ ፍሥሐ ወሰላም። ➠(ደስታ እና ሰላም) 👇👇👇👇👇 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከግንቦት 20-25 በነዚህ ቀናት በደብረ ምጥማቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሰራው ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው የነበሩ ምእመናን በመንፈስ ቅዱስ ተመልተው አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በታላቅ ቃል አመሰገኗት:: ብዙዎችም ደስታቸውን ወሰን አልፋ ያለቅሱ ነበር:: ብዙዎችም እሷ ለሰጣቸው አምላካቸው ይሰግዱ ነበር:: ብዙዎችም በፍጹም መንፈሳዊ በሆነ ፍቅር ይተቃቀፉ ነበር:: ስለ ድንግል ማርያም ክብር በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ጧፍ ሻማ ችቦ አብረትው እልል ይሉ ነበር:: ስለ ሁሉ ነገር ይህን ያደረገላቸውን አምላካቸውን እያመሰገኑ ይዘምሩ ነበር:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን:: እኛም በመንፈሰ እግዚአብሔር ተሞልተን ቅድስት ድንግልን ለማመስገን ያብቃን:: ለዚህም ነው አንዳንዶች መንፈሰ እግዚአብሔር በውስጣቸው ስለሌለ በስንፍና ቃል በድፍረት በእመቤታችን ላይ የሚናገሩት:: እኛ ግን ከነሱ የተለየን ነን እናመሰግናታለን እናከብራታለን:: አንደ ሙሉ ጤነኛ ሰው እንደ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር እንደተላከው፤ እንደ ቅድስት ኤልሳቤት በመንፈስ ካልተሞላ በስተቀር እመቤታችንን ሊያመሰግናት የሚከፈት አንደበት አይኖርም። መንፈሰ እግዚአብሔር ካላደረበትም ለእመቤታችን ሊያሸበሽብ የሚችል እግርም ሆነ እጅ አይኖረውም፤ ለእመቤታችንም የጸጋ ስግደት ሊሰግድም የሚታጠፍ ጉልበት አይኖርም:: ክብርና ምስጋና ለልጇ ይሁን:: ከኃጢአታችን በንሰሐ ሳሙና ታጥበን በመንፈሰ እግዚአብሔር ተሞልተን እመቤታችንን ለማመስገን ያብቃን ለዘላለሙ አሜን:: አዲስ! በጸሎት አስቡኝ። 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 የኛ እመቤት! 👉#የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ስም ከጸሎትና ከተማጽኖ ውጪ ልንጠራት ፈጽሞ አይገባም። 👉ሥዕለ ማርያምን ከተቀደሰና ከከበረ ቦታ ውጪ በየትም ሥፍራ ልናስቀምጠው አይገባውም። 👉ሥዕለ ማርያምን ካህን ከሆኑ ዕጣን ያጥኖታል፣ ምእመን ከሆኑ መልካም ሽቱ ይቀቧታል በምስጋናም ይማጸኗታል። 👉በሥዕለ ማርያም ፊት ውሸትና ከንቱ ንግግር ሙዜቃና ጭፈራ ሲጋራና ጥንባሆ ሊያጨሱባት አይገባውም። 👉ሥዕለ ማርያም ቤታችን ኖራ ወይ ቤቶ ኖሮ አስታራቂ ሽማግሌ አይፈልጉ እንኳን ከተጣላ ሰው ከፈጣሪ ታማልደን ታስታርቀን የለ! ሥዕለ ማርያም አስታራቂያችን ናትና! 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 በሰሚዐ ዜናሆሙ ለፃድቃን ይትፌሥሑ አሕዛብ በሰሚዐ ዜናሆሙ ለቅዱሳን ይትፌሥሑ ኃጥኣን በሰሚዐ ዜናሆሙ ለፍሡሓን አንፈርአፁ ኅዙናን በሰሚዐ ዜናሆሙ ለትጉኃን ይነቅሁ ሐካያን 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 ❖ ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን ➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ❖ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ ➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን) ❖ አሠሮ ለሰይጣን ➠(ሰይንን አሠረው) ❖ አግዓዞ ለአዳም ➠(አዳምን ነጻ አወጣው) ❖ ሰላም ➠(ፍቅር አንድነት ሆነ) ❖ እምይእዜሰ ➠(ከእንግዲህስ) ❖ ኮነ ➠(ሆነ) ❖ ፍሥሐ ወሰላም። ➠(ደስታ እና ሰላም) 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 ዕለት ዕለት የሚደርሶትን መአድ ለብቻ መመገብ በእውነት ክርስትና አይደለምና ሌሎችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች በመላክ ወደዚህ ቤተ ተክለ ሃይማኖት የቴሌግራም ገጽ ይጋብዙ (አድ) በማድረግ ቤተሰብ ያድርጓቸው። 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት አሥራ አራት በዚህች ቀን ከመንፈሳዊ ሐዋርያት ጋር አንድነት ያለው የከበረ አባት ጳኩሚስ አረፈ:: ይህ አባታ መነኮሳት በአንድነት ማኅበር ተሰባስበው በእጃቸው ሠርተው በአንድነት እንዲበሉ ሥርዓትን የሠራ ነው። በገዳሙ ማኅበር ያለ መነኲሴ ከአበምኔቱ ፍቃድ ውጪ ከገዳም መውጣት እንደማይችሉ ሥርዓትን አስቀመጠ። መነኲሴ በጸሎት ጽሙዳን ሆኖ እንዲኖሩ ዓለማዊ ሥርዓት ውስጥ እንዳይገቡ አነጋገራቸው አለባበሳቸው ምንም ያለተቀላቀለበት ዠንጉርጉር እንዳይለብሱ እንዳይጫሙ ሥርዓትን የሰራ ነው:: ስለ ዓለም ከንቱነትና ከንቱ ውዳሴ ለመንፈሳዊ ውድቀት መነሻ እንደሆነ ያስተማረ አባት ነው:: ፍጹም በሆነ ቅድስናውም ምክንያት እግዚአብሔር አምላክ በገነት ያለች የጻድቃንን ማደርያ እንዲሁ በሲኦል የስቃይን ቦታ አሳየው:: በዚህም ክርስቲያኖች መልካም ሰርተው ገነትን እንዲዎርሱ ወደ ሲኦል ከሚመራ ሥራ እንዲታቀቡ በዘመኑ ሁሉ እያስተማረ በሰላም አረፈ:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በጸሎቱ በአማላጅነቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን:: 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 ❖ ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን ➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ❖ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ ➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን) ❖ አሠሮ ለሰይጣን ➠(ሰይጣንን አሠረው) ❖ አግዓዞ ለአዳም ➠(አዳምን ነጻ አወጣው) ❖ ሰላም ➠(ፍቅር አንድነት ሆነ) ❖ እምይእዜሰ ➠(ከእንግዲህስ) ❖ ኮነ ➠(ሆነ) ❖ ፍሥሐ ወሰላም። ➠(ደስታ እና ሰላም) 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...
🔹🔹ዜና ፍልሰተ ዐጽሙ🔹🔹 ክፍል ስድስት 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከግንቦት 6-12 ለሰባት ቀን የሚነገረው ዜና ፍልሰተ ዐጽሙ የተክለ ሃይማኖት በዓሉ ነው። 🔹🔹ተአምር🔹🔹 ግንቦት 12 የሚነበበ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ የክቡርና የቅዱስ፣ የብጹዕ ተክለ ሃይማኖት ያደረገው ተአምር ይኽ ነው። ከአቡነ ፊሊጶስ በኋላ በገድል የሚበረታ አራተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ አቡነ ሕዝቅያስ ተሾመ። አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በሌሊት በራእይ ተገለጠለትና "እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ዐጽሜ የሚፈልስበት ዘመን ደረሰ፤ ስለዚህም ፈጸጽመው። በረከቴንም ታገኝ ዘንድ ዐጽሜን ተሸከም" ይህንንም ብሎት ከእርሱ ተሠወረ። አባታችን ሕዝቅያስም ብዙ ሕዝቡን ሰበሰበ። የጻድቁንም ዐጽም ማፍለስ ጀመሩ። በዚያች ዕለትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋውን ተሸክመው በምስጋናና በማኅሌት በዓል አደረጉ። ከመጨናነቃቸው የተነሣ በአንድ ሰው ላይ ሄዱበትና እግሩ ተሰበረ። የቅዱሱም አባታችንን ዐጽሙን ባስነኩቱም ጊዜ ያን ጊዜዉኑ ዳነ። የተመለከቱትም ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። የአባታችንንም ሥጋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሲያስገቡት ያቺ ዋሻ ተናደች። ከብዙ ዓመታት በኋላ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነው ንጉሥ ይስሐቅ በነገሠ ጊዜ፤ የብጹዕ ተክለ ሃይማኖት ዜናውን ሰምቶ ተገረመ። ይኽ ንጉሥ ተገርሞም አልቀረም በታላቅ ክብር ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያንጹት አዘዘ። ቤተ ክርስቲያኑን መሥራት ፈጽመው ሥጋውን ሲያፈልሱም በዙ ድውያንን ተሰበሰቡ። በዚህች ዕለትም መቃብሩን በመዳሰስ ታለቅ ተአምር ታየ። 🔹🔹ተአምር ሁለት🔹🔹 ሰማይን ቀና ብሎ ለማየት የማይቻለው ነገር ግን ዘወትር አጎንብሶ የሚሄድ አንድ ሽባ ሰውም ነበር። ራሱንም ከፍ አድርጎ አያውቅም። ለብዙ ዘመንም ነፍሱ እየተጨነቀች ይኖር ነበር። በዚህች ዕለትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሳጥን አቅፎ በቅዱስ አባታችን አማላጅነት ወደ እግዚአብሔር ለመነ። ያን ጊዜም አጥንቶቹ ተንቋቁና ደህና ሆኖ ቀጥ ብሎ ቆመ። ወደ ቤቱም የምሕረትን አምላክ እያመሰገነ ሄደ። በላዩም ላይ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የደዌው ምልክት አልተገኘም። በዚያ የተሰበሰቡትም ሁሉ ይህንን አይተው ተአምሩን አደነቁ። 🔹🔹ተአምር ሦስት🔹🔹 በጣዕር ላይ ያለች መዳን ያልቻለች አንዲት መበለትም መጣች። የሕማሟም ምክንያት አይታወቅም። ስትቀመጥም እንዳትወድቅ አራት መደገፊያዎች ያደርጉላት ነበር። ዓይኖቿም የታወሩ ነበሩ። የሚያያት ሁሉ ይገረም ነበር፤ በሁሉም ነገር ተቸግራ ትኖር ነበረና። አባታችንን ባፈለሱበት ጊዜ ያደረገውን ተአምር ሰማች። ወንድሞች ለበቁዔትና ለበረከት ብለው ካስቀመጡት ከመቃብሩ አፈር እንዲሰጧት ለመነች። ከልብሱ ጫፍና ከመግነዙም ቆርጠው እንዲሁ አስቀምጠው ነበር። ከእርሱም ሰጧት። የመግነዙን ቁራጭ በነካችው ጊዜም፣ ንጽሕናንና ቅድስናን በለበሰው በጌጠኛው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎት ወዲያውኑ ተፈወሰች። እንደዚሁ ሁላችንን የጥምቀት ልጆችን ይፈውሰን! ከጸሐፊውና፣ ከአንባቢውና ከሰሚዎቹም ጋር ጭምር። ለዓለም ዓለም፤ አሜን፣ ወአሜን። 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 በእውቱ ከሆነ ይህንን መአድ ለብቻ መመገብ በእውነት ክርስትና አይደለምና ሌሎችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች በመላክ ወደዚህ የቴሌግራም ገጽ ይጋብዙ (አድ) በማድረግ የቤተ ተክለ ሃይማኖት ቤተሰብ ያድርጓቸው። የቤተ ተክለ ሃይማኖት ቤተሰብ ቃለ እግዚአብሔር በፍጹም አይራብም! 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 መልካም ዕለተ ሰንበት! 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 የጻድቁ ልጆች ተከታተሉ ሼር አድርጉ። 🔹🔹🌸🌸🌸🔹🔹 ❖ ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን ➠(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) ❖ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ ➠(በገናና ኃይልና ሥልጣን) ❖ አሠሮ ለሰይጣን ➠(ሰይጣንን አሠረው) ❖ አግዓዞ ለአዳም ➠(አዳምን ነጻ አወጣው) ❖ ሰላም ➠(ፍቅር አንድነት ሆነ) ❖ እምይእዜሰ ➠(ከእንግዲህስ) ❖ ኮነ ➠(ሆነ) ❖ ፍሥሐ ወሰላም። ➠(ደስታ እና ሰላም) 🔸ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል! 🥚☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️ ✅ ጠቃሚ ቻናል ለነፍስ የኦርቶዶክስ ሳይኮሎጂ ✅ ሰብስክራይብ ያድርጉ፡👇 @DebreLibanosGedam24 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
Hammasini ko'rsatish...