cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ/Fasil Kenema SC Official

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ1960 ተመሰረተ!!

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
3 879
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
+1430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የአፄዎቹ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል!!🇦🇹 ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለ2016 አመት ውድድር የቡድን ግንባታ እቅዱን ቀደም ብሎ በመጀመር አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ለሶስት አመት በሚያቆይ የውል ስምምነት አስፈርሟል:: የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፀደቀ ሲሆን በቀጣይ ከስምምነት ላይ የደረሱ ተጫዋቾች ውላቸው ሲፀድቅ የምናሳውቃችሁ ይሆናል:: ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ባስቀመጠው የአምስት አመት እቅድ ውስጥ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዋነኛ አላማቸው ቅድሚያ ቡድኑን በወጣቶች መገንባት ከዛ የዋንጫ ክብሮችን ማምጣት እንደሆነ ገልፀዋል:: የጎንደር ከተማ ከንቲባ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ ባዩህ አቡሃይ ፋሲል ከነማ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ እዚህ ስለደረሰ እኛም መሰረታዊ ስራዎችን በማስቀጠል ከደጋፊያችን ጋር የተጀመሩ የስኬት መንገዶችን በማብቃት ክለባችን ትልቅ ተቋም እናደርጋለን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል:: #አሰልጣኝ_ውበቱ_አባተ እንኳን ወደ አፄዎቹ ቤት በደህና መጣህ!! . 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹 . 🇦🇹#LIKE_COMMENT_SHARE🇦🇹 . ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ!! https://t.me/FKSCOfficial https://m.facebook.com/የፋሲል-ከነማ-ስፖርት-ክለብ-ይፋዊ-ገፅ-Fasil-Kenema-S-C-Official-Page-1597743583819217 #ሼርShare_በማድረግ_መረጃውን_ለደጋፊዎች_ያጋሩ!!
Hammasini ko'rsatish...
ፋሲል ከነማ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ይጫዎታል!! ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር አፄዎቹ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ጨዋታቸውን እንዲያደርጉ በማሰብ ስታዲየሙን ካለበት ደረጃ በማሻሻል ጨዋታዎችን ለማካሄድ ዝግጁ እንዲሆን ለማድረግ በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ኮሚቴዎች በማዋቀር ስታዲየማችን ለማደስ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ወደ ስራ መግባታቸውን እየገለፁ ስታዲየማችን የፕሪሚየር ሊግ እና የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ብቁ እስኪሆን ድረስ ስራቸውን ከመላው አለም ገሚገኙ ደጋፊዎቻችን እና አጋር ድርጅቶች ጋር ለማሳካት የስታዲየም እድሳት ጅማሮ ተደርጓል!! ፋሲል ከነማ በጎንደር አፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ ጨዋታውን ማድረጉ ከሀገር ሀገር ተዟዙሩው በርካታ ጨዋታዎችን መታደም ለማይችሉ ብሎም በስፖርቱ የከተማችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይረዳን ዘንድ ሁሉም የስፖርቱ ደጋፊ ድጋፍ እንዲያደርግ በክለባችን ስም ጥሪ እናስተላልፋለን። . 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹 . 🇦🇹#LIKE_COMMENT_SHARE🇦🇹 . ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ!! https://t.me/FKSCOfficial https://m.facebook.com/የፋሲል-ከነማ-ስፖርት-ክለብ-ይፋዊ-ገፅ-Fasil-Kenema-S-C-Official-Page-1597743583819217 #ሼርShare_በማድረግ_መረጃውን_ለደጋፊዎች_ያጋሩ!!!
Hammasini ko'rsatish...
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ/Fasil Kenema SC Official✔

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ1960 ተመሰረተ!!

🇦🇹#የፋሲል_ከነማ_ስፖርት_ክለብ_ታሪካዊ_ቀን_ሐምሌ_13_2008_ዓ_ም🇦🇹 ዛሬ ሐምሌ 13 ነው...ወደኋላ 7 ዓመት ስንመለስ የምናገኘው ታሪክ የዛሬዋ ''ሐምሌ 13'' ቀን ፋሲል ከነማ ምናልባትም ከምስረታው ቀን ጋር የምትስተካከል አንፀባራቂና የማይረሳ ድል የተጎናፀፈባት ቀን ናት፡፡ ዛሬ በምናብ ወደ ኋላ 7 አመት ተመልሰን በአፄዎቹ መንደር ''ሐምሌ 13'' የሆነውን ሁሉ ሳይሆን አባይን በጭልፋ እንደሚባለው ያችን ታሪካዊ ቀን "የሐምሌ 13" ትውስታዎቻችን በጨረፍታ ልናስታውሳችሁ ወደድን። ታዲያ እናንተም በሀሳብ መስጫ ቦታው ላይ የእናንተን ትውስታ በፁሁፍና በምስል እንድታካፍሉን ከወዲሁ ተጋብዛችኋል። ፋሲል ከነማ ከተመሰረተበት 1960 ዓ.ም ጀምሮ ዘርፈ ብዙ መሰናክሎችን፣ በርካታ ውጣ ውረዶችን እና የተለያዩ ስያሜዎችን በማስተናገድ በልጆቹ ፅናት አስደሳች የአሸናፊነት ጊዜዎችን በማሳለፍ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ፋሲል ከነማ ለበርካታ አመታት ፕሪሚየር ሊግ ለመቀላቀል ጫፍ ላይ በመድረስ ሳይሳካለት በሩን እያንኳኳ የሊጉ መግቢያ በር እንዲገባ ሳይከፈትለት ሲመለስ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል። ድንበር ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቀው ፋሲል ከነማ ባሳለፋቸው ውጣ ውረዶችና መሰናክሎች ሳይበገር ያሁሉ ድካምና ጥረት ፍሬ ያፈራው ልክ የዛሬ ሰባት አመት በዛሬዋ ቀን ''ሐምሌ 13/2008 ዓ/ም'' ነበር !! ይህ ጊዜ በተለይም ጎንደር ከፍተኛ የጭንቅ ምጥ ውስጥ የነበረችበት ወቅት ሲሆን እንኳን ለሰላማዊ እግር ኳስ ጨዋታ ቀርቶ ወጥቶ ለመግባት እንኳ አስጊ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ጎንደር ከቀለሟ በተጨማሪ መዓዛዋ አፄዎቹን ዝማሬዋ ደግሞ ፋሲል ከነማን ይሰብካል። ከተማዋ የአብራኳን ክፋይ ከደሟ ጠልቃ ከአጥንቷ ፍቃ አምጣ የወለደችውን የበኩር ልጇን ፋሲል ከነማን በድል ልትሞሽር ሽር ጉዷን አሳልጠዋለች። ደጋፊዎችም ከሚኖሩበት አካባቢ ወደ አፄ ፋሲለደስ ስታድየም መትመም ጀመሩ..በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ደጋፊዎች ድልን አጭደው የደስታ ምርትን ከሚሰበስቡበት ስፍራ ከትተዋል። ጨዋታው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከ400 በላይ የሚሆኑ የስታድየም አስተባባሪዎች ባለ አንፀባራቂ መለያ ልብስ ለብሰው በተጠንቀቅ ቆመዋል። እነዚህ አስተባባሪዎች በኢትዮጵያ የሊግ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ናቸው። በወቅቱ አፄዎቹ ፕሪሚየር ሊጉን ለመቀላቀል ጫፍ የደረሱበት ጊዜ ነው። ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት በዚች ቀን ፋሲል በሜዳው ከጠንካራው ኢትዮጵያ መድህን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ አሸንፎ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያድግበትን ትኬት የሚቆርጥበት ቀን የነበረ ሲሆን ግን ደግሞ የፋሲልን ህልም ለማጨናገፍ በርካታ የተግባር እንቅፋቶች ነበሩ... ጨዋታው እስኪጀምር ከተማውንና ህዝቡን ስትቃኝ የዋለችው ፀሀይ ዝናብ ላረገዘው ደመና ቦታዋን ለቀቀች..ዝናብ ያረገዘው ደመና የከበደው የሚመስለው ሰማይ ሆዱን ከፍቶ አፄ ፋሲለደስ ስታድየምና በከተማዋ ላይ አንዠቀዠቀው በዚህ ጊዜ ከወደ ቋራ መቀመጫ የሚታየው የደጋፊዎች ትይንት አይንን የሚስብና በግርምት እጅን በአፍ የሚያስጭን ነበር። ለዶፉ አንበገርም ያሉት ቋረኞቹ ተቃቅፈው የውቅያኖስ ሞገድ በሚመስል ጭፈራ ሲዘሉ ሰማዩ ከሚያወርደው ዝናብ ጋር ተደምሮ ወደ ላይ የሚያወጡት ጢስ የአርባ አራቱ ቤተክርስቲያን ካህናት ቋራን ከበው ከርቤና ዕጣን እያጠኑት ይመስል ነበር። ከፍተኛ ዝናብ በመዝነቡ ምክኒያት ሜዳው ላያጫውት ይችላል ቢባልም ደጋፊዎች ሜዳ ላይ የተኛውን የዝናብ ቋት በጆንያ ፣ በስፖንጅ ፣ በጀሪካን ፣ በሳፋ በመጥረጊያና በተለያዩ ቁሳቁሶች ውሃውን ከሜዳው ማስወገድ ተያያዙት። ጨዋታው በአንድ ሰዓት ዘግይቶ ሲጀመር ደጋፊዎቹ ፋሲልዬ አንተን ባየው አይኔ ሌላው ለምኔ ፣ እናሸንፋለን በፋሲል ሙሉ እምነት አለን እና በሌሎች ዝማሬዎች ድጋፋቸውን ቀጥለዋል። ጨዋታው ያለግብ በጭንቅ ቀጥሎ 77ኛው ደቂቃ ላይ ውጤትና ታሪክ የቀየረች የጭንቅላት ጎል በአመለ ሸጋው አማካይ ይስሐቅ መኩሪያ ተቆጠረች። በዚያን ቅፅበት ደጋፊዎች ያሰሙት ድምፅ ከተማዋን ከጫፍ እስከ ጫፍ አናጣት። ጨዋታው በአፄዎቹ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ!! በዚህ ጊዜ ደጋፊዎች ተቃቅፈው የደስታ እንባ አነቡ ፣ ዘመሩ ፣ በአፄዎቹ ቤት ታሪክ የፃፉ ተጫዋቾች እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ በጨቀየው ሜዳ ላይ በደረታቸው ተንሸራተቱ ፣ ደጋፊዎች ሜዳ በመግባት ደስታቸውን ከተጫዋቾቹ ጋር ገለፁ ፣ ሜዳው የሰራውን የጭቃ ሸማ ለብሰው ጮቤ ላስረገጣቸው ክለብ የደስታ ምንጭ ነህ ብለው ዘመሩለት!! አፄዎቹ ''ሐምሌ 13'' ቀንን በልባቸው ላይፍቁ አተሟት!! የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ታሪካዊ የቡድን አባላት ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኝ እና ኮችንግ ስታፉች እንዲሁም አመራሮች ለዚህች ታሪካዊ ቀን እንኳን አደረሳችሁ!! እንኳን አደረሳችሁ!! . 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹 . 🇦🇹#LIKE_COMMENT_SHARE🇦🇹 . ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ!! https://t.me/FKSCOfficial https://m.facebook.com/የፋሲል-ከነማ-ስፖርት-ክለብ-ይፋዊ-ገፅ-Fasil-Kenema-S-C-Official-Page-1597743583819217 #ሼርShare_በማድረግ_መረጃውን_ለደጋፊዎች_ያጋሩ!!!
Hammasini ko'rsatish...
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ/Fasil Kenema SC Official✔

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ1960 ተመሰረተ!!

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ፈንታውን ኪዴ እና ካህሌ ታደሰ በ2011 ዓ.ም ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከነማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ክለባቸውን ደግፈው ከባህርዳር ወደ ጎንደር በሚጓዙበት ጊዜ አውቶብስ የመገልበት አደጋ ሲደርስበት በርካቶች የመቁሰል አደጋ ሲያጋጥማቸው እነዚህ ሁለት ደጋፊዎቻችን ይወታቸውን አጠዋል ሆኖም ''የሐምሌ 13'' ዘመቻን የህይወት ዘመን ደጋፊዎች በማለት የምናስታውሳቸውን ፈንታሁን እና ካህሌን የፕላቲኒየም ደረጃ መታወቂያ በማውጣት በክብር እንድናስባቸው ያደረጉልን የክለባችን ደጋፊዎች እነሱም የፕላቲኒዩም አባሎች የሆኑት ሰናይት አማረ እና ማህሌት የኋላ ይሄን በጎ ተግባር በማሰብ ወደ ተግባር ቀይረው ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ ክብር እንሰጣለን በፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ስም ምስጋናችን ይድረስ። ''ሐምሌ 13'' የመታወቂያ ማውጣት ዘመቻውን ይቀላቀሉ ክለብዎትን በተግባር ይደግፉ!! በፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ቢሮ ቀርባችሁ መታወቂያ ማውጣት ያልቻላችሁ በሀገር እና ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ደጋፊዎች በመረጣችሁት የደጋፊዎች መታወቂያ ደረጃ ብር በማስገባት ሪሲቱን ቢልኩልን አውጥተን እንልካለን። የቴሌግራም እና ዋትሳፕ ቁጥሮች፦ 0912745674 0918770424 0912614139 0911507744 🇦🇹#እናመሰግናለን!! . 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹 . 🇦🇹#LIKE_COMMENT_SHARE🇦🇹 #ሼርShare_በማድረግ_መረጃውን_ለደጋፊዎች_ያጋሩ!!!
Hammasini ko'rsatish...
የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ደረጃውን በጠበቃ መንገድ ለማደስ ኮሜቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ ። በጎንደር ከተማ የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ደረጃውን በጠበቃ መንገድ ለማደስ ኮሜቴ ተቋቁሞ ከህብርተሰቡ ሀብት የማሰባሰብ ስራ መግባቱ ተገልጿል ። የጎንደር ከተማ ተቀደሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ እንደገለፁት ለ2016 ዓ.ም ለፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ውጤተማ ሆኖ እንዲቀጥል በፋይናንስ ፣ በእውቀትና በአደረጃጀት ለማሻሻል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ። የእግር ኳስ ወደ ከተማችን ለማምጣት ተፈላጊ መስፈርቱን በሚያሟላ መንገድ የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ለማሳደስ ኮሜቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ከንቲባው ገልጸዋል ። ጎንደር ስፖርት አፍቃሪያን ያሉባት ከተማ ናት ያሉት ተቀደሚ ምክትል ከንቲባው ስታዲየሙ መታደስ ለከተማው ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል ። ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ለማደስ አካውንት ተከፍቶ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ ቴክኒክ ኮሜቴው በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ባዩህ ተናግረዋል ። መላው የከተማችን ነዋሪዎች ፣የስፖርት አፍቃሪያን ፣ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያሉ ባለሀብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ጥሪ አስተላልፈዋል ። የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም የእድሳት ቴክኒክ ኮሜቴ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል አማረ ደግሞ ኮሜቴው ከሁለት ወራት በፊት ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል ። ኮሜቴው ከመንግሥት ፣ ከፋሲል ከነማ ደጋፊ ማህበር እና ከህብረተሰቡ የተውጣጣ መሆኑን አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል ። የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ ፣ሀብት አፈላላጊ ፣ የኦዲት ፣ የሚዲያና ዶክሜንቴሽን ኮሚቴዎች መዋቅራቸውን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል ። ህብረተሰቡ ኮሚቴውን አግዞት ስታዲየሙ ታድሶ ለ2016 ዓ.ም ጨዋታ ጎንደር ላይ እንዲሆን ልንሰራ ይገባል ብለዋል ። የአፄ ፋሲል ስታዲየም የእድሳት የቴክኒክ ክፋል ኃላፊ አቶ ደመላሽ አበበ በበኩላቸው ፋሲል ከነማ የስፖርት ክለብ ባለፉት አራት ዓመታት የሚጫወተው ከከተማው ውጭ ስለሆነ ክለቡ በከተማው እንዲጫወት ስታዲየሙን ማደስ አስፈላጊ ነው ብለዋል ። ስታዲየሙን በሁለት ወራት ውስጥ መስፈርቱን በሚያሟላ መንገድ አጠናቆ ክለቡን ወደ ከተማው ለመመለስ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ደመላሽ የእግር ኳስ መጫወቻው ሜዳ ተነስቶ እንደ አዲስ እንደሚሰራ ገልፀዋል ። ለሜዳው አስፈላጊ የሆነ የግራውንድ የዉሃ ማሰባሰቢያ፣ የማልበሻ ክፋሎች ስታንዳርዱን በጠበቀ መንገድ እንደሚሰራ አቶ ደመላሽ ተናግረዋል ። የአፄ ፋሲል ስታዲየም ግንባታ ሀብት አፈላላጊ ኮሜቴ ወይዘሪት ትግስት ሲሳይ ደግሞ ስታዲየሙን ለመገንባት ሲታስብ ትልቁ ሀብት ማህበረሰቡ መሆኑን ገልጸዋል ። @FASILSC
Hammasini ko'rsatish...