cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኢትዮ የህግ እይታዎች Ethio Legal Views

ይህ ቻናል አነጋጋሪ የህግ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግበት፣ ነጻ የህግ ምክር አገልግሎት የሚሰጥበት፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከህግ አንጻር ሙያዊ ምልከታዎች የሚቀርብበት ማንኛውም ሰው አባል የሚሆንበት አሳታፊና መማማሪያ ገጽ ነው። በመሆኑም፣ እባከዎ የሚችሉትን አጽተዋጽኦ እንዲያደርጉና በሚከተለው ሊንክ ላይ ጓደኞችዎትን በመጋበዝ፣ ሼርና አድ በማድረግ እንዲጀምሩ በአክብሮት እንጠይቃለን።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
196
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ዳደር ሥራ በቀር ሌላ ሥራ ለመስራት የሚያስፈልግ ሲሆን ልዩ ውክልና እንዲኖረው አስፈላጊ መሆኑንና ተወካዩ ልዩ የውክልና ሥልጣን ከሌለው በቀር የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ለመሸጥ ወይም አስይዞ ለመበደር የማይችል መሆኑ በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2205 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ንዑስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል፡፡ በወካዩ ስም ማናቸውንም ፎርማሊቲ እያሟላ ንብረት እንዲያዛውር፣ በስሙ እንዲዋዋል የውክልና ስልጣን የተሰጠው ተወካይ በወካዩ ስም የሚገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ፣ የመለወጥ ስልጣን የለውም፡፡ በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2205 መሠረት የሚሰጥ ልዩ ውክልና በይዘቱ በልዩ ውክልና የሚፈፀሙ እያንዳንዳቸውን ተግባሮች በግልፅ የሚያመለክት መሆን ይገባዋል፡፡ የውክልና ስልጣን የሚተረጎመው ሳይስፋፋ በጠባቡ ነው፡፡ ሰ/መ/ቁ. 50985 ቅጽ 13፣[8] ፍ/ህ/ቁ. 2204፣ 2205፣ 2181/3/ የውክልና ሰነዱ ይዘት በግልፅ ውክልና ተቀባዩ የተሰጠው ስልጣን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል ስለመሆኑ እየገለፀ ስለልዩ ውክልና አስፈላጊነት የተቀመጠው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2205 በውክልና ስልጣን ሰነዱ ያለመጠቀሱ ውክልናው ልዩ የውክልና ስልጣን አይደለም ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ስለመሆኑ የሚያሳይ የሕግ ድንጋጌ የለም፡፡ ዋናውና ቁልፉ ነገር ለውክልና ተቀባዩ የተሰጡት ተግባሮች በዝርዝርና ግልጽ ሁኔታ ተጠቅሰው በውክልና ሰነዱ ላይ መገኘት እንጂ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ያለመጠቀሳቸው አይደለም፡፡ የሰነዱ ይዘት ግልጽ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች በውክልና ስልጣን ሰጪውና በውክልና ስልጣን ተቀባዩ አልተጠቀሱም ተብሎ ሰነዱ ዋጋ እንዲያጣ ማድረግ የተዋዋዮችን ሐሳብ ውጤት እንዳይኖረው የሚያደርግ በመሆኑ በውል አተረጓጎም ደንቦችም ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው የሚሆነው፡፡ ሰ/መ/ቁ. 72337 ቅጽ 13፣[9] ፍ/ህ/ቁ. 2199፣ 2055
Hammasini ko'rsatish...
ስለ ውክልና- የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም February 10, 2017Abrham Yohannes ውክልና ተወካይ የሆነ ሰው ወካዩ ለሆነው ሌላ ሰው እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚገባበት ውል አንድ ተወካይ የውክልና ስራ በሚፈጽምበት ጊዜ የወካዩን ህጋዊ ሁኔታዎችን የመለወጥ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ይህም በመሆኑ ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ የመሆን እና የወካዩን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ የማስጠበቅ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ ስለሆነም ተወካዩ ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው የወካዩን ጥቅም ብቻ በመሆኑ የጥቅም ግጭት ባለበት ሁኔታ ተወካዩ በስራው አፈጻጸም ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ምክንያቱም የጥቅም ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ተወካይ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የወካዩን ጥቅም ሊያስቀድም ይችላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ስለዚህም ተወካዩ የራሱን ጥቅም የሚመለከት ጉዳይ ሲያጋጥመው ሁኔታውን ለወካዩ ሳያሳውቅና ወካዩ ሳይስማማ ስራውን እንዳይፈጽም ይከለከላል፡፡ ስለወኪልነት የተደነገጉትን የፍ/ብሔር ድንጋጌዎች ስንመለከትም ተወካዩ ከወካዩ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እንደሚገባ እና የውክልና ስልጣኑን የሚያስቀሩ ምክንያቶች ለወካዩ ማስታወቅ እንዳለበት፤ ተወካዩ ስራውን የሚፈጽመው በተለይ ለወካዩ ጥቅም ሊሰጥ በሚችል መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት እንዲሁም ተወካዩ በራሱ ስም ከወካዩ ጋር የሚያደርገው ውል ወካዩ ካላጸደቀው በቀር ሊፈርስ እንደሚችል መደንገጋቸው ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ መሆን እንዳለበት እና ለወካዩ ጥቅም ብቻ መስራት እንዳለበት፣ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ሁሉ ሁኔታውን ለወካዩ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት የሚያስገነዝቡ ናቸው፡፡ በመሆኑም አንድ ተወካይ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ለወካዩ ሳያሳውቅ የሚያከናውነውን ስራ ወካዩ ሊቃወመው የሚችል መሆኑን እና በዚህ ሁኔታ የተከናወነው ስራም ወካዩ ካላፀደቀው በቀር ወካዩ ራሱ እንደፈጸመው ሊቆጠር እንደማይገባ ከውክልና ግንኙነት አጠቃላይ ዓላማ እና ከፍ/ብ/ህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ሰ/መ/ቁ. 14974 ቅጽ 1፣[1]  ሰ/መ/ቁ. 50440 ቅጽ 10፣[2] ሰ/መ/ቁ. 67376 ቅጽ 13፣[3] ፍ/ህ/ቁ 2198፣ 2208፣ 2209(1)፣ 2188 የአፃፃፍ ስርዓት የውሉ አጻጻፍ በተለየ ቅርፅ እንዲደረግ ሕጉ የማያስገደድ ከሆነ ይህን ውል እንዲፈጽም በቃል የሚሰጥ የውክልና ስልጣን በወካዩ ላይ ሕጋዊ አስገዳጅነት አለው፡፡ ሰ/መ/ቁ. 68498 ቅጽ 13፣[4] ፍ/ህ/ቁ. 2180 የወካይ መሞት በወካይ መሞት ምክንያት ቀሪ በሆነ የውክልና ስልጣን ተወካይ ከነበረው ሰው ጋር በወካዩ ስም የሚደረግ ውል ከጅምሩ ፈራሽና ህጋዊ ውጤት የሌለው ነው፡፡ ወካዩ የሞተ እንደሆነ፣ በሥፍራው አለመኖሩ የተረጋገጠ እንደሆነ፣ ለመስራት ችሎታ ያጣ እንደሆነ ወይም በንግድ መውደቅ ኪሣራ ደርሶበት እንደሆነ ለጉዳዩ ተቃራኒ የሚሆን ውል ካልተገኘ በቀር የውክልና ሥልጣኑ ወዲያውኑ የሚቀር መሆኑን የፍታብሓር ሕ/ቁጥር 2232 ንዑስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል፡፡ የውክልና ስልጣን መሻር ውጤት እንደራሴው ቀሪ በሆነው ሥልጣን መሠረት በሌላ ሰው ስም ወይም ወካይ በነበረው ሰው ስም በሠራ ጊዜ በስሙ የተሠራበት ስው እንደፈቃዱ በስሙ የተሠራውን ሥራ ለማጽደቅ፣ ለመቀበል ወይም ለመሻር መብት አለው፡፡ በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2191/2/ ከተደነገገ በኋላ በዚሁ በተሰጠው መብት ተጠቅሞ አንዱን መንገድ እንዲከተል ወይም እንዲመርጥ ከእንደራሴው ጋር የተዋዋሉት ሦስተኛ ወገኖች ለማስገደድ እንደሚችሉ እና ሿሚው ከሦስተኛ ወገኖች በቀረበለት ጥያቄ መሠረት ወዲያውኑ ካላስታወቃቸው እንደራሴው የሠራውን ሥራ እንዳልተቀበለው ሕጉ ግምት የወሰደ ለመሆኑ ተከታይ በሆነው ድንጋጌ ተመልክቷል፡፡ እንግዲህ ሿሚው በግልጽም ይሁን በዝምታ እንደራሴው ሥልጣኑ ቀሪ ከሆነ በኋላ የሠራውን ሥራ ያልተቀበለው መሆኑ ከተረጋገጠ የዚሁ ያለመቀበል ውጤት በቁጥር 2193 ተደንግጓል፡፡ የዚህን ድንጋጌ ይዘት ስንመለከት ሿሚው ይህንኑ የእንደራሴውን ሥራ ካልተቀበለው ምን ጊዜም ይኸው ውል ፈራሽ ነው የሚል አይደለም፡፡ ይልቁንም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1808 እስከ 1818 ድረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ተከትሎ የውሉ መፍረስ ወይም መሰረዝ ሊወሰን የሚችል መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም እነዚህኑ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በመከተል ውሉ ሊፈርስ የማይችልበት አጋጣሚ ያለ መሆኑን የሚያሳይና ነገር ግን ውሉ የሚፈርስ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ውሉ በመፍረሱ ምክንያት በቅን ልቦና ከእንደራሴው ጋር በተዋዋሉት 3ኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ካሣ የሚጠየቅበት መንገድ የሚያመቻች ድንጋጌ ነው፡፡ ሰ/መ/ቁ. 26399 ቅጽ 5፣[5] ፍ/ህ/ቁ. 1808—1818፣ 2191(2)፣ 2193 ስለማፅደቅ የውክልና ስልጣን አገልግሎት ውክልናው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ለሚከናወኑ ሕጋዊ ተግባራት እንጂ ከመሰጠቱ በፊት ተወካዩ ለፈጸማቸውን ተግባራት ሕጋዊ ውጤት አይፈጥርም፡፡ ዘግይቶ የተሰጠ የውክልና ስልጣን ተወካዩ የፈጸማቸውን ተግባራት የማጽደቅ ውጤት የለውም፡፡ ምክንያቱም አግባብነት ያላቸው የፍ/ህ/ቁ. 2190 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ሊሆኑ የሚችሉት የውክልና ስልጣን ኖሮ ተወካዩ ከውክልና ስልጣኑ በላይ አሳልፎ ለፈጸማቸው ተግባሮች እንጂ ፈጽሞ የውክልና ስልጣን በሌለበት በወካዩ ለተከናወኑ ተግባራት አይደለም፡፡ ሰ/መ/ቁ. 74538 ቅጽ 13፣[6] ፍ/ህ/ቁ. 2190 ልዩ የውክልና ስልጣን የአንድ ንብረት ባለሃብትነት በውል ለሌላ ሰው የሚተላለፈው ባለሃብት ወይም ባለሃብቱ የንብረቱን ባለቤትነት በውል ለሌላ እንዲያስተላልፍ የፀና ልዩ የውክልና ስልጣን ባለው ሰው እንደሆነ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 1፣ የፍትሐብሓር ህግ ቁጥር 1204 ንዐስ አንቀጽ 2፣ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2005 ንዐስ አንቀጽ 2 እና የፍትሐብሓር ህግ ቁጥር 2232 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎችን በጣምራ በማንበብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ሰ/መ/ቁ. 73291 ቅጽ 13፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 40(1)፣ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1204፣ 2232(2)፣ 2015(ሀ)፣ 2005(2) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ፣ የመለወጥና የንብረቱን ባለቤትነት ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ተወካይ ንብረት በመያዣ አስያዞ በወካዩ ስም ከባንክ የመበደር ስልጣን አለው፡፡ የውክልና ማስረጃ ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን የሚሰጥ ከሆነ ሕጋዊ ውጤቱ በውክልና ማስረጃው ላይ ከተጻፉት ተግባራት በተጨማሪ በውክልና ማስረጃው የተገለፁትን ጉዳዮችና እንደ ጉዳዩ ክብደትና እንደ ልምድ አሰራር በውክልና ማስረጃው የተገለጹትን ጉዳዮች ተከታታይና ተመሣሣይ የሆኑ አስፈላጊ ተግባራትን የመፈፀም ስልጣንን የሚያካትት መሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2206 ንዑስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም በውክልና ማስረጃ ቤት የመሸጥ፣ የመለወጥና ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሰው ከዚህ መለስ የሆኑ ተግባራትን የመፈፀም ችሎታ እንዳለውና በተለይም ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን እና ችሎታ እንዳለው “ለራሱ ዕዳ ዋስትና እንዲሆን አንዱን የማይንቀሣቀሥ ንብረትን በእዳ መያዣነት አድርጎ ለመስጠት የሚችለው የማይንቀሣቀሰውን ንብረት ለመሸጥ ችሎታ ያለው ሰው ነው” ከሚለው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3049 ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ሰ/መ/ቁ. 17320 ቅጽ 5፣[7] ፍ/ህ/ቁ. 2026/1/፣ 3049/2/ ተወካዩ ከአስተ
Hammasini ko'rsatish...
አግባብ ባለዉ ድንጋጌ አስገዳጅነት የሚረጋገጡና የሚመዘገቡ ሰነዶች ህጋዊ ዉጤት ህዳር 2014 ዓ.ም አግባብ ባላቸው ሕግ መሠረት ካልተረጋገጡ እና ካልተመዘገቡ ሕጋዊ ውጤት የማያገኙ ሠነዶችን አስመልክተው ከፍትሐብሔር ሕግ ከተመላከተው አንቀጾች በተጨማሪ ለጠቅላላ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ከዚህ በታች ባሉት የተለያዩ የፌዴራል አዋጆች እና ደንቦች ላይ ጭምር የተቀመጡ ስለመሆናቸው ለማሳያ ይረዳ ዘንድ እንደሚከተለዉ ተቀምጧል፡፡ 1. ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1123/2013 የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ “ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ማሕበር ለመቋቋም አባሉ የሚሰጠው መግለጫ ሰነድ ለማረጋገጥ እና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መደረግ እንዳለበት (በአንቀጽ 536 ንኡስ ቁጥር 1) የሚያመላክት ሲሆን እንዲሁም ይህ ባለ አንድ አባል ያለው ማሕበር ለመቋቋም በቅድመ ሆኔታ ዕጩ ንብረት ጠባቂ አስመልክቶ አባሉ እና ዕጩነቱን ከተቀበለው ንብረት ጠባቂ ጋር የሚያደርጉት ስምምነት በተመሳሳይ ሁኔታ በውል አዋዋይ አካል ፊት ቀርቦ ካልተረጋገጠ ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ ማሕበር ሊመሠረት እንደማይችል (በንግድ ሕጉ አንቀጽ 537(1) አስገዳጅ ድንጋጌ ተቀምጠዋል። 2. በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012 ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 474/2012 ዓ.ም • በትግበራ ላይ የሚገኝ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ለሌላ 3ኛ ወገን በሽያጭ ለማስተላለፍ (በደንቡ አንቀጽ 12) የሚደረግ ስምምነት፣ • በቴክኖሎጂ ተቀባይ እና አቅራቢ መካከል የሚደረግ የቴክኖሎጂ ስምምነት ለመፈጸም (አንቀጽ15/1/ሰ/) እና • ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘ በአገር ውስጥ ባለሀብቱ እና በውጭ ኢንተርፕራይዝ መካከል የሚደረግ ስምምነቶች (በደንቡ አንቀጽ 16 ንዑስ ቁጥር 1 (ሰ) ከላይ የተዘረዘሩ ስምምነቶች እንደ ቅድመ ሁኔታ ሰነድን ለማረጋገጥ እና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ተረጋግጠው ካልተመዘገቡ በቀር በሕግ ፊት ተቀባይነት እንደማገያኙ አስገዳጅ ድንጋጌ ናቸዉ 3. በተመሳሳይ የንግድና ምዝገባ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ለማስፈጸም በወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 392/2009 ዓ.ም በአንቀጽ 37 እና 48 ላይ እንደተቀመጠው • የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታ በሆልዲንግ ኩባንያው የቡድን አባላት መካከል ኩባንያው ስለመመስረቱ የሚደረግ ስምምነት (አንቀጽ 37 ንዑስ ቁጥር 1 ላይ እንደተቀመጠው) እንዲሁም • የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማግኘት የፍሬንቻይዘሩ (ውል ሰጪ) እና የፍሬንቻይዝ (ውል ተቀባይ) መካከል የተፈጸመ የፍሬንቻይዚንግ ውል ስምምነት (አንቀጽ 48 እንደተመለከተው) በቅድመ ሁኔታ ሰነድን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ በሕግ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርበው ካልተረጋገጡና ካልተመዘገቡ ሕጋዊ ውጤት እንደማይኖራቸው ተደንግጓል። 4. በሌላ በኩል ሠነድን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ በወጣው አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 9(1) እንደተመላከተው ካልተረጋገጠና ካልተመዘገበ ሕጋዊ ውጤት አይኖራቸውም ተብሎ ከተገለጹት መካከል የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ ብቻ ሳይሆን የውክልና መሻሪያ ሰነድም አንዱ ሲሆን የመሻሪያ ሰነድ ወካይን ከመቼ ቀንና ዓ.ም ጀምሮ ከስልጣኑ እንደሻረው እና ከተሻረ ጊዜ ጀምሮ በወካይ ስም አንዳች ሕጋዊ ተግባር እንዳይፈጸም በተሻረው የውክልና ስልጣን እንዳይሰራ አስቀድሞ ለመከላከል የመሻሪያው ሰነድ ስልጣን ባለው አካል ተረጋግጦ መመዝገብ እንዳለበት ተደንግጎ ይገኛል። ምንጭ፣ Federal Documents Authentication and Registration Agency.
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
የህግ ባለሙያዎች መድረክ

የግሩፓችን ተልእኮ ባለሙያዎች በህጎቻችን ላይ በመወያየት አቅማችንን በማጎልበት በተሻለ እውቀት የተሻለ አገልግሎት ለዜጎች እንዲሰጥ ያለመ ነው

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝና አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ፍርድ ቤት ባለመቅረባቸው መጥሪያውን እንዲያደርሱ የታዘዙ ኃላፊዎች ታስረው እንዲቀርቡ ተወሰነ *** የገንዘብ ሚኒስትሩ የመከላከያ ምስክር ሆነው ፍርድ ቤት ቀረቡ በመከላከያ ምስክርነት ለተቆጠሩት ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ለቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ ፌዴራል ፖሊስ አስፈርሞ የሰጣቸውን የፍርድ ቤት መጥሪያ ለምስክሮቹ አላደረሱም ወይም ፍርድ ቤት ቀርበው አላስረዱም የተባሉ የተቋማት ኃላፊዎችን፣ የፌዴራል ፖሊስ አስሮ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ሰኞ ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ትዕዛዝ የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀሎች ችሎት ሲሆን፣ ከሁለት ዓመታት በፊት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋን ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ክስ ተመሥርቶባቸውና በዓቃቤ ሕግ ምስክር ተሰምቶባቸው እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡ በመሆኑም በመከላከያ ምስክርነት ከቆጠሯቸው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል  የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሸዴ አንዱ ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ከባለቤታቸው ጋር በጋራ ላቋቋሙት “ሮማንና ኃይለ ማርያም ፋውንዴሽን” ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መጥሪያ የተሰጠ ቢሆንም፣ መጥሪያው ደርሷቸው ይሁን ወይም ሳይደርሳቸው ባልታወቀ ሁኔታ ፍርድ ቤት ቀርበው ሊመሰክሩ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትርና አሁን በኢጋድ (IGAD) የሰላምና ፀጥታ ዲቪዥን ዳይሬክተር ሆነው እየሠሩ ለሚገኙት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የፍርድ ቤት መጥሪያ እንዲደርሳቸው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተደጋጋሚ የተሰጠ ቢሆንም፣ ምስክሩ ይድረሳቸው ወይም አይድረሳቸው ባለመታወቁ ሊቀርቡ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ምስክሮቹ ሊቀርቡ ባለመቻላቸው የሮማንና ኃይለ ማርያም ፋውንዴሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ የሚመለከተውን ኃላፊ የፌዴራል ፖሊስ ለነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. አስሮ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት አቶ ኃይለ ማርያምና አቶ ሲራጅ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቅ የነበረው፣ ከእርሻ ትራክተር መለዋወጫ ግዥ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ነው፡፡ ሌላው በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ሲሆኑ፣ ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት የእርሻ ትራክተር  መለዋወጫ ግዥን  በሚመለከት  የገንዘብ ሚኒስትሩ እንዳስረዱት፣ እ.ኤ.አ. በ2014 ኢትዮጵያ ከፖላንድ መንግሥት ብድር በማግኘቷ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት አቶ ኃይለ ማርያም ከተመራ ልዑክ ጋር ወደ ፖላንድ ተጉውዘው ነበር፡፡ ብድሩ የተፈቀደው ለእርሻ ትራክተር መለዋወጫ መግዥያ ሲሆን፣ ግዥውን ለመፈጸም ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣት እንደማይቻል ሁለቱ መንግሥታት መስማማታቸውንና ስምምነቱም በካቢኔና በፓርላማ መፅደቁንም አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ግዥው የሚፈጸመው ከፖላንድ የመንግሥት ልማት ድርጅት እንደሆነ፣ የፖላንድ መንግሥት በብድር ከሰጠው 50 ሚሊዮን ዶላር ላይ ክፍያው እንዲፈጸም መስማታቸውንና ምንም ዓይነት ገንዘብ በጥሬው እንዳልተሰጠ እንደሚያውቁም ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አክለዋል፡፡ በወቅቱ ወደ ፖላንድ ከተጓዘው ልዑክ ጋር የመከላከያ ሚኒስትርና የሜቴክ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ሲራጅ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ ገንዘቡ እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ወለድ የብድር ስምምነት የተገኘ መሆኑን፣  ከፖላንድ መንግሥት ለኢትዮጵያ በጥሬ ገንዘብ የተሰጠ ገንዘብ እንዳልነበረ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ #ሪፖርተር
Hammasini ko'rsatish...
ስለተከራካሪ ወገኖች አለመቅረብ =========================== 1.ክርክሩን ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ግራ ቀኙ ወገኖች ካልቀረቡ የክስ መዝገቡ ይዘጋል (69(2)) ፡፡ 2. በቁ.69 (2) መሠረት የክስ መዝገብ ከተዘጋ ከሳሹ በቁ.71 መሰረት ተገቢውን ዳኝነት (በድጋሚ) እና ኪሳራ ከፍሎ መዝገቡን ለማስከፈት ይችላል፡፡ ከሳሹ የቀረው በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ካስረዳ ድጋሚ ዳኝነት ወይንም ኪሳራ ላይከፍል ይችላል፡፡ 3. ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሽ ካልቀረበ በቁ.70 መሠረት እንደ ሁኔታው ተከሳሹ በሌለበት እንዲቀጥል ወይም ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ማዘዝ ወይም ክርክሩን ለሌላ ቀጠሮ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ 4. መጥሪያው ለተከሳሹ(ሾቹ) ያልደረሰው በከሳሽ ጥፋት ከሆነ ባልደረሳቸው ተከሳሾች ላይ የክስ መዝገቡ ይዘጋል (70(መ)፡፡ 5. በቁ.70 (መ) መሠረት የክስ መዝገቡ ከተዘጋ ከሳሹ የቁ.71ን ሁኔታዎች በማሟላት መዝገቡ እንዲከፈትለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡ ቁጥር 74 ለይግባኝ መዝገብ እንጂ ለቀጥታ ክስ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ (በ70 (መ) ለተዘጋ መዝገብ)፡፡ 6. በቁ.70 (ሀ) መሠረት ተከሳሹ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ከታዘዘ በኃላ በሚቀጥለው ቀጠሮ ቀርቦ በመጀመሪያ ቀጠሮ ያልቀረበው በቂ በሆነ እክል መሆኑን ካስረዳ መከላከያውን አቅርቦ እንዲከራከር ሊፈቀድለት ይችላል (ቁ. 72) ፡፡ 7. ተከሳሽ ቀርቦ ከሳሽ ባይቀርብ፤ ሀ.ተከሳሹ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ያመነ ከሆነ ፍርድ ቤቱ በታመነው መጠን ውሳኔ መስጠት ይችላል (ቁ.73)፡፡ ለ.ሆኖም ግን ተከሳሽ ስለመነ ብቻ ለከሳሹ የሚወሰን ሳይሆን ተከሳሹ ቢያምንም ከሳሽ ያቀረበው ክስ ሕጋዊ መሆኑንና ከሳሹ የጠየቀው ዳኝነት በሕግ የሚገባው መሆኑን ፍርድ ቤቱ ማጣራት አለበት፡፡ ሐ. ተከሳሹ ከካደ መዝገቡ ይዘጋል፡፡ መ. ሆኖም ከሳሹ በቁጥር 74 በተደነገገው መሠረት የተዘጋው መዝገብ እንዲከፈትለት መጠየቅ ይችላል፡፡ ጥያቄው ተቀባይነት የሚያገኘው ከሳሹ በመጀመሪያው ቀጠሮ የቀረው በቂ በሆነ ችግር መሆኑን ካስረዳ ነው፡፡ ፍረድ ቤቱ ጥያቄውን ከተቀበለ ስለኪሣራውና ስለማናቸውም ወጪ አከፋፈል ተስማሚ መስሎ የታየውን ውሳኔ ከሰጠ በኃላ የተዘጋው መዝገብ እንደገና ተከፍቶ ነገሩ እንዲቀጥል ትዕዛዝ ሰጥቶ ጉዳዩ የሚሰማበትን ቀጠሮ ይወስናል፡፡ ትዕዛዙ የሚሰጥው የከሳሹ ማመልከቻ ለመልስ ሰጪው ከደረሰው በኃላ ነው፡፡ (በቁጥር 73 መሠረት ለተዘጋ መዝገብ ቁጥር 69 ተፈፃሚ አይሆንም)፡፡ ======================== ስለ ተከራካሪ ወገኖች መቅረብ ======================== 1. ባለጉዳዩ እራሱ መቅረቡ ግዴታ አይደለም፡፡ ስለዚህ ባለጉዳዩ እራሱ መቅረብ ካልፈለገ ወይም ካልቻለ እንደሁኔታው ከቁጥር 57-64 በተደነገገው መሰረት ነገረ ፈጁ ፣ ወኪሉ ወይንም ጠበቃው ቀርቦ መከራከር ይችላል፡፡ እነዚህም በሕግ ወይም በውል የተሰጣቸው የውክልና ማስረጃ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 2. ሆኖም ግን ውስን በሆኑና አስፈላጊ በሆኑ ሁኔታዎች ባለጉዳዩ እራሱ እንዲቀርብ ማዘዝ ይቻላል (ቁጥር 65፣ 68ና 241(3))፡፡ 3. ባለጉዳዩ እራሱ እንዲቀርብ ታዞ በቂ ባልሆነ ምክንያት የቀረ እነደሆነ ወኪሉ ቢቀርብም ስለከሳሽ ወይም ተከሳሽ ያለማቅረብ የተነገሩት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ (ቁጥር 77) ፡፡ 4. ክርክሩን ለመስማት በተቀጠረው ቀን ባለጉዳዮች እራሳቸው ከቀረቡ ማንነታቸው ከተረጋገጠ ወኪሎቻቸው ከቀረቡ ደግሞ ሕጋዊ ውክልና እንዳላቸው ከተረጋገጠ በኃላ የክስ መሰማት ሂደት ይቀጥላል (ቁጥር 69(1)እና 241(1)) ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ይግባኝ ማስፈቀጃ ============ • በህጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡ ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡ ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326
Hammasini ko'rsatish...
By tamrat kidanemaryam ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር (የውል፣ ውርስ፣ ባልና ሚስት፣ ኩባንያ፣ ንብረት ለመሳሰሉ) ጉዳዮች ለእያንዳንዱ ለሚቀርብላቸው የሰነድ ማስረጃ ቀረጥ ቴምብር እንዲመታበት ወይም እንዲከፈልበት ይጠይቃሉ። ይህ ምን ያህል ተገቢ ነው? ስለ ቴምብር ቀረጥ በወጣው አዋጅ ቁጥር 110/1990 ዓም አንቀጽ 3 ከ(1) እስከ (12) ስር ቴምብር ሊሚከፈልባቸው የሚገቡ ሰነዶች ተዘርዝረው የቀረቡ ሲሆን እነዚህም የንግድ ማኅበራት እና ሌሎች ማኅበራት መመሥረቻ ጽሁፎች፣ መያዣ፣ ውል ስምምነቶች፣ የኪራይ ውል፣ የሥራ ውል፣ የሕብረት ስምምነት፣ የዕቃ መከማቸት ማረጋገጫ ሰነድ፣ የባለቤትነት ማስመዝገቢያ ሰነድ፣ ውክልና፣ ትክክለኛነታቸው በውል አዋዋይ ሹም የተረጋገጡ ሰነዶች፣ ማገቻ ሰነዶች ወይም ቦንድ እና የግልግል ውሳኔዎች ናቸው። አዋጁ እነዚህን ሰነዶች ቀረጥ ቴምብር ካልተመታባቸው ወይም ካልተከፈለባቸው ለመጠቀም ወይም በማስረጃነት ለመገልገል እንደማይቻል ከመደንገጉ ውጪ ለፍርድ ቤት በማስረጃነት የሚቀርቡ ሰነዶች ሁሉ ቀረጥ ቴምብር መመታት አለባቸው አይልም። ስለዚህ ፍርድ ቤቶቻችን ከተጠቀሱት ሰነዶች ውጪ ለሁሉም ሰነድ ማስረጃዎች ቀረጥ ቴምብር የማስመታት አሠራራቸው ከሕግ ውጪ ስለሆነ ሊሻሻል ይገባል።
Hammasini ko'rsatish...
ኡበር ታክሲን የከሰሰችው ዓይነስውር ሴት 1 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደላት ፍርድ ቤት ኡበር ኩባንያ ለአንዲት ዓይነስውር 1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር እንዲከፍል ፈረደበት፡፡ ኡበር ይህን ያህል መጠን ያለው ካሳ እንዲከፍል የተፈረደበት 14 ጊዜ ያህል ታክሲ ፈልጋ ገሸሽ በመደረጓ ነው፡፡ ከሳሽ ሊዛ አርቪንግ እንዳለችው አንዳንድ የኡበር ሾፌሮች ክብሯን ዝቅ አድርገው አዋርደዋታል፡፡ ይህም የሆነው ዓይነስውር በመሆኗ መንገድ የምትመራትን ውሻ ላለማሳፈር ብለው ነው፡፡ አንድ የኡበር ሾፌር ደግሞ በሐሰት መወረጃሽ ደርሷል ብሎ ግማሽ መንገድ ላይ ከታክሲው አስወርዶኛል ብላለች፡፡ ገለልተኛ የገላጋይ ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ዓይነ ስውሯ የኡበር ደንበኛ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ መገለል ደርሶባታል በሚል ፍርድ ሰጥቷል፡፡ ኡበር በበኩሉ ሾፌሮቼ ተቀጣሪ ሰራተኞቼ ሳይሆኑ ኮንትራት የወሰዱ ግለሰቦች ናቸው፤ ለጥፋቱ እኔ ሳልሆን ሾፌሮቹ ናቸው መጠየቅ ያለባቸው ሲል ተከራክሯል፡፡ የሳንፍራሲስኮ ነዋሪዋ ሊዛ አርቪንግ ኡበር ታክሲ በምትጠራበት ጊዜ ብዙዎቹ እሷን ለማሳፈር ፍቃደኞች ስላልሆኑ በተለይ በምሽት ሕይወቷን አደጋ ላይ ጥለውት ያውቃሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ኡበር ስትጠራ ውድቅ ስለሚደረግባትም ለበርካታ ቀጠሮዎች መዘግየትና ለሥራ አርፍዶ መግባት ዳርጓታል፡፡ ይህ እንግልት እየደረሰባትም ለኡበር ጉዳዩን በተደጋጋሚ አመልክታ ቸል መባሏ ወደ ክስ እንድትሄድ እንዳስገደዳት ተናግራለች፡፡ የሊዛ አርቪንግ ቃለ አቀባይ እንዳሉት በአሜሪካ የአካል ጉዳተኞች ደንብ ላይ ዓይነስውራንን የሚመሩ ዉሾች ባለቤቶቹ የሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የመግባት መብት አላቸው፡፡ ኡበር ግን ይህን እያከበረ አይደለም ሲሉ ከሰዋል፡፡ የካሳውን ውሳኔ ተከትሎ የኡበር ኩባንያ ለዓይነስውራን በሚሰጠው አገልግሎቱ ኩራት እንደሚሰማው ጽፏል፡፡ የኡበር ሾፌሮችንም ከአካል ጉዳተኛ ደንበኞች ጋር በተያያዘ ስልጠና መስጠታችንን እንቀጥላለን ብሏል ኡበር፡፡ ሊዛ ለሳንፍራንሲስኮ ክሮኒክል ጋዜጣ ፍርዱን በተመለከተ በሰጠችው አስተያየት እኔ ከገንዘቡ ይልቅ መብቴ ቢከበርልኝ ነው የምመርጠው ሆኖም ቅጣቱ ጥሩ መልእከት ያስተላልፋል ብላለች፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የውርስ ኃብት ማጣራትን የተመለከቱ አንዳንድ ነጥቦች ከሰበር ውሳኔ ጋር ተገናዝቦ የቀረበ መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የተለየ ንብረት ይቆጠራል፡፡ ይህም ማለት የሟች ንብረት ከሌሎች ሰዎች ወይም ወራሾች ንብረት ጋር ሳይቀላቀል የባለቤትነት መብቱ ለወራሾች ሳይተላለፍ እንደ አንድ ልዩ ንብረት ሆኖ ሊያዝ እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 942 ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ የሟች የውርስ ሀብት ወደ ወራሾች ይተላለፍ ዘንድ እንዲሁም ከሟች የውርስ ሀብት ላይ እዳ ጠያቂ ወይም ለሟች እዳ ከፋይ ነን የሚሉ ወገኖች የየፍላጎታቸው እንዲፈጸም፤ የሟች ወራሾች ማንነታቸው እና የሚደርሳቸው ምጣኔ ድርሻ ይታወቅ ዘንድ፤ሟች ኑዛዜ የተናዘዙ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የውርስ ሀብቱ ሊጣራ የሚገባው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 946 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ ተመላክቶ ይገኛል፡፡ ይህ የውርስ ማጣራት ተግባር በምን አግባብ እንደሚከናወን፤ የውርስ አጣሪው ስልጣንና ኃላፊነት እስከምን ድረስ አንደሆነ፤ የውርስ ኃብት ላይጣራ ሚችልባቸው ሁኔታዎች፤ የውርስ አጣሪ ሪፖርትን በማጽደቅ በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ህጋዊ ውጤቱ እስከምን ድረስ እንደሆነና በዚህ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ ተቃውሞ በምን መልኩ ሊቀርብ እንደሚገባ በዚህ ጽሁፍ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ውሳኔዎች ጋር በማገናዘብ አጭር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡    የውርስ ኃብት አጣሪ ስልጣንና ተግባር   የውርስ ኃብት አጣሪ ስልጣንና ተግባር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 856 ላይ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት የሟችን ውርስ እንዲያጣራ የተሾመ ሰው ሊከውን ሚገባው÷ 1ኛ)  የሟችን ኑዛዜ መፈለግና የኑዛዜ ወራሾችን ከነ ምጣኔ ድርሻቸው ማጣራት፤ 2ኛ) መከፈያቸው የደረሱ የውርስ እዳዎችን መክፈል፤ 3ኛ) ሟቹ በኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎችን መክፈል፤ 4ኛ) የሟችና ያለኑዛዜ ወራሾችን መለየትና ምጣኔ ድርሻቸውን መጣራት፤ 5ኛ) የሟች ንብረት ምን ምን እንደሆነ ማጣራት ፤ንብረቱ እዳ ወይም እገዳ ያለበት መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ በውርስ አጣሪ ከሚከወኑ ተግባሮች ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡ አንድ የውርስ አጠሪ የሟችን የውርስ ኃብት በሚያጣራበት ወቅት የሚጣራው ንብረት የሟች መሆን አለመሆኑ አከራካሪ ሆኖ ሲያገኘው ንብረቱ የሟች ንብረት ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመመስረት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመርና በመመዘን ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁ 83665 በቅጽ 15 ላይ በሰጠው የሰበር ውሳኔ ላይ ተመላክቷል፡፡ በመሆኑም የውርስ ኃብት እንዲያጣራ የተመደበ የውርስ አጣሪ ንብረቱ የሟች የግል ኃብት መሆኑ አለመሆኑን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ማስረጃዎችን በማደራጀት የግራ ቀኙን ክርክር ከማስረጃው ጋር መርምሮ ውሳኔ እንዲሰጥ ውርሱን እንዲጣራ ላዘዘው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በኑዛዜ በተጠቀሱትና ባልተጠቀሱት ንብረቶች የውርስ ሀብት መሆን ያለመሆን ላይ ወራሾች ያልተስማሙና ክርክር ያነሱ ከሆነ የአጣሪው ሥራና ኃላፊነት ወራሾች የተስማሙባቸውን ንብረቶች የውርስ ኃብት መሆናቸውን መመዝገብ፤ ወራሾች ያልተስማሙባቸውን ንብረቶችና እዳዎች ካሉ ደግሞ ማስረጃቸውን በማሰባሰብ ማስረጃው ምን ምን እንደሚያስረዳ በሪፖርቱ ላይ በማስፈር እንዲያጣራ ላዘዘው ፍርድ ቤት ማቅረብ እንጂ ክርክሩንና ማስረጃውን ከህግ ጋር በማገናዘብ በራሱ የውርስ በሀብት ነው ወይም አይደለም? የሚል ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የሌለው መሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ በሰ/መ/ቁ 23322 በቅጽ 7 እና በሰ/መ/ቁ 66727 በቅጽ 11 በሰጠው ውሳኔ ላይ ተገልጿል፡፡     የውርስ አጠሪ የውርስ ኃብቱን ሲያጣራ ጥሪ አድርጎላቸው ያልቀረቡ ወራሾችን በተመለከተ   የውርስ አጣሪው የውርስ ማጣራት ስራውን እንዲያከናውን በፍ/ቤት ከታዘዘ በኋላ መጀመሪያ የሚያከናውነው ተግባር የውርስ ኃብቱ እየተጣራ መሆኑን የሚገልጽ የማስታወቂያ ጥሪ በፍርድ ቤቱ ማህተብ በማረጋገጥ በሟች ቋሚ መኖሪያ ቤት ላይና በሟች መኖሪያ ቀበሌ(ወረዳ) ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲለጠፍ ማድረግ ነው፡፡ የዚህ ማስታወቂያ ጥሪ ዋና አላማው የሟች የውርስ ኃብት ይገባኛል ፤ከሟች የውርስ ኃብት ላይ እዳ ጠያቂ ነን ወይም ለሟች ወራሽ እዳ ከፋይ ነን የሚሉ ወገኖች እንዲቀርቡ እና የሟች ኑዛዜ በእጁ ያለ ወገን ይህንኑ ማስረጃውን ይዞ እንዲቀርብ የሟች ውርስ እየተጣራ መሆኑን በይፋ ለማሳወቅ ነው፡፡ በዚህ ማስታወቂያ ጥሪ መሰረት ጥሪ ተደርጎላቸው ያልቀረቡ ሰዎች የወራሽነት ድርሻቸው በተመለከተ በምን አግባብ ሊስተናገዱ ይገባል የሚለው ብዙ ግዜ በውርስ ማጣራት ሒደት አዳጋች እየሆነ መጥቷል፡፡ በአንድ አንድ ቦታዎች የሟች ህጋዊ ወራሾች የውርስ ሀብት እየተጣራ መሆኑ ተገልጾ በማስታወቂያ ጥሪ ተደርጎላቸው እነርሱ ባልቀረቡበት ሁኔታ  ሌሎች ወራሾች በመረዳጃ እድር ውስጥ የሟች ልጆች መሆናቸው ተመዝግቦ ይገኛል በማለት እነርሱ ባልቀረቡበት ከእድር በመጣው መረጃ መሰረት ድርሻቸው ተጠብቆ የውርስ ሀብቱ ይጣራ የሚል ሀሳብ ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት  ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፡፡ በውሳኔውም ላይ “የውርስ አጣሪው ጥሪ አድርጎላቸው ያልቀረቡ ሰዎች ሌላ ቦታ ይኖራሉ ተብሎ ስለመኖራቸው ከመረዳጃ እድር መዝገብ ላይ ተዘርዝርው ስለተገኙ ውርስ አጣሪው የወራሽነት ድርሻ አላቸው በማለት የሚያቀርበው የውሳኔ ሀሳብ አግባብነት ያለው አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከየትኛውም ቦታ የሚቀርቡ ማስረጃዎች ሁሉ ዋጋ የሚሰጣቸው ስላልሆኑ በመረዳጃ እድር መዝገብ ይገኛል የተባለው ሰነድ የሟች ወራሽነት ለጊዜው ለመወሰን ብቃት የሌለው ማስረጃ በመሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ 962(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያስገነዝበናል፡፡ ሌሎች ወራሾች አሉ ከተባለም ተጠሪው የክርክሩ ተከፋይ መሆን አለባቸው” በማለት ወስኗል፡፡   በመሆኑም በመረዳጃ እድር ውስጥ ስም ተጠቅሶ መገኘት ወራሾች ጥሪ ተደርጎላቸው ባልቀረቡበት ሁኔታ ያለኑዛዜ ወራሽነት ለማረጋገጥ ብቃት ያለው ማስረጃ አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡   የውርስ ሀብት ማጣራት የግድ የማይሆንበት የሕግ አግባብ   ወራሾችም ሆነ የውርስ ሀብቶች ተለይተው በግልጽ በሚታወቁት ወቅት ከወራሾች መሀከል አንዱ በግልጽ ተለይቶ የሚታወቀው የውርስ ኃብት በሌሎች ወራሾች የተያዘ እንደሆነ የውርስ ሀብቱ ሳይጣራ ድርሻቸው ያካፍሉኝ የሚል ቀጥተኛ ክስ በድርሻቸው ግምት ልክ ጉዳዩን ለማየት የሥረ ነገር ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 946 ጀምሮ የተደነገጉ ደንጋጌዎች ስንመለከት ወራሾች በራሳቸው ወይም በተመረጠ ሌላ ሰው ውርስ እንዲጣራ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማመልከት እንዲችሉ ቢመላከትም በቀጥታ የክፍፍል ክስ የውርስ ሀብቱ ሳይጣራ የመመስረት መብት የላቸውም የሚል ክልከላ ግን በህጉ አልተቀመጠም፡፡  
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.