cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school

Eshet Pre-Primary,Primary and Middle school 👉 @eshetprime2013 Eshet Library 👉 @eshetprimelibrary

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 480
Obunachilar
+224 soatlar
+237 kunlar
+7930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 09 ት/ጽ/ቤት                                                                                               የእሸት ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በቀን 09/09/2016ዓ.ም ከአጠቃላይ መ/ራን፣ የወተመህ ሾል አስፈፃሚዎች በተገኙበት ውይይት አካሄደ። 🤌የትኩረት ነጥቦች 1. የ2016ዓ.ም በጀት ዓመት የ9ወር ዕቅድ አፈፃፀምግምገማ                                            2. የተማሪዎች ውጤት ትንተና እና ምዘና ስርዓት መገምገም በተመለከተ                              3.የ2016 ዓ.ም የስርዓተ ት/ት ትግበራና የመማር ማስተማር ስራውን ከማሳለጥ አንፃር የትኩረት ነጥቦች ዙሪያ                                                  4.የት/ቤት ማሻሻል ላይ የተሰሩ ስራዎች ዙሪያ    5. የ2016ዓ.ም በጀት ዓመት የትምህርት ሴክተሩ ቁልፍ ተግባራት እና የትኩረት ነጥቦችን የተቋሙ ማህበረሰብ በውል ተገንዝቦ ለውጤታማነትና ግብ ተኮር ስራዎችን መስራት # የመማር ማስተማር ስራው የተሳለጠ ለማድረግ # የክፍለ ጊዜ ብክነት በተመለከተ # የትምህርት ይዘት ሽፋን ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ሁሉም የተቋሙ የትምህርት አመራሮች እና መ/ራን በተገኙበት ውይይት ተካሄደ።                   "የጋራ መግባባት ለውጤታማ መማር ማስተማር"                                                   የት/ቤቱ ስርዓተ ት/ት ም/ር/መ/ር                                                          ግንቦት 2016ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
ፒያሳ_ሰባ_ደረጃና አካባቢዋ ገፅታ በከፊል
Hammasini ko'rsatish...
#አስተምሮት #ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ 👉5ት ድንቅ ትምህርቶችን እነሆ ለቅምሻ፦ The Laws of Human Nature የተሰኘው የሮበርት ግሪን ድንቅ መጽሐፍ #ሰውና_ተፈጥሮው በሚል ርእስ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ዋለ ። ታዋቂውን 48 Laws of POWER የተሰኘውን መጽሐፍ 48ቱ የኃያልነት ሕጎችን በሚል በተረጎመችው #ሃኒም_ኤልያስ የተተረጎመ ሲሆን፣ ልክ እንደ #የኃያልነት_ሕጎች_መጽሐፍ ጥፍጥ ብሎ ከተዘጋጀው #ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ ላይ ለቅምሻ 5ቱን ድንቅ ትምህርቶች እነሆ ብለናል፦ #አንድ #መርዛማ_ሰዎችን_አስወግድ ከመርዛማ ሰዎች ጋር አብዝተን የምንገናኝ ከሆነ በአካልም ሆነ በአእምሮ ሊጎዱን ይችላሉ ይለናል። እነዚህ ከልክ ያለፈ ትችት የሚሰጡ፣ ምቀኛ፣ ትዕቢተኛ፣ ጠበኛ ወይም ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎችን ያጠቃልላል።  እነዚህን ባህሪያት በራሳችን እና በሌሎች እንዴት መለየት እንዳለብን እና ራሳችንን ከእነሱ እንዴት ማራቅ እንዳለብን ያስተምረናል። #ሁለት #ስሜታዊነትህን_ተቆጣጠር ስሜታችን ምን ያህል በጥልቅ እንደሚገዛን እና ውሳኔዎቻችንን እና ድርጊቶቻችንን እንዴት እንደሚነካ አናውቅም። ምክንያታዊነትን በማዳበር እነዚህን ስሜታዊ ተፅእኖዎች እንዴት መቋቋም እንደምንችል ማወቅ የግድ ይለናል። እራሳችንን ጠንቅቆ ማወቅ፣ ስሜቶቻችንን ከሥሮቻቸው መፈተሽ፣ የምላሽ ጊዜያችንን ማዘግየት፣ የአስተሳሰብ እና የስሜታዊነት ሚዛንን ማግኘትን የመሳሰሉ ስልቶችንም ሮበርት ግሪን በመጽሐፉ ይጠቁመናል። #ሶስት #ከጓደኞችህ_ጋር_አብረህ_ወደ_ገደል_አትግባ ከሌሎች ጋር ለመስማማትና ብቻችንን ላለመሆን ብለን የሌሎችን አስተያየት ወይም ግምት ከልክ በላይ እንዳንቀበል ያስጠነቅቀናል።  ይህ ግለሰባዊ አቅማችንን እንድናጣ እና ለቡድን አስተሳሰብ እንድንጋለጥ ሊያደርገን ይችላል። #አራት #ሳታቋርጥ_የተሻለ_ነገርን_ፈልግ ባለን ነገር እንዳንረካ እና ሌላ ቦታ ያለን የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ነገር እንድንፈልግ ይገፋናል። ከመጠን በላይ የሆነ ምሬትም ወደ ብስጭት፣ ጭንቀት፣ መሰላቸት ወይም ሱስ እንደሚመራን፣ ከዚህ ይልቅም እስካሁን ያገኘነውን በምስጋና ተቀብለን፣  ራሳችንን በማሻሻል ላይ ማተኮር እንዳለብን ያሳየናል። #አምስት #በሰዎች_ጭምብል_ስር_ምን_እንዳለ_ተመልከት ሮበርት ግሪን፣ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እውነተኛ ሀሳባቸውን እና ስሜታቸውን ከራስ መተማመናቸውና ከአካላዊ ውበታቸው ስር  እንዴት እንደሚደብቁ ያሳየናል።  በሌሎች ቃላት እና ድርጊቶች ውስጥ ያሉ የማታለል ምልክቶችን እንዴት መለየት እንደሚቻል ያብራራልናል። እንዲሁም በሰዎች ፊት ሀቀኝነታችንን እና ታማኝነታችንን ሳናጣ እንዴት መጫወት እንዳለብንም ያስረዳናል። #ሰውና_ተፈጥሮው መጽሐፍ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ይውላል። 👉ሌሎች የሮበርት ግሪን ምርጥ የእንግሊዝኛ መጽሐፍት እጅግ በጥራት ታትመው በገበያ ላይ፦ #The_Laws_of_Human_Nature
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
የጓሮ አትክልት በእሸት
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በጥራት ማደግ! ሁለት አይነት እድገቶችና ትልቅነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ነው፡፡ 1. ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሰዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በዝና፣ በስልጣን እና በመሳሰሉት ነገሮች ሲያድጉ፣ “ውጫዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ምንም እንኳን በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውና እንዲያውም ለጥቅም የሚውል ቢሆንም ብቻውን ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ 2. “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ሰዎች በመልካም ስብእና፣ በጤናማ አመለካከት፣ በስሜት ብልህነት፣ በራእይ እና በጥበብ ሲያድጉ፣ “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ከማንኛውም ነገር በፊት ሊቀድም የሚገባው የእድገትና የትልቅነት ዘርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ውጫዊ እድገትንና ትልቅንን እያስመሰዘገ ውስጣዊ እድገት ሲጎድለው ከራሱ ሕይወት ጀምሮ እስከ ቤተሰቡ፣ የስራ ስምሪቱና በሃገር ደረጃ የሚያስከትለው ቀውስ ይህ ነው አይባለም፡፡ የገንዘብ አቅሙን ለማይረባ ነገርና ለሕገ-ወጥ ተግባር የሚጠቀም ማነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በዝናውና በታዋቂነቱ የሚኩራራውና ሰውን የሚንቀው ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በስልጣኑ ተጠቅሞ ሰውን የሚደቁስና እንደፈለገ የሚሆን ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን? በመጀመሪያ በውስጣችን እንደግ! ከሁሉም በፊት በጥራትና በብቃት ትልቅ እንሁን! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Hammasini ko'rsatish...
👍 3