cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ቅዱሳን ንዑዳን

Eotc ye gebre yohannes mezmurat ፣ እግዚአብሔር ከፈቀደ የእለቱን የቅዳሴ ምስባክ፣ ሃይማኖተ አበው እና ጠቃሚ መንፈሳዊ ቪድዮችን እንለቃለን አንድ አንድ ጥያቄዎችም እንጠይቃለን @EMNE_TSYON @unitte_bot

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
340
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
-330 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ዳግመኛም በዚህች ዕለት በቂሣርያው በቅዱስ ባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ፡- ቅዱስ ባስልዮስ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ከሠራ በኋላ በውስጧ የሚያኖረውን የእመቤታችንን ሥዕል ሊያሠራ መሳያ ሠሌዳ ፈለገ፡፡ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ቤት ጥሩ ሠሌዳ እንዳለ ነገሩትና ሄዶ ባለጸጋውን ሠሌዳውን እንዲሰጠው ለመነው፡፡ ባለጸጋውም ‹‹የልጆቼ ነው አልሰጥም›› አለው፡፡ በትዕቢትም ሆኖ በታነጸቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብን ነገር ተናገረ፡፡ ወዲያውም ወድቆ ክፉ አሟሟት ሞተና ልጆቹ ፈርተው ሠሌዳውን አምጥተው ለባስልዮስ ሰጡት፡፡ እርሱም ያንን ሠሌዳ የእመቤታችንን ሥዕል አሳምሮ ይስልበት ዘንድ ለሰዓሊ ወስዶ ሰጠው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን በራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጠችለትና ከአመፀኛ ሰው የተገኘ ነውና በዚያ ሰው ሠሌዳ ሥዕሏን እንዳያስል ከለከለችው፡፡ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሳለበትን ሠሌዳም የት እንደሚገኝ ነገረችውና ባስልዮስ ሄዶ በታላቅ ክብር አምጥቶ በቤተ ክርስቲያኑ አስቀመጠው፡፡ ከሥዕሏም ሥር ድውያንን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስ ጀመረ፡፡ በዚህም ብዙዎች ድንቅ የሆነ ፈውስን አገኙ፡፡ የከበረች ሥዕሏ ከተቀመጠበት ምሰሶ ሥር ጸበል ፈለቀና በዚኽም ብዙዎች ተፈወሱ፡፡ ይህም የተፈጸመው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት ዕለት በሰኔ 21 ቀን ነው፡፡ የብርሃን እናቱ የእመቤታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን ሰኔ 21-ለአዳም ዘር ሁሉ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች ንግሥተ ሰማይ ወምድር ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓሏና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል ነው፡፡ + ዳግመኛም በዚሀች ዕለት እመቤታችን ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ከተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ከነገረችው በኋላ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገች፡፡ + አስቀድሞ ከከሃዲውና ከጨካኑ መኮንን ከአርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ አንዱ የነበረው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጢሞቴዎስ ተጋድሎውን በድል ፈጸመ፡፡ + ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት ባረዷት ሴት ላይ ላደረገው ታላቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ፡፡ + ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ያጠመቀውና በኋላም ዲቁናና ቅስና የሾመው አባ ከላድያኖስ ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም አባ ሜልዮስ ባረፈ ጊዜ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 4ኛ የሆነ ነው፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፡- ይህም ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከምስር የተገኘ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡ እርሱም አስቀድሞ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ጣዖትን እንዲያመልክ የሚያዝ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ትእዛዝ በግዛቱ ሁሉ በተነበበ ጊዜ ይህ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከሕዝቡ መካከል ተነሥቶ የንጉሡን የአዋጅ ደብዳቤ ቀደደው፡፡ ደብዳቤውን ከቀደደው በኋላ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ‹‹ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም›› ብሎ መሰከረ፡፡ የንጉሡ የዲዮቅልጥያኖስ ባለሟል የሆነው መኰንን ይህንን የቅዱስ ጢሞቲዎስን ድፍረት በተመለከተ ጊዜ ይዞ ክፉኛ አስደበደበው፡፡ ዳግመኛም ሰውነቱ ሁሉ እስኪደቅ ድረስ እንዲደበድቡት አዘዘ ነገር ግን ጌታችን መልአኩን ልኮ ፈውሰው፡፡ ከሥቃዩም ድኑ ፍጹም ጤነኛ ሆኖ አደረና በቀጣዩ ቀን ወደ መኰንኑ ቀርቦ አሁንም በድጋሚ ‹‹ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ መሰከረ፡፡ መኰንኑም ይዞ እጅግ አሠቃየው፡፡ ሰውነቱንም በመጋዝ ቆራርጦና ሰነጣጥቆ ሰቀለው፡፡ በብረት ምጣድም አድርጎ ሥጋው እንደ ሰም እስኪቀልጥ ድረስ በእሳት አበሰለው፡፡ ከከተማ ውጪም አውጥቶ ጣለው፡፡ አሁንም ጌታችን ፍጹም ጤነኛ አድርጎ ፈወሰውና ወደ መኰንኑ ተመልሶ ሄዶ ‹‹ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም አንተ ከሃዲ እፈር›› ብሎ ድጋሚ መሰከረ፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው በዙያው የነበሩ በጣም ብዙ አሕዛብ በጌታችን አምነው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡ መኰንኑም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ሰኔ 21 ቀን አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነት አክሊልን እንዲቀዳጅ አደረገው፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ + + + + + ++ + ++ + ++ + ++ + + የእመቤታችን ዓመታዊ በዓልና በዓለም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ስለመታነጻቸው፡- ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል፡፡ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፡፡ እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና ባርናባስ በፊሊጲስዮስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው፡፡ አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስም መልእክት ላኩባቸው፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ፡፡ ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ፡፡ ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው፡፡ ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ፡፡ ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው፡፡ ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው፡፡ የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት፡፡›› ኤፌ 1፡13፣ ቆላይ 1፡18፣14፡፡ እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው፡፡ ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ፡፡ እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ፡፡ ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል፡፡ በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡ ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኩራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፡፡ እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸው ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር፡፡ ሰኔ 20 ቀን ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን ሰኔ 20-በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት ያለጭቃና ውኃ በሦስት ድንጋዮች ብቻ በተወደደ ልጇ እጅ የታነፀችበት ዕለት ነው፡፡ + ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤልሳዕ ዐረፈ፡፡ ኤልሳዕ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ጠባቂ ነው›› ማለት ነው፡፡ ዐፅሙ የሞውተን ሰው ያስነሣ ታላቅ ነቢይ ሲሆን ኢዮራም፣ አካዝያስ፣ ኢዩና እንዲሁም ዮአስ በተባሉ በአራት ነገሥታት ዘመን ትንቢት የተናገረ ሲሆን የትንቢቱም ዘመን ከ50 ዓመት በላይ ነው፡፡ ታላቁ ነቢይ ኤልያስ በመንገድ ሲሄድ የሳፋጥ ልጅ አልሳዕን በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው፡፡ ኤልያስም ሄዶ መጎናጸፊያውን በላዩ ጣለበት፡፡ ኤልሳዕም እርሻውን ትቶ ተከተለው፡፡ ተመልሶም በመምጣት በሬዎቹን አርዶ ሕዝቡን መግቦ በፍጹም ልቡ ኤልያስን ተከትሎ ብዙ ዓመት ሲያገለግለው ኖረ፡፡ ኤልያስ በሚያርግበት ጊዜ ኤልሳዕን ‹‹ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳልወጣ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ›› አለው፡፡ ኤልሳዕም ‹‹በአንተ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ሆኖ ይድርብኝ›› አለው፡፡ መምህሩም ‹‹…ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ብታየኝ ይደርብህ›› አለው፡፡ ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሄዱ በመሀል የእሳት ፈረስና የእሳት ሠረገላ መጥቶ ኤልያስን ነጥቆ ወሰደው፡፡ ኤልሳዕም ይህን በተመለከተ ጊዜ ‹‹የእስራኤል ኃይላቸውና ጽናታቸው አባ አባ…›› ብሎ ጮኸ፡፡ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ አላየውም፡፡ መጠምጠሚያውንም ጣለለትና በራሱ ላይ ወረደች፡፡ በእርሷም የዮርዳኖን ወንዝ ለሁለት ከፍሎ ተሻግሮባታል፡፡ 2ኛ ነገ 2፡1-14፡፡ ኤልሳዕም እንደምኞቱ በመምህሩ በኤልያስ ላይ ያደረሰውን የመንፈስ ቅዱስን ሀብት በእጥፍ ስለተቀበለ ኤልያስ የዮርዳኖስን ወንዝ አንድ ጊዜ ሲከፍል ኤልሳዕ ግን ሁለት ጊዜ ከፈለ፡፡ ኤልያስ አንድ ሞት ሲያስነሣ ኤልሳዕ ግን ሁለት ሞታንን አስነሥቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ወደ ኢያሪኮ ሲገባ የሀገሪቱ ሰዎች ውኃቸውን ሲጠጡት ሴቶቹ እንደሚመክኑ ነገሩት፡፡ እርሱም ‹‹ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ›› ብሎ ወደ ምንጩ ውሃ ሄዶ ጨውን ጨመረው፡፡ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ፣ እርሱን ሲጠጡ የሚመክኑትም ሴቶች ወላዶች ሆኑ፡፡ ወደ ቤቴልም በወጣ ጊዜ ከከተማው ሲወጡ ታናናሽ ልጆችን አገኘ፡፡ እነርሱም ‹‹አንተ ራሰ በራ ውጣ›› እያሉ ሲዘባበቱበት የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ቢረግማቸው ወዲያው ሁለት ድቦች ከዱር ወጥተው 42 ልጆችን ገደሉ፡፡ ኤልሳዕ ሌላው የሚታወቅበት ነገር የመበለቲቷን ቤት በበረከት በመሙላቱ ነው፡፡ ሴቲቱ ወደ ኤልሳዕ መጥታ ‹‹የምታውቀው የእግዚአብሔር ሰው የሆነው ባሌ ስለሞተ አሁን ባለዕዳ ሁለቱን ልጆቼን ወስዶ በባርነት ሊገዛቸው›› አለችው፡፡ እርሱም በቤቷ ምን እንዳለ ጠየቃት፡፡ ‹‹ለእኔ ለባሪያህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም›› አለችው፡፡ እርሱም ከጐረቤቶቿ ባዶ ማድጋዎችን ተውሳ እንድታመጣ ነግሯት ማድጋዎቹን ሁሉ በጸሎቱ በተአምራት በዘይት ሞልቶላታል፡፡ እርሷም ዘይቱን ሸጣ ለባለ ዕዳው ከፈለች፡፡ የተረፈውንም ከልጆቿ ጋር ተመገበች፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ መካን ስለነበረችው ስለሱነማዊቷ ሴት ግያዝ ነግሮት ኤልሳዕ ካስጠራት በኋላ ‹‹በሚመጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታቀፊአለሽ›› ብለ ከነገራት በኋላ በዓመቱ ፀንሳ ወልዳለች፡፡ ልጁም ካደገ በኋላ ከአባቱ ጋር ወደ አዝመራ ወጥቶ ሳለ ታመመና በእናቱ እቅፍ እያለ ሞተ፡፡ በሞተም ጊዜ በእግዚአብሔር ሰው በነቢዩ አልጋ ላይ አስተኝታው በሩንም ዘግታበት ወጣች፡፡ ሎሌዋን ይዛ አህያዋን ጭና የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ ወዳለበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣችና የልጇን መሞት ነገረችው፡፡ ኤልሳዕም ሄዶ የሞተውን ልጇን ከሞት አስነሣላትና ‹‹ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ›› አላት፡፡ እርሷም ለኤልሳዕ ከሰገደችለት በኋላ ልጇን ወሰደች፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንን በዮርዳኖስ ውኃ እንዲጠመቅ ካደረገው በኋላ ከለምጹ ፈውሶታል፡፡ ንዕማንም ከለምጹ ከዳነ በኋላ ለኤልሳዕ ወርቅና ብር ልብስም ሊሰጠው ሲል አልሳዕ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምሎ አልቀበልም አለው፡፡ ንዕማንም ‹‹እነሆ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ›› ብሎ ከመሰከረ በኋላ ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር ወስዶ ወደ ሀገሩ ሶርያ ሄደ፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግያዝ ግን ንዕማንን በመንገድ ተከትሎ ‹‹ሁለት ጕልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ወደ እኔ መጥተዋልና አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ›› በማለት በኤልሳዕ ስም ዋሽቶ ተቀበለ፡፡ ኤልሳዕም ግያዝ በሥውር ያደረገውን ዐውቆ አዘነ፡፡ ወደ እርሱም ተመልሶ በመጣ ጊዜ ‹‹ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ?›› አለው፡፡ እርሱም ‹‹እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሄድሁም›› አለ፡፡ ኤልሳዕም ‹‹ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? ›› ብሎ ያደረገውን እንዳወቀበት ከነገረው በኋላ ‹‹እንግዲህስ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ ለዘላለምም በዘርህ ላይ ይጣበቃል›› አለው፡፡ ግያዝም እንደ በረዶ ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ፡፡ ከዚህም ሌላ ኤልሳዕ ውኃ ውስጥ የወደቀውን የብረቱን ምሳር በውኃው ላይ ዕንጨቱን ጥሎ የሰመጠውን ብረት ተንሳፎ እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በዱር ሰፍሮና ተደብቆ ሳለ የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕ ‹‹ሶርያውያን በዚያ ተደብቀዋልና በዚያ ስፍራ እንዳታልፍ ተጠንቀቅ ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ፡፡ የእስራኤልም ንጉሥ በዚያ ባለመሄድ ራሱን አዳነ፡፡ የሶርያም ንጉሥ ባሪያዎቹን ጠርቶ ‹‹ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ ንገሩኝ?›› አላቸው፡፡ ከባሪያዎቹም አንዱ ‹‹ጌታዬ ሆይ በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል›› አለው፡፡ የሶርያ ንጉሥ ኤልሳዕ ያለው በዶታይን እንደሆነ ሲነግሩት የዶታይንን ከተማ ከበባት፡፡ የኤልሳዕ ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ የከበባቸውን ጭፍራና ፈረሶቻቸውን ሲመለከት እጅግ ፈራ፡፡ ኤልሳዕም ‹‹ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ›› አለው፡፡ ‹‹አቤቱ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥ›› ብሎ በመጸለይ የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፡፡ ኤልሳዕም በጸሎቱ ሁሉንም ዕውር አደረጋቸው፡፡ ወደ ሰማርያም እየመራቸው ከወሰዳቸው በኋላ ዳግመኛ ያዩ ዘንድ ጸለየና ሁሉም ማየት ቻሉ፡፡ የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ አልሳዕን ‹‹አባቴ ሆይ?›› ባለው ሰዓት እንዳይገድላቸው ይልቁንም አብልቶ አጠጥቶ እንዲልካቸው ነገረው፡፡ እነርሱም በልተው ጠጥተው ሲያበቁ ወደ ጌታቸው ሄዱ፡፡ ከዚያም በኋላ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራዊቱን ሁሉ ሰበሰበና ወጥቶ ሰማርያን ከበባት፡፡ በሰማርያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ በሀገራቸው የሶርያ ሰዎች ሰፍረው ተቀመጡ፡፡ በዚህም ጊዜ እናት ልጇን ቀቅላ እስክትበላ ድረስ እጅግ አሠቃቂ ታላቅ ርሃብ ሆነ፡፡ ይህም ክፉ የርሃብ ዘመን በነቢዩ ኤልሳዕ ጸሎት በአንዲት ቀን ተለውጦ የጥጋብ ዘመን ሆኗል፡፡ 2ኛ ነገ 6፡8-33፣ 7፡1-20፡፡ ኤልሳዕም በዘመኑ ትንቢትን እየተናገረ እጅግ ታላላቅ ተአምራን እያደረገ እግዚአብሔርንም ሕዝቡንም ሲያገለግል ከኖረ በኋላ ሰኔ 20 ቀን ዐርፏል፡፡ ከሞተም በኋላ ዐፅሙ የሞተን ሰው
Hammasini ko'rsatish...
አስነሥቷል፡፡ 2ኛ ነገ 13፡21፡፡ ይኸውም የሞአብ ሰዎች አገራቸውን ከበው ሳለ አንድ ሰው ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት አደጋ ጣዮች አዩአቸው፡፡ እነርሱም ደንግጠው ሬሳውን በአልሳዕ መቃብር ላይ ጣሉት፡፡ በዚህም ጊዜ ሬሳው የአልሳዕ ዐፅም በነካው ጊዜ አፈፍ ብሎ ከሞት ተነሥቶ በእግሮቹ ቆሟል፡፡ የነቢዩ የቅዱስ ኤሌሳዕ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ + + + ዳግመኛም በዚኽች ዕለት በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት ያለጭቃና ውኃ በሦስት ድንጋዮች ብቻ በተወደደ ልጇ እጅ የታነፀችበት ዕለት ነው፡፡ የዚኽም ቤ/ክ የቅዳሴ በዓል ነገ በ21 ስለሚከበር ነገ ላይ አብረን እናየዋለን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ሰኔ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞ ❇️አባ_ገሪማ (ይስሐቅ) መደራ❇️ ✞ =>አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ፡፡ +እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ: መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል:: +አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር:: +ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው:: +እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር:: +አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ (800 ሜትር) ተጠራርጎ ሸሸ:: +ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ_ይስሐቅ_ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡ +አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል:: +ጻድቁ ወንጌልን: ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:- 1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር "በጽባሕ ይዘርዕ: ወበሠርክ የአርር" እንዲል:: 2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር:: 3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ:: 4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች:: 5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል:: +ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ: መታሰቢያህን ያደረገ: እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል፡፡ ✞ አባ ለትጹን የዋህ ✞ =>ስመ ጥሩ ጻድቅ አባ ለትጹን በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ የተወለዱ: ¤በፍጹም ተግሣጽ ያደጉ: ¤ከልጅነታቸው ጀምሮ ራሳቸውን በሕገ ወንጌል የመሩ: ¤አንድ ቀን በሰሟት የወንጌል ቃል የመነኑ: ¤ገዳም ገብተው በትሕትና ለዘመናት ያገለገሉ: ¤በመጨረሻም ወደ ትልቅ ተራራ ወጥተው ተጋድሏቸውን የፈጸሙ ታላቅ አባት ናቸው:: +ከየዋሕነታቸው የተነሳ ኃጢአተኛ ሰው ሲያገኙ ራሳቸው ንስሃ ይገቡ ነበር:: አንዴ ግን እናቱን 10 ጊዜ በዝሙት ያረከሰ: ስትጸንስም መርዝ አጠጥቶ ጽንሱን በማሕጸኗ የገደለና በሥጋ ወደሙ ላይ የተዘባበተ ሰው ሊሞት ሲል ደረሱ:: +አጋንንት ሲዖል ታች ሲጥሉትም ተመለከቱ:: ኃጢአቱ ጭንቅ ቢሆንም የእርሱን ንስሃ ሊቀበሉ ጀመሩ: ከንስሃቸው ጽናት የተነሳ ሞቱ:: ጌታችን ከሞት አስነስቶ "አትለምነኝ: አልምረውም" አላቸው:: +ጻድቁ ተስፋ አልቆረጡምና ቀጠሉ:: ለ2ኛ ጊዜ ሞቱ:: አሁንም ቀጠሉ: 3ኛ: 4ኛ: 5ኛ ጊዜም ሞቱ:: በ6ኛው ግን መፍትሔ መጣ:: ጌታችን አእላፍ መላእክትን አስከትሎ: ያችንም ኃጥእ ነፍስ ይዞ መጣ:: "ፍርዴ አይታጠፍምና ወደ ገነት አላስገባትም:: ስለ አንተ ጽድቅና የዋሕነት ደግሞ ሲዖል አልጥላትም:: ስለዚሕም እንዳልተፈጠረች ትሁን" ብሎ እፍ አለባት:: ፈጥና ወደ ትቢያነት ተቀየረች:: +ጻድቁም የፈጣሪያቸውን ቸርነት አድንቀው ሰገዱ:: ከብዙ ዘመናት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐረፉ:: ✞ አባ_ዸላሞን_ፈላሲ ✞ =>ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ ገዳማውያን አንዱ አባ ዸላሞን የአባ ለትጹን ወዳጅ ነበር:: ይሕ ቅዱስ ከአጋንንት ጋር በገጠመው ጦርነት ምክንያት ለየት ይላል:: ከ60 ዓመታት በላይ እንኳን ሳቅና ደስታ ቀና ብሎም ሰው አላየም:: +በነዚሁ ዘመናት ሁሉ ቅንድቡ እስኪላጥ አልቅሷል:: በዓለም ያሉ አጋንንት ሁሉ ተሰብስበው አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: በወዳጁ በአባ ለትጹን ጸሎትና በትጋት አሸንፏቸው ዛሬ ዐርፏል:: =>ቸሩ አምላካችን ከታላላቁ ቅዱሳን ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን:: =>ሰኔ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ብጹዕ አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ 2.አባ ለትጹን ዐቢይ ወየዋሕ 3.አባ ዸላሞን ፈላሲ 4.ቅድስት አርሴማ ጻድቅት 5.ሰማዕታት እለ አኮራን 6፡ ፯፼ ፹፻ ሰማዕታት ማኅበረ ቅዱስ ተክለሃ ይማኖት ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት 2፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ 3፡ ቅዱሳን መክሲሞስ ወደማቴዎስ 4፡ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ =>+"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:28-31) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
Hammasini ko'rsatish...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

ናቸው እንጂ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ለአባታችን አዳምና ለእናታችን ለሔዋን ‹‹መልካምና ክፉውን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብሉ (ዘፍ 2፡18›› ሲል መቼም ቢሆን አትብሉ ማለቱ እንደሆነ ያለ ነው፡፡ በጾም ወቅት በፈቃዳችን ሥጋችንን ስለምናደክም ‹‹መቼም የማይጾሙትን›› የበለጠ ልናደርግ፣ ‹‹መቼም ከማይበሉት›› ደግሞ የበለጠ ልንከለከል እንችል ይሆናል፡፡ ይህ ማለት ግን የጾም ወቅት ሲያልፍ ወደ ነበርንበት እንመለስ ማለት አይደለም፡፡ በጾም ወቅት የነበሩንን መልካም ነገሮች ከጾሙም በኋላ ይዘናቸው ልንቀጥል ይገባል እንጂ፡፡ በጾም ወቅት የተውናቸውን የሚጎዱን ነገሮች ደግሞ ከጾም በኋላ መልሰን ልንይዛቸው አይገባም፡፡ እንደተውናቸው ልንቀጥል ይገባል እንጂ፡፡ ሰለዚህ በጾም ወቅት ያለንን ተሞክሮ በማጽናት ‹‹ መቼም የማይጾሙትን›› መቼም አለመጾም፣ ‹‹መቼም የማይበሉትን›› ደግሞ መቼም አለመብላት ይገባናል፡፡ ይህንን ስናደርግ ‹‹የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፡- እነሆኝ ይላል። ኢሳ 58፡8-9›› እንደተባለው ይሆንልናል፡፡ የ‹‹ #ቀሳውስት_ጾም›› ወይስ የ #ክርስቲያኖች_ሁሉ_ጾም? የሐዋርያትን ጾም አንዳንዶች ‹‹የቀሳውስት ጾም›› ሲሉት ይሰማል፡፡ ይህም ከአሰያየሙ ጋር የተያያዘ ብዥታን በመጠቀም ላለመጾም የሚፈልጉ ወገኖች ያመጡት አስተሳሰብ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ‹‹የሐዋርያት›› የሚለውን ቃል ብቻ በመውሰድ ጥንት ይህንን ጾም ሐዋርያት ብቻ እንጂ ሕዝቡ አልጾመውም፤ ዛሬ ደግሞ በሐዋርያት እግር የተተኩ ካህናት (ቄሶች) ናቸውና ጾሙም የእነርሱ ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ብዙውን ጊዜም ቀሳውስት አበክረው ስለሚጾሙትና በሕዝቡም ዘንድ ይህ ስለሚታወቅም ጭምር ነው ይህ አስተሳሰብ የመጣው፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ይህን የአዋጅ ጾም ጳጳስ፣ ቄስ/መነኩሴ፣ ዲያቆን፣ ሰንበት ተማሪ ምዕመን ሳይል በ40 እና በ80 ቀን የተጠመቀና ዕድሜው ከሰባት ዓመት በላይ የሆነው ሁሉ እንዲጾም አውጃለች፡፡ እኛም እነርሱን ተከትለን፣ በእነርሱ ሥርዓት በመመራት፣ በሐዋርያት ላይ ያደረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብት በእኛም ላይ እንዲያድርብን በየዓመቱ ጾመ ሐዋርያትን ሌሎችንም አጽዋማት አክብረን መጾም እንደሚገባን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስኗል (ፍት.ነገ. 15፡ 586)፡፡ #የሐዋርያት_ጾም_የእኛም_ጾም_ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›› እንዳለ (ኤፌ 2፡20) በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ለታነጽን ለእኛ ለክርስቲያኖች የሐዋርያት ጾም የእኛም ጾም ነው፡፡ የሐዋርያት ጾም  ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ስብከተ ወንጌልን ለመፈጸም በየሀገሩ ከመሰማራታቸው በፊት በሁሉም ነገር እግዚአብሔር እንዲረዳቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ እኛም የሐዋርያትን ጾም ስንጾም ሁል ጊዜ በንስሐ ታጥበን እና ነጽተን ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን ቀሪ ዘመናችንን እግዚአብሔር አምላክ እንዲባርክልንና ሰላምን ፍቅርን እና ጤናን እንዲሰጠን መጾም ይኖርብናል:: ይህ የሐዋርያት ጾም በሐዋርያት እግር የተተኩ የቤተክርስቲያንን አገልጋዮችም አገልግሎታቸውን እንዲባርክላቸውና ምዕመኑን ወደ መልካም ጎዳና እንዲመሩ የሚጸልዩበት ጾም ነው፡፡ በአጠቃላይ በሐዋርያት ጾም የሐዋርያት ክብራቸውና አገልግሎታቸው ይታሰባል፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን ነው፡፡ በዚህ ጾም ሐዋርያት ሁሉን ትተው ጌታን መከተላቸው፣ ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውና ስለ ቅዱስ ስሙ በጽናትና በጥብዐት መከራ መቀበላቸው ይዘከራል፡፡ ምዕመናን እና ካህናትም የቅዱሳን ሐዋርያትን መንፈሳዊ ተጋድሎ እያሰብን በዘመኑ ሁሉ በፍቅር በተዋበ የመታዘዝ ፍርሃት የየራሳችንን መዳን እንፈጽም ዘንድ (ፊልጵ. 2፡12) ጾምን በመጾም፣ ጸሎትን በመጸለይ ከእግዚአብሔርና በንፁህ ደሙ ከዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጋር ያለንን ፍጹም አንድነት ልናጸና፣ ራሳችንን ከኃጢአት ከበደል አርቀን በመታዘዝ ጸጋ የጾምን በረከት ልንቀበልበት ይገባል፡፡ ለዚህም የ #እግዚአብሔር ቸርነት፣ የ #እመቤታችን አማላጅነት የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት ጸሎት ይርዳን፡፡ አሜን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ሰኔ 17 #ጾመ_ሐዋርያት፦ የሐዋርያት ጾም የእኛም ጾም ነው! የሐዋርያትን አስተምህሮ የምትከተለው ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁሉ በሥርዓት እንዲሆን ስለሚገባ ለጾምም ሥርዓትን ሠርታለች፡፡ በዚህ መሠረት ሰባት የአዋጅ አጽዋማትን አውጃለች፡፡ ከእነዚህም መካከልም ጾመ ሐዋርያት (የሐዋርያት ጾም ወይም በተለምዶ ሥሙ- የሰኔ ጾም) (The Fast of the Holy Apostles) አንዱ ነው፡፡ ይህ ጾም ቅዱሳን ሐዋርያት የሥራቸው መጀመሪያ አድርገው ስለጾሙት አስቀድሞ ‹‹የጰንጤቆስጤ ጾም›› ወይም ‹‹የደቀ መዛሙርት ጾም›› ይባል ነበር፡፡ ከኒቅያ ጉባዔ በኋላ እስከ ዛሬ የምንጠቀምበትን ‹‹የሐዋርያት ጾም›› የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡  ሐዋርያትም የጾሙት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲጾሙ አስተምሯቸው ስለነበር ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ እንደጻፈው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው?” ብለው በጠየቁት ጊዜ “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ (ማቴ 9፥15-16)” በማለት እንዲጾሙ አዟቸዋል፡፡ይህንን አብነት በማድረግ ሐዋርያት ወንጌልን የሚሰብኩትን ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር (የሐዋ 13፥3፤4፥25)፡፡ የሐዋርያት ጾም በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተጻፈው መጽሐፈ ድዲስቅሊያ፣ በኣራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተጻፈው መጽሐፈ ቀለሜንጦስ፣ እንዲሁም ቅዱስ አትናቴዎስ ለንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በጻፈው መልእክት ላይ ተብራርቶ ይገኛል፡፡ ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስን ሰፍረውና ቆጥረው ባስረከቡን ሐዋርያውያን አበው መሰረትነት የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን ሁሉ የመታዘዝ ምልክት የሆነ የሐዋርያትን ጾም እንጾማለን፡፡ #ጾመ_ሐዋርያት: #ቅድመ_ጰራቅሊጦስ ቀደምት የቤተክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስረዱት ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታችን ዕርገት እስከ ኀምሳኛው ቀን (ለ10 ቀናት) ድረስ በጾምና በጸሎት ቆይተዋል፡፡ እነዚህንም 10ቀናት የጾሙት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ እያለ ‹‹ እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤  እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው…ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም›› (ዮሐ 14፡16-18) ብሎ የሰጣቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ ነበር፡፡ ይህንን ጾም በመጾም ሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ራሳቸውን አዘጋጅተውበታል፡፡ ዛሬም ካህናት ክህነት ከመቀበላቸው በፊት፣ አዳዲስ ተጠማቂዎችም ከጥምቀት በፊት እንዲሁም ክርስቲያኖች ሁሉ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ከመቀበላቸው በፊት የሚጾሙት ይህንን አብነት አድርገው ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ለመቀበል ራስን በጾምና በጸሎት ማዘጋጀት ያስፈልጋልና፡፡ #ጾመ_ሐዋርያት: #ድኅረ_ጰራቅሊጦስ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላም ጾምን የአገልግሎታቸው መጀመሪያ አድርገውታል፡፡ ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት ስለሁለት ዓላማ ነው፡፡ አንደኛው ስለተሰጣቸው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ አምላካቸውን ለማመስገን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ  በዓለሙ ሁሉ ዞረው ለሚሰብኩት ወንጌል ራሳቸውን ለማዘጋጀት ነው፡፡ ስለዚህም ነው መንፈሳዊ አገልግሎትና ስብከት የዚህ ጾም አንኳር ነጥቦች የሆኑት፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ መጾማቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት አድርገው ነው፡፡ እርሱ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ጌትነቱን ለመመስከር ከወረደ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄዶ በዚያ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ጾሟልና እነርሱ ደግሞ ኃይል ይሆናቸው ዘንድ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት ከተቀበሉ በኋላ ጾምን የሥራቸው ሁሉ መጀመሪያ አድርገዋል፡፡ አንዳንድ መዛግብት በመጀመሪያዎቹ ዘመናት የሐዋርያት ጾም የሚጀምረው ከጰራቅሊጦስ አንድ ሳምንት በኋላ ነበር ይላሉ፡፡ ከዚያም በ258ዓ.ም ከበዓለ ጰራቅሊጦስ እስከ ሐዋርያት በዓል (The Feast of the Holy Apostles)  (ሐምሌ 5) ድረስ እንዲሆን አባቶች ደነገጉ በማለት ያስረዳሉ፡፡ ይህም  የተረደገው የቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ በኔሮን ቄሳር በሮም አደባባይ ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ዕለት አብሮ ለማሰብ እንዲረዳ ነው በማለት ያጠናክሩታል፡፡ መጽሐፈ ድዲስቅሊያ ደግሞ ሐዋርያት 40 ቀን እንደጾሙ ከዚያም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ እግራቸውን አጥቧቸው ለስብከተ ወንጌል እንደተሰማሩ ያስረዳል፡፡ ‹‹ #እናንተ_ስትጦሙ ›› እና ‹‹ #አንተ_ግን_ስትጦም ›› መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ጾም የፈቃድ ብቻ ሳይሆን ትዕዛዝ መሆኑንም ለሐዋርያቱና ለሚከተለው ሕዝብ ሲያስተምር ‹‹ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። ማቴ 6፡16-18›› ብሏል፡፡ በዚህም ትምህርቱ እርሱ የሚወደው ጾም ምን አይነት እንደሆነና እንዲሁም የማኅበርና የግል ጾም መኖሩን ‹‹እናንተ ስትጦሙ›› እና ‹‹አንተ ግን ስትጦም›› ብሎ ለይቶ አስተምሯል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም የተወደደ ጾም እንዴት አይነቱ እንደሆነ ነቢያት አስቀድመው ‹‹የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?›› ብለው ጽፈዋል፡፡ ኢሳ 58፡6-8 ‹‹ #መቼም_የማይጾሙ›› እና ‹‹ #መቼም_የማይበሉ›› በቤተክርስቲያናችን ትምህርት ‹‹መቼም የማይጾሙ›› ወይም ‹‹ሁሌም የሚበሉ›› የሚባሉ ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህም በጾምም ይሁን በፍስክ የሚበሉ ወይም የሚደረጉ ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል የሕያው እግዚአብሔርን ቃል መመገብ፣ ለእርሱና ለቅዱሳኑ ምስጋናን ማቅረብ፣ መልካም ነገርን መስማት፤ ማየት፤ ማሰብ፣ መናገርና መሥራት ይገኙበታል፡፡ አንድ ሰው ሁል ጊዜ የእግዚብሔርን ቃል መመገብ ምስጋናውንም ምግብ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ትዕዛዙንም ዘወትር በመፈጸም ለአምላኩ ያለውን ፍቅር ሊገልጽ ይገባዋል፡፡እነዚህ ጾም ሲገባ ምግብን ተክተው የሚገቡ፣ ጾም ሲወጣ ደግሞ ሥጋን ተክተው የሚወጡ አይደሉም፡፡ ሁል ጊዜ ሙሉ የሕይወት ዘመናችንንም ልናደርጋቸው የሚገቡ ናቸው እንጂ፡፡ ስለዚህ ነው ‹‹መቼም የማይጾሙ›› የተባሉት፡፡ ከእነዚህ መከልከል በራሱ ኃጢአት ነውና፡፡ በተመሳሳይ ‹‹መቼም የማይበሉ›› ወይም ‹‹ሁሌም የሚጾሙ›› የሚባሉ ነገሮችም አሉ፡፡ እነዚህም የኃጢአት ሥራዎችና ወደ ኃጢአትም የሚመሩ ነገሮች ናቸው፡፡ ክፉ ማየት፣ ክፉ መስማት፣ ክፉ ማሰብ፣ ክፉ መናገር፣ ክፉ ማድረግና እነዚህም የመሳሰሉት ነገሮች መቼም መበላት ወይም መደረግ የሌለባቸው ስለሆኑ ሁል ጊዜ ከእነዚህ መጾም ያስፈልጋል፡፡ በስህተትም ከእነዚህ የቀመሰ ወይም የበላ ዋናውን ጾም ገድፏልና በቶሎ ወደ ንስሐ ሊቀርብ ይገባዋል፡፡ እነዚህ በጾም ወቅት የሚከለከሉ የጾም ወቅት ሲያልፍ ደግሞ የሚፈቀዱ አይደሉም፡፡ በማንኛውም ጊዜ የሚጾሙ
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.