cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

All Tip Media

ብዙ ማንበብ ብዙ ነገር እንድታይ ያረጋሀል Read more see more!

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
204
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የማስጠንቀቀያ ደውሎች ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት ስለራሳቸዉም ሆነ ስለአካባቢያቸዉ መልካምና ክፉ ነገሮችን እያዩ ይኖራሉ፡፡ መልካም ነገሮችን ወደራስህ ማስገባት እንዳለብህ ሁሉ ጠቃሚ ያልሆኑን ነገ አንተን ሊያፈርሱ የሚችሉትን የራስ ማንነቶች ላሳይህ... • 'ሰዉ ምንም አያዉቅም' ብለህ ከደመደምክ • ስራህን መጥላት • ባልደረቦችህን ሁሉ ከጠላህ • ከቤተሰብህ ጋር መጣላት • ምንም ጓደኛ ከሌለህ • ሁልጊዜ የሰራተኞችህን እርዳታ ከፈለክ • ጠዋት ጠዋት ከደበረህ • ነገን ማየት ካስጠላህ ወይም ለነገ ምንም ጉጉት ከሌለህ • ሁሌ የምትነጫነጭ ከሆነ • ከገባ ጀምሮ ‘እዚህ መስሪያ ቤት አልቆይም!’ እያልክ ሁሌ የምትዝት ከሆነ • ሰዎች እያወሩ የምታቋርጣቸዉ ከሆነና ምንም የማታዳምጥ ከሆንክ • ሁሌ የምታዝን ከሆነ - ከላይ ያነበብካቸዉ ነገሮች በተደጋጋሚ ካጠቁህ እራስህን መርምር፡፡ ማንም ሰዉ ላይ እጅህን አትቀስር፡፡ ችግሮችህን ለመቅረፍ ለራስህ ጊዜ ስጠዉ እንጂ ፈፅሞ ችላ አትበለዉ፡፡ @zreaders @zreaders @zreaders @zreaders
Hammasini ko'rsatish...
Secrets of Success- 1 1. Sleep less. This is one of the best investments you can make to make your life more productive and rewarding. Most people do not need more than 6 hours to maintain an excellent state of health. Try getting up one hour earlier for 21 days and it will develop into a powerful habit. Remember, it is the quality not the quantity of sleep that is important. And just imagine having an extra 30 hours a month to spend on the things that are important to you. 2. Set aside one hour every morning for personal development matters. Meditate, visualize yourday, read inspirational texts to set the tone of your day, listen to motivational tapes or read greatliterature. Take this quiet period to vitalize and energize your spirit for the productive day ahead.Watch the sun rise once a week or be with nature. Starting the day off well is a powerful strategy for self-renewal and personal effectiveness. 3. Do not allow those things that matter the most in your life be at the mercy of activities thatmatter the least. Every day, take the time to ask yourself the question "is this the best use of mytime and energy?" Time management is life management so guard your time with great care. 4. Use the rubber band method to condition your mind to focus solely on the most positive elements in your life. Place a rubber band around your wrist. Each time a negative, energy sapping thought enters your mind, snap the rubber band. Through the power of conditioning, your mind will associate pain with negative thinking and you will soon possess a strongly positive mindset. 5. Always answer the phone with enthusiasm in your voice and show your appreciation for the caller. Good phone manners are essential. To convey authority on the line, stand up. This will instill further confidence in your voice. 6. Throughout the day we all get inspiration and excellent ideas. Keep a set of cards (the size of business cards; available at most stationary stores) in your wallet along with a pencil to jot down these insights. When you get home, put the ideas in a central place such as a coil notepad and review them from time to time. As noted by Oliver Wendell Holmes: "Man\'s mind, once stretched by a new idea, never regains its original dimensions." 7. Set aside every Sunday evening for yourself and be strongly disciplined with this habit. Usethis period to plan your week, visualize your encounters and what you want to achieve, to readnew materials and inspirational books, to listen to soft soothing music and to simply relax. This habit will serve as your anchor to keep you focused, motivated and effective throughout the coming week. 8. Always remember the key principle that the quality of your life is the quality of your communication. This means the way you communicate with others and, more importantly, the way you communicate with yourself. What you focus on is what you get. If you look for the positive this is what you get. This is a fundamental law of Nature. 9. Stay on purpose, not on outcome. In other words, do the task because it is what you love todo or because it will help someone or is a valuable exercise. Don\'t do it for the money or the recognition. Those will come naturally. This is the way of the world. 10. Laugh for five minutes in the mirror each morning. Steve Martin does. Laughter activates many beneficial chemicals within the body that place us into a very joyous state. Laughter also returns the body to a state of balance. Laughter therapy has been regularly used to heal persons with varied ailments and is a wonderful tonic for life\'s ills. While the average 4 year old laughs 500 times a day, the average adult is lucky to laugh 15 times a day. Revitalize the habit of laughter, it will put far more living into your life. @zreaders @zreaders @zreaders @zreaders
Hammasini ko'rsatish...
ፓስፖርት ለምታወጡ ፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የፓስፖርት አገልግሎትን ተገልጋዬች ባሉበት ቦታ ሆነው በኦንላየን ምዝገባ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውሷል። ተገልግላዮች በማንኛው አካባቢ ባለና ኢንተርኔት አገልግሎት ባለበት የሞባይል ስልክ ወይም ኮምፒዩተር ላይ በመጠቀም www.ethiopianpassportservices.gov.et የሚለውን ሊንክ ተከትለው በእራሳቸው ወይንም በሌላ ቅርብ የቤተሰብ አባል ወይም በጓደኛ እንዲሞሉላቸው ማድረግ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ፡፡ ክፍያው የሚፈፀመውም በባንክ አማካኝነት ስለሆነ ቀጠሮ ለመያዝ ወደኤጀንሲው ቢሮ ተገልጋዩ በአካል መምጣት አይጠበቀበትም። የ "ኦንላየን አገልግሎት እንሰጣለን" በማለት በኤጀንሲው ዙሪያ ያሉና የክፍያ አገልግሎት ያለአግባብ የሚጨምሩ ፣ የተገልጋዩን መረጃ በጥራት የማይሞሉ፣ የተገልጋዩን ሳይሆን የራሳቸውን ስልክ ቁጥር በተገልጋዩ መረጃ ላይ በመፃፍ ለተገልጋዩ ተገቢው የፅሁፍ መልእክት እንዳይደርሰው የሚያደርጉ ፣ እንደልደት ምስክር ወረቀትና የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ያሉ አስፈላጊ መረጃዎችን በማጓደል ተጨማሪ ክፍያ የሚያስከፍሉ፣ የተጭበረበረ እና በሚመለከተው አካል ያልተረጋገጠ የልደት ሰርተፍኬት ከሚያቀርቡ ህገወጥ ደላሎች ስላሉ ተገልጋዩ እራሱን እንዲጠብቅ ኤጀንሲው አሳስቧል። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
Hammasini ko'rsatish...
ጠቃሚ ጤና መረጃ በቂ እንቅልፍ ባለመተኛትዎ የሚያጋጥሞትን የጤና ችግሮች ልብ ይበሉ 1. በቂ እንቅልፍ ማጣት አእምሮችን ተግባሩን በአግባቡ እንዳይወጣ ያደርጋል፡-እንደ አሜሪካው የበሽታዎች መከላከል ማእከል መረጃ መሰረት እንቅልፍ ማጣት አንዱ የማህበረሰብ የጤና ችግር ነው፡፡ በየዕለቱ ከ ሰባት ሰዓት በታች ተኙ ማለት በአጭሩ ችግሮችን የመፍታት ክዕሎትዎ ፣ አመክንዮትዎ ላይ፣ በጥልቅ የማሰብ ብቃትዎ ላይ ችግር በመፍጠር የአእምሮዎን ብቃት ደካማ ያደረገዋል፡፡ 2. በቀላሉ ነገሮችን የሚረሱ ያደርጎታል፡- በቂ እንቅልፍ ማጣት በነገሮች ላይ ያሎትን ትኩረት ደካማ ከማድረጉም ባሻገር ነገሮችን ለመረዳት ዘገምተኛ ስለሚያደርጎት በቀላሉ ያዩትንም ሆነ የሰሙትን ነገሮች እንዳያስታውሱ በማድረግ በሰዎች ዘንድ‹‹ ልበ-ቢስ ›› ያሰኞታል፡፡ ምክንያቱ ቢሉ ደግሞ እንቅልፍ የነርቭ ግንኙነትን በማጠናከር ነገሮችን ማስታወስ እንድንችል ተፅህኖ ስለሚያሳርፍ ነው፡፡ 3. በቂ እንቅልፍ ማጣት በቀላሉ ብስጩ እንድንሆን ያድርገናል፡- እንፍቅልፍ አጥተው ሲያድሩ አይኖን እንኳን ሳይቀር በደስታ አይከፍቱም፣ስሜትዎ ስለሚረበሽ ነገሮችን የሚያዩበት መንገድ በሙሉ አሉታዊ ወይም ኔጌቲቭ በመሆኑ በቀላሉ ይበሳጫሉ፡፡የዚህ ምክንያት ደግሞ አእምሮዎ በእንቅልፍ ምክንያት በቂ እረፍት ባለማግኘቱ የተነሳ በአግባቡ ነገሮችን ላለማከናወኑ አንዱ መገለጫው ይህ የስሜት መረበሽ ነው፡፡ 4. ድባቴ ውስጥ ሊያስገባዎት ይችላል፡- በእንቅልፍ ምክንያት ከሚያጋትመን የስሜት ወይም የሙድ መዛባት መካከል ድባቴ ወይም መደበት አንዱ ነው፡፡ በመላው ዓለም በድባቴ ከሚሰቃዩና ራሳቸውን ከሚያጠፉ ሰዎች መካከል አሥር እጥፍ የሚሆኑት በዘላቂ የእንቅልፍ ማጣት በሽታ(ኢንሶሚና) የተጠቁ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የእንቅልፍ እጦት እና ድባቴ በኃይለኛው ግንኙነት አላቸው፡፡ 5. የተሳሳተ ውሳኔ ወይም ድምዳሜ እንዲደርሱ ያደርጎታል፡- በቂ እንቅልፍ አጡ ማለት በስራ ላይ ያልዎት ብቃት ስለሚቀንስና ችግሮችን የመፍታት ብቃትዎ ደካማ እንዲሆን ስለሚያደርግ ከባድ ውሳኔ የሚጠይቁ ነገሮችን ሳያገናዝቡ በእንዝላልነት ኃላፊነት እንዲወስዱ ያደርጎታል፡፡ 6. ሞገደኛ አሽከርካሪ እንዲሆኑ ያደርጎታል፡- የእንቅልፍ እጦት በቂ ጥንቃቄ እንዳይኖሮት ያደርጋል፣የንቃትዎን መጠን ይቀንሳል እንዲሁም ነገሮችን የመገንዘብ ብቃትዎን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ነገሮችን በቸልተኛነት እንዲወስኑ በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎች ሰዎች አካል ብሎም ሕይወት መጥፋት መክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እኛ አገር በለሊት ዕቃ ጭነው ከአገር አገር የሚንቀሳቀሱ በተለይ የአይሱዙ መኪና አሽከርካሪዎች የዚህ ችግር ሰለባ መሆናችውን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ 7. ልብዎ ለጉዳት ሊዳርግ ይችላል፡- የእንቅልፍ እጦት መላ ሰውነታችንን ለችግር የሚጥል ሲሆን አንዳንዶቹ የጤና ችግሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚታዩ ሲሆን በረጅም የጊዜ ሂደት ውስጥ ከሚታዩት መካከል የልብ ጤና ችግር ተጠቃሽ ነው፡፡ ለልብ ሕመም ችግር ከሚጥለን ምክንያት ውስጥ ታዲያ በእንቅልፍ እጦት ምክንያት የሚከሰቱት የደም ግፊት፣የልብ ድካምና ስትሮክ የተሰኙት የጤና ችግሮች ናቸው፡፡ 8. የቆዳ መጎሳቆል ያስከትላል፡- በቂ እንቅልፍ መተኛት ቆዳችን ራሱን እንዲያድስ ከማድረጉም በተጨማሪ ለአንዳንድ የቆዳ በሽታዎች መፍትሔ ነው፡፡ በዚህም ተነሳ በቂ እንቅልፍ ዘወትር ማጣት ከአይናችን ስር ያላው ቆዳችን እንዲጠቁር፣የአበጠ አይን እንዲኖረን እና ድብዝዝ ያለ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ 9. የሰውነት ክብደትዎ እንዲጨምር ያደርጋል፡-በቂ እንቅልፍ ማጣት ጋርሊን የተሰኘ የምግብ ፍላጎት የሚጨምር ሆርሞን በመጨመርና ሌፕቲን የተሰኘ የምግብ ፍላጎት የሚቀንስ ሆርሞን በማጥፋት ብዙ ምግብ እንድንመገብ በማድረግ የሰውነታችን ክብደት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ 10. የግብረ-ስጋ ( የወሲብ) ፍላጎትዎ እንዲቀንስ ያደርጋል፡- እንቅልፍ ማጣት የሰውነት ድካምን ከማስከተሉም ባሻገር በተለይ የወንዶችን የዘር ፍሬ በመቀነስ ለወሲብ የሚያደርጉትን መነሳሳት በእጅጉ ይጎዳል፡፡ ፍላጎትም ይቀንሳል፡፡ 11. በቀላሉ ለበሽታ እንዲጋለጡ ያደርጋል፡፡ በቂ እንቅልፍ ማጣት የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን በማዳከም በተለይ ጉንፋን ዘወትር እንዲጎበኞት መፍቀድ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቂ እንቅልፍ ማጣት በሄፐታይተስ ቢ እና በካንሰር በሽታዎች እንድንጠቃ በር ከፋች ነው፡፡ 12. ምንም አይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ኃይል እንዲያጡ ያደርጎታል፡- በእንቅልፍ እጦት የተነሳ ሰውነቶ ይደክመዋል፣ይዝላል በዚህ የተነሳ ተንቀሳቅሰው የፈለጉትን ለማከናውን ትልቅ እንቅፋት ይሆናል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት ........... ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች @zreaders @zreaders @zreaders @zreaders
Hammasini ko'rsatish...
ባይወደውም እናገረዋለው • በህይወትህ ያጋጠመህን ነገር ሁሉ ሶሻል ሚዲያ ላይ(እነ ፌስ ቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ኢሞ ታንጎ ቫይበር ዋትአፕ ወዘተ...) አትለጥፍ አለቀ! ምክንያቱን ማወቅ ትፈልጋለህ ? ካልክ እሺ... • እንደማንኛዉም ነገር ሶሻል ሚዲያን በልኩ መጠቀም ምንም ጉዳት የለዉም...ነገር ግን ከመስመር ሲያልፍ ጉዳት ማስከተሉን መርሳት የለብህም ለምሳሌ፣ • ፖስት ከሚደረገዉ ነገር 95 ፐርሰንቱ ሰዎች ጉረኛ መሆናቸዉን ሊያሳዩ ሲፈልጉ የሚያደርጉት ነገር ነዉ፡፡ • የሆነ ሃይቅ ዳር ጁስ እየጠጣህ የተነሳኸዉን ፎቶ ፖስት ብታረግ 'እኔ እዚህ ዘና እያልኩ ነዉ አዳሜ!' እንደማለት ነዉ • ምርጥ ልብስ ለብሰህ የተነሳኀዉ ፎቶ 'እንደዚህ ፋሽን አዋቂ ነኝ ...አንተ ግን አደለህም' ለማለት ነዉ • እዚህ ጋር ግን ጨለምተኛ አስተሳሰብን ለማበረታታት አይደለም፡፡ በራስ መተማመን እኮ አሪፍ ነዉ፡፡ እኔም ሆንኩ አንተ የምንፈልገዉ ማንነት ነዉ፡፡ • ከጓደኞችህ ጋር ስትዝናና የተነሳኸዉን ፎቶ ፖስት ማድረግህ መጥፎ ነገር ነዉ? በፍፁም አይደለም! ይሁን እንጂ በጣም በብዛት እንደሱስ ፖስት የሚደረገዉ 'የእወቁልኝ እዩልኝ' አይነት ልምድ ብዙ ሰዎች ስለራሳቸዉ የበታችነት ስሜት እንዲጨምር ያደርጋል • እነዛም ሰዎች 'ከማንም አላንስም' በሚል መፈክር የፖስት መለጠፍ ጦርነት ዉስጥ ተዘፍቀዉ ሲፖስቱ ይነጋል ፣ይመሻል፣ አመት ይቀየራል! የዚህ ሁሉ ነገር ዉጤቱ ምን የሚሆን ይመስልሃል? እራሱን እየሸወደ የሚኖር 'የፖስት መፈንቅለ መንግስት' ያደረገ ህብረተሰብ መፍጠር! • ስለዚህ ሌላ ጊዜ ላይ ፖስት ማድረግ የምትፈልገዉ ነገር አንዳንዴና አስፈላጊ መሆኑን ካመንክበት ብቻ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ፖስት ከማድረግህ በፊት ይሄንን ጥያቄ ራስህን ጠይቅ... “ ሌሎችን ሰዎች የሚያስደስት ነዉ? ፖስት ያረኩት ለሌሎች መልካም እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል?” መልስህ አዎ ከሆነ ፖ፡፡፡፡ስ፡፡፡፡ት! 👇👇👇👇 JOIN 👇👇👇👇👇 @zreaders @zreaders @zreaders @zreaders 🙏🙏🙏 መልካም ምሽት🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
#Attention በ5 ክልሎችና በ2 የከተማ አስተዳድሮች ኤችአይቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ። በጋምቤላ፣አማራ፣ ሀረሪ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በላይ በመሆኑ በወረርሽኝ ደረጃ እንደሚገኙ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ማሳወቁን etv ዘግቧል። በሀገር ደረጃ የኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ከፍተኛ የስርጭት መጠን ያለባቸው ፦ - ጋምቤላ 4.6 በመቶ - አዲስ አበባ 3.4 በመቶ - ድሬዳዋ 2.5 በመቶ - ሀረሪ 2.4 በመቶ - አፋር 1.4 በመቶ - ትግራይ 1.2 በመቶ - አማራ 1.2 በመቶ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በWHO መረጃ ከሆነ አንድ በሽታ ወረርሽኝ ነው የሚባለው የስርጭት ምጣኔው 1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሲሆን፣ እንደ ሀገር የኤች አይ ቪ/ኤድስ የስርጭት መጠን 0.93 በመቶ ስለሆነ በወረርሽኝ ደረጃ አይደለንም ተብሏል። በማህበረሰብ ደረጃ ከፍተኛ የስርጭት ምጣኔ የሚታይባቸው ሴተኛ አዳሪዎች ሲሆን ቁጥሩ 23 በመቶ ነው ተብሏል። በመቀጠልም፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ ሴቶች ላይ 19 በመቶ ሆኖ ይታያል። የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ ኮንስትራክሽን ሳይት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ አፍላ ወጣቶች ላይ ከ2 በመቶ በላይ የስርጭት ምጣኔ ያሳያል። በከተማ ያለው የስርጭት ምጣኔ 3 በመቶ ሲሆን በገጠር ያለው ደግሞ 0.4 ደርሷል ተብሏል። በተጨማሪ በወንዶች ያለው የስርጭት ምጣኔ ከሴቶች ይልቅ ዝቅ ብሎ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ የHIV የስርጭት ምጣኔ 61 በመቶ የሚሸፍኑት ሴቶች ሲሆኑ ፣ 39 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍኑት ወንዶች እንደሆኑ ተገልጿል። (ኢብኮ) @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
Hammasini ko'rsatish...
ማመዛዘን አንድ ጊዜ አባት ከቢሮ ድክም ብሎት ቤት ሲገባ ልጁ ሁለት ፖም ይዞ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ አባት ፈገግ አለና ልጁን አንዱን ፖም እንዲሰጠዉ ጠየቀዉ፡፡ ይህን የሰማዉ ልጅ ሁለቱንም ፖሞች አንድ አንዴ ገመጥ ገመጥ አደረጋቸዉ፡፡ በዚህ ጊዜ አባት ተቆጣ... “አንተ ሆዳም! እንደዚህ ይደረጋል! አንዱ አይበቃህምና ነዉ ሁለቱንም ለመብላት የምትጣደፈዉ...!” እያለ የንዴት መትረየሱን አርከፈከፈዉ፡፡ ልጅ አዝኖ እንዲህ አለ “አባዬ እኔኮ ሁለቱንም የገመጥኩት ከሁለቱ የትኛዉ በጣም እንደሚጣፍጥ ለማወቅ ነዉ ...ይሄ በጣም ይጣፍጣል...ስለዚህ እንካ ላንተ! እኔ የቀረዉን ልብላ' ብሎት ለአባቱ የሚጣፍጠዉን ፖም ሰጠዉ፡፡ አባት እንባዉን መቆጣጠር አልቻለም፡፡ አንዳንዴ ነገሮች ምንም ሳይገቡን መጮህ፣ መናደድና መቆጣት እንፈልጋለን፡፡ አንድን ነገር ዉጤቱን ገምተን ከምንጀምር ቀረብ ብለን ከመሰረቱ ብንረዳ የበለጠ መልካም ነዉ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።።።።።።።።።።።። @Zreaders @Zreaders @Zreaders @Zreaders 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ሠናይ ቀን ይሁንላችሁ
Hammasini ko'rsatish...
ህይወት እና ብክነት •ምርጥ ሃሳቦች በአእምሮህ ዉስጥ እየመጡ በተግባር ካላዋልካቸዉ • እራስህን ከሌሎች ጋር የምታነጻጽር ከሆነ • የሚጠቅምህ ነገር ላይ ሳይሆን የማይጠቅምህ ላይ ጊዜህን ካቃተልክ • ሰዎች ስለኔ ምን ያስቡ ይሆን ብለህ መጨነቅ ከጀመርክ • ትላንት ስላሳለፍከዉ ህይወት ሁሌ የሚቆጭህ ከሆነ • ነገ ምን እሆናለሁ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ • እቅድህ በጣም ከበዛ • ሰዉን ለመለወጥ ሁሌ የምትሞክር ከሆነ • ምንም የማይጠቅም ክርክር ዉስጥ እራስህን ካገኘህ • ለምትሰራዉ ነገር ደንታ ቢስ ከሆንክ ህይወትህን በጣም እያባከንከዉ ነዉና ንቃ! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ #share #like #Join👇 @Zreaders @Zreaders @Zreaders @Zreaders 🙏🙏መልካም ቀን ተመኘውላችሁ🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
1፡ ለመሆኑ ምን ባደርግሽ ነዉ እንደዚህ የጠላሽኝ? 2፡ ማን እኔ? 1፡ እራስሽ! 2፡ መቼም ሰዉ አልጠላም! ሁሉንም ሰዉ እወዳለሁ 1፡ ሁሉንም መዉደድሽ እኔን እንዳትጠዪ አያደርግሽም 2፡ የመጥላት ደረጃ ላይ አልደረስኩም...አለ አይደል አንዳንዴ አቁስል ነገር ስለሆንክ ዉስጤን ታደማዋለህ 1፡ ህምም... እኔ ግን እጠላሻለሁ 2፡ እዉነት? 1፡ አዎ! 2፡ ለምን? 1፡ ጥላቻሽ በደረጃ ስለሆነ 2፡ ማለት? 1፡ ሰዉ ስጠላ ደረጃ አልመድብም! ወይ መዉደድ ወይ መጥላት አለቀ! 2፡ አሃ!እኔን የጠላከኝ ደረጃ መዳቢ... 1፡ ነሽ! 2፡ ይህን ያህል ካሳዘንኩህ ይቅርታ! 1፡ ብቻ መልካምነት ለራስ ነዉ ዉስጥሽና ዉጪሽ አንድ አይነት ማድረግ ቢያቅትሽ እንኳን ብታመሳሳዪዉ መልካም ነዉ፡፡ 2፡ ተቀብያለሁ! አንተን ደግሞ ልምከርህ? 1፡ እሺ.. 2፡ ስሜትህ ማንነትህን አይቆጣጠረዉ! ስሜትህን አሸንፈዉ አልቅስ አልቅስ ስላለህ ብቻ አታልቅስ ጩህ ጩህ ስላለህ ብቻ አትጩህ! ነገሮችን መዝነህ ብትናገር ጥሩ ይመስለኛል፡፡ 1፡ በለዉ! ምክርሽን ወድጄዋለሁ 2፡ አዎ ውደደዉ! አንዳንዴ ዉበትን፣ ቁንጅናን፣ ስብእናን፣ ስታይልን፣ ፋሽንን ብቻ ሳይሆን ምክርን፣ ሃሳብን፣ ዉሳኔን፣ ቃላትን ዉደድ! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 @zreaders @zreaders @zreaders @zreaders https://t.me/joinchat/AAAAAFeZBRpK9VacGHq04A https://t.me/joinchat/AAAAAFeZBRpK9VacGHq04A
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.