cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ውስተ ቀራንዮ ነጽሩ(የምድያም ምድር)

እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
471
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
የልደቱ ምስጢር . . ማርያም ንፅሕይት ወወለደት ዘበኲራ፤ ይህንንን ተአምር ምን አንደበት ያዉራ? ህዝቅኤል በትንቢት እንደተናገረው፤ የተዘጋዉን ደጅ ወልድ እንደከፈተዉ፤ የከፈተዉን በር ቆልፎ እንደዘጋዉ፤ በኤፍራታ ምድር ዜናዉን ሰማነዉ። ጥንት የሌለዉ ስጋ ቀዳማዊ ሆኖ፤ በርሷ ዘንድ አደረ ለፈቃዱ ታምኖ። በወንጌል ትዕዛዙ በፈቃድ ርስቱ፤ ከአንዲት ብላቴና በጎል መገኘቱ። የኤፍራታዉ ህፃን ልደቱ ሲነገር፤ እጅግ ያስደንቃል የስጋዌዉ ምስጢር። የንግሥና ዘዉድን መንበርን ሳይሻ፤ ትንቢቱን ፈፀመ ሊሆነን መካሻ። በልዩ ሰላምታ ብስራትን የሰማች፥ ይኲነኒ ብላ ቃልን የፀነሰች፤ እናትም ድንግልም ሆና የተገኘች። ዕፀ ጳጦስ ፀዳል ለባሽ፤ ለደከመ እንባን አባሽ። ንፅሕት ዘር እመብርሃን፤ ለተባለች ዳግሚት ሔዋን፤ እዉን በርሷ ዘመን፤ ተፈጥሬ ቢሆን፤ በራፌን ከፍቼ እቀበላት ይሆን ? መደቤን ለቅቄ አሳርፋት ይሆን? ወይስ እንደ አህዛብ ሁሉ...... ማንነቷን ሳላዉቅ እዘጋባት ነበር? በዋሻ እንድትወልድ እፈርድባት ነበር? ጥያቄ ለራሴ? ጥያቄ ለነፍሴ? ምንም ሳልረዳ ሳላዉቀዉ ትርጉሙን፤ ሳከብር የኖርኩኝ የጌታ ልደቱን። ፍቺዉን በሆዴ በአልባሴ እየደለልኩ፤ እልፍ ልደታትን በከንቱ አሳለፍኩ። ለካ............... ድልዳል በሌለበት በጎል መወለዱ፤ በጠባብ ሰዉነት ከሰማይ መዉረዱ። በዕፅ የወደቀ ደካማዉን አዳም፤ በዐፅ ላይ ተሰቅሎ ስብራቱን ሊያክም። ገነት ቢከረቸም በሴት የተነሳ፤ ዳግመኛ ሊከፍተዉ ..... ከስጋዋ ስጋ ነፍሷን ነፍስ ነሳ። ትርጉሙን ስንፈታ የልደቱን ምስጢር፤ ሽፍንፍኑን ቅኔ የቀኒቱን ዉቅር። የተስፋ ጉልላት መደሰቻዉ ቃል ነው፤ የፍቅር ባለቤት ልደቱ ፍቅር ነው። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ✍✍@ediwub
Hammasini ko'rsatish...
++ ሥነጽሑፍ - የእመቤታችን የመማጸኛ ግጥም ! ( ርዕስ - ወደ እኔ ነይ - ንዒ ኀቤየ ) ምንዳቤዬን አይቶ - የሚሔድ ሰው እንጂ - መጪ በሌለበት፣ መጎስቆሌን ሰምቶ - የሚጸየፍ እንጂ - ጎብኚ በራቀበት፣ ከተወዳጅ ልጅሽ - ከክርስቶስ ጋር ነይ፣ እንድትባርኪን - እንድትቀድሽን - ስንከብር እንድናይ። ከቀደሙት አበው - ከአዳም ከአቤል - ከሴት ኄኖስ  ጋራ፣ ወደ እኔ ነይ ድንግል - በፍቅር ሱባኤ - ስምሽን ስጠራ፣ በልዑል አምላክ ፊት - ሞገስን ካገኙ - እጅግ ከከበሩ፣ በዝክረ ስማቸው - ሄኖክ ኖሕና ሴም - በሚል ከተጠሩ፣ አባታችን አብርሃም - ይስሐቅና ያዕቆብ - ቀደምት አባቶችሽ፣ ለዓለም መመኪያ - ተስፋ እንድትሆኚ - አንቺን የወለዱሽ፣ ምልጃቸው ያሻኛል - ፍቅራቸው ያሻኛል - ወደ እኔ ነይ ድንግል - እነዚህን ይዘሽ። ከሙሴም ጋራ ነይ - ከአሮንም ጋር ነይ - ከካህናት ጋር ነይ፣ በምስክር ድንኳን - አንቺን ከመሰሉሽ - በምድረ በዳ ላይ። ለእስራኤል ሁሉ - ርስት ካካፈለ - ከመስፍን ወነቢይ፣ ከኢያሱ ጋራ - ፀሐይን ካቆመ - በገባዖን ሰማይ፣ ከሳሙኤል ጋራ - ዳዊትን ከቀባው - ቀርነ ቅብዕ አፍልቶ፣ ለመንግሥት ካበቃው - ከበጎች መካከል - ከእረኝነት ጠርቶ፤ ባክሽ ነይ ድንግል ሆይ - 'ንዒ ንዒ' ስልሽ - እንዳትቀሪ ከቶ። ካባትሽ ዳዊት ጋር - በጥዑም መዝሙሩ - አንቺን ከሚጠራሽ፣ 'በወርቅ የተሸለምሽ - የርግብ ክንፍ ነሽ - ደግሞም በብር ያጌጥሽ'፣ እያለ በዜማ - ከሚያመሰግንሽ - ነይ ከርሱ ጋር ባክሽ። እነዚህ ሁለቱ - ቃላቸው ታላቅ ነው - ትንቢታቸው ሠናይ፣ ኢሳይያስ ኤርምያስ - ኃያል ሰባክያን - ከእነርሱ ጋርም ነይ። ነይ ወደኔ ድንግል ከኤልሣዕ ኤልያስ - ነቢያተ እስራኤል፣ ከዕዝራ ሱቱኤል ጋር የልቡናን ጽዋዕ - ካጠጣው ዑራኤል፣ ከሕዝቅኤል ጋር ነይ - ደግሞም ከዳንኤል፣ ከሚናገሩት ጋር - ስለ ሰማይ ምሥጢር - ስለ ኅቡዕ ልዑል፣ ንጉሥን አቅልለው - አምላክን አግንነው - በጸሎት ከተጉት - በእቶኑ ሥፍራ፣ ከነ አናንያ - ከነ አዛርያ - ከሚሳኤል ጋራ፣ ነይ ወደኔ ድንግል - ስምሽን ስጠራ። ስለ አምላክ ሲሉ - ብዙ ከሰበኩት - ነቢያተ ይሁዳ፣ በሰማርያ ሆነው - ልጅሽን ከሣሉት - በትንቢት ሰሌዳ፣ በባቢሎን ዘልቀው - ሕዝብን ካስተማሩት - ነቢያተ ልዑል፣ ከሁሉም ጋር ሆነሽ - ንዒ ንዒ ማርያም - ንዒ ንዒ ድንግል። ምንጭ ፦ (ዲ/ን ሕሊና በለጠ ፥"ንዒ ኀቤየ" የሚለውን የሰዓታት ክፍልንና በውስጡ የተጠቀሱትን አበው ብቻ በማንሣት የተሰናዳ )
Hammasini ko'rsatish...
❤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጉዞ ወደ ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ጀምረዋል…!! _________ ❤ "…ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሃገረ አሜሪካ ሲከታተሉ የቆዩትን ህክምና በሚገባ አጠናቀው ዛሬ በሙሉ ጤንነት ወደ ቅድስት ሃገራቸው ኢትዮጵያና ወደ መንበራቸው ጉዞ ጀምረዋል። መልካም ጉዞ… ይፍቱኝ ይባርኩኝ አባቴ…!! ❤ “… በእግዚአብሔር ዘንድ ተክለ ሃይማኖት ክቡር ነው፤ ዘወትርም መንፈስ ቅዱስ በመቃብሩ ላይ ይረባል። በተክለ ሃይማኖት ወንበር የተቀመጠ ተክለ ሃይማኖት ነው። ”ገድለ ተክለ ሃይማኖት ም61 ቁ9 ገጽ 204። እናም ቅዱስ አባቴ ሆይ ከመናፍቅ… እና ከአክራሪ ነውጠኛው ፀረ ተዋሕዶ አህዛብ ጋርማ ተደርቤ በመቆም ነውረኛ አልሆንም። አባት መቼም አባት ነው አለቀ ! ❤ ነገ ጷጒሜን 1 በብፁዕ አቡነ አብርሃም እየተመራ በመንበረ ፖትርያሪክ ከፍተኛ አቀባበል ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ ይደረጋል፡፡ • መልካም መንገድ… ይፍቱን ይባርኩን።
Hammasini ko'rsatish...
ጥብቅ ማሳሰቢያ **** ነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም """"""""""""""""""""""""""""" አዲስ አበበ -ኢትዮጵያ """""""""""""""""""""" ሰምኑን የቤተክርስቲያናችን ባልሆኑ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የቤተክርስቲያናችንን አርማ በመጠቀምና የቤተክርስቲያናችን ማኅበራዊ መገናኛዎች በማስመሰል ልዩ ልዩ ዜናዎችን በመሥራት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚሞክሩ ድረ ገጾች እየተሰራጩ መሆኑን ደርሰንበታል። እነዚሁ ድረ ገጾች ላይም በተለይ የቤተክርስቲያናችን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት መግለጫ በማስመሰል የሚያስተላልፏቸው ዘገባዎች ሐሰተኞች ከመሆናቸውም በላይ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ስም የተከፈቱ የቲዩተርም ሆነ የፌስ ቡክ አካውንት የሌለ መሆኑን እየገለጽን ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ በቤተክርስቲያናችን መገናኛ ብዙሃንና በሕዝብ ግንኙነት ድረ ገጾች ብቻ የሚያስተላለፉ መሆኑን እየገለጽን ሕዝበ ክርስቲያኑ ከነዚህ ህጋዊ የቤተክርስቲያናችን መገናኛ ዘዴዎች ውጪ የሚተላለፉ መልእክቶች ሁሉ የሐሰት መረጃዎች መሆናቸውን በመረዳት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር ከተከፈቱ ሐሰተኛ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን በመጠበቅና ለክፉ ዓላማ ማሳኪያ ተብለው የተከፈቱ መገናኛ አውታሮችን እንዲጋለጡ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች። መረጃው ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር በማድረግ እንዲተባበሩን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች። የኢኦተቤክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Hammasini ko'rsatish...
ትንሣኤሽን ልየዉ ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣ በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ። ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣ ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ። ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣ አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ። ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ድንግል ላመስግንሽ በዉቡ ዝማሜ፣ ፅናፅል ከበሮን ከፊት አስቀድሜ። እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣ ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ። ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣ በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Hammasini ko'rsatish...
ይህን ያውቁ ኖሯል? 📝ለሰባኪያን መቆሚያ ከፍ ያለ ቦታና አትሮንስ በቤተክርስቲያን መጠቀም የተጀመረው ከ386 ዓ.ም አከባቢ ባለው ዩሐንስ አፈወርቅ ነው። ቅዱስ ዩሐንስ አፍወርቅ በሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ በብዛት ይሰበሰብ ነበር። ነገር ግን የዩሐንስ ቁመት አጭር ነበረና ከፍ ብሎ ለሕዝብ እንዲታይና ድምፁም እንዲሰማ መቆሚያ ስፍራና ያጽሐፍት ማንበቢያ አትሮንስ ተሰራች። ቤተክርስቲያንም ከዚያ ዘመን ጀምሮ አትሮንስን ትጠቀምበት ጀመር። 📝ኑዛዜ በቤተክርስቲያን የተጀመረው ሕጋዊና ድንግል ከሆነው የእስክንድርያ 12እኛ ፓትራያርክ ከአባታችን ከቅዱስ ድሜጥሮስ ወዲህ ነው።አባታችን በከንቱ አምተውት የነበሩ ምእመናን በእግዚአብሔር ፋቃድ ክብሩ ቀተገለጠላቸው ጊዜ አባታችን ይቅርበለን ብለው ንስሐ ሲገቡ ይፍትሕ ይኅድግ ብለው ናዝዘዋል። ኑዛዜም ያን ጊዜ ተጀምሯል። 📝አንገት ላይ ማተብ ማሰር የተጀመረው ቀን5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሶርያ ያስተምር በነበረው በአባታችን በያዕቆብ ዘእልበረዲ ነው። አባታችን እያስተማረ በሚያጠምቅበት ጊዜ ለተጠመቁትና ያልተጠመቁት እየተቀላቀሉ ቢያስቸግሩት ለማየት ይቻል ዘንድ ለተጠመቁት ምዕመናን ማተብ ያስርላቸው ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማተብ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች መለያ ምልክት ሆነ። ከመ/ር ቴዎድሮስ በየነ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
"ማር" በምድርም "ያም" በሰማይ . . . ሀዘኔ በርትቶ፣ ስትጨነቅ ነፍሴ፣ ፈገግታዬ ጠፍቶ፣ ሲታወወክ መንፈሴ፣ ወድቄ ከፊትሽ፣ አድኚኝ እላለሁ፣ አልቅሼ ከደጅሽ፣ ከሀዘኔ እወጣለሁ፣ ማንስ ብዬ ልጥራዉ? እናቴ ስምሽን፣ በምንስ ልግለፀዉ? ጥዑም መዓዛሽን፣ ማር በምድር፣ ያም በሰማይ፣ የሥላሴን ክብር፣ አጉልታ ምታሳይ፣ እሙ ለፀሐይ ጽድቅ፣ የእግዚአብሔር ከተማ፣ ጥምን የምታርቅ፣ ፍቅር ለተጠማ። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️ በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
( ያንተን ሙሴ ስጠን ! ) የንፁኃን ደም ሲጎርፍ ፥ ምድር በደም ታልላ ዋይታና ጩኸት ሲበረታ ፥ የፈርዖናዊያን ግፍ ፅዋውን ሲሞላ የራሄል እንባ ፥ ሲፈስስ ... በልጆቹ ደም ተነክሮ ፥ የእናት አንጀት ሲላወስ "አምላከ እስራኤል አዶናይ የለም ወይ በዚህ ሰማይ?" የሚል የፍጥረት ሲቃ ፥ ምድርን ሲያናውጣት በመፅሐፍ ያነበብነው ፥ ይሄ የግፍ ጊዜ፥ የሰቆቃ ወራት በእኛ ለኢትዮጵያውያን ሲደርስ ፍርድ ሲገመደል ፥ እውነት በግፍ ሲታመስ ... አገዛዝ ሲፀናብን ፥ የህዝብ ልብ ሲታወክ ድረስልን ጌታ ፥ ሙሴን ለእኛ ላክ። እውነት ነው ... ! የሙሴን መገለጥ ስለመራብ ፥ ስለ ፅኑ ናፍቆት ፥ ስለ ሙሴ ስስት ባንተ ያልተቀባውን ፥ አንተ ያልሾምከውን ፥ ሙሴ ነህ በማለት የራሳችን ሙሴ ፥ ልናቆም ፥ ቀብተን ልናነግስ ቃላት በመደረድር ቅኔን ስንቀኝ ርሱን ስናወድስ ፥ ርሱን ስናሞግስ... ብናሳዝንህም በዚህ ስንፍናችን ጌታ ይቅር በለን ፥ አሁን ድረስልን "የእኛን ሙሴ" ወስደህ ፥ "ያንተን ሙሴ" ስጠን። #መታሰቢያነቱ ፦ ለአራት አመታት በኢትዮጵያ ለዘለቀው የንጹሐን ሰላሚዊ ዜጎች አሰቃቂ ግድያና ሀብት ንብታቸውን ተዘርፈው ለተፈናቀሉ ወገኖቼ ትሁንልኝ ! አቤቱ ክንድህ በክፉዎች ላይ ይጽና፤ በነፈሰ ገዳዮች ላይ የቅጣት ጂራፍህ ይጩህ፤ አቤቱ ግፈኞችን ተበቀል !
Hammasini ko'rsatish...
ሰላም
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
"ኃጢአት ለመሥራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ጽድቅ ለመሥራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ፡፡ ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ ንስሐ አባትህን ለማግኘት ግን ጊዜ የለህም፡፡ በሥጋ ስትራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢኾን) ትበላለህ፤ ነፍስህ የክርስቶስ ሥጋ ከራባት ግን ዘመናት ተቆጠሩ፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባብ አሳተኝ ያለችውንና፥ ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋን ታስታውሳለህን? እንግዲያውስ፥ አንተም እንደ እርሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፡፡ ይህ ሲነገርህም በተግባር እንጂ በከንፈርህ መልስ ለመስጠት አትጣር፡፡" አስተውል ወዳጄ አስተውል ወዳጄ ያለፈው ዘመን ይብቃህ የኃጢያት ቫይረስ እንዳይገልህ በንስሐ ህይወት ተመለስ !!" ❤️መልካም ምሽት
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.