cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

TIKVAH-SPORT

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
222 687
Obunachilar
+12424 soatlar
+1 6147 kunlar
+4 38130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ጃሬድ ብራንዝዌት ኤቨርተንን ላይለቅ ይችላል ! የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን አማካይ አማዱ ኦናና ወደ አስቶን ቪላ ማምራት በማንችስተር ዩናይትድ የሚፈለገውን ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር ሊያስቀረው እንደሚችል ተገልጿል። አማዱ ኦናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ ለአስቶን ቪላ ለመሸጥ የተቃረበው ኤቨርተን ከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ ካልቀረበላቸው ጃሬድ ብራንዝዌትን በዚህ ክረምት ላይሸጡት እንደሚችሉ ተነግሯል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ለ 21ዓመቱ ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት 50 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ሒሳብ አቅርበው በኤቨርተን ውድቅ እንደሆነባቸው ይታወሳል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
👍 27 2😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጃሬድ ብራንዝዌት ኤቨርተንን ላይለቅ ይችላል ! የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን አማካይ አማዱ ኦናና ወደ አስቶን ቪላ ማምራት በማንችስተር ዩናይትድ የሚፈለገውን ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር ሊያስቀረው እንደሚችል ተገልጿል። አማዱ ኦናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ ለአስቶን ቪላ ለመሸጥ የተቃረበው ኤቨርተን ከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ ካልቀረበላቸው ጃሬድ ብራንዝዌትን በዚህ ክረምት ላይሸጡት እንደሚችሉ ተነግሯል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ለ 21ዓመቱ ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት 50 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ሒሳብ አቅርበው በኤቨርተን ውድቅ እንደሆነባቸው ይታወሳል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ዩናይትድ ተጫዋቹን ሊሸጥ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊ ካምብዋላ ለስፔኑ ክለብ ቪያሪያል ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ቪያሪያል ተጨዋቹን በ10 ሚልዮን ዩሮ ለመግዛት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ቪያሪያልን በይፋ ለመቀላቀል ቀጠሮ እንደተያዘለት ተዘግቧል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
41👍 34👎 10😁 5👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
አስቶን ቪላ አማዱ ኦናናን ሊያስፈርም ነው ! በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ቤልጂየማዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አማዱ እናና ከኤቨርተን ለማስፈረም መቃረባቸው ተነግሯል። የ 22ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች አማዱ እናና በአስቶን ቪላ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ አማዱ እናናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም መስማማታቸው ተዘግቧል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
👍 62😁 11 3🔥 3👏 2🤬 2
Photo unavailableShow in Telegram
የወርቅ ጫማውን ስድስት ተጨዋቾች ሊያሸንፉ ይችላሉ ! ዩኤፋ ያለውን ህግ ማሻሻሉን ተከትሎ የዘንድሮውን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስድስት ተጨዋቾች ሊጋሩት እንደሚችሉ ተገልጿል። በነገው የፍፃሜ ጨዋታ ሀሪ ኬን እና ዳኒ ኦልሞ ወይም ሌላ ተጨዋች ግብ ማስቆጠር የማይችል ከሆነ የወርቅ ጫማው ለስድስት ተጨዋቾች እንደሚሰጥ ተነግሯል። የወርቅ ጫማውን ለማሸነፍ ሀሪ ኬን ፣ ዳኒ ኦልሞ ፣ ሙሲያላ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ሽራንዝ እና ሚካውታድዝ በሶስት ግቦች በመምራት ላይ ይገኛሉ። ዩኤፋ ከዚህ በፊት ተጨዋቾች በእኩል ግቦች ሲያጠናቅቁ ብዙ ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ያቀበለውን ተጨዋች ይመርጥ ነበር። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
👍 125😁 21 12😱 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
" ከሜሲ ጋር መጫወት እፈልጋለሁ " ላሚን ያማል ስፔናዊው የባርሴሎና ተስፈኛ ኮከብ ላሚን ያማል አርኣያው እንደሆነ ከሚናገርልት አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ጋር መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል። " ከሜሲ ጋር መጫወት እፈልጋለሁ " የሚለው ያማል በቀጣይ አርጀንቲና ኮፓ አሜሪካን እንደምታሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ ስፔን የአውሮፓ ዋንጫን ካሸነፈች በ " Finalissima " ከእሱ ጋር መጫወት እችላለሁ " ሲል ተናግሯል ። በኮፓ አሜሪካ እና አውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች መካከል የሚደረገው የ " Finalissima " ዋንጫ ጨዋታ በሚቀጥለው ክረምት ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
214👍 61😁 31👎 11👏 6🔥 2🤬 2
Photo unavailableShow in Telegram
" ጀርመን ውስጥ የኬንን የዋንጫ ጥማት አስቀጥያለሁ " ዳኒ ኦልሞ የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ ሀሪ ኬን ዋንጫ እንዳያሸንፍ የማድረግ ስራውን አለማጠናቀቁን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል። " ጀርመን ውስጥ የዋንጫ እርግማኑን ሊያነሳ የተቃረበውን ሀሪ ኬን አስቁሜው አስቀጥዬለታሁ " የሚለው ዳኒ ኦሎም " አሁንም ስራዬ አልተጠናቀቀም " ሲል ተናግሯል። ባለፈው አመት ባየር ሙኒክ ላይ ሀትሪክ በመስራት የጀርመን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ሌፕዚግ እንዲያሳካ ያገዘው ዳኒ ኦልሞ " ነገም ሀትሪክ መስራት እና ማሸነፍ ህልሜ ነው " ብሏል። የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት 4:00 በስፔን እና እንግሊዝ መካከል ይደረጋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
😁 380👍 95👎 25 9
Photo unavailableShow in Telegram
" እንዴት ለቤተሰብህ ላትከላከል ትችላለህ " ማርሴሎ ቤልሳ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ በኮሎምቢያ ጨዋታ በተፈጠረው ክስተት የደቡብ አሜሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና አዘጋጇ አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል። አሜሪካ ውድድሩን በብቃት ልታስተናግድ አለመቻሏን የገለፁት አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ ቡድናቸው የተጫወተባቸውን ሜዳዎች " ተቀባይነት የሌላቸው " ሲሉ ተችተዋል። የቀረቡት የልምምድ ስፍራዎች ጥራት የሌላቸው መሆኑንም አያይዘው የገለፁት አሰልጣኙ የነበረው የደህንነት ሁኔታም አስተማማኝ አለመሆኑ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል። በስታዲየሙ የነበረው የፀጥታ አካል የዩራጓይ ተጨዋቾች ቤተሰቦችን ከሰከሩ ደጋፊዎች እንኳን ሊጠብቅ አልቻለም ነበር ሲሉ ማርሴሎ ቤልሳ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የዩራጓይ ተጨዋቾች ሊጣልባቸው ስለሚችል ቅጣት ሀሳብ የተጠየቁት አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ " ለእናትህ ፣ እህትህ እና ልጅህ እንዴት ላትከላከል ትችላለህ ?" ሲል መልሰዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
👍 257 22👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
የዌምበልደን ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታወቁ ! ለአንድ መቶ ሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የ 2024 የታላቁ የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ተፋላሚዎች በሁለቱም ፆታዎች ተለይተው ታውቀዋል። በወንዶች የዌምበልደን ፍፃሜ የባለፈው አመት የፍፃሜ ተፋላሚዎች ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ እና ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች በድጋሜ ተገናኝተዋል። ባለፈው አመት ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ የሰባት ጊዜ የዌምበልደን አሸናፊውን ኖቫክ ጆኮቪች በመርታት የውድድሩ ወጣት አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር። በፍፃሜው ኖቫክ ጆኮቪች ከአራት ተከታታይ የዌምበልደን ድል በኋላ ባለፈው አመት የተቀማውን ክብር ለመመለስ ሲፋለም ወጣቱ ካርሎስ አልካራዝ በድጋሜ የድል ካባውን ለመድፋት ይፋለማል። የአለም ቁጥር ሁለቱ የሜዳ ቴኔስ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች ከአለም ቁጥር ሶስቱ ካርሎስ አልካራዝ የሚያደርጉት የፍፃሜ ፍልሚያ የፊታችን እሁድ ይደረጋል። በሴቶች የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ቼክ ሪፐብሊካዊቷ ባርቦራ ክሬቺኮቫ ከጣልያናዊቷ ጃሴሚን ፓኦሊኒ ጋር ተገናኝተዋል። የአለም ቁጥር ሰባቷ ጃሴሚን ፓኦሊኒ እና የአለም ቁጥር ሰላሳ ሁለቷ ባርቦራ ክሬቺኮቫ የፍፃሜ ጨዋታቸውን በዛሬው ዕለት ያደርጋሉ። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
👍 97 5
ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ አዲስ አበባ ደርሷል ! ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ናኒ ዛሬ ጠዋት ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መጥቷል። ተጨዋቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የመቻል 80ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ተካፋይ ተካፋይ ለመሆን የቀረበለትን ግብዣ ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም ናይጄሪያዊው የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ንዋንኮ ካኑ በምስረታ በዓሉ ለመካፈል ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ታውቋል። ተጫዋቾቹን የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ፣ የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፈ ጌታሁን እና የመከላከያ ሚዲያ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳ አቀባበል አድርገዋል። ምንጭ - የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሚዲያ @tikvahethsport     @kidusyoftahe
Hammasini ko'rsatish...
👍 251 41👎 20😁 9🤔 4🥰 2👏 1🙏 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.