cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አስኮ ማስታወቂያ (Mahi trading agent)

👉 ለወቅታዊ መረጃ 👉 ለሁነቶች ዝግጅት 👉 ለማስታወቂያና ፊልም ሥራ 👉 ቤት እና መኪና ገዥና ሻጭ አከራይና ተከራይ አገናኝ 👉 የተለያዩ ጉዳዮችን ለማስፈጸም #ASKO ለበለጠ መረጃ +251910683587 (+251916834309) ሐዋሳ( ኢትዮጵያ)🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
260
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዝዳንታዊ እጩ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ አለፈ በኮንጎ ብራዛቪል ከሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መካከል ዋንኛ የሆኑት ብሪስ ፓራፌት ኮልላስ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በትላንትናዉ እለት ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ህይወታቸዉን ለማትረፍ ለተሻለ ክህምና በሚል በህክምና አዉሮፕላን ዉስጥ እያሉ እረፍታቸዉ ተሰምቷል፡፡ ኮንጎ ብራዛቪል በትላንትናዉ እለት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያካሄደች ሲሆን ኮልላስ የምርጫ ቅስቀሳ ማጠናቀቂ ቀነ ገደቡ በሆነ ባሳለፍነዉ አርብ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ቅዳሜ እለት በኦክስጅን መተንፈሻ ላይ ሆነዉ ዜጎች ድምጻቸዉን እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የስኳር ህመም እንዳለባቸዉ የተነገረዉ የ61 ዓመቱ ኮልላስ የቀድሞ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ልጅ እና እርሳቸዉም በበርካታ የሀላፊነት ስፍራ ያገለገሉ ሰዉ ናቸዉ፡፡የትላንትቱ የኮንጎ ምርጫ ሰፊ ተሳትፎ ያልተደረበት መሆኑን ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡ በስምኦን ደረጄ/ብስራት ሬድዮ
Hammasini ko'rsatish...
ቴሌግራም ቻናሎች የቀጥታ የውይይት መድረክ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚፈጥሩበትን ሁኔታ አመቻቸ። በኢትዮጵያ አሁን ላይ መልዕክት ለመለዋወጫ እንዲሁም መረጃን ለማግኘት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው የቴሌግራም የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ በየጊዜው በሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች ይበልጥ ለመገልገል ምቹ እያደረጉት ይገኛሉ። በቅርቡ የድምጽ መልዕክት መለዋወጫን (Voice Chat) ያስተዋወቀው ቴሌግራም አሁን ላይ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ አድርጎ ለተጠቃሚው በቻናልና በግሩፕ የቀጥታ የውይይት መድረክ መፍጠር የሚያስችለውን አሰራር ዘርግቷል። በዚህም በቀጥታ የድምጽ ስርጭቱ የተሳታፊዎች ቁጥር አይወሰንም፤ የድምጽ ልውውጡን መቅዳትና ማስቀመጥ ያስችላል እንዲሁም በውይይቱ ለመሳተፍ እጅ ማውጣት የሚያስችሉ ማዘመኛዎች ተደርገውበታል። ማሻሻያዎቹን ለመጠቀም የቴሌግራም መተግበሪያዎትን ያዘምኑ (Update) via :Hulaadiss @askotrustedinfo
Hammasini ko'rsatish...
በሐዋሳ ከተማ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት ተካሄደ‼️ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች እና ለሕዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ላይ የኬሚካል ርጭት ተካሄደ። በሐዋሳ ከተማ በትናንትናው ዕለት ብቻ የኮቪድ ናሙና ከሰጡ 200 ግለሰቦች ውስጥ 68ቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
#የሀዋሳዋ_የመድረክ_መሪ_እንስት 🎤🎤 #በተለይም ሴቶች በብዛት ሲሳተፉበት እምብዛም በማይስተዋለዉ የመድረክ ሥራ በርካታ ተፅዕኖዎችን ተቋቁማ እዉቅናን ያተረፈች ወጣት። #በርካታ ሁነቶችን በስኬት ያዘጋጀች እያዘጋጀችም የምትገኝ #የተለያዩ የጥበብ ሥራዎች በክልል ከተሞች እንዲስፋፉ በማቀናጀት የድርሻዋን እየተወጣች የምትገኝ #እንስት #ፕሮሞተር ቤቲ (ቤተልሔም ሰሎሞን) #ሴት_ልጅ_ትችላለች🙏🙏🙏 #በተለይም_ሴቶች_ከኢኮኖሚ_ጥገኝነት_ለመላቀቅ_ሳይታክቱ_መትጋት_ሳያማርጡ_መሥራት_አለባቸዉ!! #ሥራ_ፆታ_የለዉም !! ትለናለች 🙏🙏 🇪🇹ዕሁድ በደቡብ ቴሌቪዥን የመዝናኛ 👉ፕሮግራም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት 👧 እንግዳ ሆና ልምዷን ታጋራናለች። ዕሁድ ሪሞታችሁን ደቡብ ቲቪ ላይ በማድረግ ይጠብቁኝ። መልዕክቷ ነዉ ፕሮሞተር ቤቲ ሀዋሳ 🙏🙏🙏በርቺ🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በጉራጌ ዞን በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ቦታ ተረከበ‼️ አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በሆቴል ኢንቨስትመንት ለመሰማራት 5 ሺህ 352 ካሬ ሜትር ቦታ መረከቡ ተገለፀ፡፡ በዞኑ በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል። via :-Esat
Hammasini ko'rsatish...
አዳማ፡ አዳማ ሆስፒታል የኮሮና ታካሚዎች ከአቅሜ በላይ ሆኑብኝ አለ መጋቢት 8፤ 2013 ዓ.ም. (አዲስ ዘይቤ፡ አዳማ) የኮሮና ታካሚዎች ቁጥር ማስተናገድ ከሚችለው በላይ እንደሆኑበት የአዳማ ጤና ኮሌጅና ሆስፒታል አስታውቋል፡፡ የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶ/ር በቀለ ለሜሳ እንደተናገሩት ማኅበረሰቡ ላይ የሚታየው መዘናጋት በመባባሱ ቫይረሱ በፍጥነት እየተዛመተ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የአዳማ ሆስፒታል ከአቅም በላይ በሆነ መንገድ ሠራተኞችን በማስተናገድ ላይ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር በቀለ፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተመደበው አካል ሕግ እየጣሰ ይገኛል ብለዋል፡፡ ሆስፒታሉ በአሁን ሰዓት በጽኑ ህሙማን ክፍሉ ውስጥ ከ34 በላይ ታካሚዎች እንዳሉት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
#ሀምበሪቾ 777 #ገመሻ ፍል ውሃ #7 የወንዞች ጅረት #599_የኢትዮጲያ ብር ብቻ #ለጥንዶች 900 ቅዳሜ 25/7/13 አይቀርም 5ሰው ለጋበዘ 1 ትኬት በነፃ የምዝገባ ቦታ ሀዋሳና አዲስ አበባ ናዝሬት እንዳያመልጥዎ ግሩም የመዝናኛ አማራጭ። ጥንዶች ይበረታታሉ ሙሽሮች VIP ተዘጋጅቶላችኋል ለተጨማሪ መረጃ +251902917695 +251911399175
Hammasini ko'rsatish...
ትግራይ፡ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር በዋስ መለቀቃቸው ተነገረ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር በዋስ መለቀቃቸውን ፖሊስ ዛሬ ለፍርድ ቤት ገለጸ። ፖሊስ ዛሬ ለተሰየመው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንደተናገረው ቀዳሚ ምርመራ አስኪሰማ ድረስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 28 መጀረት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም በዋስ መፈታታቸውን ገልጿል። በተጨማሪም የቀድሞ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት ወ/ሮ ህርይቲ ምህረተአብ እና የቀድሞው የትግራይ ክልል መስተዳደር አማካሪ የነበሩት አቶ ወልደጊዮርጊስ አሰፋ በዋስ ከእስር እንዲወጡ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተነግሯል። በእነአቶ ስብሐት ነጋ የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩት እነዚህ ግለሰቦች በዋስ እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው ዐቃቤ ሕግ እያካሄደ ባለው የምርመራ ሂደት ተጠርጣሪዎቹን በእስር ለማቆየት የሚያበቃ በቂ ማስረጃ አለማግኘቱን በመጥቀስ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን በመጠየቁ ነው። በተጨማሪም ዛሬ ችሎቱ በተመለከተው የክስ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት አቶ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ሰሎሞን ኪዳኔ፣ ቅዱሳን ነጋና የሌሎችም ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በቀዳሚ ምርመራ እንዲታይ ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱን ጠይቋል። በዋስ ከእስር መለቀቃቸው የተገለጸው የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ እጃቸውን መስጠታቸው የተነገረ ሲሆን ከሦስት ወራት በላይ በአስር ላይ ቆይተዋል።
Hammasini ko'rsatish...
ምርጫ ቦርድ በምርጫ አስፈጻሚ ምልመላ የፖሊሲ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል በምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ በተመለከተም የቦርዱ ሊቀመንር ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ በመግለጫው“ትልቅ የፖሊሲ ለውጥ ነው ያደረግነው” ያለ ሲሆን፤ “ብዙዎቹ ፓርቲዎች ልብ አይሉትም እንጂ ከአሁን ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ያስፈጸሙ ደግመው በአስፈጻነት እንዳይመዘገቡ አድርገናል” ብሏል። ከምርጫ አስፈጻሚዎች መካከል ችግር አለባቸው የሚሏቸው ካሉ በተጨባጭ ማስረጃ ከታገዘ እርምጃ የማይወስድበት ምክንያት እንደሌለም ቦርዱ አስታውቋል።
Hammasini ko'rsatish...