cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሀይማኖቴን ልወቅ (የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርት)

አንድ ጌታ አንድ ሀይማኖት አንዲት ጥምቀት ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕ4:-5

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
250
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

18. የአጥቢያ ኮከብ የአጥቢያ ኮከብ የብርሃን ፋና ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥነህ ቶሎ ና እኛን አሰማን 2 የሰላም ዜና አዝ.............. ለዘረንጦስ ለቲዮብስታ የሆንክላቸው መከታ ምድራዊ ንግስናን ንቀህ ሰማያዊ ክብር አገኘህ ሰዐለነ ጊዮርጊስ 2 ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ አዝ................. በሚያመልኳቸው ጣዖታት ያፈሩ ሰባው ነገስታት ድል ያረካቸው ጊዮርጊስ አማልደን ከኢየሱስ ሰዐለነ ጊዮርጊስ 2 ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ አዝ................ ስጋህ አመድ ሆኖ ቢዘራ በደብረ ይድራስ ተራራ የአመለከው አድኖሃል ሰባት አክሊላት ደፍተሀል ሰዐለነ ጊዮርጊስ 2 ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ አዝ................ ለዘረንጦስ ለቲዮብስታ የሆንክላቸው መከታ ምድራዊ ንግስናን ንቀህ ሰማያዊ ክብር አገኘህ ሰዐለነ ጊዮርጊስ 2 ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ @hayemanotenlewek @hayemanotenlewek
Hammasini ko'rsatish...
[_ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ?_] ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦ "ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ። በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ። እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ። በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ። ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ። ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው። እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21) ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም። ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ። ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9) አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች። ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!! [_ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ]
Hammasini ko'rsatish...
Music
Hammasini ko'rsatish...
ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማእት.mp34.47 MB
ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማዕት ይቅርታን ለመነ እሱን ለወገሩት ለአይሁድ አማፅያን የጠየቀ ምህረት ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማዕት 2 የስምዖን የሀና የእምነታቸው ፍሬ በአኖስ ከተማ ተወለደ ዛሬ ኦሪትን ተማረ ከገማልያል እውነት ሊመሰክር ሊሆነን መምህር አዝ ሊቀ ዳቆን ሆኖ ጉባዬ ሲመራ መልኩ እንደ መላዕክት እጅግ የሚያበራ ምግባርና እምነቱ ተመስክሮለታል ወልድን በመንበሩ በክብር አይቶታል አዝ አገር ለአገር ዞሮ ወንጌል አስተማረ ስለ ክርስቶስ ፍቅር እውነት መሰከረ ከአይሁድ ወገኖች ማንንም ሳይፈራ በክብር ተሰዋ ለስጋው ሳይራራ አዝ ቅድስና ሞልቶ እያየ ፈጣሪን እውነት ቢነግራቸው የፅራርያሙን ሁሉም አንድ ሆነና ቄዳርላይ ወገሩት ቁጥሩ ማይለካ ድንጋይ ከመሩበት  @hayemanotenleweke
Hammasini ko'rsatish...
Music
Hammasini ko'rsatish...
ኦ እስጢፋኖስ ሰማእት.mp32.17 MB
ኦ እስጢፋኖስ ሰማዕት 2 አክሊልን አገኘህ ከጌታ በእውነት የወንጌልን ትምህርት ቀዳሚ ሰማዕት ስለመገብካቸው " " አይሁዶች ወገሩህ ጨክኖ ልባቸው በድንጋይ ሲወግሩህ ቀዳሚ ሰማዕት በጣም ተጨነቀ " " ለሚወግሩት ሰዎች ይቅርታን ጠየቀ 2 አዝ የወንጌል በር ከፋች ቀዳሚ ሰማዕት የተባልከው ቅዱስ " " ተመሰከረልህ ከእውነተኛው ንጉስ ስራ ያስደንቃል ቀዳሚ ሰማዕት እጅግ ድንቅ ስራ " " በአንተ ተበተነ የወንጌል አዝመራ 2 አዝ የድቁናን ስራ ቀዳሚ ሰማዕት በክብር የፈፀምክ " " የስላሴ ዙፋን ተከፍቶ ያየህ የድንጋይ ሩምታ ቀዳሚ ሰማዕት ያላዘናጋህ " " ቀዳሚ ሰማዕት እስጢፋኖስ ነህ አዝ ዙፋኑ ተከፍቶ ቀዳሚ ሰማዕት ቀና ብሎ አየ " " ነፍሴን ተቀበላት በማለት ፀለየ ጌታም ተቀበለው ቀዳሚ ሰማዕት ቃሉንም ሰማለት " " ሰማያዊ አክሊል ወደ እርሱ ላከለት 2  @hayemanotenleweke
Hammasini ko'rsatish...
✞በዙሪያችን ካሉ✞ በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምሥክሮች በዕምነት በምግባር ከጸኑት እናቶች ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት(፪) ሐብት እና ንብረቷን ውበቷን የናቀች ንግሥት መባልን በእምነት የተወች የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ምስክር የቅድስት አርሴማ እጹብ ነው የእርሷ ክብር(፪) አዝ= = = = = እግዚአብሔር ጽናቷን የመሰከረላት በቤቱ በቅጽሩ መታሰቢያ አላት የወንጌሉን ብርሃን ለዓለም ያበራች ሠማዕቷ አርሴማ ለእኛም አማላጅ ነች(፪) አዝ= = = = = ይኸው በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ገለጻት ለረድኤት በረከት ምክንያት አደረጋት አክሊል ተጎናጽፋ ታይታለች በክብር ዛሬም በልጆቿ በረከቷ ይደር (፪) አዝ= = = = = እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ(፪) ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ "በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" ኢሳ፶፮፥፭ @hayemanotenleweke
Hammasini ko'rsatish...
በዙሪያችን ካሉ.mp34.23 MB
ገደ ወዲያውም ዐረፈ አባ ሳሙኤልም ቀበረው ገድሉንም ጻፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሙሴ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 2 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሙሴ ዘረሰየ እምዓለም ተፈልጦ። ቈጽለ ሆሣዕና አራዘ ወፍሬ ዘይቶን ሥብጦ። በብዙኅ መከራ አምድኅረ ሰይጣን አስፈጦ። እግዚአብሔር መሐሪ መንገደ ገዳም ሜጦ። ኀበ ሥጋሁ የዓርፍ ወነፍሶ ይትሜጦ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 3። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እምዳኅዕ"። መዝ 55፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ተሰ 3፥13-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1፥8-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል 18፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ አንበስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @hayemanotenleweke
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.