cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አል-በያን የሀይማኖት ንፅፅር ቻናል

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው።(አልኢምራን:64) ግሩፓችንን ለምትፈልጉ:- @Albayan_Group ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ @AbaisacommentBot

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
414
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አልሃምዱሊላህ ሱመል አልሃምዱሊላህ ! ጌታየ ሆይ ! ምስጋና ይድረስህ ! አሏህ (ሱ.ወ) ስንት ደጋግ ባሪያዎች ..ሪሳላውን ለማድረስ የሚጣደፉ፣ሰው ሰራሽ ድንበርን ተሻግረው በየቋንቋው መልእክቱን ለሰው ልጆች አሻግረው ለማድረስ የተሰለፉ እልፎች አሉት አልሃምዱሊላህ ! ልቤ እጅጉን በደስታ ተነካ ...ዓይኔም አነባ... ይህን እንድል ያደረገኝ ትላንት በአጋጣሚ ጽሁፍ ስፈልግ ያገኘሁት ዌብሳይት ነው ። እስከ ዛሬ ይሄን ዌብሳይት ሳላውቅ በመቅረቴ በራሴ አፍሪያለሁ። ስላገኘሁት የሚሰሩትን ስራ በማየቴ ደግሞ እጅግ ተገርሚያለሁ። አልቅሻለሁ ጭምር ። ዌብሳይቱ https://www.islamic-invitation.com/ ይሰኛል። ''ወደ ኢስላም ግብዣ'' ልትሉት ትችላላችሁ ። እናም ይህ ዌብሳይት በአብዝሃኛው ትኩረቱን ከኢስላም ውጭ ለሆኑ ሰዎች ጥሪ በማድረግ ላይ ይሰራል። በስንት አይነት ቋንቋዎች እንደሚሰራ ታውቋላችሁ ?! ሱብሀነሏህ እኔ ዌብሳይቱ ላይ ገብቼ በወፍ በረር በቆጠርኩት ከ280 በላይ በሆኑ የዓለም ቋንቋዎች ስለኢስላም ያስተምራል። በእያንዳንዱ ቋንቋ ስር ስትገቡ የቁርዓን ተፍሲርን ጨምሮ ስለ ኢስላም የሚያስተምሩ በርካታ የ ፒዲኤፍ መጽሃፍትን ታገኛላችሁ ። በሀገራችንም ቋንቋዎች ከነዚህ ዝርዝሮች ውስጥ ይገኛሉ። የተለያዩ መጽሃፍትን ታገኛላችሁ ። በተለይም ሙስሊም ያልሆናችሁ ወገኖቼ ዌብሳይቱን እንድትጎበኙ ግብዣየ ነው ። የሚገርመው ነገር ደግሞ 24 ሰዓት ቻት ላይ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች የሚጠይቁትን ጥያቄ ለመመለስ ዌብሳይቱ ላይ የሚሰሩ አሉ። ወዲያውኑ እንደተጻፈላቸው ምላሽ ይሰጣሉ። ጥያቄ ለሚጠይቅ ጥያቄ ሸሃዳ ለሚፈልግ ሸሃዳ ያስይዛሉ ። ታዲያ ይሄ እጅግ አያስደስትም ? አያስለቅስም ? ልብ በሉ ከ280 በላይ በሚሆኑ የዓለም ቋንቋዎች በዘመኑ ቴክኖሎጂ የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሪሳላ ለማድረስ የተሰለፉ ጀግኖች ናቸው። በነገራችን ላይ በፍቃደኝነት ከነሱ ጋር መስራት ለምትፈልጉም ፎርም ይልኩላችኋል። እድለኞች ከሆናችሁ ይጠሯችኋል። እናም ኢስላም ድንበር ዘለል የሆኑ በርካታ ባሪያዎች እንዳሉት ባስተዋልኩ ጊዜ እጅጉን ተደስትኩ ። የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ዓላማ አውቆ ለሱ ከመልፋት በላይ ምን መታደል አለ። እኔም የተወሰኑ መጽሃፍት ፒዲኤፍ አውርጃለሁ። አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን ። እናንተም ዌብሳይቱን ትጎብኙና መጽሃፉን አውርዳችሁ ትጠቀሙ ዘንድ ግብዣየ ነው። Go on with your language: የሚለው ላይ ቀስቷን ተጭናችሁ የምትፈልጉትን ቋንቋ ትመርጡና ከዚያ መጽሃፍቱን አውርዳችሁ ማንበብ ነው ። አላህ ከሚጠቀሙበት ያድርገን https://www.islamic-invitation.com/ (አብዱረሂም አህመድ)
Hammasini ko'rsatish...
Islamic Invitation Center for free Islamic materials

Islamic Invitation Center. We are concerned Muslims with various national backgrounds, education and skills, united by our belief (Tawheed). Bank for free islam books with conviction in the Qur'an and the Sunnah.

አስደሳች ዜና! **** 17/03/2014 💧የዩኒቨርሲቲ ማለፊያ ፈተና ወስዳችሁ ውጤታችሁን እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ሁሉ። 💦 እነሆ በጅማ ከተማ አንጋፋው እና እድሜ ጠገቡ የኑር አጁፕ መስጅድ ወጣቶች ጀመዓ ኢንትራንስ ተፈትነው ውጤት እየተጠባበቁ ላሉ ተማሪዎች ልዩ አጫጭር የዐቂዳ ሪሳላ ኪታቦች ፓኬጅ አዘጋጅቷል። በመሆኑም ማንኛውም ወንድ እና ሴት ተማሪ ፣ የትም ዩኒቨርሲቲ ይምመደብ ፣ አቂዳውን በአግባቡ ተረድቶ ለመጠበቅ ፍላጎት ያለው ሁሉ ተጋብዟል። ትናንሽ ኪታቦች በመሆናቸው ከዚህ በፊት ምንም የኪታብ ቂረዐት ላይ አለመሳተፎ ስጋት አይግባዎት። እርሶ ዝግጁ ይሁኑ እንጂ ምርጫዎን ለማስቀደም ዝግጁ ነን። ለተፈታኞች ቅድሚያ የምንሰጥ ቢሆንም ፍላጎቱ ያለው ሁላ መሳተፍ ይችላል። 💥 አድራሻ: ጅማ አጂፕ ኑር መስጅድ መድረሳ የትምህርት ቀን: በሁለት ቀን ልዩነት(ሁለት ቀን ትምህርት ሁለት ቀን እረፍት) ሰዓት: ከአስር በኃላ 🍀 እዚህ ትምህርት ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተማሪ በዚህ ቦት @NUMJ_bot ስሙን ፣ ተፈታኝ መሆን አለመሆኑን እና ከአማረኛ እና ከኦሮመኛ የሚቀለውን ቋንቋ በመፃፍ እስከ 30/03/2014 መላክ ይችላል። #ላልሰማ_አሰሙ #share ✍ #ኑምጅ_ዳዕዋ
Hammasini ko'rsatish...
ከዚህ በፊት በስቅለት ጉዳይ ላይ ያቀረብኩት ሙግት ነው። አድምጡት። « https://t.me/Albeyan_channal»
Hammasini ko'rsatish...
3.61 MB
ሱረቱል አንፋል(የጦር ዘረፋዎች ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ የጦር ዘረፋ ማለት ምርኮ ማለት ሲሆን።ዘረፋ የምትለዋ ቃል መውሰድን ማግኘትን ይገልፃል።ቃሉ ሁል ጊዜ Negative/አሉታዊ ትርጉም የለውም።ስለ ምርኮ ይህን መጣጥፍ አንብቡ https://t.me/Wahidcom/1349 ስለ ምርኮ የወረደ ከሆነ የምርኮ ምዕራፍ ተብሎ መሰየም ስለሚገባው በዚያ ተጠርቷል። 8:1 *ከምርኮ* الْأَنفَالِ ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡ ሱረቱ ተውባህ(የንስሃ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ 2፥102 ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አልሉ፡፡ አላህ “ከእነሱ ጸጸታቸውን” يَتُوبَ عَلَيْهِمْ ሊቀበል ይከጀላል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ ሱረቱ ዩኑስ(የዮናስ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ በነብዩ ዩኑስ(ዮናስ)ስም የተሰየመ ምዕራፍ ነው።ቃሉ በ አንቀፅ98 ተጠቅሷል። 10:98 ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን *የዩኑስ* يُونُسَ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡ ሱረቱል ሁድ(የሁድ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ሁድ የአሏህ ነብይ ነው። በሃዲስ ከተጠቀሱት 4የዓረብ ነብያት(ሁድ ሷሊህ ሹዓይብና ነብዩ ሙሀመድ) መካከል ናቸው። 11:53 አሉ፡- «*ሁድ* هُودُ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም… ሱረቱ ዩሱፍ(የዮሴፍ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ዩሱፍ የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦ 12:4 *ዩሱፍ* يُوسُفُ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ። ሱረቱ ረዕድ (የነጎድጓድ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ “ረዕድ” الرَّعْدُ ማለት ነጎድጓድ ማለት ሲሆን ስያሜው በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦ 13 ፣13 *ነጎድጓድም* الرَّعْدُ አላህን በማመስገን ያጠራል፡፡ መላእክትም እርሱን ለመፍራት ያጠሩታል፡፡ ነጎድጓድ አንኳ አሏህን የሚያመልክና የሚያመሰግን መሆኑን በደንብ እንድናተኩር ይመስላል ስያሜው የተሰጠው ሱረቱ ኢብራሂም ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ “ኢብራሂም” إِبْرَاهِيمُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦ 14፣35 *ኢብራሂምም* إِبْرَاهِيمُ ባለ ጊዜ አስታውስ «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡ ሱረቱል ሒጅር(የሒጅር ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ “ሂጅር” الْحِجْرِ የሸለቆ ስም ነው። በመዲናና በሻም መካከል የሚገኝ ቦታ ሲሆን 15: 80 *የሒጅርም* الْحِجْرِ ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ በሚለው ላይ ስያሜው ተጠቅሷል።መልክተኛን ነብይን መቃወም ከባድ ቅጣት እንዳለው አሏህ ስለ ስያሜው ስናጠና እንድናስተነትን አድርጓል። @Albeyan_channal
Hammasini ko'rsatish...
ጥያቄ ለመውሊድ አክባሪዎች? ነብዩ ﷺ በየሳምንቱ ሰኞ የሚፆሙት የተወለዱበት ቀን ስለሆነ ነው ትሉ የለ? ነገ ሰኞ ነው ሺርክ፣ ቢድአ፣ ጫትና ጭፈራ ይቅርባችሁ ነብዮን ﷺ ተከተሉ ፁሙ። የነብዮ ወዳጅነታችሁን አሳዮ።
Hammasini ko'rsatish...
የዛሬዋ እለት በሰሀቦች ዘንድ ታላቁ ሀዘን የተፈጠረበት የሀዘን ቀን ነው።ምክንያቱ ለአለማት ብርሀን የሆኑት፣የነብያት አውራ ፣የሰው ልጆች ፈርጥ ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሞቱበት ቀን ነው። የሞታቸው ሀዘን ለሁላችንም ወዳጆች ሞት መፅናኛ ነው። ❝ከናንተ መካከል ሰው የሞተበት ካለ በኔ ሞት ይፅናና❞ ብለዋልና። የነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ሞት ሰሀቦችን አቃጠለ ግማሹ፣ «የሳቸውን ሞት የሚነግረኝ ካለ አንገቱን እቀላለሁ » ይላል፣ሌላው «በእርሶ ሞት የደም ስሬ የተቆረጠ ያህል ተሰማኝ» ይላል።ሌላው አዛኑን ማውጣት አቅቶት ይወድቃል።ያብዳል፤እኛስ ወንድሞቼ በሳቸው ሞት ቀን በዚህ ቀን ለመወለዳቸው ኺላፍ ያለው ሲሆን ምኑን እንደሰት፣ምኑን እንጨፍር፣ምኑን እናሽቅ? ወንድሜ በእኔ እልህ ይዘህ በጠማማ መንገድ ላይ ከመቆየት ይልቅ እውነትን ፈልገህበት ቁርዓንና ሀዲስን አጥና። አላህን እንፍራ ዲኑን አናበላሽ። «ሁሉም አዲስ ነገር ቢደዓ ነው፣ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው፣ሁለም ጥመት ወደ እሳት የሚመራ ነው።» https://t.me/Albeyan_channal ✍ኢብኑ-ነዚፍ ነኝ ሰላም።
Hammasini ko'rsatish...
አል-በያን የሀይማኖት ንፅፅር ቻናል

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው።(አልኢምራን:64) ግሩፓችንን ለምትፈልጉ:- @Albayan_Group ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ @AbaisacommentBot

“እነሆም፥ ከጻፎች አንዳንዶቹ በልባቸው፦ ‟ኢየሱስ አምላክ ነኝ ብሎ እያሰበ መሆን አለበት” አሉ።” ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ ‟ስለ ምን በልባችሁ እንዲህ ያለ ሰይጣናዊ ነገር ታስባላችሁ?” አላቸው — ማቴዎስ 9÷3-4 (CEV Bible) ▸ አዎ እንዲህ ያለ ነገር ማሳብ በራሱ ሰይጣናዊ አሳብ ነው። https://t.me/mahircomp123
Hammasini ko'rsatish...
ሱረቱል ማኢዳህ(የማእድ/ምግብ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ይህ ሱራ የተሰየመው በአስገራሚ ክስተት ነው።ነብዩ ኢየሱስ ለህዝቦቹ ምግብ በተዓምር መልኩ ከሰማይ እንዲወርድ አሏህን የለመነበት።ባርያ እንጂ ፈጣሪ አለመሆኑን ዱዓ አድራጊ (ጌታውን ከጃይ)መሆኑ የተወሳበት ሱራ ነው።ሐዋርያት ተዓምር ማየት ፈልገው እንዲህ አሉ;– 5፣112 ሐዋርያት፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ ከሰማይ *ማእድን* مَائِدَةً ሊያወርድልን ይችላልን» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ምእመናን እንደ ኾናችሁ አላህን ፍሩ» አላቸው፡፡ በዚህ አንቀፅ ነው የምግብ ምዕራፍ ተብላ የተሰየመችው። ስያሜውን ብቻ ማየት ሳይሆን ለምን በማን በምን እንደተሰየመ ማጣራት ምሁራዊነት ነው። ይህ አንቀፅ ለከሃዲያን ራስ ምታት ነው።ኢየሱስ ተአምር ለማሳየት ፈጣሪውን የለመነ ደካማ የአሏህ ባሪያ መሆኑ የተገለፀበት አስገራሚ ሱራ ነው። ሱረቱል አንዓም(የቤት እንስሳ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ስያሜውን በውስጡ በብዙ ቦታ እናገኘዋለን።ለምሳሌ ያህል Surah Al-An’am (الانعام), verses: 142 وَمِنَ ٱلْأَنْعَٰمِ حَمُولَةً وَفَرْشًا : ከለማዳ እንስሳዎችም የሚጫኑትንና የማይጫኑትን (ፈጠረ)፡፡ አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ብሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና፡፡ የሙሽሪኮችን የባዕድ አምልኮ የሚቃወም፣አጠቃላይ በለማዳ እንስሳዎች ዙሪያ ስለ ጥቅማቸው ስለተፈቀዱና ለመብላት ስለተከለከሉ እና ሌላም ሌላም የተዳሰሰበት ነው። ክርስቲያን ወገኖች በስያሜው ማሾፋቸው ልክ አለመሆኑን በራሳቸው መፅሃፍ የሰፈረውን መመልከት በቂ ነው። «ኦሪት ዘፍጥረት»ን።ስለ ፍጥረት የሚዳስስ ምዕራፍ ነው።ስያሜውን ከፍጥረት(በሰው በእንስሳ በሰማይ ምድር)የተወሰደ ነው።ተመሳሳይ ይዘት አለው። ሱረቱል አዕራፍ(የአዕራፍ ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ አዕራፍ” الْأَعْرَافِ ማለት ”ኮረብታ”ማለት ነው።ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦ 7፤46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ፡፡ *በአዕራፍም* الْأَعْرَافِ ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አልሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም። በጀነትና በጀሃነም መካከል ባለ ኮረብታ ስም የተሰየመ ነው።ሱረቱል አዕራፍ።የሱራ ስያሜዎችን በቀላሉ ለመረዳት በብዛት "ስለ…የሚናገር" በሚል ተክተን ብናነበው የተሻለ ነው።ለምሳሌ ስለ ቤት እንስሳ የሚዳስስ ፤ስለ ሴቶች የሚዳስስ፣ ስለ ዮሴፍ የሚዳስስ።ሁልግዜ ግን ተግባራዊ አይደለም። @Albeyan_channal @Albayan_Group
Hammasini ko'rsatish...
ሱረቱ አሊ-ዒምራን (የዒምራን ቤተሰብ ምዕራፍ) 📖 ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ አዝ ዘህራወይን(ሁለት ነፀብራቆች) ተብለው ከተጠሩት አንዷ ሱራ ነች። ሱራዋ በኢየሱስ እናት በማርያም/መርየም አባት ስም የተሰየመ ሲሆን።አባቷ ዒምራን እንደሆነ የታወቀ ነው።በተፍሢር ኪታቦች ደግሞ የእናቷ ስም ሐና ተብሎ ይጠራል።በባይብል ላይ ግን እናቷም አባቷም ስማቸው አልተጠቀሰም።ዒምራን(አባቷ) በአንዳንድ የተደበቁ መፅሃፍ ቅዱሶች ለምሳሌ በያዕቆብ ወንጌል ውስጥ ኢያቂም በሚል ተጠርቷል።መርየም የዒምራን ልጅ መሆኗ ቁርአን ግልፅ ባለ መልኩ አስቀምጧል። 66፥12 *የዒምራንን ልጅ መርየምንም… በዚህ የሱራ ስም ብዙም ትችት ባይነሳበትም ነገር ግን ስለ ዒምራን ማንነት ማወቁ የተሻለ ነው በሚል ነው።ሱራው ስለ ዒምራን ቤተሰቦች ታሪክን ያካተተ ነው።ስለ ሚስቱ ስለ ልጁ ስለ ልጅ ልጁ(ኢየሱስ)። “ኣሊ–ዒምራን” َءَالَ عِمْرَٰنَ ማለት የዒምራን ቤተሰብ ማለት ነው። ስያሜው በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦ 3፥33 አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ *የዒምራንንም ቤተሰብ* وَءَالَ عِمْرَٰنَ በዓለማት ላይ መረጠ፡፡ 🔰አንዳንድ ሙስሊሞች የሚሳሳቱት ስህተት አለ።ሱረቱ ዒምራን ብለው ይጠሩታል። ኣሊ(የ…ቤተሰብ) የምትለዋን ይዘሏታል።ይህ መስተካከል አለበት።መሆን ያለበት ሱረቱ ኣሊ ዒምራን ነው። ሱረቱ አል-ኒሳእ (የሴቶች ምዕራፍ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ በአብዛኛው በውስጡ ስለ ሴቶች የሚያወሱ አንቀፆችን የያዘ ሱራ ነው።ለዚያም ይመስላል የሴቶች ምዕራፍ የተባለው።በሴቶች ስም ሱራህ መሰየሙ ምንም የተለየ ነገር አይደለም ባይ ነኝ።እኛ ሴቶች ሱራ ተሰይሞልናል የሚለው አባባል ትንሽ…ምክንያቱም አንድ አካል በሱ ስም በሱ ግብር ሱራ መሰየሙ ግለሰቡን ምንም የሚጨምርለት ነገር አይኖርም።ወደፊት እንዳስሰዋለን።በሱረቱል መርየም እና በሱረቱል ዓንከቡት። የሱራው ስም በዚህ ይገኛል። 4፥4 *ሴቶችንም* النِّسَاءَ መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፡፡ ለእናንተም ከእርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾን ብሉት፡፡ በዚህ አሰያየም የሚነሳው ትችት አናሳ ነው። @Albeyan_channal @Albayan_Group
Hammasini ko'rsatish...
አል-በቀራህ (የላሚቷ ምዕራፍ) 📖 ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ አዝ ዘህራወይን(ሁለት ነፀብራቆች) ተብለው ከተጠሩት አንዷ ሱራ ነች።ሱራዋ በታሪካዊቷ ላም የተሰየመች ናት። Surah Al-Baqarah (البقرة), 2:67 - ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «አላህ ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለ ጊዜ (አስታወሱ)፡፡«መሳለቂያ አድርገህ ትይዘናለህን?» አሉት፡፡ «ከተሳላቂዎች ከመኾን በአላህ እጠበቃለሁ» አላቸው፡፡ 2:68 - «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች (ዕድሜዋን) ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ይላችኋል፤ የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡ 2:69 - «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ ላም ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ 2:70 - «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ይግለጽልን፤ ከብቶች በኛ ላይ ተመሳሰሉብን፡፡ እኛም አላህ የሻ እንደኾነ በእርግጥ ተመሪዎች ነን» አሉ፡፡ 2:71 - «እርሱ እርሷ ያልተገራች ምድርን (በማረስ) የማታስነሳ እርሻንም የማታጠጣ (ከነውር) የተጠበቀች ልዩ ምልክት የሌለባት ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ «አሁን በትክክል መጣህ» አሉ፤ ሊሠሩ ያልተቃረቡም ሲኾኑ አረዷት ፡፡ 2:72 - ነፍስነም በገደላችሁና በርሷም (ገዳይ) በተከራከራችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ አላህም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ ገላጭ ነው፡፡ 2:73 - «(በድኑን) በከፊሏም ምቱት» አልን፤ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል፡፡ ይህ ታሪክ በጣም አስደማሚና በጣም አስተማሪ ተዓምርም የታየበት ክስተት ነው።በሙሳ ዘመን አንድ ባለሀብት ይኖር ነበረ።አንድ የዚህ ባለሀብት የወንድሙ ልጅ ቆንጆ ሴት ልጁን ለትዳር ጠየቀው።ባለሀብቱም በፍፁም ለድሀ እንደማይድር ገለፀለት።ሀብቷን ለመውረስ አስቦ ነው ብሎ ገመተ።ይህን ግዜ አጎቱ እስኪሞት መጠባበቅ ጀመረ። ትዕግስቱ ሲያልቅ አንድ ቀን ራቅ ያለ ቦታ አግኝቶ ገደለው። ከመንደራቸው ርቆ አስክሬኑ ተጥሎ ተገኘ።የሟቹ ቤተሰብም አስክሬኑ ያረፈበትን ነዋሪ ሰዎች በገዳይነት ፈረጁ።አጎቱን የገደለው ሰውም ገዳይነቱን ደብቆ ያዙኝ ልቀቁኝ አለ።ጉዳዩን ለነብዩ መሳ(ሙሴ)አደረሷቸው።ከዚያም 2:67 - ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «አላህ ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለ ጊዜ (አስታወሱ)፡፡ 📌ላም እረዱ ብሎ አዘዛቸው። ይህን ግዜ እኛ ቁም ነገር ይዘን አንተ ትሳለቅብናለህነረ አሉት። «መሳለቂያ አድርገህ ትይዘናለህን?» አሉት፡፡ «ከተሳላቂዎች ከመኾን በአላህ እጠበቃለሁ» አላቸው፡፡ ከዚያም የማይጠየቅ ጥያቄ ጠየቁት።ነብያቸውን ተጨቃጨቁ እነርሱ ላይም ጫና ፈጠሩ። የላሟን ዕድሜ፣መልክ፣ተግባር በአሰልቺና ሊያገኟት በማይችል መልኩ ጠየቁት። 🔰አንድ አማኝ(ሙእሚን) የሆነ ሰው የታዘዘውን ሰምቶ ይፈፅማል እንጂ ለምን እንዲህ ለምን እንዲያ አይልም የሚለውን አሏህ በዚህ ታሪክ ያስተምረናል። 👉የናቁትን ተግባር /ላም ካረዱ በኃላ እንዲህ ተባሉ 2:73 - «(በድኑን) በከፊሏም ምቱት» አልን፤ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል፡፡ ከላሟ ከፊል ስጋ ወስዳችሁ ሟቹን መታ አድርጉት ብሎ አዘዛቸው።ሟቹን በስጋው መታ ሲያደርጉት በአሏህ ሃይል ከሞተበት ተነሳ ።የገደለኝ ይህ ነው በማለት ገዳዩን ተናግሮ ተመልሶ ሞተ።። ይህ አስገራሚ ና አስተማሪ ታሪክ በአስገራሚ ስያሜ ተሰይሟል (የላሚቷ ምእራፍ)በሚል። 📌ለዚህ ምዕራፍ በቂ ስያሜ የተሰጠበት እንደሆነ ታሪኩን በማየት መገንዘብ ይቻላል። ክርስቲያን ወገኖች በደፈናው ከመተቸት ይልቅ…ከልብ መመርመር የተሻለ ነው። @Albeyan_channal @Albayan_Group
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.