cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Muktarovich Ousmanova

Ethiopia forever

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
62 659
Obunachilar
-3224 soatlar
-1657 kunlar
-38230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ከትናንት በስቲያ ከጅማ እስከ ወለጋ እንዲሁም እስከ ወላይታ የተሰማው ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ ምንድን ነበር? የከባድ ጦር መሳርያ ድምፅ ነው፣ መብረቅ ነው፣ ከሌላ አለም የመጣ ባዕድ ነገር ነው ወዘተ የሚሉ በርካታ መላምቶችን ተመልክቻለሁ። በጠፈር ሳይንስ እና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት የአስትሮፊዚክስ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን በላይ ይህን መረጃ ሰጥተውኛል: - ከተመለከትኳቸው ምስሎች መረዳት የቻልኩት ወደቁ የተባሉት አካላት የሚቲዮራይት ስብርባሪ መሆናቸውን ነው - የጅማ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ዲፓርትመንትን በዚህ ዙርያ አነጋግሬ ያገኘሁት ምላሽ ተመሳሳይ ነው፣ ወድቆ የተገኘው አካል ወደ ዩኒቨርስቲው ለምርመራ እንዲወሰድ ሀሳብ አቅርቤያለሁ - ይህ ከፍተኛ ድምፅ የተሰማው ከደቡብ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ነው፣ አጋሮ አካባቢ አንዳንድ ስብርባሪ ተገኝቷል ሚቲዮራይት ከሌላ ጠፈር (outer space) በመነሳት ምድር ላይ የሚያርፍ ድንጋይ/አለት ሲሆን ወደ ምድር ከባቢ አየር ሲገባ በሰበቃ (friction)፣ ሀይለኛ ግፊት እና በኬሚካል ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ድምፅ እና ብርሀን ይፈጥራል። Credit: ዶ/ር ሰለሞን በአሁኑ ወቅት የአለም አቀፈ አስትሮኖሚካል ህብረት ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አማካሪ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። ለሙያዊ አስተያየታቸው አመሰግናለሁ። ሙሉ መረጃው ኢትዮጵያ ቼክ ላይ ይገኛል: https://t.me/ethiopiacheck/2379 Image: Social Media Elias Meseret
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ የቴሌግራም ቻናል ጥቆማ‼️👇 መረጃ ለማድረስ እንዲሁም ለመከታተል ቴሌግራም ተመራጭ እየሆነ ነው❗ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያልተሰሙ እና አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተል ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው join በማድረግ ተከታተሉ። ብዙ አዳዲስ መረጃዎችን ታገኛላችሁ እንዲሁም በቻናሉ ማስታወቂያ ብታሰሩ እጅግ አዋጪ ነው። ቻናሉን ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ👇👇👇👇👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
Hammasini ko'rsatish...
በዶናልድ ትራምፕ ላይ የተኮሰው ግለሰብ ማንነት ታወቀ የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተኮሰው ግለሰብ ቶማስ ማቲው ክሩክስ የተባለ የ20 ዓመት ወጣት መሆኑን አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው በጆሯቸው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጥቃት ፈጻሚው ወደ ዶናልድ ትራምፕ ከመተኮሱ በፊት የሕዝብ መጨናነቅ በነበረት ቅስቀሳው ላይ ሌላ ሰው መግደሉም ተሰምቷል። ግለሰቡ ወዲያውኑ በደህንነት ሰዎች የተገደለ ሲሆን ሕግ አስከባሪዎች ይህ ክስተት እንዲፈጠር ያሳዩት ክፍተት ጥያቄ እያስነሳ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
ሰበር ዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው። ቆስለዋል። የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት እና የሪፐብሊካን ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትረምፕ ፔንሰልቬኒያ፣ ባትለር ውስጥ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ጭንቅላታቸው አካባቢ ጉዳት የደረሰባቸው ሲኾን፣ በአኹኑ ወቅት ግን ደኅና መኾናቸውን የምርጫ ቅስቀሳ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ባይደን የዶናልድ ትራምፕ ጉዳት ለክፉ እንደማይሰጣቸው በማወቃቸው ተረጋግተዋል። ድርጊቲን ኮንነዋል የትረምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ባወጣው መግለጫ፣ የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ እጩ ጥቃቱ ከደረሰባቸው በኋላ በአካባቢው በሚገኝ የህክምና ተቋም፣ አገልግሎት ማግኘታቸውን አስታውቋል። ትረምፕ "ሴክሬት ሰርቪስ” በመባል የሚታወቀው፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጥበቃ አገልግሎት፣ ማመስገናቸውን የምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ስቲቨን ቼኡንግ አስታውቀዋል። #Trump #Biden #Rally #PresidentialElection2024 #voa
Hammasini ko'rsatish...
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) በተማሪዎቹ ጠለፋ ላይ መግለጫ አወጣ። ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ሲመለሱ የተጠለፉትና ቤተሰባቸው የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ የተደረጉ 100 ተማሪዎች ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት መሳቡ ይታወቃል። መንግስት አስለቀቅኩ ቢልም ተማሪዎቹ አልተለቀቁም። ቤተሰባቸው አንዳንድ ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል። OLA በመግለጫው ጠለፋውን የፈፀመው መንግስት ነው ብሏል።
Hammasini ko'rsatish...
በቢሾፍቱ፤ ቤተክርስቲያንዋ ይዞታዬን በኃይል ተነጠቀኩኝ አለች የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከልን ይዞታ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የቤተክርስቲያኒቱ ይዞታ በህገወጥ በጉልበት መንጠቁን ቤተክርስቲያኗ አስታወቀች። አስተዳደሩ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ይዞ በመግባት ችካል በማስቀመጥ የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለግለሰቦች አስተላልፏል ስትል ከሳለች። የከተማው አስተዳደር ላለፉት 30 ዓመታት በቤተክርስቲያንዋ የተያዘውን 40 ሺህ የሚገመት ካሬ ሜትር ይዞታ በታጠቁ ሰዎች አማካኝነት በኃይል በመቀማት ሐምሌ 3 ቀን 2016 ለግለሰቦች አስተላልፏል፡፡ የቤተክርስቲያንዋ ና የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ካውንስል መሪዎች ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ይህ ዓይነቱ መድልዎ እና ጥቃት በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥላቻ ባላቸው ግለስቦቸ የተቀነባበረ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ ከመግለጫው ቀደም ብሎ ከአዲስ አበባ ዋናው ጽሕፈት ቤት ወደቦታው ያቀኑት የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች የማዋከብ የማሸማቀቅ እና ወደ እስር መውሰድ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ተፈጽመውባቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት፣ከፍተኛ አመራሮችና የፌዴራል መንግስት አካላት ይህ ጉዳይ የህዝብ ሰላም በማይፈልጉ አካላት በልማት ሰበብ እየተሰራ የለውን ህግ መንግስቱን የጣሰ ስራ አንድታስቆሙልን እና አስቸኳይ ምላሸ እንዲሰጡን ሲሉ ጠይቀዋል። የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ያለውን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። አስተዳደሩ ፈቃደኛ ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
❗️አፓርታማ በማይገዛ ብር እንይ ሪልስቴት ግቢ ያለው ቪላ ቤት በጀሞ እየተሸጠ መሆኑን ሰምተዋል? 🔥 በ 20% እና 30% ቅድመ ክፍያ ድጋሚ የማይገኝ እድል 👉G+2 250 ካሬ ባለ 6 መኝታ ከ 5.6 ሚሊየን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ (20%) 👉G+2 120 ካሬ ባለ 4 መኝታ ከ 3.3 ሚሊየን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ (20%) 👉G+1 120 ካሬ ባለ 3 መኝታ ከ 3.8 ሚሊየን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ (30%) አሁን ይደውሉ ፥ ሳይት ይጎብኙ ከዛ ይወስኑ +251967770077 Telegram - https://t.me/Apartmentconsultant Whatsapp - https://wa.me/251967770077?text
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በመጨረሻም የኬንያው ፕሬዝደንት የህዝብን ጥሪ ተቀብለው የታክስ ህግ እንዲቀርብ አርገዋል፣ አልሰሩልንም፣ አይወክለንም የተባለውን ሙሉ ካቢኔያቸውን በትነዋል! ህዝቡ ደስታውን አደባባይ በመውጣት እየገለፀ ይገኛል። #PeopePower Image: Citizen Via Elias Meseret
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
"በተደረገ ጥብቅ ኦፕሬሽን ከ167 ታጋች ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ ተለቀዋል"--- የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ "እውነት ይሆን?" ብዬ የታጋቾች ቤተሰቦችን፣ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ወንጌላዊያን ህብረትን እና የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንትን ማምሻውን ጠየቅኩ። ምላሹ ይህን ይመስላል: "አሁንም ልጆቻችን በእገታ ስር ናቸው፣ የማስለቀቂያ ገንዘብ ከህዝብ እየለመንን ነው። በዚህ ግዜ እንዲህ አይነት መረጃ ማውጣት የጭካኔ ስራ ነው"--- የታጋቾች ቤተሰቦች "ታግተው ያሉ በርካታ ተማሪ አልተለቀቁም፣ ተለቀቁ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከየት እንደመጣ አናውቅም። እንደውም አሁን ተማሪዎቹን ወደ ወለጋ እንደወሰዷቸው እየሰማን ነው"--- የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ወንጌላዊያን ህብረት "አንዴ መረጃ ሰጥቻለሁ፣ እኔ ጋር ለምን ትደውላላችሁ?"--- የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ Via Elias Meseret
Hammasini ko'rsatish...
ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ በሃሰት ከባለቤቱ 500,000.00 ብር የተቀበለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። #FastMereja የ63 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ እና የ5 ልጆች አባት የሆነው አቶ ገብረ ተንሳኢ ተክላይ ከወይዘሮ ዘነበች በርሄ ጋር ለ14 አመታት በትዳር ተጣምረው በአሶሳ ከተማ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው 4 ልጆችን አፍርተዋል። በትዳር ህይወታቸው ውስጥ ምንም አይነት እንከን እንደሌለ የሚገልፀው አቶ ገብረተንሳኢ ተክላይ ወይዘሮ ዘነበችን ከማግባቱ በፊት አንዲት ሴት ልጅ እንዳለችውና እሷም ለብቻዋ አዲስ አበባ እንደምትኖር በመግለፅ ይህንን እኩይ ተግባር ለመፈፀም የተነሳሳውም የግል ልጁን ለመርዳት እንደሆነ ተናግሯል። ከሚኖርበት አሶሳ ከተማ ወደ ነቀምት ከተማ በመጓዝ " ኦጌቲ" በሚባል ሆቴል ውስጥ ለሁለት ቀናት አልጋ ይዞ በመተኛት ከሆቴሉ አስተናጋጆች የ21 ዓመት ልጅ የሆነውን ወጣት ገመቹ ዮናስን በመግባባት የአጋችና ታጋች ድራማውን አብሮት እንዲሰራና ለዚህም ታግቻለሁ ብሎ ከሚላክለት ብር ላይ 25,000 ብር እንደሚሰጠው በመንገር ያሳምነዋል። በዚህም መሰረት ባል አቶ ገብረተንሳኢ ተክላይ በሸኔ ታግቻለሁ ብሎ ለባለቤቱ ደውሎ በመንገር ስልኩን ይዘጋል። ሚስት ወይዘሮ ዘነበች የምትይዘው የምትጨብጠው ይጨንቃታል። ከ24 ሰዓታት በኋላ ወጣት ገመቹ ዮናስ ደውሎ ኦነግ ሸኔ ነን አግተነዋል 800,000 ብር ካላስገባሽ ባልሽን አታገኝውም ይላታል። ሚስት እባካችሁ የልጆቼ አባት ነው እንዳትገሉብኝ ለምኘም ቢሆን ያገኘሁትን ብር እልክላችኋለሁ ስትል መልስ ሰጠች። ዘገባው ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነው።
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.