cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Admas Media - አድማስ ሚዲያ

ይህ Admas Media -አድማስ ሚዲያ - ኦፈሽአል ቴሌግራም ነው። የሚወዱትን Admas Media -አድማስ ሚዲያ ማህበራዊ ገፅ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። This is Admas Media - አድማስ ሚዲያ Official Telegram Channel መልዕክት መቀበያ እና ለማንኛውም አይነት ጥያቄ @Admas_media_bot እንዲሁም ለማስታውቂያ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
4 127
Obunachilar
-224 soatlar
-257 kunlar
-41530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ዜጎች በየዓመቱ ስራ አጥ ይሆናሉ ተባለ በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ዜጎች በየዓመቱ ስራ አጥ እንደሚሆን የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ 71 በመቶ የሚሆነው ዜጋ በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም የሚፈጠረው የስራ እድል ግን ከ50 በመቶ በታች መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ወንድማገኝ ታዬ ለአራዳ ገልጸዋል። በዚህም በየዓመቱ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ዜጋ ስራ አጥ እንደሚሆን የሴንትራል ስታቲስቲክስ ዳታ ጥናት ያመላክታል ነው ያሉት ባለሙያው። የህዝብ ቁጥር መጨመርና ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር አለመመጣጠን፣ ከማምረቻው ዘርፍ ይልቅ የአገልግሎት ዘርፉ መስፋፋትና የሚቀጥረው ሰው አነስተኛ መሆን የራሱ ድርሻ እንዳለውም ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ከሚፈጠር የስራ እድል ውስጥ 80 በመቶው በመንግስት በኩል መሆኑም ለዚህ የራሱ ድርሻ አለው ነው ያሉት። ይህን ለመቅረፍም የግሉ ዘርፍ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ በስፋት መስራት እንዳለባቸው ባለሙያው አስገንዝበዋል። ከዚህ ባለፈም የመስራት ባህልን ማሳደግ፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትና መሰል የመፍትሄ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባም አስረድተዋል።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በቻድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን መልቀቂያ አስገቡ! በቻድ የሁንታ መሪ በሆኑት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢንቶ ከሁለት ሣምንት በፊት በፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሰክሰስ ማስራ የሥልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸውን ዛሬ አስታውቀዋል። የ40 ዓመቱ ማሃማት ዴቢ ምርጫውን 61 በመቶ ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ሲታወቅ፣ ከነገ በስቲያ ሐሙስ በሚደረግ ሥነ ስርዓት ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙ በመጠበቅ ላይ ነው። መሃማት ዴቢ፣ ለ30 ዓመታ ሃገሪቱን የገዙት አባታቸው ከሶስት ዓመታት በፊት በአማጺያን መገደላቸውን ተከትሎ፣ 15 ዓባላት ያሉት ወታደራዊ ሁንታ የሽግግር ፕሬዝደንት አድርጎ ሾሟቸው ነበር። እርሳቸውም የ40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሰክሰስ ማስራ፣ ከአራት ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸውም ቀደም ብሎ የዴቢ ጠንካራ ተቃዋሚ የነበሩ መሆናቸው ይነገራል። በፕሬዝደንታዊ ምርጫው 18.5 በመቶውን ድምፅ ብቻ አግኝተዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማስራ የአገዛዙ መጠቀሚያ ናቸው ሲሉ ይከሳሉ። ማስራ ቀድመው አሸናፊነታቸውን አውጀው የነበረ ሲሆን፣ ፓርቲያቸው ምርጫውን “ጭንብል” ሲል ጠርቶታል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቡድኖችም ምርጫው ተአማኝም፣ ፍትሃዊም እንዳልነበር ገልፀዋል። Via VoA
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ በህንፃ መሰረት ግንባታ በደረሰ የድንጋይ እና አፈር መደርመስ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ። ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 3:45 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት የረር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ  ህንጻ  ለመገንባት  የመሰረት ስራ ላይ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። አደጋዉ የደረሰዉ ሰራተኞቹ  በስራ ላይ እንዳሉ  ስራዉ ከሚከናወንበት አጠገብ የነበረና አፋፍ ላይ ያለ  የግለሰብ መኖሪያ ቤት  የዉሀ ልክና ድንጋይ እ አፈር  በሰራተኞቹ ላይ በመናዱ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የግለሰቡን አስከሬን ከተጫነበት አፈርና ድንጋይ ስር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። በማናቸዉም የግንባታ ስራዎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ አለመስራት መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ አሰሪዎችና የዘርፉ ባለሞያዎች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የግንባታ ፈቃድ ሰጪ አካላትም ተገቢዉን ክትትል ቁጥጥር ማድረግ ይገባቸዋል። ቤቶቹ የግለሰብ ቤቶች መሆናውንም ኮሚሽኑ አስታውቃል አስከሬኑን ለማውጣት 1:30 መፍጀቱም ተነግራል።
Hammasini ko'rsatish...
የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ በመሙላቱ ምክንያት ግድቡን ለማስተንፈስ የተለቀቀው ውሃ የጎርፍ አደጋ እንዲከሰት አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ፡፡ የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ በመሙላቱ ምክንያት ግድቡን ለማስተንፈስ የተለቀቀው ውሃ የኦሞ ወንዝ በከፍተኛ መጠን እንዲሞላ እና ወንዙ ከዚህ ቀደም በጎርፍ ከሚያጥለቀልቃቸው ቦታዎች በተጨማሪ በሌሎች ቦታዎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንዲከሰት አስተዋጽዖ ማድረጉ ኮሚሸኑ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ውስጥ ባሉ 12 የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ሕጎችና ሰነዶች አንጻር መገምገሙን አስታወቀ፡፡ በግምገማውም የመፈናቀል መንስኤዎችን፣ በመፈናቀል እና ድኅረ መፈናቀል ወቅት የደረሱ ጉዳቶችን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እና አሳሳቢ ሁኔታዎችን መለየቱን ነው ያስታወቀው፡፡ የኦሞ ወንዝን በከፍተኛ ሁኔታ መሙላት እና የዳሰነች ወረዳ በርካታ አካባቢዎችን በጎርፍ መጥለቅለቅ ተከትሎ፣ ሰዎች ለመፈናቀል ከመዳረጋቸው ባሻገር በሕይወታቸውና በንብረታቸው እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በሚያገኙባቸው ተቋሟት ላይ  ጉዳት የደረሰ መሆኑን የክትትል ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ በዚህም መሠረት ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተፈናቃዮችን ቅድሚያ በሰጠ መልኩ ለተፈናቃዮች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ ሰብአዊ ድጋፍ የማቅረቡ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት) አባል ሀገር እንደመሆኗ መንግሥት በስምምነቱ የተጠበቁ መብቶችን በተቻለ መጠን እና ፍጥነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ እንደዚሁም በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰት መፈናቀልን ለማስወገድ እና መፈናቀል ሲከሰትም የሰብአዊ መብቶች መርሖችን የተከተለ ዘላቂ መፍትሔ ለማመቻቸት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሠሩ ይገባል” ብለዋል።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ኤችአይቪ ገዳይነቱ እየጨመረ መሆኑ ተሰማ❗️ ኤችአይቪ ኤድስን ጨምሮ በግብረ ስጋ ግንኝነት የሚተላለፉ በሽታዎች ገዳይነት እየጨመረ ነው ተብሏል። የአለም ድርጅት አዲስ ያወጣው ሪፖርት በብዙዎች ዘንድ ችላ የተባለው ኤቺ አይቪ ኤድስ እና ሌሎች በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለለፉ በሽታዎች በአመት 2.5 ሚልየን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡ ድርጅቱ በተለይ በአሜሪካ እና አፍሪካ የሚገኝውን ከፍ ያለ የበሽታውን ስርጭት ከ7.8 ሚልየን ወደ 0.7ሚልየን ለመቀነስ እቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይሁንና በ2022 ከ15-49 እድሜ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ  አንድ ሚልዮን አዲስ ኢንፌክሽን ተመዝግቧል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
አዲስ አበባ‼     አዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትናንት ከሌሊቱ 10:10 ሰዓት አቡኒ የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ላይ ተነስቶ በነበረዉ የእሳት አደጋ ፋብሪካዉ በከፊል መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ። የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢፕድ በሰጡት መረጃ እንዳሉት የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ስምንት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የዉሀ ቦታ ከ56 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርቷል። ባለሙያው የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል። በአደጋዉ ለመልሶ መጠቀም ግልጋሎት የሚዉሉ ጥሬ ዕቃዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ፋብሪካዉ በከፊል ወድሟል። በፋብሪካዉ የአደጋ ደህንነትን መስፈርት ያልጠበቁ ያገለገሉ የፕላስቲክ ዉጤቶች ክምችት እንዲሁም ስፍራዉ የአደጋ መቆጣጠር ተሽርከርካሪውችን የማያስገባ መሆኑ ለአደጋዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ አድርጓል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት የፈጀ ሲሆን  በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። (ኢፕድ)
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት እየተባለ በሚጠራ አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ የአፈር ናዳ መከሰቱ ተነገረ፡፡ ህንጻ ለመገንባት የአፍር ቁፋሮ እያደረጉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች አፈር እንደተናደባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ከአፈር ናዳው እስካሁን ድረስ አንድ ሰው ብቻ ማውጣት እንደተቻለ የገለጹት ነዋሪዎቹ በቦታው ያለው ነገር የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሰራተኞች ባሁኑ ሰአት በቦታው መገኝታቸቀው የተነገረ ሲሆን ሰራተኞቹን ለማዳን ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡የአፈር ናዳው የደረሰው ህንጻው ከህንጻው አጠገብ ባሉ መኖርያ ቤቶች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ Via Ethio FM
Hammasini ko'rsatish...