cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አልኮረሚ / Alkoremi

ይህ የአልኮረሚ ኦፊሴላዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። በፌስቡክ እና በዩትዩብም alkoremi ብለው ቢፈልጉ ያገኙናል። --- ማንኛውም አስተያየት እና ሐሳብ በ @AlkoremiBot ይላኩልን።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
675
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ብዙ ሚስት በኢሥላም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا "ኒካሕ" نِكَاح የሚለው ቃል “ነከሐ” نَكَحَ ማለትም “አገባ” ወይም “ተዳራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጋብቻ” ወይም “ትዳር” ማለት ነው፥ በኢሥላም ሐላል ጋብቻ በተቃራኒ ፆታ"hetero sexual" መካከል ያለ እንጂ በተመሳሳይ ፆታ"homo sexual" መካከል ያለው ጋብቻ ሐራም ነው። የሥነ-ጋብቻ ጥናት"matrimony" እንደሚያትተው የጋብቻን ሒደት በሁለት ይከፍለዋል፥ እርሱም አንድ ወንድ ለአንድ ሴት አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ጋብቻ"monogamy" እና አንድ ወንድ ለብዙ ሴት አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ጋብቻ"polygamy” ነው። ፓሎጋሚ እራሱ ለሁለት ይከፈላል፥ እርሱም አንድ ወንድ ለብዙ ሴት ጋብቻ"polyandry" እና አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ጋብቻ"polygyny” ነው። በኢሥላም አንድ ወንድ በፍትሕ እኩል ማስተዳደር ከቻለ ሁለት ወይም ሦስት አሊያም አራት ማግባት ይችላል፦ 4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ። አለማስተካከልን ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا "ማስተካከል" ለሚለው የገባው የግስ መደብ "ተዕዲሉ" تَعُولُوا ሲሆን የስም መደቡ "ዐድል" عَدْل ነው፥ "ዐድል" عَدْل ማለት "ፍትሕ" ማለት ሲሆን አንድ ተባዕት በፍትሕ ሁለት ወይም ሦስት አሊያም አራት እንስታትን እኩል ሐቃቸውን መጠበቅ ካልቻለ ከጥብቆች ምእምናት አንዲቷን ወይም ያንን ማድረግ ዐቅም ከሌለው እጆች ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ማግባት ይችላል፦ 4፥25 ከእናንተም ውስጥ ጥብቆች ምእምናት የኾኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ወጣቶቻችሁ ያግባ፡፡ وَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ مِنكُمْ طَوْلًا أَن يَنكِحَ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ فَمِن مَّا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُم مِّن فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ ነቢያችን"ﷺ" ከአራት በላይ ያገቡበት ምክንያት አንደኛ እርሳቸው ያገቡት "ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ" የሚለው ከመውረዱ በፊት ነው። ሁለተኛ "ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት" የሚለው ቃል "ኢሥቲስናእ" اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም “ፍትቅታ”exceptional” ሆኖ የመጣ ነው፦ 35፥1 ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ሶስት ሶስት፣ አራት አራት ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ الْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَاعِلِ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا أُولِي أَجْنِحَةٍ مَّثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۚ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ሶስት ሶስት፣ አራት አራት ክንፎች ናቸው ማለት ኢሥቲስናእ ነው፥ ምክንያቱም አሏህ "በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል" ስለሚል ከአራት ክንፎች በላይ ጂብሪልን ባለ ስድስት መቶ ክንፍ ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 332 ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ” ጂብሪልን በተፈጥሮ ቅርፁ ባለ ስድስት መቶ ክንፍ ያለው ሆኖ አይተውታል”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ ‏{‏ لَقَدْ رَأَى مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَى‏}‏ قَالَ رَأَى جِبْرِيلَ فِي صُورَتِهِ لَهُ سِتُّمِائَةِ جَنَاحٍ ‏.‏ በተመሳሳይ መልኩ የነቢያችን"ﷺ" ከአራት በላይ ማግባት አሏህ ያሻው ስለሆነ ነው። "አሏሁ አዕለም" اَللّٰهُ أَعْلَم ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Hammasini ko'rsatish...
ብዙ ሚስት በባይብል በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا ባይብል ላይ "አንድ ብቻ አግቡ" የሚል መመሪያ የለም፥ ከዚያም ባሻገር ከአንድ በላይ ማግባት የተከለከለበት አንድ ጥቅስ የለም፥ ከዚያ ይልቅ ከአንድ በላይ ያገቡ የአምላክ ባሮች ብዙ ሰዎች በቁና ናቸው። ለናሙና ያክል፦ 1. ያዕቆብ ዘፍጥረት 31፥17 ያዕቆብም ተነሣ፥ ልጆቹንና “ሚስቶቹንም” በግመሎች ላይ አስቀመጠ። 2. ጌዴዎን መሣፍንት 8፥30 ለጌዴዎንም “ብዙ ሚስቶች” ነበሩትና ከወገቡ የወጡ ሰባ ልጆች ነበሩት። 3. ሕልቃና 1ኛ ሳሙኤል 1፥2 ሕልቃና ሁለትም ሚስቶች ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ። 4. ዳዊት 1ኛ ሳሙኤል 25፥43 ዳዊትም ደግሞ ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ወሰደ፤ "ሁለቱም ሚስቶች" ሆኑለት። 1ኛ ዜና መዋዕል 14፥3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም “ሚስቶችን” ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ። 5. ሰሎሞን 1ኛ ነገሥት 11፥3 ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ "ሰባት መቶ ሚስቶች" ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት። 6. አሽሑር 1ኛ ዜና መዋዕል 4፥5 ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ የተባሉ "ሁለት ሚስቶች" ነበሩት። "አይ ከላይ የተዘረዘሩት ሰዎች ብዙ አገቡ እንጂ ፈጣሪ ብዙ እንዲያገቡ አልፈቀደላቸውም" ከተባለ ፈጣሪ አለመከልከሉ በራሱ መፍቀዱን ያሳያል። ሲቀጥል አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ካሉት እንዴት መንከባከብ እንዳለበት የተናገረው ፈቅዶ ነው፦ ዘዳግም 21፥15 ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ”ሁለት ሚስቶች” ቢኖሩት፥ ፈጣሪ ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክል ኖሮ አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት ምን ዓይነት እንክብካቤ ማድረግ እንዳለበት ሕግ ያወጣ ነበርን? ፈጣሪ ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክል ኖሮ ለዳዊት ለዛውን የሰውን ሚስቶችን ይሰጠው ነበርን? ፈጣሪ የዳዊት ጌታ ተብሌ የተጠቀሰውን የሳኦን ሚስቶች ሰቶት ነበር፥ ከዚያ የበለጠም ካስፈለገ እንደሚጨምርለት ቃል ገብቶለታል፦ 2ኛ ሳሙኤል 12፥8 "የጌታህንም "ሚስቶች" በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር። ፈጣሪ ለዳዊት የሳኦን ሚስቶች ካልበቃው ሊጨምርለት እንደሚችል መናገሩ በራሱ ከአንድ በላይ ማግባት ሐላል መሆኑን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። የአዲስ ኪዳን ነብይ ኢየሱስ ነው፥ ኢየሱስ፦ "ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው" አላለም። እርሱ በብሉይ የነበረውን ሕግ አልሻረም። ሌላው እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ ነው፥ ሲጀመር ጳውሎስ ነብይ አይደለም። ሲቀጥል የሚናገረው በሞኝነት እንጂ ጌታ አዞት አይደለም፥ ንግግሩ የራሱ እንጂ የጌታ አይደለም፦ 1ኛ ቆሮ 7፥12 ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም። 2ኛ ቆሮ 11፥17 እንደዚህ ታምኜ ስመካ “የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም”። ሢሰልስ ጳውሎስ፦ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ወይም ለእያንዳንዲቱ ባል ይኑራት" አለ እንጂ ለእያንዳንዱ ለራሱ አንዲት ሚስት ትኑረው አሊያም ለእያንዳንዲቱ ለራሷ አንድ ባል ይኑራት አላለም፦ 1ኛ ቆሮ 7፥2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት። ለእያንዳንድህ እና ለእያንዳንሽ ብር እሰጣችኃለው ማለት የብሩ መጠን ስላልተገለጸ አንድ ብር ብቻ ተብሎ እንደማይተረጎም ሁሉ ባል እና ሚስት መባሉ የቁጥሩን መጠን በፍጹም አያሳይም፦ መዝሙር 62፥12 አንተ "ለእያንዳንዱ" እንደ ሥራው ፍዳውን ትሰጣለህና። ሮሜ 2፥6 እርሱ "ለእያንዳንዱ" እንደ ሥራው ያስረክበዋል። "እያንዳንድ"every" የሚለውን ቃል "አንድ"one" ብሎ መረዳት የተንሸዋረረ መረዳት ነው። "ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው" ያሉት ምዕራባውያን እንጂ ባይብል አይደለም። ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክሉም ከአንድ በላይ ዝሙት ማድረግ የአንድ ሰው መብቱ እና ነፃነቱ ነው የሚል መርሕ አላቸው፥ ምዕራባውያን በ 17ኛው ክፍለ-ዘመን ሰው እንዲዋለድ እና እንዲባዛ ስላልፈለጉ እንጂ የመጡበትን ዳራ የክርስትናን መሠረት አድርገው አይደለም። ለዛ ነው ግብረ-ሰዶም እንዲስፋፋ የተፈለገው፥ ይህንን እንደ ሥልጣኔ የምዕራቧ ቤተክርስቲያን ግብረ-ሰዶም ታጋባለች። ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ዝሙት ሲፈቅዱ ኢሥላም ደግሞ ከአንድ በላይ በሐላል ኒካሕ ማድረግ ይፈቅዳል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Hammasini ko'rsatish...
የምታዩት ሰው ፕሮፌሰር ጌሪ ሚለር ይባላል፣ የክርስቲያን ሚሺነሪ እና የስነ-መለኮት ሊቅ ነው፣ ታድያስ እንደተለመደው በቁርኣን ውስጥ ስህተትን ፍለጋ ጉዞ ጀምሮ ለብዙ ዓመታት ቁርኣንን በዐረብኛ አጥንቷል፣ አህመድ ዲዳትን ጨምሮ ከብዙ ሙስሊም ዐቃቤዎች ጋር ክርክር ገጥሞ ተወያይቷል፣ አልሃምዱሊላህ አሁን ስሙ አብዱል-አሐድ ነው። https://t.me/mahircomp123
Hammasini ko'rsatish...
የኢማን መዳከም ምልክቶች ብዙ ሲሆኑ እንደየድክመቱ ሁኔታና ደረጃ ከሰው ሰው ይለያያል። ከነኚህም ምልክቶች መካከል፡- -        የታዘዙበትን ነገር በሚፈለገው መልኩ ከመፈፀም አንፃር መሳነፍ፡፡ -        የአምልኮ ተግባራትን በሕያው ልብ አለመፈፀም፣  -        ለሱብሒ ሶላት ዘግይቶ መነሳት፣ -        የጀመዓ ሶላትን አለመናፈቅ፣ -        የግዴታ ሶላቶችን ቤት መስገድ፣ -        ግዴታዎች ባለመወጣት አለመጨነቅና አለማዘን፣ -        ወደ ጁመዓ ሶላት ዘግይቶ መሄድ። -        ከሶላት በኋላ ተጣድፎ መውጣት፣ -        የሱንና ሶላቶችን መተው፣ -        ተመራጭ ሶላቶችን አለማሰብ፣ ለምሳሌ የዱሓ እና የኢስቲኻራ ሶላቶች፣ -        ከቁርአን መራቅ፣ -        ቁርአንን በሕያው ልብ አለማንበብ፣ -        የቁርኣንን መልዕክቶች አለማስተንተን፣ -         ዚክር (አላህን ማውሳት) መተው፣ -        ከዱዓ መሳነፍ፣ -        ለሐላል ሐራም መርህ አለመጨነቅ፡፡፡ -        አልባሌ ነገር እየሠሩና እያወሩ ማምሸት፣ -        ሰዉን አለማክበር፣ -        ለዓለማዊ ጥቅም መጓጓት፣ -        ባገኙት አለመርካት፣ -        ለዲናዊ ትምህርት ትኩረት መንፈግ፣ -        ሱንናን ማጣጣል፣ -        ለሚናገሩት አለመጨነቅ፣ -        የባህሪ መክፋት፣ -        በቀደር አለማመን፣ - የአላህን መሻት አለመውደድ፣ -        ብሶት ማብዛት ፣ መነጫነጭ፣ -        የሰዎችን ችግር አለመካፈል፣ ለድሆች አለማዘን፣ -        ለወንድማዊ ትስስር አለመጨነቅ፣ -        ክርክር ማብዛት፣ -           https://t.me/NejashiPP
Hammasini ko'rsatish...
Nejashi Printing Press

ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።

🌾 ስለዘካተል-ፊጥር አጭር ማስታወሻ🌾 1⃣ ትርጉም:- ዘካተል-ፊጥር(ሶደቀተል-ፊጥር):- የረመዷንን ወር ፆም በመጨረስ ግዴታ የሚሆን ሶደቃ(ምጽዋት) ነው። 2⃣ የመደንገጉ ሒክማ(ጥበብ) 💡ለፆመኛው ሰው በረመዳን ፆም ላስገኛቸው ያልተገቡ እና ውድቅ ንግግሮች ማጥሪያ 💡ለሚስኪኖች በጎ ለመዋል እና የዒድ ቀን ከልመና እንዲብቃቁ ማድረግ 💡የዒዱን ቀን ደስታ አብሮ ለመጋራት 💡አላህ የረመዷንን ፆመ ለመጨረስ ስላበቃን ለአላህ ምስጋናን የምንገልፅበት 3⃣ ሑክሙ(ሸሪዐዊ ድንጋጌው) ✔️ዘካተልፊጥር መስጠት ግዴታ ነው። ከዐንደላህ ቢን ዑመር(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አለ:- "የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘካተል-ፊጥርን ግድ አደረጉ። ከተምር አንድ ዘንቶ፣ ወይም ከገብስ አንድ ዘንቶ(ግድ አደረጉ)። ሙስሊም የሆኑ ባሪያም ጨዋም ላይ፣ ሴትም ወንድም ላይ፣ ትንሽም ትልቅም ላይ (ግድ አደረጉ)። ሰዎች ወደ(ዒድ) ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።) 4⃣ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች ▫️የዒድ ለሊት እና ቀን ለራሱ እና በርሱ ላይ መቀለብ ግዴታ ከሚሆኑበት ሰዎች ቀለብ በላይ ያለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። 5⃣ ማውጣት ግድ የሚሆነው ከማን ነው? ✅ ከራሱ እና በርሱ ስር ላሉ የሚቀልባቸው ሰዎች(እንደ ሚስቶች፣ ልጆች...) ✅ ሆድ ውስጥ ላለ ጽንስ ማውጣት የተወደደ ነው። 6⃣ የሚወጣው ምንድን ነው? ✔️ዘካተል-ፊጥር የሚወጣው በአካባቢው በአብዛኛው ለምግብነት ከሚውል እህል ነው። ✅ የእህሉን ዋጋ በገንዘብ ቀይሮ መስጠት አያብቃቃም። 7⃣ የሚወጣው የእህል መጠን ✨ ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ዘንቶ ዘንቶ:- በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኝ🤲 የሚይዝ መስፈሪያ ነው። 8⃣ ለማን ነው የሚሰጠው? 🔖 በሚያወጣው ሰው አገር ላሉ ደሀ እና ሚስኪኖች 9⃣ ⏰የሚወጣበት ጊዜ 📍በላጩ ጊዜ የዒድ ቀን ጧት ከዒድ ሶላት በፊት ነው። 📍ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል። 🕌 ከዒድ ሶላት ቡኃላ ማዘግየት አይፈቀድም🔖ሐዲስ በአማርኛ:- Telegram: https://t.me/HadithAmharic Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic
Hammasini ko'rsatish...
🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌 1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት 2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት 3-🚿 ሸዋር መውሰድ 4-👚 ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ 5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ) 6-🌹 ሽቶ መቀባት 7-🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ 8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ 9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ 10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ 🔖ሐዲስ በአማርኛ: Telegram: https://t.me/HadithAmharic Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic
Hammasini ko'rsatish...
ጾምን ከሚያበላሹ ነገሮች:- 1⃣ መብላት እና መጠጣት:- 💭 ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ጾሙ አይበላሽም። 2⃣ ምግብን እና መጠጥን የሚተኩ ነገሮች:- 💉 ምግብ ነክ መርፌ እና መድሓኒቶች ጾምን ያፈርሳሉ። 🩸ለህመምተኛ የሚሰጥ ደም ጾምን ያፈርሳል። 3⃣ የግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈፀም:- 🔵 የፍቶት ጠብታ(መንይ) ቢፈስም ባይፈስምየግብረ-ስጋ ግንኙነት ጾም ያበላሻል። 4⃣ የፍቶት ጠብታን በፍላጎት እና ምርጫ ማፍሰስ(ኢስቲምናእ):- ❌ በመተሻሸት፣በእጅ፣ ደጋግሞ በመመልከት፣ በመሳም.. ወዘተ ከፈሰሰ ጾም ያበላሻል። 💤 በእንቅልፍ ልብ የሚከሰት የዘር ፍሬ መፍሰስ(ኢሕቲላም) ጾም አያበላሽም። 5⃣ አውቆ ማስታወክ:- 🥛ከቁጥጥር ውጭ በራሱ ከወጣ ጾም አያበላሽም። 6⃣ የወር አበባ እና የወሊድ ደም መፍሰስ:- 🩺 ከተለመደው የወር አበባ ቀን ውጭ በበሽታ ምክንያት የሚፈስ ደም(ኢስቲሓዷ) ጾም አያበላሽም። 💡 ከሰውነት ደም ማውጣትን መተው የተመረጠ ነው:- 🆎 ለዋግምት ወይም ደም ለመለገስ ደም ማውጣት ለሊት ማድረጉ ይመረጣል። 🩸ለህክምና ምርመራ ናሙና፣ ነስር፣ ቁስል እና ጥርስ በመንቀል የሚፈስ ደም ምንም ችግር የለውም። 🔖ሐዲስ በአማርኛ:- Telegram: https://t.me/HadithAmharic Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic 🔈ለሌሎችም ያስተላልፉ 🔂
Hammasini ko'rsatish...
Du'aa'ii Soommanaan furan! አንድ ሰው ሲያፈጥር ጊዜ የሚያደርገው ዱዓ ! ﻋﻨﺪ ﺍﻹﻓﻄﺎﺭ ﺗﻘﻮﻝ ﻣﺎ ﻛﺎﻥ ﻳﻘﻮﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ ، ﻓﺈﻥ ﻣﻦ ﺳﻨﺘﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺃﻧﻪ ﻛﺎﻥ ﺇﺫﺍ ﺃﻓﻄﺮ ﻗﺎل ( ﺫﻫﺐ ﺍﻟﻈﻤﺄ ﻭ ﺍﺑﺘﻠﺖِ ﺍﻟﻌﺮﻭﻕ ﻭﺛﺒﺖ ﺍﻷﺟﺮ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ) 📚[ ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎمع) [(4678) በአማርኛ ሲነበብ፦ ዘሃበ ዘመዑ ወብተለቲል ዑሩቁ ወሰበተል አጅሩ ኢንሻ አሏህ ትርጉሙም፦" ጥም ተወገደ ጎሮሮዎችም ረጠቡ በአሏህ ፍቃድ አጅሩም ፀደቀ።" ማለት ነው። ★★★★★★★★★★★★ Du'aa'ii Soommanaan furan. ﻋﻨﺪ ﺍﻹﻓﻄﺎﺭ ﺗﻘﻮﻝ ﻣﺎ ﻛﺎﻥ ﻳﻘﻮﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ ، ﻓﺈﻥ ﻣﻦ ﺳﻨﺘﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺃﻧﻪ ﻛﺎﻥ ﺇﺫﺍ ﺃﻓﻄﺮ ﻗﺎل ( ﺫﻫﺐ ﺍﻟﻈﻤﺄ ﻭ ﺍﺑﺘﻠﺖِ ﺍﻟﻌﺮﻭﻕ ﻭﺛﺒﺖ ﺍﻷﺟﺮ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ) 📚[ ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎمع) [(4678) [ Zahaba zama'u, wab-ttalatil uruuqu wasabatal ajru in-shaa Allaah] Share godhaa! Waliin gahaa. Sababaa keetiin namni tokko yoo Du'aa'ii tanaan fure Ajrii argatta.
Hammasini ko'rsatish...
🔴ረመዳን ሙባረክ! የሳውዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳስታወቀው የረመዳን ጨረቃ ታይቷል። በዚህም መሰረት ነገ ማክሰኞ የረመዳን የመጀመሪያው ቀን ይሆናል።
Hammasini ko'rsatish...
عن أَبي هُريرة رضي الله عنه، عن النبيِّ ﷺ قَالَ: [ لاَ يتَقَدَّمَنَّ أَحَدُكمْ رَمَضَانَ بِصَومِ يومٍ أَوْ يومَيْنِ، إِلاَّ أَن يَكونَ رَجُلٌ كَانَ يصُومُ صَوْمَهُ، فَلْيَصُمْ ذلكَ اليوْمَ] 📚متفقٌ عَلَيْهِ 🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸 ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው ነቢዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- [ አንዳችሁ ረመዷንን አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን በመፆም አይቀደም፤ ሱና ሲፆም የነበረ(ያስለመደ) ሰው ሲቀር፣ ያንን ቀኑን ይፁም።] 📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። 🔖ሐዲስ በአማርኛ:- Telegram: https://t.me/HadithAmharic Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic
Hammasini ko'rsatish...