cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

መረጃ COVID-19(corona) ETHIO-WORLD

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
136
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገብተው በደቡብ አፍሪካ እስር ቤት ውስጥ የነበሩ 218 ዜጎች ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ በዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ #አዲስማለዳ @tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Hammasini ko'rsatish...
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለ2013 በጀት ዓመት 4 ቢሊየን 214 ሚሊየን 594 ሺህ 256 ብር አጽድቋል፡፡ ከበጀቱ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ከፌደራል መንግስት ድጎማ፣ ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ከከተማ አስተዳደሩ ከሚሰበሰብ ግብርና 734 ሚሊየን ብር ከተለያዩ የልማት አጋሮች ከሚገኝ እንደሚሸፈን ተገልጿል። @tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Hammasini ko'rsatish...
የደቡብ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ! የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ አመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀዋሳ መካሄድ ጀመሯል። ምክር ቤቱ በ3 ቀናት ቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። @tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Hammasini ko'rsatish...
ህብረተሰቡ የአየር ትንበያን በአግባቡ በመከታተል ራሱን ከአደጋ ቀጣናዎች እንዲያርቅ ጥሪ ቀረበ! ዛሬ በሚጀምረው የነሃሴ ወርም መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ መዝነቡ ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ ህብረተሰቡ በዚህ ወቅት ሊፈጠር ከሚችል የወንዞች ሙላት እና ከጎርፍ አደጋ ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና ብሄራዊ ሜትሪዮሎጂ ኤጀንሲ አሳስበዋል። ሰሜናዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን እንዲሁም የእነዚህ ሀገራት አዋሳኝ አካባቢዎች በቀጣዮች ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚያስተናግዱም የኢጋድ የአየር ንብረት ለውጥ ቅድመ ትንበያ ቢሮ ይፋ አድርጓል። የአየር ፀባይ ትንበያዎችን በአግባቡ በመከታተል ራሱን ከአደጋ ቀጣናዎች እንዲያርቅ ለህብረተሰቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ እንዲሁም የሰሞኑ ከባድ ቅዝቃዜ ለተከታታይ ቀናት ሊዘልቅ እንደሚችል ተነግሯል፡፡ የቅዝቃዜው ምክንያትም የሆነው ከደቡብ ህንድ እና ከደቡብ አትላንቲክ ውቅያኖሶች የሚገባው እርጥበት አዘል ከባድ ነፋስ ነው ተብሏል፡፡ #FBC #ShegerFM #IGAD @tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Hammasini ko'rsatish...
በከተማዋ 495 የህዝብ መጸዳጃ ቤቶችና 151 የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሾች ሊገነቡ ነው! በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር 495 የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ መታጠቢያ(ሻወር) ቤቶችና በ151 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የመመገቢያ አዳራሾች ለመገንባት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የልማታዊ ሴፍትኔትና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አስታውቋል። በልማታዊ ሴፍትኔት አማካኝነት የሚካሄዱት ግንባታዎችም ለ33ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። በአዲስ አበባ ከተማ በሶስት ዙሮች 410ሺ ሰዎች በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል፡፡ #EPA @tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Hammasini ko'rsatish...
ጾመ ፍልሰታ! በኦርቶዶክስ እምነት እና በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ እኩሌታ ለሚጾመው ጾመ ፍልሰታ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ ምዕመናንም ጾሙን ኮቪድ-19ን በመከላከል፣ የተቸገሩትን በመርዳት ማሳለፍ እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ እንዲሁም በቅርቡ በተከሰተው ሁከት የሞቱ ወገኖችን በማሰብ ፣ያዘኑትን በማፅናናት የወደመውን ንብረት በጋራ ድጋፍ መልሶ በማቋቋም ፣ዘረኝነትንና ጥላቻን በኢትዮጵያዊ አብሮነት ወደ ፍቅር በመመለስ ፆምን ማሰብ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ለመላው የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ! መልካም የጾም ወቅት ይሁንላችሁ! @tikvahethmagazine @tikvahmagBot
Hammasini ko'rsatish...
SMART ELECTRONICS / ስማርት ኤሌክትሮኒክስ ኦርጂናል ስልክ መግዛት አስበው የት እንደሚያገኙ ከተጨነቁ፤ ኦርጅናልና አዳዲስ ስልኮች ከሙሉ ህጋዊ ዋስትና ጋር በማይታመን ዋጋ ማግኘት ከፈለጉ ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉና የዋጋ ዝርዝሮችን መግኘት ይችላሉ https://t.me/joinchat/AAAAAEQeR9_lTfIGOZrZxw ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇 0921667933 0913393937 አድራሻ... ቦሌ መድሀኒያለም ቤክ ዝቅ ብሎ ሰላም ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ላይ ስማርት ኤሌክትሮኒክስ
Hammasini ko'rsatish...
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ:- በቫይረሱ ከተያዙ መካከል 43 ወንዶችና 18 ሴቶች ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ዕድሜያቸው ደግሞ ከ15-70 እንደሆነ ታውቋል። የተገኙት ከአዲስ አበባ(48)፣ ከአማራ ክልል ደሴ (1)፣ አፋር ክልል ዱምቲ(3)፣ ከኦሮሚያ ክልል (2) ፣ ጅግጅጋ(7) በኮሮና የተያዙ በድምር 61 ሰዎች ናቸው። ከ61 መካከል 11 የውጭ ሃገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፤ 5 ሰዎች በሽታው ካለበት ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፤ የተቀሩት 45ሰዎች ደግሞ የጉዞ ታሪክም ሆነ ንክኪ የሌላቸው ናቸው። ተጨማሪ 23 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 151 ደርሷል
Hammasini ko'rsatish...
#ሰበር_ዜና‼️ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3757 የላብራቶሪ ምርመራ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጡ። ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ቴዎድሮስን በሰላሳ ቀናት በድርጅታቸው ውስጥ "መሰረታዊ ለውጥ" እንዲያመጡ ያሳሰቡ ሲሆን አለበለዚያ ግን አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ለድርጅቱ የምታደርገውን ድጋፍ ታቋርጣለች ሲሉ ለዶ/ር ቴድሮስ በጻፉት ደብዳቤ አስጠንቅዋል። ፕሬዝዳንቱ ለዶ/ር ቴዎድሮስ የጻፉትን ደብዳቤ በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት የሚጠበቅበትን በሚገባ ስላለመወጣቱ ሲናገሩ ቫይረሱ ከቻይናዋ ዉሃን በተነሳበት ወቅት "በተደጋጋሚ ስለ ቫይረሱ ስርጭት አስመልክቶ ይቀርቡ የነበሩ ተጨባጭ መረጃዎችን ችላ ብሏል" ሲሉ ወቅሰዋል። አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት በተደጋጋሚ ቻይናን "ሲያንቆለጳጵስ" ነበር በማለት የዓለም ጤና ድርጅት "መሰረታዊ የሆነ ማሻሻያ ካላደረገ" በማለት በጊዜያዊነት ያቋረጡትን የአሜሪካ ድጋፍ በቋሚነት ለማድረግና "አባልነታችንንም እናስብበታለን" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
Hammasini ko'rsatish...