cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የወንቅሸት ልጆች

"እግዚአብሔር እረኛዬ ነዉ የሚያሳጣኝም የለም በለመለመዉ መስክ ያሳድረኛል በዕረፍት ዉሃ ዘንድ ይመራኛል ነፍሴን መለሳት ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ" መዝ. (23)፡1-3 በዚህ channel የ አባታችን የአባ ዮሀኒስ ተስፋ ማርያም ድንቅ ስራወች እና የተለያዩ የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎች ይተላለፉበታል። የ አባታችን ፀጋ እና በረከት ይደርብን፡ አሜን። ለመቀላቀል

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
441
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

+++ስላልሠጠኽኝ አመሰግንሃለሁ!+++ በአንድ ወቅት አንዲት ወፍ እንቁላል የምጥትልበት እና የክረምቱን ዝናባማ ወራት የምታሳልፍበት ጎጆ መሥሪያ ቦታ እየፈለገች ነበር። በዚህ ፍለጋዋ ወቅት ሁለት ዛፎችን ተመለከተችና ቀርብ ብላ መጠለያ ቦታ ልትጠይቃቸው ወሰነች። ወደ አንደኛው ዛፍ ጠጋ ብላ ፤ መጠለያ መፈለጓን ነገረችው ፤ ዛፉም መጠለያ ይሰጣት ዘንድ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገለጸላት። ወፏም በመጀመሪያው ዛፍ ምላሽ ተናድዳ ፤ ወደ ሁለተኛው ዛፍ ተጠጋች ፤ መጠለያ መፈለጓን ነገረችው። ሁለተኛውም ዛፍ በደስታ "ጥያቄሽን በእሺታ ተቀብያለሁ እኔ ላይ ተጠለዪ ፣ ቤትሽም ፣ መኖሪያሽም በዚሁ ይሁን" አላት። ወፊቱም ተደስታ በሁለተኛው ዛፍ ላይ ቤቷን አበጃጅታ ፤ እንቁላልዋን ጣለች ፤ ዝናባማው ወራትም ወዲያውኑ ጀመረ። የሚዘንበው ዝናም ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ ፤ የመጀመሪያው ዛፍ ወደቀና ጎርፍ ወሰደው። ይህን የተመለከተችው ወፍ በሽሙጥ አነጋገር "አየህ ዕጣ ፈንታህ ይኼ ነው ፤ ለእኔ መጠለያን እምቢ ስላልኽ ፤ እግዚአብሔር በዚህ ቀጣህ" አለችው። ዛፉም ፈገግ እያለ "ከነበርኩበት ኹኔታ አንፃር ይህን ክረምት እንደማላልፍ እንደምወድቅ አውቅ ነበር ፤ የአንቺ እና የልጆችሽ ሕይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በማሰብ መጠለያ ስትጠይቂኝ እምቢ አልኩሽ" ሲል መለሰላት። ወፊቱም የእምቢታውን ምክንያት በተረዳች ጊዜ ስለዛፉ አዘነች ፤ ከእርሷ ሀሳብ ልቆና ርቆ ስላሰበላት ስለበጎነቱም በልቧ ውስጥ አከበረችው። +++ "የምትለምኑትን አታውቁም።" (ማቴ. 20: 22) +++ + በሕይወታችን የምንሻውን ነገር መከልከላችን ፤ ማጣት ወይም ከስኬት መጓደል ማለት አይደለም። ማን ያውቃል የለመነው ነገር የማጣታችን ምንጭ ፣ የመጥፊያችን ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ፤ "የፈለጉትን አለማግኘትም ሥጦታ ነው!" + በእምቢታ የመለሱልን ወይም የከለከሉን ሁሉ ደግነት የራቃቸው ፣ ፍቅር አልባዎች አይደሉም። እናት ልጇ እሳት መንካት ሲፈልግ ፤ ጥቅምና ጉዳቱን እንደማይለይ አውቃ እንደምትከለክለው ፤ ክልከላዋም የጥላቻ ሳይሆን የፍቅር እንደሆነ ፤ እንዲሁ የሚከለክለን ሁሉ ጠላታችን ሳይሆን ወዳጃችንም እንደሆነ እናስተውል!! + የአንዳችን መውደቅ ሌሎችንም ለውድቀት እንዳይዳርግ ፤ እያንዳንዳችን ስለራሳችንም ፣ በዙሪያችን ስላሉ ስለሌሎች ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን እናስብ!!! + በእኛ ሕሊና "እገሌ እኮ እንዲህ ነው ፤ እንዲህ ለማለትም ፈልጎ ነው" ብለን ስለሰዎች በእርግጠኝነት የምናስበው ሀሳብ የምንገልጠው ቃል ፤ ሁልጊዜ አሸናፊና የመጨረሻው ትክክለኛ ሀሳብ ነው ብለን ከማሰብ እንከልከል ፤ የሰውን ልቡና የሚመረምር እግዚአብሔር ነውና!!! ስብሐት ለእግዚአብሔር ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
Hammasini ko'rsatish...
የቀጠለ ✔❖ ከዚያም በክርስቲያኖች ጠላት በከሓዲው መክስምያኖስ ላይ ዘመተበት፤ ከዚያም መክስምያኖስ ሰምቶ ጦሩን ይዞ መጣበት፤ በመክስምያኖስ ጦር ላይ ዐድረው ድል ያደርጉ የነበሩ አጋንንት በቈስጠንጢኖስ ጦር ላይ ያለውን ትእምርተ መስቀል ባዩ ጊዜ ተለይተውት በኼዱ ጊዜ ድል ተነሣ፤ ርሱም ከጥቂቶች ጋር ራሱን ለማዳን “ወተጽዕኑ ዲበ ተንከተም ወተንከተምኒ ንህለ ወተሠጥመ መክስምያኖስ ምስለ ሰራዊቱ” ይላል ወደ ሮሜ ለመሻገር በድልድይ ላይ ሲወጡ ድልድዩ ፈርሶ ከሰራዊቱ ጋር ሰጥሟል፡፡ ✔❖ ከዚያም በድል አድራጊነት ንጉሥ ቈስንጢኖስ ወደ ሮሜ በገባ ጊዜ ካህናቱ ሕዝቡ መብራት ይዘው፤ “መስቀል ኀይልን መስቀል ጽንዕነ መስቀል መዋዔ ጸር” እያሉ እየዘመሩ ተቀበሉት፤ ርሱም እናቱ ቅድስት እሌኒ እያስተማረች ያሳደገችው፤ በኋላም ምእመናን ይልኩለት የነበረው፤ በሰሌዳ ሰማይ ላይ የተመለከተው፤ አኹንም በአንጾኪያ ምእመናን ይዘው የተቀበሉትን አይቶ ትክክለኛውን ሃይማኖት በመረዳት ከሀገሩ ሶልጴጥሮስን አምጥቶ ተጠምቋል፡፡ ✔❖ ከዚያም ዐዋጁን ባዋጅ በመመለስ “አብያተ ጣዖታት ይትዐጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ” (አብያተ ጣዖታት ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ) የሚል ታላቅ ትእዛዝን አዘዘ፤ የጌታችንንም መስቀል እንድታወጣ እናቱ እሌኒን ወደ ኢየሩሳሌም ላካት፨ ✔ ❖ ይኽስ እንደምንድ ነው ቢሉ የጌታችን መስቀል ከጌታችን ዕርገት በኋላ ሙት እያነሣ፣ ደዉይ እየፈወሰ ለክርስያኖች ታላቅ ክብር በመኾኑ፤ አይሁድ በዚኽ ቀንተው ጒድጓድ ቈፍረው በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም ኹሉ ቤቱን የሚጠርግ ጒድፉን አምጥቶ እንዲያፈስስበት በማዘዛቸው ቦታው የቆሻሻ መጣያ ኾኖ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣችበት ድረስ ለ፫፻ ዓመታት ያኽል ተቀብሮ ኖረ፡፡ ✔❖ ልጇ ቆስጠንጢኖስም በመስቀሉ ኀይል የክርስቲያኖች ጠላት የኾነውን መክስምያኖስን ድል ከነሣ በኋላ በሶል ጴጥሮስ ተጠምቆ ክርስቲያን ኾነ፤ ርሷም ልጄ ክርስቲያን ከኾነ ኢየሩሳሌም ኼጄ የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት አሠራለኊ፤ የጌታዬ መስቀልን ከተቀበረበት አስወጣለኊ ብላ ስዕለት ተስላ ነበርና ያ በመፈጸሙ ደስ ተሰኝታ፤ ለልጇ ነገረችው፤ ርሱም በደስታ ብዙዎች ሰራዊትን ስንቅ አስይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ላካት፤ በደረሰችም ጊዜ ሱባኤን አድርጋ የመስቀሉ ጠላቶችን በጽኑ እስራት አሰረቻቸው፤ በኋላም አሚኖስና ኪራኮስ የሚባሉ በዕድሜ የጠገቡ ሽማግሌዎችን ብትጠይቃቸው ሊነግሯት ፈቃደኛ አልኾኑምና በጽኑ እስራት ብታስጨንቃቸው፤ ታሪኩን ነገሯት፤ ቦታውንም ጠቈሟት፡፡ ✔❖ ከዚያም በጸሎቷ ላይ ቅዱስ መልአክ ተገልጾላት በዕጣን ጢስ አማካይነት እንደምታገኘው ተረድታ፤ መስከረም ፲፮ ደመራን አስደምራ በእሳት እንዲቃጠል አድርጋ እጅግ ብዙ ዕጣንን ብታስጨምር ጢሱ ወደ ሰማያት ወጥቶ መስቀሉ ካለበት ቦታ ላይ ተተክሎ ሰገደ፤ ርሷም ፈጣሪዋ እግዚአብሔርን በፍጹም ደስታ አመስግና ቊፏሮውን ከመስከረም ፲፯ ዠምሮ እስከ መጋቢት ፲ ድረስ እንዲቈፈር አስደርጋለች፤ በቊፋሮው ወቅትም የፈያታዊ ዘየማንና የፈያታዊ ዘጸጋም መስቀል ቢገኙም ዕውር አላበሩም፣ ሕሙማንን አልፈወሱም፡፡ ✔❖ ከዚያም መጋቢት ፲ ጌታችን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት ቅዱስ መስቀሉ ተገኘ፤ በዚኽ ጊዜ ከሕሙማን ላይ ቢያደርጉት ኹሉንም ፈወሳቸው፣ ዕዉራን በሩ፣ ሙታንም ተነሡ፡፡ ከዚኹም ጋር የተወጋበት ጦሩ፣ የተቸነከረባቸው ቅንዋት ኹሉ ተገኝተዋል፤ ርሷም በፈረሷ ልጓም ላይ የመስቀል ምልክትን አስቀርጻበታለች፡፡ ✔❖ ርሷም ጌታችን ተአምራት በሠራባቸው ቦታዎች አብያተ ክርስቲያናትን በማሠራት፤ በተለይም በጎልጎታ የተሠራው ቤተ ክርስቲያን መስከረም ፲፯ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን በተገኙበት ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ተከብሯልና፡፡ ርሷም ለድኾችና ለጦም አዳሪዎች ብዙ መልካም ነገርን በማድረግ ግንቦት ፱ በሰላም ዐርፋለች፡፡ ✔❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ስለ ቅድስት እሌኒ በዐርኬው ላይ፡- “ሰላም ለእሌኒ ውስተ ምድረ ሕይወት ኤልዳ ምክረ መንፈስ ቅዱስ አመ ወሰዳ ለዘሐይወ በድን በለኪፈ መስቀል ቅድመ ዐውዳ እምአይቴ አንተ ትቤሎ ወእምአይ አንግዳ ዘተረከብከ ግዱፈ በበዳ” (የመንፈስ ቅዱስ ምክር በወሰዳት ጊዜ ኤልዳ ወደ ተባለች የሕይወት ምድር የኼደች ለኾነች ለዕሌኒ ሰላምታ ይገባል፤ በአደባባይዋ ፊት መስቀልን በመንካት የዳነውን በድን በበረሓ ወድቀኽ የተገኘኽ አንተ እንግዳ ከወዴት ነኽ አለችው) በማለት መስቀሉ ከወጣ በኋላ ስለተደረገላት ተአምር ጽፏል፡፡ "ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኀኒት ኀይልነ ወጸወንነ" (ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ)
Hammasini ko'rsatish...
❖መስቀሉን ያስወጣችው የእሌኒና የቆስጠንጢኖስ ታሪክ❖ ✔❖ ይኽ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ የአባቱ ስም ቊንስጣ የእናቱ ስም እሌኒ ነው፤ ከሓዲው መክስምያኖስ በሮሜ በአንጾኪያ እና በግብጽ ነግሦ በነበረ ጊዜ አባቱ በራንጥያ ለሚባል ሀገር ንጉሥ ነበር፤ እሌኒ ከርሱ ቆስጠንጢኖስ ከወለደችው በኋላ አባቱ ቊንስጣ እነርሱን ሮሐ (ሶርያ) ላይ ትቷቸው ወደ በራንጥያ ተመለሰ፡፡ “ወይእቲ ነበረት እንዘ ተሐጽኖ ለወልዳ ወመሀረቶ ትምህርተ ክርስትና ወኮነት ዘትዘርዕ ውስተ ልቡ ምሕረተ ወሣሕለ ላዕለ ሕዝበ ክርስቲያን” ይላል፤ ርሷም ልጇን የክርስትና ትምህርትን አስተማረችው፤ ይቅርታንና ርኅራኄን በክርስቲያን ወገኖች ላይ እንዲያደርግ በልቡናው መልካም ዘርን ትዘራበት ነበር፡፡ ✔ ❖ ከዚያም ቈስጠንጢኖስ አካለ መጠን ሲያደርስ ወደ አባቱ ሰደደችው፤ አባቱም የጥበቡን ብዛት አይቶ በመደሰት ከበታቹ መስፍን አድርጎት በመሾም በመንግሥቱ ሥራ ላይ ኹሉ ሥልጣንን ሰጥቶታል፤ “ወእምድኅረ ክልኤቱ ዓመት አዕረፈ አቡሁ ወተመጠወ ቈስጠንጢኖስ ኲሎ መንግሥተ ወገብረ ፍትሐ ርቱዐ” ይላል፤ ከኹለት ዓመት በኋላ አባቱ በማረፉ ቈስጠንጢኖስ መንግሥቱን ኹሉ ተረክቦ የቀና ፍርድን የሚፈርድ ኾነ፤ ከርሱ በፊት የነበሩ ነገሥታት የጫኑባቸውን ጽኑ አገዛዝ ከሰዎች ላይ የሚያስወግድ ኾነ፤ በዚኽ ምክንያት ኹሉም ወደደው፤ ዝናውም በብዙ ሀገሮች ላይ ተሰማለት፡፡ ✔❖ በአንጾኪያ ያሉ ክርስቲያኖችም የቈስጠንጢኖስን ፍርድ መጠንቀቁን፣ ድኻ መጠበቁን እየሰሙ ከከሓዲው ከመክስምያኖስ አገዛዝ እንዲያድናቸው የልብሰ ተክህኖውን ቅዳጅ፣ የመስቀሉን ስባሪ ይልኩለት ነበር፤ ርሱም ስለደረሰባቸው መከራ በእጅጉ እያዘነ እንዴት አድርጎ እንደሚያድናቸው ያስብ ነበር፤ “ወእንዘ ይነብር ውስተ ዐውድ ወናሁ አስተርአዮ በመንፈቀ መዓልት መስቀል ዘሕብሩ አምሳለ ከዋክብት ወዲቤሁ ጽሑፍ በልሳነ ዮናኒ ኒኮስጣጣን ዘበትርጓሜሁ በዝንቱ ትመውዕ ጸረከ ወአንከረ ብርሃኖ ለመስቀል ሶበ ርእየ እንዘ ይከድኖ ለብርሃነ ፀሓይ” ይላል ከዕለታት ባንዳቸው በአደባባይ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ከቀኑ በስድስት ሰዓት ጊዜ ሕብሩ እንደከዋክብት የኾነ መስቀል በጸፍጸፈ ሰማይ ላይ ሲታየው፤ በላዩም በዮናኒ ቋንቋ ኒኮስጣጣን የሚል ጽሑፍ ነበረው፤ ትርጓሜውም በዚኽ ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ ማለት ሲኾን፤ ርሱም የመስቀሉ ብርሃን የፀሓይን ብርሃን ሲሸፍነው አይቶ ተደንቋል፡፡ ✔❖ ይኽነንም ያየውን ለሊቃውንቱ በጠየቃቸው ጊዜ አውስግንዮስ የሚባል ሕጽው በዚኽ መስቀል አምሳል ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ ማለት ነው ብሎ ተረጐመለት፤ መልአኩም ሌሊት በራእይ ታይቶት አስረዳው፤ “ወነቂሆ እምንዋዮሙ ጸንዐ ልቡ ወገብረ መስቀለ ዘወርቅ ወረሰዮ መልዕልተ አክሊለ መንግሥቱ ወአዘዞሙ ለኲሎሙ መኳንንቲሁ ወሐራሁ ከመ ይግበሩ መስቀለ በኲሉ ንዋየ ሐቅሎሙ” እንዲል ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ልቡ ጸናና የወርቅ መስቀልም አሠርቶ በነገሠበት ዘውድ ላይ አደረገው፤ መኳንንቱንና ወታደሮቹን ኹሉ መስቀል አሠርተው በጦር መሣሪያቸው ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸውና እንዳላቸው አደረጉ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የዕውራንን ዓይን እያበራ፣ ልዩ ልዩ ደዌ ያደረባቸውን እየፈወሰ ተዓምራት በማድረጉ በሰቀሉት ሰዎች ዘንድ ባሳደረው ቅንዓት በአልባሌ ሥፍራ፣ በከተማ ጉድፍና ጥራጊ ማከማቻ ውስጥ ተጥሎ ለ300 ዓመታት ያህል ከቆየ በኋላ ተፈልጎ የተገኘበት ታሪካዊ በዓል ነው፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ለሦስት ምዕት ከተቀበረበት የቆሻሻ ሥፍራ የተገኘው በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት በንግሥት ዕሌኒ አማካይነት ሲሆን የበዓሉም መከበር ይህንኑ ይዘክራል፡፡ ንግሥት እሌኒ ከመንፈሳውያን አበው (አረጋዊውን ኪራኮስን ያስታውሷል) በተነገራት መሠረት ያዘጋጀችው የደመራ እንጨትና በደመራው ላይ የተደረገው የዕጣን ጢስ ወደላይ ወጥቶ ተመልሶ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ አመልክቷል፡፡ በዚያው ላይ ቁፋሮ ተካሂዶ መስቀሉ ተገኝቷል፡፡ መስከረም 17 ቁፋሮ የተጀመረበት፣ መስቀሉ ተገኝቶ ከወጣ በኋላ በስሙ የተሠራው ቤተመቅደስ የገባበትና ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ቀን በየዓመቱ በስብሐተ እግዚአብሔርና በመንፈሳዊ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በዋዜማው መስከረም 16 ደመራ ይደመራል፣ ጸሎተ ወንጌል ይደርሳል፣ መዝሙርና ሽብሸባ ይቀርባል፡፡ በመጨረሻም ደመራው ይለኮሳል፡፡ ንግስት ዕሌኒ በመስከረም ማስቆፈር የጀመረችው የቆሻሻ ክምር ተንዶ መስቀሉ የተገኘው በመጋቢት 10 ቀን ቢሆንም በወርኃ ጾም (ያውም በዐቢይ ጾም) ተድላ ደስታ ማድረግ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን የተከለከለ በመሆኑ የመስቀሉን በዓል ማክበር የማይቻል ሆነ፡፡ በአበው ውሳኔም ቁፋሮው የተጀመረበትና ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት መስከረም 17 በደስታና በተድላ እንዲከበር ተደረገ፡፡ የመስቀሉ መገኝት ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ደስታ ቢሆንም በአገራችን በኢትዮጵያ ያለው ሃይማኖታዊና ባሕላዊ አከባበር በሌሎች ዘንድ የለም፡፡ አገራችንን ከሌሎች የተለየች ያደረጋትም ይህ የበዓል አከባበርና በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ገንዘብ ልናደርገው የቻልነው ግማደ መስቀል (የመስቀሉ የቀኝ ክንፍ ስባሪ) በአገራችን መኖር ነው፡፡ በአጼ ዳዊት ዘመን የመጣው ግማደ መስቀል መጀመሪያ በመናገሻ ከተማ ምዕራባዊ እርከን በምትገኘው አምባ (መናገሻ) ማርያም ገዳም ካረፈ በኋላ ለዘለቄታው እንዲቀመጥ የተወሰነው ሌላ ቦታ በመሆኑ በራዕይና በልዩ ልዩ ሁኔታ በተገለጸው ምልክት መሠረት በተፈጥሮ አቀማመጧ የመስቀል ቅርጽ ባላት በግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ገዳም ሊቀመጥ ችሏል፡፡ ከዚህ መንፈሳዊ ትርጉም ጎን ለጎንም የመስቀሉ ልጆች የሆኑት የኢትየጵያውያን ባሕላዊ የአከባበር ትውፊት ክርስቲያናዊ ትርጉምም ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትም፡፡ የደመራ በዓል በሚከበርበት ጊዜ ሁሉ ምዕመናን ተሰብስበው በየቋንቋቸው እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፡፡ ከጥቢ ጋር የተያያዘ ዝማሬ («ኢዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ» ዓይነት) በማቅረብ በዕልልታና በሆታ ደስታቸውን ይገልጣሉ፡፡ ደመራው በችቦ እሳት ተለኩሶ አመድ እስኪሆን ከተቃጠለ በኋላ ሕዝቡ አመዱን በጣቱ በመንካት ግንባሩ ላይ የመስቀል ቅርጽ ያበጃል፡፡ ትርኳሹን እየተሻማ ወደየቤቱ ይወስደዋል፡፡ ይህም የአከባበር ትውፊት ጥምቀተ ክርስትና በሌላቸው ብዙ ሕዝቦችም ዘንድ ሲፈጸም መታየቱ ቤተክርስቲያናችን ከጊዜ ብዛት በደረሱባት የተለያዩ ችግሮች ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን ለማስፋፋት ባልቻለችባቸው ቦታዎች የቀደሙ አበው ጥለውት የነበረው የወንጌል መሠረት በሕገ ልቡና ተጠብቆ መቆየቱን የሚያመለክት ነው፡፡ በሐፁረ መስቀሉ የጠበቀን በደመ መስቀሉ የዋጀን አምላክ ይክበር ይመስገን🙏
Hammasini ko'rsatish...
✝ “በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።” መዝሙር 65፥11 ✝ 🌼 እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም በፍቅር በጤና አደረሰን! አደረሳችሁ! 🌻 መልካም አዲስ አመት 2013 🌻
Hammasini ko'rsatish...
ጷግሜ 3 ቅዱስ እሩፋኤል 🙏 ቅዱስ እሩፋኤል ማን ነው ሼር??? እንግዲህ ከባህሪው ቅድስና ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦ የሚለይ እግዚአብሔር አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ፀጋ ከሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት መካከል በስልጣኑ ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) የሆነ በሹመት ፈታሔ ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ) ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን የሚያበራ) ሰዳዴ አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር) ፈዋሴ ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ)፣ አቃቤ ኆኅት (የምህረትን ደጁ የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን እንዲህ በማለት ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ» (ጦቢ.12÷15) ይህ የከበረ ታላቅ መልአክ ሰሙ የእብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት ውጤት ነው፡፡ ሩፋ ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን ኤል ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጠል ስመ አምላክ ነው ይህም « መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ….. ስሜ በእርሱ ስለሆነ . አታስመርሩት» (ዘጸ.23÷20-22) እዳለው ነው፡፡ ታዲያ ሩፋኤል የሚለው በጥምረት ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ የሚለውን ይተካል «በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው፡» (ሄኖ.6÷3) ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል(ዳን.4÷13 ዘጸ. 23÷20 መዝ. 90÷11-13 ) ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡(ዘካ.1÷12) በፈሪሀ እግዚአቤሔር እና በአክብሮተ መላእክት ያሉትን ድናቸዋል (ዘፍ.49÷15 መዝ.3÷37) « እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ መርጦ በወደዳቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የይቅርታ መላእክትን ያመጣል» (ሮሜ.9÷22) ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀመናብርትን ድንቅ ገቢር ተአምራቱን ያዩ ምዕመናን ……የወላድ ማኅፀን እንዲፈታ ስለተሸመ ከጌታ አዋላጅ ብትኖር ባትኖርም ሐኪም ሩፋኤል አይታጣም በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ የባላገር ሴቶች ሁሉ የመልአኩን መልክ አንግተው ማርያም ማርያም ይላሉ ማየጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ …… እያሉ ደጅ ጠንተው ይማጸኑታል፡፡ ዜና ግብሩን ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተናገረለት በመነሳት በቅዱሳን ላይ ድንቅ የሆነ እግዚአብሔር በመልአኩ አድሮ ያደረጋቸውን ተግባራት አበው የበረከት ምንጭ በሆነ ድርሳኑ ላይ አኑረው የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ሰጥተውናል፡፡ በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው ብዙ ድንቅ ሥራዎች መሀል ጥቂቶቹን እነሆ ~~~> በሥነ-ስዕሉ የተማጸኑ፣ በምልጃው ታምነው የጸኑ ቴዎዶስዮስንና ዲዮናስዮስን በገሃድ ተገልጾ ለንግስናና ለጵጵስና ክብር አብቅቷቸዋል፡፡ ~~~> የንጉስ ቴዎዶስዮስ ልጅም ጻድቁ አኖሬዋስም በፈጣሪው ህግ እየተመራ የሊቀ መናብርቱን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ አሳንጾ ሲያስመርቅ ለበለጠ ክብር ልቡን አነቃቅቶ ለታናሽ ወንድሙ ለአርቃዴዋስ የነጋሢነት ስልጣኑን ትቶ መንኖ በስውርና በጽሙና እዲኖር ረድቶታል፡፡ ~~~> በሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን አባቶች ለሊቀመናብርቱ ክብር በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያሳነጹትን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ በወደቡ አጠገብ በእስክንድሪያ ሳለች ጠላት ዲያቢሎስ አነዋውጾ ለምስጋና የታደሙትን ምዕመናን ሊያጠፉ አሣ አንበሪውን ቢያውከው ወደ ሊቀመናብርቱ ተማጽነው እርዳን ቢሉ ፈጥኖ ደርሶ በበትረ መስቀሉ (ዘንጉ) ገሥጾ ከጥፋት ታድጓቸዋል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍም እንደተገለጠው ~~~> ሣራ ወለተ ራጉኤልን አስማንድዮስ ከተባለው የጭን ጋንኤን ሲታደጋት የጦቢያን አባት የጦቢትን ዓይን አበራለት (መጽሐፍ ጦቢት) ከዚህም አልፎ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት (እንትኩይን) ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም ያበቃቸው ይኸው ፈታሔማኅጸን የልዑል እግዚአብሔር መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት ያሳድርብን አሜን !!!
Hammasini ko'rsatish...