cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳሰ ታደሰ ተከታዮች

ይህ channel የተለያዩ መረጃዎች ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉንም በአንድ ላይ ያካተተ ሲሆን ❖❖❖❖❖ 1/ ስለ ሀገር ጉዳይ 2/ ስለ ጠፈር ሳይንስ 3/ ስለ ኢትዮጲያ እና ስለ ኢትዮጲያውያን የቀደመ የነበረ ታሪክ 4/ በ 4ቱም አቅጣጫ ስላሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች እንመክርበታለን የዚህ Channel ዋነኛ አላማ ኢትዮጲያዊ የሆነ ወጣት መፍጠር ነው:: ✍✍ ኢትዮጲያ ትቅደም

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
257
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

'አቶ አበረ አዳሙ ህይወታቸው ያለፈው በድንገተኛ ህመም ነው' የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ህይወታቸው ያለፈው በድንገተኛ ህመም መሆኑ ለማወቅ ተችሏል። አቶ አበረ ፥ ዛሬ ጠዋት የህመም ስሜት ተሰማኝ ብለው ወደ ሆስፒታል ከሄዱ በኋላ ነው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሞታቸው የታወቀው። tikvahethiopia @hektaa
Hammasini ko'rsatish...
በሱማሌ ክልል ኮራኋይ ዞን ሸላቦ ወረዳ ሰላል ቀበሌ ማዕከል ትናንት ምሽት በጣለው ዝናብ ከ160 በላይ በግና ፍየሎች በደራሽ ጎርፍ መወሰዳቸው ተሰምቷል።
Hammasini ko'rsatish...
የጲላጦስ ፍርድ ተሸንፏል‼️ (ስንታየሁ ቸኮል፤ የህሊና እስረኛ ከቃሊቲ ወህኒ ቤት) ያጠፋነው ጥፋት የለም። የጠሉን ሃይሎች ግን አሉ። በግፍ የበደልነው ሰው የለም። የበደሉን ገዥዎች ግን ዛሬም በሥልጣን ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች ሕዝቡን በማደናገር በንፁሃን ዜጎች ላይ የበቀል ኢላማቸውን ለማስፈፀም የክፋት ክስ እያቀረቡ ስለ ትንሳኤውና ስለ ኢትዮጵያ መፃኢ ዕድል የሚናዘዙ የሀሰት ነብዮች ናቸው። ከሰው ማምለጥ ይቻል ይሆናል። ከባለትንሳኤው ግን ፈፅሞ አይቻልም። ልቦናን ማሞኘት ፈፅሞ አይሳካም፤ ሁሉን የፈጠረ ሁሉን ያውቃልና። መቼም አይሳካም። ንፁሃንን በሀሰት ክስ እያንገላቱ፤ በአደባባይ እየዘበቱ ስለ አንድነት ማውራትም ይከብዳል። ርግጥ ነው ትናንትም ይህ ተደርጓል። ዛሬም እየተደገመ ይገኛል። ሆኖም ነገ ያሉት ለጥቂት ጊዜ ቢቆዩ እንጂ ረዥም ርቀት አይጓዙም፤ ሀሰተኞች ናቸውና። የጲላጦስ ፍትሕም ከሽፏል። ተንኮታኩቷል። በክርስቶስ ድል ተደርጓል። ሀቀኞች የወህኒ አጥሩን ጥሰው ከገዥዎች ወጥመድ ነፃ የሚወጡበት ጊዜ ቅርብ ነው። በሚቀጥለው ምርጫ በአዲስ አበባ ትልቅ ሕዝባዊ አብዮት ይፈጠራል ብየ አስባለሁ። ሕዝቡ በነቂስ ተመዝግቦ፤ በነቂስ ድምፅ ሰጥቶ ካለበት እስራት ነፃ ይወጣል የሚል ተስፋ አለኝ። የጲላጦስ እስረኛ ሁሉ ነፃ ይወጣል። ያን ጊዜ በድል ያሸንፋል። ይህ እንደሚሆን ለአፍታም አልጠራጠርም። መልካም የትንሳኤ በዓል❗️ ©ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ
Hammasini ko'rsatish...
በመላው አለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሣኤው በዐል በሰላም አደረሳችሁ በዐሉን የደስታ የበረከት ይድርግልን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ህይወቱ አለፈ። አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በኮቪድ-19 ምክንያት በተወለደ በ50 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። አርቲስት መስፍን በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር። በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር። አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም ፣ በመንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ ፣ ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል። አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር። ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
Hammasini ko'rsatish...