cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ስለ ጤና

ይህ ቻናል የሀገራችን ሕዝብ በጤናው ዘርፍ ያለውን የመረጃ ክፍተት ለመሙላት በኢትዮጵያውያን ሀኪሞች የተጀመረ ቻናል ነው። አሁን ደሞ ያጋጠመንን ወቅታዊ ችግር በተመለከተ ለወገናችን መረጃ ይደርስ ዘንድ ቻናሉን ለቤተሰብ እና ጓደኛ ሼር ያርጉ። ለሀሳብና 👇👇አስተያየት ይሄን ይጠቀሙ @amaniona

Ko'proq ko'rsatish
Efiopiya12 030Til belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
165
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ሳይንቲስቶች አሁን ነገሮችን ያከበደባቸው ምክንያት ማሕበራዊ ርቀት ነው። በማሕበራዊ ርቀት ምክንያት ጉንፋንን የመሳሰሉ ቫይረሶች ከሰው ሰው መዛመታቸውን ለጊዜው ገታ አድርገዋል። አጥኚዎቹ ኮሮናቫይረስና ሪኖቫይረስ አንድ ላይ አድርገው በማኖር በጋራ መዝለቅ ይችሉ እንደሆን ለመለየት ሙከራ አድርገዋል። ኮሮናቫይረስና ሪኖቫይረስ በአንድ ጊዜ ከተለቀቁ ጉንፋን አምጪው ሪኖቫይረስ ይረታል። ሪኖቫይረስ ከኮሮናቫይረስ 24 ሰዓት ቀድሞ ከገባ ኮሮናቫይረስ ጭራሽ ድርሽ አያደርገውም። ኮሮናቫይረስ ቀድሞ ገብቶ ሪኖቫይረስ 24 ሰዓታት ዘግይቶ ቢገባ እንኳ ኮሮናቫይረስን ማስወጣት ይችላል። በፈረንጆቹ 2009 የተከሰተውን የስዋይን ፍሉ ወረርሽኝ አውሮፓ ውስጥ ቀዝቀዝ ያደረገው በተመሳሳይ ወቅት ተከስቶ የነበረው ሪኖቫይረስ እንደሆነ ይገመታል። ሌሎች ጥናቶች ደግሞ እንደሚያመላክቱት ሪኖቫይረስ የተጠቁ ሴሎች የመከላከል አቅማቸው እንዲጎለብት ያደርጋል። ይህ ደግሞ ኮሮናቫይረስ እንዳይዛመት ያደርገዋል። ነገር ግን ኮሮናቫይረስ የክረምቱ ወራት ካለፈ በኋላና የመከላከል አቅም ከተዳከመ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል። ወደፊት የሚመጡ የክረምት ወራት ምን ዓይነት ተፅዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ከአሁኑ መገመት ያዳግታል። ኮሮናቫይረስ ወደፊትም ቢሆን ስርጭቱን ሊቀጥል እንደሚችል እሙን ነው። ሌሎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ጠፍተው የነበሩ ቫይረሶችም ብቅ ብቅ ማለታቸው አይቀርም። ለዚህ ነው ተመራማሪዎቹ አሁንም የአፍና አፍንጫ ጭምብል መጠቀም ዋነኛ መላ ነው የሚሉት።
Hammasini ko'rsatish...
ጉንፋን የሚያሲይዙ ቫይረሶች የኮቪድ ቫይረስን ከሰውነት ውስጥ ማስወጣት ይችላሉ ይላሉ አጥኚዎች። (( ምንጭ ቢቢሲ)) አንዳንድ ቫይረሶች ሰውነታችን ላይ ጉዳት ለማድረስ ፉክክር ከእኩዮቻቸው ጋር ፉክክር ያደርጋሉ። የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ጉንፋን የሚያስከትለው ሪኖቫይረስ ኮሮናቫይረስን ይረታል። ነገር ግን ጥቅሞቹ ቆይታቸው አጭር ሊሆን ይችላል፤ ቢሆንም ኮሮናቫይረስ በሰፊው የሚሰራጭ ስለሆነ ኮቪድን መፎካከሩ አይቀርም ነው የሚሉት አጥኚዎቹ። አፍንጫችሁ፣ ጉሮሮዋችሁ አሊያም ሳንባችሁ ውስጥ ያሉ ሴሎችን በሥርዓቱ አንደተሰደሩ ቤቶች ውሰዷቸው። ቫይረሱ አንዴ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ በሩን ከፍቶ ሌሎች ቫይረሶች እንዲገቡ ያደርጋል አሊያም በሩን ዘግቶ ብቻውን መኖር ይጀምራል። ኢንፍሉዌንዛ በጣም ራስ ወዳድ ከሚባሉ ቫይረሶች አንዱ ነው። ይህ ቫይረሱ ብዙ ጊዜ ብቻውን ነው ሰውነታችን ላይ ጉዳት የሚያደርሰው። ሌላ ቫይረስ አያስጠጋም። እንደ አዴኖቫይረስ ያሉ ተዋህሲዎች ግን ሌሎች ቫይረሶችን ማስጠፋት ይወዳሉ። ሳርስ-ኮቭ-2 የተሰኘው ቫይረስ ነው ኮቪድን የሚያመጣው። ይህ ቫይረስ ከሌሎች ቫይረሶች ጋር ተቀላቅሎ መኖር ይችላል። (ከታች ይቀጥላል … 👇👇)
Hammasini ko'rsatish...
ዛሬ በተለምዶ የጨጓራ ህመም ስለሚባለው እና በ እንግሊዝኛው Gastritis or Peptic ulcer disease ስለሚባለው እንነጋገራለን እስቲ በመጀመሪያ በተለምዶ የጨጓራ ባክቴሪያ ስለሚባለው Helicobacter Pylori ወይም በምህጻረ ቃሉ H.Pylori ትምሽ እንበል። (ለሌሎች አሁኑኑ ሼር አድርጓቸው) ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ የሚባለዉ ባክቴሪያ የጨጓራ ህመም ባላቸውም በሌላቸውም ሰዎች የሚኖር ሲሆን አልፎ አልፎ የጨጓራ ኢንፌክሽን እንዲከሰት የሚያደርግ የባክቴሪያ አይነት ነው። ይህ ኢንፌክሽን በብዛት የሚከሰተዉ በልጅነት የዕድሜ ክልል ነዉ፡፡ ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ እና የትንሹ አንጀት የመጀመሪያ ክፍል (Deudnum) ቁስለት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሁነኛ መንስዔዎች አንዱ ሲሆን ኢንፌክሽኑ በአለማችን ከግማሽ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ አንደሚታይ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ የህመሙ ምልክቶች ብዙዎች የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ እንፌክሽን የተፈጠረባቸዉ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አይታይባቸዉም/ላይኖራቸዉ ይችላል ፡፡ የህመም ምልክቶችም ከታዩ የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ • የሆድ ላይ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት • ጨጓራዎ ባዶ ሲሆን የሚባባስ የጨጓራ ላይ ህመም • ማቅለሽለሽ • የምግብ ፍላጎት መቀነስ • በተደጋጋሚ ማስገሳት • የሆድ መንፋት • የክብደት መቀነስ (ለመቀነስ ሳይፈልጉ) መከሰት ናቸዉ፡፡ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚጠበቅብዎ መቼ ነዉ? የሚያሳስብዎና ቀጣይነት/በተደጋጋሚ የሚከሰት የህመም ስሜት ካለዎ እንዲሁም የሚከተሉት ምልክቶች ካሉ ባፋጣኝ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ • ከፍተኛና የማያቋርጥ የሆድ ላይ ህመም ካጋጠመዎ • የመዋጥ ችግር ካለዎ • ደም የተቀላቀለበት ወይም የአስፋልት ሬንጅ የመሰለ/ የጠቆረ ሰገራ ከወጣ • ቀይ ወይም የቡና አተላ የመሰለ ነገር ካስታወከዎ በአፋጣኝ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ ለኢንፌክሽኑ ሊያጋልጥዎ የሚችሉ ነገሮች • በተፋፈገ/በተጨናነቀ ቦታ መኖር • ንፁህ የዉሃ አቅርቦት በሌለበት መኖር • በማደግ ላይ ባሉ/ባላደጉ አገሮች/ የሚኖሩ ሰዎች፡ ንፅህናዉ በማይጠበቅ ሁኔታ ዉስጥ መኖር • የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ባክቴሪያል እንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች • የደም ምርመራ • የትንፋሽ ምርመራ/ዩሪያ ብሬዝ ቴስት • የሰገራ ምርመራ ናቸዉ፡፡ ሊደረግ የሚችል ህክምና የባክቴሪያዉ እንፌክሽን መኖሩ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያዎ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባክቴሪያዉን ሊያጠፋ የሚችሉ መድሃኒቶች ሊያዝልዎ ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ሊያደርሰዉ የሚችለዉ ጉዳት/ Complications ከጨጓራ ባክቴሪያ እንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶች • ቁስለት፡- የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራዎን መከላከያ እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ የጨጓራ አሲዱ ጨጓራዎ ላይ ቁስል አንዲከሰት ያደርጋል፡፡ • የጨጓራ ሽፋን እንዲቆጣ ያደርጋል- የጨጓራ ባክቴሪያ ጨጓራዎን በመቆጥቆጥ እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡ • የጨጓራ ካንሰር፡- የጨጓራ ባክቴሪያ ለተወሱ የጨጓራ ላይ ካንሰሮች መከሰት ዋነኛ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡ @yamangroup
Hammasini ko'rsatish...
ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል፡፡ ዋናው ነገር ውሃው ወደ በረዶ እሲኪቀየር መታገሱ ላይ ነው፡፡ አንተም ህይወቴ አሁን ተቦክቶ፤ አሁን ኩፍ ብሎ፤ አሁን ተጋግር፤ አሁን ካልቆረስኩት ሙቼ እገኛለው አትበል፡፡ ሁሉም ነገር የሂደትና የትዕግስት (የመጠበቅ) ጉዳይ ነው፡፡ ከእንቁላል ጫጬት እንደሚገኝ የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን ጫጬቱ እንቁላሉን ሰብሮ ሳይወጣ ተቻኩለክ አንተ ብትሰብረው የምታገኘው ሁለት እግር ያለው ጫጬት ሳይሆን ፈሰሽ አስኳልን ነው፡፡ የአብዛኞቻችን ችግር ምን እንደሆነ ታውቃለክ ወዳጄ መጠበቅ ሚባል ነገር አንወድም፡፡ ትዕግስት ብሎ ነገር አልፈጠረብንም፡፡ ለማንኛውም መልካምና ታጋሽ ሁናችሁ ዋሉ፡፡ 🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
Hammasini ko'rsatish...
[Forwarded from አትሮኖስ] ማንበብ የሚችል ሁሉ ያንብበው 3 ግዜ ትበላለህ ? ገላህን መሸፈኛ አለህ ? ቀን ደክሞህ ውለህ ማታ ምታርፍበት ጎጆ አለህ ? እንግዲያውስ እወቅ አንተ በአለም ላይ ካሉት ከ75% በላይ ሰዎች የተሻለ ኑሮ ላይ ነህ !! : ኪስህ ውስጥ አንዳድንድ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ምትገዛበትና ምትፈልግበት ቦታ ምትንቀሳቀስበት ገንዘብ ካለህ ? አንተ ከአለማችን 18% ሃብታሞች ውስጥ !! አንዱ ነህ ። ይቺን ቅጽበት ያለምንም ህመም በሙሉ ጤንነት እያሳለፍክ ነው? : በዚች ሰአት በአለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ከሚያጣጥሩትና አልጋ ላይ ሁነው ከሚሰቃዩት ውስጥ አይደለህምና ትልቁ እድለኛ ነህ : ይሄን መልእክት እያነበብክና እየተረዳኸው ነው ? ልብ በል በአለም ላይ ከ3 ቢሊዮን በላይ ማየት ማንበብ ማይችሉ እንዲሁም የአይምሮ ህመምቶኞች ይህን ማድረግ አይችሉምና ከነሱ ውስጥ አንዱ ባለመሆንህ ትልቁ እድለኛ ነህ !! : ስለሌለህ ነገር እያሰብክ ከማዘን ይልቅ ቆጥረህ በማጨርሰው የፈጣሪህ ስጦታ ደስተኛ ስትሆን ህይወትህ የበለጠ ቀላል ይሆናል!! ሁሌም ፈጣሪን እናመስግነው ፡፡ በኔበኩል ተመስገን ፈጣሪ :: ምንጭ ??
Hammasini ko'rsatish...
Thank u so much
Hammasini ko'rsatish...
​ሱሰኝነት እና እራስን ማታለል =================== ለበርካታ የሱስ ተጠቂዎች ከሱስ ለመላቀቅ በሚያደርጉት ጉዞ ትልቁ መሰናክል የሚሆንባቸው እራስን ማታለል ነው፡፡ እራሳቸውን ማታለል ትተው እውነታውን የተቀበሉ ግን ከሱስ የመላቀቅ ጉዞቸውን እንዳሳጠሩ በመስኩ ምርምር ለሚያደርጉ ተመራማሪዎች የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ ለምሳሌ ከሱስ የተላቀቀ አንድ ወጣት የምስክርነት ቃሉን ሲሰጥ አንዲህ ነበር ያለው " .... በመጨረሻም ለእራሴ ፍጹም ታማኝ ሆንኩ ለቤተሰቦቼ እና ለጓደኞቼ ኩራት እንዳልሆንኩ አምኜ ተቀበልኩ ... " ብዙ ጊዜ ምንም ችግር የለብኝም፣ ሱሰኛ አይደለሁም፣ ብዙ ተጠቃሚ አይደለሁም፣ ማንንም አልጎዳሁም፣ ለመዝናናት ያህል ነው የሚሉ ቃላት እራሳችንን ከምናታልልባቸው ውሸቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ከሱስ ለመላቀቅ በምናደርገው ትግል ውስጥ እራስን ማታለል ትልቁ ጦርነት ነው፡፡ ጦርነቱ ሱሰኝነትን በሚክዱ እና በሚቀበሉ ሁለት ኃይላት (አስተሳሰቦች) መካከል የሚደረግ ጦርነት ነው፡፡ ሱሰኝነትን የሚክደው ኃይል ካሸነፈ ከሱሰኝነት ለመላቀቅ የምናደርገው ትግል ውጤት አልባ ይሆናል፡፡ ሱሰኝነትን የሚቀበለው ኃይል ካሸነፈ ከሱሰኝነት ለመላቀቅ የሚደረገው ትግል በድል ይጠናቀቃል፡፡ እራስን ማታለል ህይወታችንን ሙሉ በሱሰኝነት እየተጓዳን መኖርን መምረጥ ነው፡፡ እውነታውን መቀበል ከባድ ቢሆንም ለአፍታ በሙሉ አስተዋይነት ከእራሳችን ጋር አንምከር፣ ለእራሳችን ታማኝ እንሁን፣ በመጀመሪያ እኛ ጋር ያሉ እወነታዎችን እንቀበል ከእዚህ በኋላ ምናልባት እርዳታ ካስፈለገንም እርዳታ ወደምናገኝባቸው ማዕከላት መሄድ እንችላለን፡፡ ###################### እናንተም ሌላውንም ይጠቅማል ብለዉ ካሰቡ ሼር በማድረግ መልካምነትን እናስፋፋ !!! @BiniGirmachew
Hammasini ko'rsatish...
👩🏽‍🦰👱🏽‍♀️የፀጉር መርገፍ👱🏽‍♀️👩🏽‍🦰 የፀጉር መርገፍ በጭንቅላታችን ላይ ያለን ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ አካላቶቻችን ላይ ያለን ፀጉር ያጠቃልላል፡፡ ለዛሬ የፀጉር መርገፍ መንስኤዎችን እና የፀጉር መርገፍን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገራለን፡፡ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? 👉🏾 በዘር፡- ወንዶች ላይ የፀጉር መሸሽ እና መመለጥ፤ ሴቶች ላይ ደግሞ የፀጉር መሸሽ እና መሳሳት 👉🏾 ሰውነታችንን በሚያጠቁ በሽታዎች፡- የታይሮይድ ህመሞች፣ የካንሰር ህመሞች 👉🏾 መድሃኒቶች፡- የካንሰር ህክምናዎች እጅግ በጣም የሚያጠብቅ ሹሩባ 👉🏾 የአእምሮ ጭንቀት 👉🏾 ለፀጉር እድገት የምንጠቀማቸው ግብአቶች ስለመንስዔው ማወቅ የፀጉር መርገፍን እንዴት መከላከል እንዳለብን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል፡፡ 🗒 ፀጉራችን ከመርገፉ በፊት የምናያቸው ምልክቶች...🗒 -የፀጉር መሳሳት -በአንዳንድ የፀጉራችን ክፍል ውስጥ ባዶ የሆኑ ቦታዎች መኖር -ፀጉራችንን በምናበጥርበት ወይም በምንታጠብበት ጊዜ የሚታይ የፀጉር መርገፍ የፀጉር መርገፍን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ማድረግ ያሉብን ነገሮች -ለፀጉር የምንጠቀማቸው ግብአቶች ከተፈጥሮ የተሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ -ሹሩባ በምንሰራበት ወቅት ላላ አድርጎ መሰራት -ጭንቀታችንን ለቅርብ ለምንለው ሰው ማውራት -በበሽታዎችና በመድሃኒቶች የሚመጡ የፀጉር መርገፎችን ከሃኪማችን ጋር በመነጋገር ማስተካከያዎችን ማድረግ -እንደ ፊታችን ሁሉ ፀጉራችንንም መንከባከብ ፀጉራችንን እንዴት መንከባከብ ይኖርብናል? 👉🏾ማንኛውም ነገር ለማደግ ግብአት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለፀጉርም ግብአት ያስፈልጋል፡፡ ፀጉራችንን በንፅህና መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚመቸንን ሻምፖ እና ኮንዲሽነር በመሞከር ፀጉራችን ላይ የሚመጣውን ለውጥ ማስተዋል፤ የምንጠቀማቸው ግብአቶች ሰልፌት የሌላቸው መሆኑን በእቃው ላይ የሚፃፈውን ንጥረ ነገር ማየት ይኖርብናል፡፡ 👉🏾ለፀጉራችን የሚስማማንን ቅባት መለየት፤ ፀጉር ከሰው ሰው ስለሚለይ እኛም ለፀጉራችንን የሚስማማንን ፀጉር በምናየው ለውጥ መወሰን ይኖርብናል፡፡ ለፀጉራችን ቢያንስ በ2 ሳምንት አንድ ጊዜ የተለየ እንክብካቤ ማድረግ ማለትም አቮካዶ፣ እርጎ፣ ቅቤን ፀጉር ላይ በመቀባት መንከባከብ ይኖርብናል። ምንጭ @siletenawot
Hammasini ko'rsatish...
Ethio Health Jobs® Ethio Health Jobs አላማው የጤና ባለሙያዎች በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ በቀላሉ በስራ ላይ እንዲሰማሩ ማስቻል ነው። ለማንኛውም አይነት ጥያቄና አስተያየት https://t.me/Gedi_M https://t.me/Ethiohealthjobs
Hammasini ko'rsatish...
Gedi

Keep the faith!