cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የሸህ ሠዒድ አህመድ ሙሰጠፍ የደረሰና የፈትዋ ቻናላ🌷🌷

https://t.me/joinchat/AAAAAFVkjGbrgfpiE2pFVw ۞ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡۞ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ የሸህ ሠዒድ አህመድ ሙሰጠፍ አድሰ ቹናል የደረሰና የፈትዋ ሼር አድርገው ለአህት ለውንድሞች

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
405
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

መውደድ ዒባዳህ ነው ❗ 🔸ዲናችን ላይ አንድ ነገር "መልካምና ጥሩ" የሚባለው ቁርኣንና ሐዲሥ እንዲሁም የመጀመሪያው የኢስላም ትውልድ መልካም ነው ያለው ነገር ብቻ ነው። በቁርኣንም ይሁን በሐዲሥ "መውሊድ አክብሩ" የሚል ትዕዛዝ አልተላለፈም፣ ሰሓባዎችም ይሁን ተከታዮቻቸው መውሊድን *አላከበሩም* ፣ አራቱም የዲን/የፊቅህ መሪዎች (እነ ኢማም አሽሻፊዒይ)ም ይሁን ስድስቱ የሐዲሥ ኪታቦች ጸሃፊዎች (እነ ቡኻሪይና ሙስሊም) መውሊድ ይከበር ብለው ያስተላለፉትና የተናገሩት ምንም ነገር የለም።ሰፊና ወይም ሚንሃጅ ላይ (ባቡል- ወይም ኪታቡል-መውሊድ የሚል ርእስ አለ እንዴ? ¡ ) 🔹ይልቅ መውሊድ የተጀመረው ምርጡ እና የመጀመሪያው የኢስላም ትውልድ ካለፈ በኋላ አራተኛው ክፍለ-ዘመን ላይ ነው።መሰራጨት የጀመረውና በስፋት የታወቀውም ሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ላይ ሲሆን ያሰራጩትና ያስፋፉት ሰሜን ዒራቅ አካባቢ የሚገኙ ክርስቲያኖች የዒሳን ልደት ሲያከብሩ ያዩ "ፋጢሚዩን" የሚባሉ ዲንን ለግል ዓላማቸው ይጠቀሙ የነበሩ፣ አንዴ እንኳ ሐጅ አድርገው መዲናንም ዘይረው የማያውቁ ከዲን የራቁ ባለስልጣኖችና ፖለቲከኞች ናቸው!። ይህም የታሪክ መጽሐፍት ላይ በሰፊው የተዳሰሰ ጉዳይ ነው!። ስለዚህም መውሊድ የነቢዩ ﷺ ውዴታ መገለጫ ነው ብሎ ማመን ትልቅ ስህተት ነው።የነቢዩ.ﷺ ውዴታ ዒባደህ ከመሆኑ አንጻር ነቢን ﷺበዚህ መልኩ መውደድ ይቻላል ብሎ መናገርና ማመን ዲኑ ላይ ህግ ማውጣት ነው፤ 🔸ኢስላም ላይ ደግሞ ያለ ግልጽ ማስረጃ ህግ ማውጣት አይቻልም። ሲጀምርም ከእንደዚህ ዓይነት ነገሮች አንጻር ዲኑ ምሉእ ነው። እኛ ዲኑን መከተልና የተደነገጉ ነገሮችን መተግበር እንጂ አዲስ ህግ የማውጣት መብት የለንም። ስለዚህ መውሊድ ሱንናህ እና ትክክለኛ የነቢዩ ﷺ ውዴታ መግለጫ ሊሆን አይችልም። 🔹"ደጋግ ቀደምቶች በሄዱበት ብቻ እንሂድ፣ ለነሱ የበቃቸው ለኛም ይብቃን፣ ከቆሙበት እንቁም፣ ባልዋሉበት አንዋል፣ ያላሉትን አንበል፣ እውነት የነቢዩﷺ ወዳጆች ከሆነን ልክ ሰሓባዎች ይወዷቸው በነበረው መልኩ እንውደዳቸው!፤ መቼም ከሰሓባዎች በላይ እኛ እርሳቸውን አንወድም! ታዲያ ሰሓባዎች ያላደረጉትን ነገር ለምን እናደርጋለን?!...? ከነሱ የበለጠ እናውቃለን? ወይስ የኛና የነሱ መንገድ ይለያያል?! 🔅("አደራችሁን የእኔን መንገድ/ሱንናህ ተከተሉ፣ አላህ የመራቸው የቅን ተተኪዎቼንም መንገድ ተከተሉ... አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ...") ይህ የነቢያችንﷺምክር ነው። ከልቡ እሳቸውን የሚወድ ምክራቸውን ይተገብራል፤ ሰሓባዎቻቸውን ይከተላል። ✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም@ዛዱል መዓድ 12/3/1442ዓ.ሂ -------------//-------------- 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/~~~~~~~~~~~~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
Hammasini ko'rsatish...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

Repost from N/a
አፈር ነው ትራሤ ▬▭▬▭▬▭ አፈር ነው ትራሴ የዘላለም ልብሴ ሚስጥሩን ተረጂ ባክሽ ይግባሽ ነፍሴ ከለሩ የማይቀይር አቧራና ጭቃ እሱ ነው ድራቤ ዱንያ ስታበቃ ቀለም ያልተቀባ ቀይም ይሁን ቢጫ አፈር ነው ትራሴ የኔ መጋጌጫ ~ አፈር ነው ትረሴ የኔ የነገ ጎጆዬ ዱንያን ስሰናበታት ስሆን ለብቻዬ ደፋ ቀናአልኩኝ ዱንያን ላጌጥበት አምሬ አጊጬ በዉበት ላይ ዉበት ሸክላ ተሰባሪ መሆኑን ዘንግቼ ተመላሽ አፈር ነኝ ከጭቃ ተሰርቼ ~~~ ባይገባኝ ነው እንጂ ሚስጥሩን ባላዉቀዉ ዛሬን ስሽበለበል ህይወቴን ሳደምቀዉ በዱኒያ ሳማርጥ ከለርና ቀለም አፈር ነው ትራሴ ተቀያሪ የለም ~ ትዋባለች ቤቴ!! ትዋባለች ቤቴ በአፈር ተገንብታ ትጠብቀኛለች ቀድማ ተዘጋጅታ አፈር ነው ድራቤ ከታችም ከላይም ብልጭልጯን ዱኒያ ተመልሼ አላይም ትኬቴ ሢቆረጥ መሄጃዬ ሲቃረብ የምተኛበት አፈር በልኬ ተሰርቶ በአፈር ይመረጋል ድንጋይ ተመስርቶ አፈር ነው ትራሴ የዘላለም ልብሴ ➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬
Hammasini ko'rsatish...
የሙሳና የፊርዐውን ታሪክ ክ/1
Hammasini ko'rsatish...
1የሙሳና_የፊርዐውን_ታሪክ_በኡስታዝ_አሕመድ_ኣደም.mp37.63 MB
🏝የሙሳና የፊርዐውን ታሪከ🏝 -ከታሪኩ የምናገኛቸው ጥቂት ጠቃሚ ነጥቦች ጋር ክፍል/2 የዕለተ እሁድ ሙሐረም 11/1439 ዓ .ሂ ልዩ ትምህርት 🔊በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎https://goo.gl/EJX5PH 🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸 🌐https://telegram.me/ahmedadem
Hammasini ko'rsatish...
🏝የሙሳና የፊርዐውን ታሪከ🏝 ክፍል/1 የዕለተ ቅዳሜ ሙሐረም 10/1439 ዓ .ሂ ልዩ ትምህርት 🔊በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎https://goo.gl/zpuMBd 🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸 🌐https://telegram.me/ahmedadem
Hammasini ko'rsatish...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

(2) የሙሳና የፊርዐውን ታሪክ-1.mp310.61 MB
🔸ሱረቱል ዩሱፍ በቃሪእ አፊፍ ታጁ 🍃@dawatulanbiya🍂
Hammasini ko'rsatish...
1.86 MB
መልካም ቀደምቶች (ሠለፎች) በቢድዐ ሰዎች ላይ የነበራቸው አቋም እንዴት ነበር?! : [✍🏻በኢብን ሽፋ 7/6/1439 ዓ.ሂ የተፃፈ ከተወሰነ ማሻሻያ ጋር በድጋሚ የተፖሰተ] : አንተ እውነተኛ የሀቅ ተከታይ ከሆንክ ስለ ቢድዐ ሰዎች ጠንከር ያለን ንግግር ስትሰማና ስታነብ አትበርግግ!። ቀደምቶችህ በቢድዓ ሰው ላይ የሚከተለው አይነት አቋም ነው የነበራቸው፣ እውነት አንተ ደጋግ ቀደምቶችን የምትከተል ከሆንክ አትደናበር። በይሀቂይ (ረሂመሁላህ) ስለ ኢማሙ ሻፊዒይ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ:- “ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁላህ) በአፈንጋጮችና በቢድዓ ሰዎች ላይ ጠንካራ ነበሩ፣ በነርሱም ላይ ያላቸውን ጥላቻቸውንና ኩርፊያቸውን ግልፅ ያወጡት ነበር።" [መናቂቡ ሻፊዒይ ጥራዝ 1/469] ኢማሙ አህመድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “አንድ ሰው በሙብተዲዕ ላይ ሰላምታን ካቀረበ እሱ ያንን የቢድዐ ሰው ይወደዋል ማለት ነው።" [ጦበቃቱል ሀናቢላ ጥራዝ 1/196] ይህ የኢማሙ አህመድ ንግግር የቢድዐ ሰዎችን መውደድ እንደማይፈቀድ አመላካች ነው። ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይሉ ነበር:- “አላህ ሆይ! እኔ ዘንድ ለቢድዐ ባለቤት ውለታን አታድርግለት፣ (ውለታ ካለብኝ) ልቤ ይወደዋልና።" [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሉሱንነቲ ወልጀማዐህ ጥራዝ 1/140] የቢድዐ ሰው ውለታ ያለበት እውነታውን ቢያውቀውም መናገር ይከብደዋል። ይህ ደግሞ አላህ ይጠብቀንና በተጨባጭ የታየ ነገር ነው። በቢድዐ ሰው ላይ ውለታው እያለበት ወደ ሌላ ጥቅማዊ ቅሬታ ውስጥ ሳይገቡ ሀቁን በትክክል ረግጦ በመናገር የሚጓዝ ሰው እጅግ በጣም ቆራጥነት የሚታይበት ሊሆን ይችላልና መልካም ነገር ይከጀልለታል። ፉደይል ኢብን ዒያድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “የቢድዐ ባለቤቶችን የወደደ ሰው አላህ ስራውን አበላሽቶበታል፣ የእስልምናን ብርሃንም ከልቡ አውጥቶበታል።" [ሸርሁ ሱንነህ ሊልበርበሃሪይ 138–139 አል ኢባነህ ሊብኒ በጣህ ጥራዝ 2/460] ከመውደድ አልፎ ለነሱ መከታ የሚሆነው ደግሞ ከነሱ የከፋ አደጋ ነው!። ምክንያቱም ውዴታ አንዳንዴ ወደ ውጭ ጎልቶ ላይወጣበት ይችላል፣ ለነሱ ከተከላከለና መከታ ከሆነ ግን ከባድ አደጋ ነው!። ዐብዱላህ ኢብኑ ዳውድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “ከሀቅ ምልክቶች ሀይማኖትን በስሜት የሚይዝን ሰው መጥላት ነው፣ ሀቅን የወደደ ሰው በእርግጥም የስሜት ባለቤቶችን/የቢድዓ ሰዎችን መጥላት ግዴታ ሆኖበታል።" [ሲየር አስሰለፍ አስሷሊሂን ሊተይሚይ ጥራዝ 3/1154] በዚህን ጊዜ ሰለፊይነት ስም ብቻ እስኪመስል ከቢድዐ ሰዎች ጋር ሊኖረን የሚገባው አቋም ወርዷል። እንዲህ ያሉ የቀደምቶችን ከባባድ አቋምም "በድሮ ቢድዓቸው ጠንካራ በነበሩ ሰዎች ላይ የነበረ አቋም ነው እንጂ የዚህን ጊዜ የቢድዓ ባለቤቶችን አይመለከትም" በማለት በድፍረት ያለ ኀፍረት የሚናገር ሰለፊይነትን ሞጋች ነው ያለው። የኔ ጥያቄ:- እንዲህ ያሉትን የቀደምቶችን አቋም ያብራሩ (ሸርህ) ያደረጉት ዓሊሞች የአንተን ያህል አልገባቸውም ነው??? የአሁን ጊዜ የቢድዓ ሰዎች ልዩነታቸው ምኑ ላይ ነው??? የጀህሚያዎችና የሙዕተዚላዎች ውጤቶች አሽዓሪውና አሕባሹ የለም? ከላይ የጠቀስኳቸውንና ኸዋሪጅን ጨምሮ ሁሉንም አይነት ፊርቃ የሚያካትተው ኢኽዋኑ የለም? እስቲ ንገረኝ በፈጠረህ እነዚህ ዐቂዳቸው ከድሮዎቹ ምኑጋ ነው የተለየብህ? በእርግጥ አንድ ነገር ያስማማናል፣ የአንተ አቋም ከደጋግ ከቀደምቶች ተለይቶ ተሸርሽሮብህ ከሆነ እውነትህን ነው። በተረፈ ግን አታታልል!፣ ጠንቅቀህ እያወቅክ ሀቅን በባጢል አትደባልቅ። የፈጠረህ የልብህን ምስጢር ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቀው አላህ እንዲህ ይላል:- ﴿وَلا تَلبِسُوا الحَقَّ بِالباطِلِ وَتَكتُمُوا الحَقَّ وَأَنتُم تَعلَمونَ﴾ البقرة ٤٢ “እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡” አልበቀረህ 42 #Join ⤵️ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Hammasini ko'rsatish...
[ኢብን ሽፋ Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

የሸይኽ ሙሀመድ ቢን አማን አልጃሚይ (ረሂመሁላህ) ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ድንቅ ምክር!! الشيخ العلم د. محمد أمان الجامي – رحمه الله– : إني ناصح لكم أيها الشباب أن تتريثوا فيما تسمعون وفيما تقرؤون وبمن تتصلون، وعليكم أن تكونوا حول كبار علمائنا من مشايخنا أهل العلم والتجربة والتريث والتأني في الأمور قرة عيون السلفية بالأجوبة الجامية صـ ( 362 ) ➡️ ሸይኽ አማን ጃሚ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ :– " እናንተ ወጣቶች ሆይ እኔ በምትሰሙት ፣ በምትቀሩት ፣ በምትገናኙት ሰው ላይ ረጋ እንድትሉ እመክራችኋለሁ ። ከትላልቅ ዑለሞቻችንና መሻኢኾቻችን እነዚያ ልምድ ያካበቱ ፣ በነገሮች ላይ እርጋታ ያላቸው ከእነሱ ጎን እንድትሆኑ አደራ " ። http://t.me/bahruteka
Hammasini ko'rsatish...
[ኢብን ሽፋ Ibn Shifa]

የሸይኽ ሙሀመድ ቢን አማን አልጃሚይ (ረሂመሁላህ) ዘመን ገሻጋሪ የሆነ ድንቅ ምክር!! الشيخ العلم د. محمد أمان الجامي – رحمه الله– : إني ناصح لكم أيها الشباب أن تتريثوا فيما تسمعون وفيما تقرؤون وبمن تتصلون، وعليكم أن تكونوا حول كبار علمائنا من مشايخنا أهل العلم والتجربة والتريث والتأني في الأمور قرة عيون السلفية بالأجوبة الجامية صـ ( 362 ) ➡️ ሸይኽ አማን ጃሚ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ :– " እናንተ ወጣቶች ሆይ እኔ በምትሰሙት ፣ በምትቀሩት ፣ በምትገናኙት ሰው ላይ ረጋ እንድትሉ እመክራችኋለሁ ። ከትላልቅ ዑለሞቻችንና መሻኢኾቻችን እነዚያ ልምድ ያካበቱ ፣ በነገሮች ላይ እርጋታ ያላቸው ከእነሱ ጎን እንድትሆኑ አደራ " ። http://t.me/bahruteka

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.