cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዲያቆን ወልደ ሰንበት መጣጥፎች ፣ ትምህርቶች

ይህ መንፈሳዊ ቻናል ትምህርቶች ፣መጣጥፎችን ፣ወጎች የሚተላለፉበት ነው። እንዲሁም የበአላት ወረቦች ፣ምስባክ ያገኙበታል ይህ ቻናል በባለቤቱ የተከፈተ ቻናል ነው

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 135
Obunachilar
-224 soatlar
-67 kunlar
-1630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🕊 [ † እንኳን ለእናታችን ቅድስት ሰሎሜ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል እና ለበዓለ ቅዱስ ሜሮን በሰላም አደረሳችሁ † ] † 🕊   ቅድስት ሰሎሜ   🕊 † የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ከመረጣቸው ፴፮ [36] ቱ ቅዱሳት አንስት የቅድስት ሰሎሜን ያሕል ያገለገለ: ክብርም የተቀበለ የለም:: ከእመቤታችን ቀጥሎ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ ያልተለየች ብቸኛዋ ሰው ናትና:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ቅድስት ሰሎሜ ከነገደ አሮን በሚመዘዝ የዘር ሐረግ እናቷ ማርያም ትባል ነበር:: አባቷ ደግሞ ክቡር አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ነው:: ቅድስት ሰሎሜና እመቤታችን የእህትማማች ልጆች ናቸው:: ቅድስት ኤልሳቤጥም ዝምድናዋ ተመሳሳይ ነው:: የ ፫ [3] ቱ እናቶች [ሐና: ማርያምና ሶፍያ] የማጣትና የሔርሜላ ልጆች በመሆናቸው እህታማቾች ናቸው:: "ጥቂት ነገሮች ስለ እናታችን ቅድስት ሰሎሜ " ፩. የአረጋዊ ዮሴፍ ልጆችን [ወንድሞቿን] እንደሚገባ አሳድጋለች:: ፪. ጌታችን በተወለደ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረች:: የእመቤታችን መውለድ እንደ ሌሎች ሴቶች መስሏት ድንግልን ስለ ነካች እጆቿ ተቃጥለዋል:: ምሕረት ጠይቃ ጌታን ስትዳስሰው ግን ተፈወሰች:: ፫. እመ ብርሃን ስደት ስትወጣ ቅድስት ሰሎሜ "ባንቺ የደረሰ በኔም ይድረስ" ብላት አብራ ተሰዳለች:: ረሐቧን ተርባለች:: ጥሟን ተጠምታለች:: በሐዘኗ አዝናለች:: አብራት አልቅሳለች:: ለ፫ [3] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ያን ሁሉ ጭንቅ አብራ ተካፍላለች:: ድንግል እመቤታችን እሾህ ሲወጋት ታወጣላት: እንቅፋት ሲመታት ደሟን ትጠርግላት ነበር:: ባለቤቱ አድሏታልና ጌታችንን አንዴ በጎኗ ታቅፈው: አንዴም በጀርባዋ ታዝለው: አንዳንዴም ትስመው ነበር:: "መለኮትን ማቀፍ: ማዘልና መሳም ምን ይደንቅ! ለቅድስት እናታችን አንክሮና ምስጋና በጸጋ ይገባል!" ከስደት ከተመለሱ በሁዋላም ለ፳፭ [25] ዓመታት ከጌታና ከድንግል ማርያም ጋር ኑራለች: አገልግላቸዋለችም:: ጌታችን ተጠምቆ ማስተማር ሲጀምርም ተከተለችው:: እርሱም ከ፴፮ [36] ቱ ቅዱሳት አንስት ደምሯታል:: ለ፫ [3] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ከዋለበት ውላ: ካደረበት አድራ ተምራለች:: እንደሚገባም አገልግላለች:: አምላክ ሲሰቃይ ከጐኑ: ሲሰቀልም ከእግረ መስቀሉ ነበረች:: ብርሃነ ትንሳኤውም ከተገለጠላቸው ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: ከመድኃኔ ዓለም ዕርገት በሁዋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላ በሐዋርያት ዘመን የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን አገልግላለች:: እድሜዋ ምን ቢገፋ ለወንጌልና ለማዕድ ተግባር ተግታለች:: ወገኖቿ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋት በዚህች ዕለት በመልካም ዕረፍት ወደ ፈጣሪዋ ሔዳለች:: † 🕊   ቅብዐ ሜሮን   🕊 † ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ የምንከብርበትን ቅብዐ ሜሮን አፍልቆልናል:: በስደቱ ጊዜ ጌታችን በምድረ ግብፅ ደክሟቸው ካረፉበት ቦታ ላይ የዮሴፍ በትርን ቆራርጦ: በኪነ ጥበቡ ውሃ አፍልቆ: አጠጥቶ: ትልልቅ ዛፎች አደረጋቸው:: እዛውም ላይ ቅብዐ ሜሮንን አፈለቀ:: ቅብዐ በለሶንም ይሏቸዋል:: በሁዋላም የጌታችን ወዙ በታጠበ ጊዜ ተቀላቅሎበታል:: ዛሬ እኛም: ንዋየ ቅድሳትም የምንከብረው በዚሁ ቅዱስ ቅብዐት ነው:: አምላካችን እግዚአብሔር በቅድስት ሰሎሜ ላይ ያሳደረውን ጸጋ በእኛም ላይ ያሳድርልን:: 🕊 [ † ግንቦት ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. እናታችን ቅድስት ሰሎሜ [ከ ፵፮ [36] ቱ ቅዱሳት አንስት] ፪. ታላቁ አባ ሔሮዳ ሰማዕት ፫. ፴ ሺህ "30,000" ሰማዕታት [የአባ ሔሮዳ ማሕበር] ፬. ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት ፭. ቅዱስ ቅብዐ ሜሮን [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት ፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት ፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት ፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ ፭. አቡነ አቢብ [አባ ቡላ] ፮. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ " ሰንበትም ካለፈ በሁዋላ መግደላዊት ማርያም: የያዕቆብም እናት ማርያም: ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ:: ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በሁዋላ ወደ መቃብር መጡ . . . ወደ መቃብርም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል አዩና ደነገጡ:: እርሱ ግን አትደንግጡ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ:: ተነስቷል: በዚህ የለም . . . አላቸው:: " [ማር.፲፮፥፩-፰] (16:1-8) [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
[ ስንክሳር ግንቦት - ፳፭ - ] .mp33.18 MB
[ ስንክሳር ግንቦት - ፳፬ - ] .mp33.01 MB
🕊 [ † እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ] የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ [ማቴ.፪፥፩-፲፰] (2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ፪ [2] ዓመቱ የጥበብ ሰዎች [ሰብአ ሰገል] ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት:: ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፩ [1] አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች:: ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች:: - የአምላክ እናቱ - እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች:: - ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች:: - የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች:: - የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች:: - የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች:: - እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች:: ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና:: መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ? ፩. ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና [ኢሳ.፲፱፥፩ 19:1, ዕን.፫፥፯ 3:7] ፪. ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ [እሥራኤል]: ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና:: ፫. ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: [ኢሳ.፲፱፥፩] (19:1) ፬. የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ:: ፭. ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: ፮. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና ፯. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው:: ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን:: 🕊 [ † ግንቦት ፳፬  [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ ፪. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ ፫. ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት ፬. ቅዱስ አልዓዛር ካህን [የአሮን ልጅ] [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፪. ቅዱስ አጋቢጦስ [ጻድቅ ኤዺስቆዾስ] ፫. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፬. ቅዱስ ሙሴ ፀሊም ፭. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ ፮. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ ፯. "፳፬ 24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ሱራፌል] ፰. አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ [ኢትዮዽያዊ] " ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: " [ራዕይ.፲፪፥፬-፯] (12:4-7) [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
[ ስንክሳር ግንቦት - ፳፫ - ] .mp34.41 MB
[ ስንክሳር ግንቦት - ፳፪ - ] .mp33.88 MB