cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የቅዱስ ዮሴፍ እና የአሳይ ት/ቤት ግቢ ጉባኤ

የቅዱስ ዮሴፍ እና አሳይ ትምህርት ቤት ግቢ ጉባዔ ኦፊሻል ቴሌግራም ቻናል፡፡ ተቀላቅለው አብረን የእግዚአብሔርን ቃል እንማር፡፡

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
257
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል። እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል። የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና። በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል። ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።” ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ። የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ። በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)። በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል። አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163)
201Loading...
02
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።» ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
392Loading...
03
✍✍ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት) ✍✍✍✍✍✍✍✍ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ? 👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል። ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ። 👉 ሰንበትን ሊያጸናልን የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ 👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። "ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ" (ዮሐ20:29) የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን     ...............ይቆየን...........
511Loading...
04
''እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ጥቂት ነው የሚሠጥህ ግን ብዙ ነው!'' (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
482Loading...
05
አንድ ደቂቃ ወስደው ያንብቡት ድንቅ ምክር ነው (ለሌሎች ያጋሩት) በሠርጉ ዋዜማ እናት ወንድ ልጇን ምን አለችው? የኔ ልጅ አሁን አንተ ትልቅ ሰው ነህ። ነገ ሌላ እናት ታገኛለህ አዲስ ሰው ምግብህን ያበስላል ምስጢርህን ይካፋላል እኔ ከእንግዲህ ይህንን አላደርግም አዲሷን እናትህን ውደዳት። እሰከመጨረሻው በእጆቿ ላይ ከመተኛትህ በፊት ምክሬን ልስጥህ! አንድ ቀን ከአባትህ ጋር እየተነጋገርን ነበር በጣም በስሜት ሆነን እንጯጯህ ነበር በቁጣ ስሜት ውስጥ ሆነን ሳላ እኔ በድንገት አንተ የማትረባ ስለው በጣም ተሸማቀቀ ወደ እኔ እየተመለከተ እንዴት እንደሱ ትያለሽ ? ሲለኝ ቀበል አድርጌ አዎ አንተ የማትረባ ሞኝ እብድ ብዬ ያለ የሌለውን የስድብ ናዳ አወረድኩበት ታድያ እሱ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? እሲቲ ገምት? ሊደበድበኝ ይችል ነበር ግን እጆቹን ሳያነሳ ምንም ሳይለኝ መዝግያውን አላትሞ ወጥቶ ሄደ። ልጄ አባትህ ቢመታኝና ፊቴን ቢያበላሸው አንተ ዛሬ በተበላሸው ፊቴ ታዝንብኝና ታፍርብኝ ነበር እሱንም እንደ አባት አትቆጥረውም ሁሌ ታዝንበት ነበር የምትኮራበት አባት አይሆንህም ነበር። ልጄ ሚስትህን እንዳትመታት! ብትሰድብህም ብታዋርድህም ከአጠገቧ ለግዜው ዞር በል ኋላ ላይ ነገሮች ይስተካከላሉ። እንግዲህ ሚስትህ ስታበሳጭህ ይህንን የእኔን ታሪክ አስታውስ! ካቋረጥኩበት ልቀጥል...... ልክ ብቻየን ትቶኝ እንደሄደ ስለሰደብኩት በጣም ፀፀተኝ .. ታድያ የተጣላን ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ አብረን አደርን በሚቀጥለው ቀን ማድረግ የሚገባኝን ሁሉ አድርጌ ይቅርታ ጠየኩት እርሱም ተቀበለኝ .. ታድያ የዛን ቀን ምን አደረኩ መሰለህ የሚወደውን ምግብ አዘጋጅቼ ስሰጠው ደስ እያለው በላ ካዛ ቀን በኋላ ከአፌ ክፉ ቃል አልወጣኝም ለእሱ ያለኝ ክብር እስር እጥፍ እየጨመረ መጣ። አንድ በጣም አስፈላጊ ነገር ማድርግ ያለብህ ነገር አለ። ሚስትህን። በደንብ አድምጣት ጋሻና መከታ ሁናት በጭንቅ ግዜ ከጎኗሁን ጓደኞችህ ቢጠሉዋትም ያንተ ንግስት እንደሆነች አሳያቸው ታውቃለህ አጎትህ አይወደኝም ነበር አባትህ ግን ስለኔ ያለውን አሳምኖት ሓሳቡን አስለውጦት እኔን ይደግፈኝ ነበር። ልጄ.. . አንድ ቀን አባትህ 3 ሰዎች ወደ ቤት ጋብዟቸው ነበር አንደኛው የስራ አለቃው ሲሆን ሁለቱ ጓደኞቹ ነበሩ ምግብ አብስዬ ሁሉን አሟልቼ ካቀረብኩ በኋላ አንድ ነገር ረሳሁ ጨው አልጨመርኩም ነበር በጣም አፈርኩኝ አባትህ ወድያው ምግቡን እንደቀመሰ ወደኔ ተመልክቶ ወደ እነሱ ዞር አለና በጤና እክል ምክንያት ከወር በፊት ምግብ ውስጥ ጨው እንዳትጨምር አዝዣት ነበር ብሎ ሲስቅ ሁሉም ሳቁና እባክሽ ጨው ስጭን ብለው ሁሉም እንደፍላጎቱ ጨምረው ተመገቡ። እንግዶችም በሄዱ ግዜ ተንበርክኮ ጌታ ሆይ ስለዋሸው ይቅር በለኝ አለ። ሚስትህ ልክ እንደ ህፃን ናት አንዳንዴ ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባት አታውቅ ይሆናል ነገር ግን ተነስተህ ስለ እሷ ስትል ተናገርላት። ልጄ.. . ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ልንገርህ.. .ወሲብ ጥሩ ነገር ነው።ሚስትህ በወሲብ የምትደሰተው ካንተ በላይ ከሆነ አይግረምህ። ታውቃለህ አንዳንድ ቀን እኔን በጣም ያስፈልገኛል እሱ ግን እስከዚህም ይሆናል ሌላ ግዜ ደግሞ እሱን በጣም ያስፈልገዋል እኔ ግን እስከዚህ እሆናለው... አንድ ማውቅ ያለብህ ነገር እራስ ወዳድ አትሁን አንደኛው ሌላኛውን መረዳት አለበት። አስቸጋሪ ግዜያት ይመጣል አባትህን ለመደገፍ ስል ሁለት ቦታ ስራ እሰራ ነበር  ታድያ አንድ ቀን ምሽት በጣም ደክሞኝ ወደ መኝታ ክፍል ሳመራ እሱ በጣም ተነቃቅቶ ጠበቀኝ ግን አልተቃወምኩም ቢደክመኝም ፍላጎት እንዳለው ሰው ሆንኩለት ነገር ግን እንደጠበቀው ስላልሆንኩለት ፊቴን አይቶ በመረዳት ምን ሆነሻል? አለኝ ምንም አልኩት ከዚያ ስለተረዳኝ እቅፍ አድርጎ የመኝታ ታሪኮችን/bed time story/ እየነገረኝ እንቅልፍ ወሰደኝ ... ወሲብ የሁለት ሰው የእዕምሮና የአካል ዝግጁነት ይጠይቃል። አንዳንዴ ሚስትህን በደንብ ተመልከታትና ተረዳት። ልጄ.. .ከሚስትህ ጋር የትም መሄድ ልማድ አድርገው ከስራህ ውጭ ሰትሆን ከሚስትህ ጋር አሳልፍ አንድ ሰው ከሚስትህ ውጭ ብቻህን ቤቱ እንድትመጣ ከጋበዘህ ተጠንቀቅ ብልህ ሁን። እኔን እንደምትወደኝ ችግሮችህን እንደምትነግረኝ አውቃለው አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮአል። ከነገ በኋላ ሚስትህ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባት። ከእሷ ጋር ስትጋጭ ወድያው ወደኔ አትሩጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ታገሳት ከዚያ ነገሩ ጋብ ሲል ተነጋገሩ ፀልዩበት ስለ እሷ ለሌላ ሰው ለማንም አትናገር ። በመጨረሻም በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣችው ጠይቁኝ ጥሩ ትዳር እንደሚኖርህ ተስፋ አደርጋለው አንተ ምርጥ ልጄ ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ ወደ ፈጣሪ ፀልይ ሁሌም የእርሱን እርዳታ እሻ!!! #Anani Moti Like, Comment, Share.Lot's of thanks. @beteafework         @beteafework @beteafework         @beteafework @beteafework         @beteafework
492Loading...
06
"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል፤ የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ በአንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡" #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
380Loading...
07
“ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምስሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” (ቅዱስ እንድርያስ ዘቀርጤስ)
430Loading...
08
#የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር በቤተ ክርስቲያናችን ትዉፊት መሰረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ፣ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡ እኛም ከእንደነዚህ ዓይነት አሰናካዮች በመለየት ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረዉ እና ራሳችንን መልዕክቴ ነው፡፡ ለዚህም የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡
410Loading...
09
#ልደታ_ለማርያም (#ግንቦት_1) በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና። እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ። ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው። በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው። በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
460Loading...
10
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው። በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።" የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን (Orthodox and Bible fb page)
471Loading...
11
#እመቤቴ_ሆይ፤ ባትወለጂ እግዚአብሔርን በሥጋ ተገልጦ እናየው ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ ፍቅር፣ ምሕረት እና ፍጹም መልካምነት በእውነት ሥጋን ነሥተው በክርስቶስ እናይ ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ንጽሕና በሰውነት ተገልጦ እናይ ነበርን? በፍጹም። ይኸውም ያንቺ የቅድስና ሕይወት ነው። ከሊቃውንት አንዱ የአንቺ አንዲቷ ትንፋሽ ከቅዱሳን ሁሉ ገድል፣ ምስጋና እና ምልጃ ሁሉ የከበረች እንደሆነች ተናገረ። ይህ ሁሉ ከሰው ኅሊና ስለሆነው ንጽሕናሽ ነው። በዘወትር ቋንቋችን አንቺን "ንጽሕት" ብቻ ማለት ንጽሕናን ማጉደፍ ይሆናል እኮን። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያንቺ ንጽሕና እና ቅድስና በቃል ከመነገር ይልቅ፤ በዝምታ የልብ ለኆሳስ ቢመሰገን የተገባ ነው። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔር ትእዛዝ በምልዓት ሲፈጸም፤ ሕጉ ሲደረግ ምን እንደሚመስል በምን እናውቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የክህነት ንጽሕና በምን ይጠበቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የንስሐ መንገዱን ማን ያመለክተን ነበር? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ መታዘዝ፡ የእኛን ዐመጸኛነት እንዴት ይገስፀዋል? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ ትሕትና፡ የኔን ትዕቢት ይሰብረው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል? ስለ አምላካዊው ኀይሉ፤ ጠላት ሰይጣን ለልጅሽ ይገዛል። የልጅሽ የክርስቶስን ስም ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። አንቺ ግን በትሕትናሽ ሰይጣንን አራድሽው። እርሱ መንፈስ ሲሆን "ሥጋ ለባሽ" ብሎ በሚንቃት "በአንዲት ሴት" መሸነፉ ሁልጊዜም ግራ ይገባዋል። ስምሽን የሚጠሩ ሰዎች ፊትም መቆም አይቻለውም። ስምሽን ሲጠሩ ኀይላቸውን ትተው ኀይልሽን ይይዛሉና። ይኸውም እግዚአብሔር ነው። ስምሽን ሲጠሩ ትዕቢታቸውን ጥለው በትሕትናሽ ይጋረዳሉና። ስምሽን ሲጠሩ ጥርጣሬያቸውን በሃይማኖትሽ ያሸንፋሉና። በንጽሕና ቀሚስሽ ስለ እድፈታቸው ከሚከሳቸው ይጋረዳሉና። ሰይጣን ከእነርሱ ዘንድ አይቀርብም። እመቤቴ ሆይ አንቺ ባትወለጂ ከመልካሙ ሁሉ በአፍአ በቀረን ነበር እኮን። አሁንም "መጥተን" ሳለን የቀረን አታድርጊን። እኛ ራሳችንን ብንተው፤ አንቺ አትተዪን። እኛ ብንርቅ፡ አንቺ አትራቂን። እኛ ብንዘነጋ፡ አንቺ አትዘንጊን። መሐርነ፡ ወተሣሃልነ! (ምንጭ፦ Micky Asres) #ይቀላቀሉ @beteafework        @beteafework @beteafework        @beteafework @beteafework        @beteafework
421Loading...
12
ክርስቶስን መውደድ እንዴት? (በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) አንድ በጣም የምንወደው እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ እጅግ በጣም ከመደሰታችን የተነሣ የምናደርግለት ኹላ ሊጠፋብን ይችላል፡፡ እንደምንወደው፣ እንደናፈቀን እንነግሯለን፡፡ ከዚያም በላይ የሚወደውን እናቀርብለታለን፡፡ ባይኖረን እንኳን ስላላቀረብንለት እናዝናለን፡፡ ያለንን፣ ቤት ያፈራውን ግን እናቀርብለታለን፡፡ ስለምንወደውና ስለናፈቀን ርሱን የሚያስከፋ ነገር ምንም አናደርግም፡፡ ብናደርግም ወዳጃችንን ኾን ብለን ለማስከፋት ብለን የምናደርገው አይደለም፡፡ እንወዷለን የምንለው እንግዳችንን ትተን ሌላ ሥራ አንሠራም፡፡ በቃላት ብቻ እወድኻለኁ ብንለው፥ ነገር ግን በተግባር እንግዳችንን መውደዳችን ባንገልጥ ግን እንግዳችን ያዝንብናል፡፡ ከቃላችን በላይ ተግባራችንን ስለሚያይም እንደምንወደው ብንነግረውም አያምነንም፡፡ መውደድ የቃላት ጨዋታ ሳይኾን በተግባር የሚገለጥ ነውና፡፡ ልክ እንደዚኹ ፍጹም ሰው ኾኖ፣ ባሕሪያችንን ባሕርይ አድርጐ ወደ እኛ የመጣውን ክርስቶስን እንደምንወደው እየተናገርን፥ ነገር ግን በተግባር የምናሳዝነው ከኾነ መውደዳችን ትክክለኛ መውደድ አይደለም፡፡ ብንወደው ኖሮ ልክ ከላይ እንደገለጥነው እንግዳችን የሚበላ ነገርን እናቀርብለታለን፡፡ የክርስቶስ መብሉስ ምንድነው? እርሱ እራሱ እንዲኽ ሲል ነግሮናል፡- “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው” /ዮሐ.4፡34/፡፡ ተርቦ ስናየው የሚበላ ነገርን እንስጠው፤ ተጠምቶ ስናየው የሚጠጣ ነገርን እንስጠው፤ ርሱም ይቀበለናል፡፡ የሚቀበልንም ስለሚወደን ነው፤ ከማንወደው ሰው ስጦታን አንቀበልምና፡፡ ስጦታችን ትንሽ ሊኾን ይችላል፤ ነገር ግን አፍቃሪያችን ነውና ስለ ስጦታችን ታናሽነት አልቀበላችኁም አይለንም፡፡ ስጦታችን በርሱ ዘንድ ትልቅ ነው፡፡ በስንፍና አንያዝ እንጂ ስጦታችን አምስት ሳንቲምም ልትኾን ትችላለች፤ ርሱ ግን ወዳጃችን ነውና አምስት ሳንቲም ናት ብሎ ስጦታችንን አያቃልላትም፡፡ እንደ ድልብ ስጦታ አድርጎ አምስት ሳንቲሟንም ይቀበልልናል እንጂ፡፡ ስጦታችንን የሚቀበለው ድኻ ስለኾነ አይደለም፡፡ ስጦታችንን የሚቀበልልን ስለ ስጦታችን ታላቅነት ሳይኾን ስለ ልቡናችን ኀልዮት (intention) ነው፡፡ ስለዚኽ ስንሰጥ ክርስቶስ ስለተቀበለን ትንሽዋንም ስጦታችንን ይቀበል ዘንድ በቤታችን ታዛ ስለገባ ልናመሰግነው ይገባል፡፡ እውነተኛ ሐሴት ማለትም ይኸው ነው፤ በመቀበል ሳይኾን በመስጠት የምናገኘው፡፡ ወደ ቤታችን፣ ወደ ሕይወታችን የመጣው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ነፍሱን አሳልፎ ለሞት የሰጠው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ፍቅሩ ግን እዚኽ ላይ አላበቃም፡፡ አኹንም እኛ ጋር እየመጣ ነው፡፡ ሐዋርያው “ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን” ብሏል /2ኛ ቆሮ.5፡20/፡፡ ስለዚህ ተርበውና ተጠምተው ወደ እኛ የሚመጡት ሰዎች የክርስቶስ መልእክተኞች ናቸው ማለት ነው፡፡ የንጉሡን መልእክተኛ፡የሚያባርር ታድያ ማን ሞኝ ነው? ነገር ግን ብዙዎቻችን ሞኞች ኾነናል፡፡ የነገሥታት ንጉሥ የክርስቶስ መልእክተኞችን እያባረርናቸው ነውና፡፡ ክርስቶስን እንወድኻለን እያልን በተግባር ግን እናባርረዋለን፡፡ ከዚኽ የበለጠ ምስኪንነት ከወዴት ይገኛል? ክርስቶስን በቃል እወድኻለኁ እያሉ በተግባር ግን ርሱን ማባረር የማይጠቅም ብቻ ሳይኾን የሚጐዳን ጭምር ነው፡፡ እንኪያስ ተወዳጆች ሆይ! ክርስቶስን በቃልም ገቢርም እንውደደው፡፡ በታላቁ እንግዳችን በክርስቶስ ደስ መሰኛታችንን በተግባር እንግለጠው፡፡ ይኽን እንድናደርግ ርስቱንና መንግሥቱንም እንደ ቸርነቱ እንዲያወርሰን እኛን በመውደዱ ወደ እኛ የመጣው ደግሞም የሚመጣው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!!
531Loading...
13
#ክፉ_አሳብ ልጆቼ! ከመጀመሪያውኑ ክፉ አሳብ ባታስቡ መልካም ነው፡፡ ካሰባችሁ ግን ቢያንስ አትናገሩት፡፡ በዚያው በሕሊናችሁ ውስጥ እያለ ዝም አሰኙት፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም ወዳለመኖር ይኼዳል፡፡ እኛ ሰዎች ነን፡፡ በመኾኑም ብዙውን ጊዜ ክፉ፣ ያልተገቡና ጸያፍ ነገሮችን እናስባለን፡፡ ነገር ግን ቢያንስ እነዚህን አሳቦች አንናገራቸው፤ ቢያንስ ወደ ቃል አንለውጣቸው፡፡ ወደ ውጭ እንዳይወጡ አምቀን እንያዛቸው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እየከሰሙና እየደከሙ እየጠፉም ይኼዳሉ፡፡ አንድን እንስሳ ወደ ጉድጓድ ብትጥሉትና ጉድጓዱንም በመክደኛ ብትከድኑት ያ ወደ ጕድጓድ የጣላችሁት እንስሳ የሚተነፍሰውን አየር አጥቶ ይሞታል፡፡ ምናልባት ጥቂት ቀዳዳ ካገኘ ግን በዚያች ቀዳዳ በምትገባው አየር በሕይወት መቆየት ይችላል፡፡ ሲጨንቀውም እናንተን ክፉኛ ለመጉዳት ይዝታል፤ ከወጣም በኋላ ይጎዳችኋል፡፡ ልክ እንደዚሁ እናንተም በልቡናችሁ የተመላለሰውን ኩላሊታችሁ ያጤሰውን ክፉ አሳብ መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖረው አድርጋችሁ ብትከድኑት (ብታፍኑት) ይሞታል፤ ከመኖር ወዳለመኖር ይለወጣል፡፡ በአንደበታችሁ በመናገር ጥቂት ቀዳዳ ከከፈታችሁለትና እንደ እንስሳው እንዲተነፍስ ከፈቀዳችሁለት ግን ክፉው አሳብ ክፉ ግብርን ይወልዳል፡፡ ያቆጠቁጣል፡፡ በአሳብ ሳለ ከጎዳችሁ በላይም በገቢር ተወልዶና ተለውጦ ክፉኛ ይጎዳችኋል፡፡ (#የክርስቲያኖች_መከራ #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ገጽ 7➛በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
511Loading...
14
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- #ሰኞ #ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ #ማክሰኞ #ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 #ረቡዕ #አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ #ሐሙስ #አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ #አርብ #ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ #ቅዳሜ ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ #እሁድ #ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
813Loading...
15
"ከሙታን ተነሥቶ ሲኦልን እረግጦ በሞት ሞትን ደመሰሰው" (መጽሀፈ ኪዳን)
610Loading...
16
Media files
620Loading...
17
#ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦ #ቀዳም_ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) #ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም) @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
851Loading...
18
ጴጥሮስ ሆይ እስከ ፈራህና ፈጥነህ እስከ ካድክ ድረስ ለእኔ ነው ትል ዘንድ በድጋሚ ሌላ መስቀል አላየህ፣ እንደ ብረትም የተሳለ አንደበት ሰጥቶህ ነበር። ጴጥሮስ ሆይ አንተስ ያለ እሳትና ያለእንጥረኛም ፈጽመህ አቀለጥከው። ጴጥሮስ ሆይ ከሰው ሁሉ ለገጽህ ግርማ ሰጥቶህ ነበር፤ ብርሃናቸው የማይጠፋ ዓይኖችን የሰጠህ ሲሆን ስለጌታህ አንዲት ጥፊ ትቀበል ዘንድ ዛሬ አልታገሥክም። ጴጥሮስ ሆይ የመንግሥት ሰማያትን መክፈቻ የሰጠህን ልጄን በካድከው ጊዜ አልፈራህም፤ በሊቀ  ካህናቱም ግቢ አልታገሥክም፤ በእርሱ ፈንታም ለዓለሙ ሁሉ የታመነ ጠባቂ አድርጎ ሾመህ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ ጌታህ አንድ ጊዜ እንኳ ጥቂት መከራ አልተቀበልክም። ጴጥሮስ ሆይ ለዓለሙ ሁሉ አባት ትሆን ዘንድ ሾመህ፤ አንተ ግን ለልጄ የወንድማማችነት ፍቅርን አላደረግህም። ጴጥሮስ ሆይ አምላካዊ እጁን በራስህ ላይ ጫነ፤ አንተ ግን ከመካድህ በፊት ዛሬ በራስህ ላይ የእሾህ አክሊል ይጭኑብህ ዘንድ አልፈቀድክም። ጴጥሮስ ሆይ ልጄ ለአንተ ወዳጅህ እንጅ እንደ ጌታህ እንዳልሆነ አስብ። ልጄን እንደዚህ ትክደው ዘንድ ለአንተ አግባብ ኣይደለም። ጴጥሮስ ሆይ ከእኛ ጋራ ይህ ሁሉ ድካም እንዳገኘው እንደ አባቴ ዮሴፍ ብትሆን ኖሮ። ጴጥሮስ ሆይ እንደ እርሱ ወደ ኄሮድስ ቢጎትቱህ በግብጽ ምድርም ከእኛ ጋራ መከራ ተቀባይ ብትሆን እንደ እርሱ መታገሥ ባልቻልክም ነበር እንጃ። አባቴ ጸድቁ ዮሴፍ ሆይ በአጥንቶችህ ላይ የሰማይ ጠል ይውረድ። ነፍስህም ዕፀ ሕይወትን ትመገብ፤ ከእኛ ጋራ ታግሠህ መከራ፡ ስትቀበል እንደ ጴጥሮስ ልጄን አልካድከውምና። ጴጥሮስ ሆይ ወደ ፍርድ አደባባይ አልወሰዱህ በባለ ሥልጣኖችም ፊት አላቆሙህ ፈጥነህ ጌታህን ካድከው። ድንግል በዮሐንስ ቤት እንደዚህ ስታለቅስ ሳለ ዮሐንስ እያለቀሰ መጣ እርሷንም እያለቀሰች አገኛት። ድንግል እመቤታችንና ዮሐንስም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርስ በርሳቸው እየተላቀሱ ሁለቱም አብረው ነበሩ። ዮሐንስም ድንግልን እናቴ ሆይ ጌታችንን ጴጥሮስ ስለካደው አታልቅሺ አላት፣ አሳልፎ እንደ ሰጠው እንደ ይሁዳ ነውር የለበትምና። በእራት ጊዜ ጴጥሮስ ሆይ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ሲለው መምህሬን ሰምቻለሁና። ጴጥሮስም እንደዚህ በአንተ ላይ ይደረግ ዘንድ አይገባም፤ ጌታዬ ፈጣሪዬም እስከ ዘላለሙ ድረስ እልክድህም መሞት ይሻለኛል፤ እንደዚህም በእኔ ላይ አይሆንም፤ ስለ አንተ ነፍሴን አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ። ከዚህ ቀደምም መምህራችን ጌታ መምህሬ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ሲገሥፀው ሰምቻለሁ። ሰይጣን ባለጋራዬ ወግድ ከኋላዬ ዕንቅፋት ሁነህብኛልና ሰው ሰውኛውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና አለው። አሁንም እመቤቴ እናቴ ሆይ ስለ አባቴ ጴጥሮስ መካድ አታልቅሽ ለኃጢአተኞች ሁሉ ለንስሐ ምሳሌ ነውና። በቃሉ ያመነውን የጌታችንን ቃል አስተባብሎ ነበርና። በሐዘኗ የሚገኝ በረከት ከዐይንዋ የፈሰሰ የዕንባ ውኃ ጸጋ ለዘላለሙ ከእኛ ጋራ ይኑር አሜን። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ_ሦስት_ሰዓት)
300Loading...
19
የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ ከሕይወት ይልቅ፡ ሞት፡ ይገባሃል፤ እያሉ፡ ያንን ሊቀ ካህናት፡ ይዘልፉት፡ ነበር። በአንድነት፡ ከዘለፉትም፡ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ፡ ይዘውት፡ ሄዱ፤ ወደ ንጉሥም ይወስዱት፡ ዘንድ፡ ተስማሙ። የድንግል፡ ማርያም፡ በረከት የተወዳጅ ልጅዋም፡ ምሕረት፡ ከእኛ፡ ጋራ፡ ለዘላለም ይደርብን፤ አሜን። (#ግብረ_ሕማማት)
610Loading...
20
#የማርያም_ሐዘን - ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት የሚነበብ ልመናዋ፡ ክብሯ፡ ለዘላለሙ፡ ከእኛ ጋር ይኑርና፡ አንድ፡ አምላክ፡ በሆነ በአብ በወልድ፡ በመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ስም አምኖ የብህንሳ፡ ኤጲስቆጶስ፡ አባ ሕርያቆስ ድንግል፡ ማርያም፡ እመቤታችን ስላለቀሰችው፡ ልቅሶ፡ በዛሬው፡ ቀን የደረሰው ይህ ነው፤ አሜን። ወደ ዮሐንስ ቤትም በደረሰች ጊዜ አልዘገየችም። ወደ ቀራንዮ፡ ተመልሳ፡ ልትሄድ፡ የተወዳጅ፡ ልጅዋን፡ የመከራውን፡ ፍጸሜ፡ ታይ፡ ዘንድ፡ ቸኰለች፡ እንጂ። በመስቀል፡ ላይ፡ ነፍሱን፡ በፈቃዱ፡ ሰጥቶ፡ ዝም፡ በአለ፡ ጊዜ፣ በምድር፡ ላይ፡ ስለሆነው፡ ንውጽውጽታና፡ በሰማይም፡ ስለተደረጉ፡ አስደናቂ፡ ተአምራቶች፡ ሀገሪቱ፡ ሁሉ፡ ተሸበረች። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ምድር፡ ስትናወጽ፡ ጨለማ፡ በምድር፡ ሁሉ፡ ስትሰለጥን፡ አይታ፡ እነሆ፡ እነዚህ፡ ተአምራቶች፡ የልጄ፡ የሞቱ፡ ምልክቶች፡ ናቸው፡ ብላ፡ ጮኸች። እንዲህ፡ ስትልም፡ ዳግመኛ፡ ዮሐንስ፡ ደርሶ፡ እያለቀሰ፡ ከእርሷ፡ ዘንድ፡ ቆመ። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ዮሐንስ፡ ሆይ፡ በመስቀል፡ ላይ፡ ልጄ፡ በእውነት፡ ሞተን፡ አለችው። እርሱም፡ ራሱን፡ ዝቅ፡ አድርጎ፡ እናቴ፡ ሆይ፡ አዎን፡ ሞተ፡ አላት። ፮፤ ከዚህም፡ በኋላ፡ ታላቅ፡ ልቅሶ፡ ሆነ። በዚያችም፡ ሰዓት፡ ድንግል እመቤታችንን፡ ፍጹም፡ ጩኸትና፡ ልቅሶ፡ ጸናባት፤ በመረረ፡ ልቅሶም፡ እየጮኸች፡ ልጄ፡ ሆይ ከዚህ፡ ካገኘህ፡ የሞት፡ ፃዕር፡ የተነሣ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ፡ ሹም፡ ወይም፡ በሐዘን፡ የተሰበረውን፡ ልቤን፡ አይቶ፡ በማስተዋል፡ የሚፈርድልኝ፡ ዳኛ፡ አላገኘሁም፡ አለች። መኰንን፡ ሆይ፡ እንደ፡ ሕጉ፡ የምትፈርድስ፡ ቢሆን፡ ኖሮ፡ ንጉሥ፡ ልጄን፡ እንደራበው፡ እንደጠማው፡ የአይሁድ፡ ወገኖች፡ ባልሰቀሉትም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ ፈራጅ፡ ብትሆን፡ ባርያ፡ በጌታው፡ ፈንታ፡ መሞት፡ በተገባው፡ ነበር። በበርባን፡ ፈንታ፤ ሹም፡ ሆይ፡ በቅን፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ልጄን፡ ባልሰቀልከውም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ከልጄ፡ ይልቅ፡ ይሁዳ፡ ለሞት፡ የተገባው፡ በሆነ፡ ነበር። ሹም፡ ሆይ፡ ፍርድን፡ የምታውቅ፡ ቢሆን፡ ልጄን፡ ሥጋውን፡ አራቁተህ፡ መስቀል፡ ባልተገባህም፡ ነበር። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ ወንበዴውን፡ አድነህ፡ ጻድቁን ባልገደልከውም፡ ነበር። ዳኛ፡ ሆይ፡ መልካም፡ ፍርድን፡ የምታውቅ ብትሆን፡ ኑሮ፡ ጦሮች፡ በላይህ ላይ ሲያንዣብቡ፡ ጽኑዕ፡ የሆነውን፡ ባልገደልከውም ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ የጌታህን፡ ፊት፡ ባፈርክ ነበር። እኔ፡ ስለጦርነት፡ ሰልፍ፡ ስሰማ፡ የንጉሥ፡ ልጅ፡ በጦርነቱ፡ ውስጥ፡ የተያዘ፡ እንደሆን፡ እንዳይሞት፡ ስለእርሱ፡ እጅግ፡ በርትተው፡ እየተዋጉ፡ ወደ፡ አባቱ፡ በፍጹም፡ ጌትነትና፡ ክብር፡ እስከ፡ አደረሱት፡ ድረስ፡ ይጠብቁታል ። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ፡ ለምን፡ እንዲህ፡ ሆነ፡ በጠየቅኸው፡ ጊዜ፡ ዕውነቱን፡ አስረዳህ፣ ግን፡ በአንተ፡ ዘንድ፡ የተጠላ፡ ሆነ፡ ሐሰትን፡ ወደድክ፤ እምነትህንም፡ በሐሰቱ፡ ላይ፡ አጸናህ፤ እንግዲህ፡ ከእውነተኛው፡ ከእርሱ፡ በቀር፡ ማንን፡ ትጠይቃለህ። በፊትህ፡ የቆመው፡ እርሱ፡ እውነተኛ፡ እንደሆነ፡ አታውቅምን፡ እርሱም፡ በዕውነት፡ ሕይወት፡ ነው። ንጽሕት፡ ድንግል፡ ሆይ፡ በኢየሩሳሌም፡ ከተማ፡ በዚች፡ ትውልድ፡ መካከል የሆነውን፡ ታላቅ፡ ግፍ፡ እዪ፣ እነሆ፡ ከእነርሱ በሚበልጠው፡ ላይ፡ ተሰብስበው፡ ስም ለሞት ፍርድ፡ ሰጥተውታልና። ከዚህ፡ ሁሉ፡ በኋላ፡ ክርስቶስ፡ በመስቀል ላይ፡ እንደሆነ፡ ነበር፣ የመቶ፡ አለቃውን በዕውነት፡ ይህ፡ ሰው፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡ ብሎ፡ አመነ፤ እሊህ፡ ተአምራቶቹ በሁሉ፡ ዘንድ፡ ታመኑ። ፳፣ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ሳለ ምዕመናን ሁሉ፡ በአንድነት፡ አለቀሱለት። ስለጌታ፡ ስቅለት፡ ከሄሮድስ፡ ዘንድ ወደ መጣው፡ የመቶ፡ አለቃ፡ ጲላጦስ ልኮ አስመጥቶ፡ ወደ፡ ቤቱ፡ አስገብቶ፡ ወንድሜ ሆይ፡ ይህን፡ ጸድቅ፡ ሰው፡ አይሁድና ሄሮድስ ያደረጉትን፡ አየህን? ይህ፡ ሁሉ ተአምራት በምድር፡ እስኪሆን፡ ድረስ፡ በግፍ ሰቀሉት። ወንድሜ፡ ሆይ፡ በእውነት፡ እነግርሃለሁ፤ እነዚህ፡ ከፋቶች፡ ሁሉ፡ የተፈጸሙት፡ በሄሮድስ፡ ምክር፡ እንጂ፡ በእኔ፡ ፈቃድ፡ አይደለም፤ እኔ፡ እንዳይሞት፡ ልተወው፡ ወደድኩ፤ ነገር፡ ግን፡ ሄሮድስ፡ በዚህ፡ ደስ፡ እንደማይለው፡ ባየሁ፡ ጊዜ፡ ይሰቅሉት፡ ዘንድ፡ ለአይሁድ፡ ሰጠኋቸው፡ እንጂ። ተመልከት፡ አሁን፡ ለእግዚአብሔር፡ ስለ፡ ሰቀልነው፡ ልጄ፡ ምን፡ ብድርን፡ እንከፍላዋለን፡ አለው፣ የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ፡ ከጲላጦስ፡ ጋር፡ ደሙ፡ በሄሮድስና፡ በካህናት፡ አለቆች፡ ላይ፡ ነው፣ እያሉ፡ መራራ፡ ልቅሶ፡ አለቀሱ። በዚያን፡ ጊዜ፡ ጲላጦስ፡ ልኮ፡ የካህናት፡ አለቆች፡ ቀያፋና፡ ሐናን፡ ወደ፡ ጉባዔው አስጠርቶ፡ እናንተ፡ በግፍ፡ ደምን፡ የምትጠጡ፡ ተኵላዎችና፡ ቀበሮዎች፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ወደ፡ ሞተው፡ የናዝሬት፡ ሰው፡ አሁን፡ ተመልከቱ፣ ደሙም፡ በእናንተና፡ በልጆቻችሁ፡ ላይ፡ ይሁን፡ አላቸው። እነርሱግን፡ ደስ፡ በመሰኘት፡ እያፌዙ፡ ደረታቸውን፡ እየደቁ ፊታቸውንም፡ እየነጩ፡ እስከ፡ ሽህ፡ ትውልድ፡ በእኛና፡ በልጆቻችን፡ ላይ፡ ይሁን፡ ኣሉ። እነርሱም፡ እንደ፡ ሕጋችን፡ ፈጽመናል፡ ስለምን፡ እንፈራለን? እንደነግጣለን፡ አሉት። ጲላጦስም፡ የሐሰት፡ ሕግ፡ ፈጸማችሁ፡ እንጂ፡ ይህ፡ ሕግ አይደለም፡ ኣለ፤ አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባልከው፡ እነሆ፡ ልብሶችሁ፡ ተቀደዋል። ሕጉም፡ ሊቀ፡ ካህናቱ፡ ልብሶቹን፡ በቀደደ፡ ጊዜ፡ ከክህነት፡ አገልግሎት፡ ይከልከል፡ ይላል። ቀያፋም፡ እኔ፡ ልብሴን፡ የቀደድኩት፡ እርሱ፡ በእግዚአብሔርና፡ በሕጋችን፡ ላይ፡ የስድብ፡ ቃል፡ ስለ፡ ተናገረ፡ ነው፡ ብሎ፡ መለሰለት። ጲላጦስ፡ እንግዲህ፡ በሊቀ፡ ካህናት፡ ሥርዓት፡ ወደ፡ መቅደስ፡ ኣንተ፡ እንድትገባ አልፈቅድልህም፡ እንደ፡ ሕግ፡ አፍራሽ፡ እንጂ ። አንተ፡ ወደ፡ መቅደስ፡ እንደገባህ ሌላው ቢነግረኝ፡ ቸብቸቦህን፡ ከአንተ ላይ እቆጣለሁ፡ አለው። ቀያፋም፡ ከአንተ፡ በፊት፡ ብዙ ጊዜ አልፎአል፤ ብዙዎችም፡ ሹማምንት የሚቀድሙህ፡ አሉ፤ እስከ፡ ዛሬ፡ የካህናት አለቆችን፡ ወደ፡ መቅደስ መግባትን፡ የከለከላቸው፡ አለን፡ ብሎ፡ መለሰለት። ይህንም፡ ያለ፡ የሄሮድስን፡ ሥልጣን በመተማመን፡ ነበር፤ ጲላጦስም፡ ይህን፡ ሁሉ ተአምር፡ ስታይ፡ ከሕዝቡ፡ ሁሉ፡ ጋር፡ አሁንም፡ ልብህ፡ አያምንምን፡ አለው። ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባለ፡ ቀያፋም፡ አንተስ፡ በዚች፡ አገር፡ አዲስ፡ ተክል፡ ነህ፣ ይህ፡ ምልክት፡ የሆነበትን፡ ነገርና፡ የተደረገውን፡ ኣታውቅም። ይህ፡ ይቅርታ፡ የሚደረግበት፡ የመጋቢት ወር፡ ፀሐይና፡ ጨረቃ፡ ዑደታቸውን፡ ፈጽመው፡ ተራክቦ፡ የሚያደርጉበት፡ ሲሆን፡ በዚሁ፡ ወር፡ መሠርያኖች፡ ጨረቃን፡ እንደ፡ ደም፡ የሚሆንበትን፡ ያደርጋሉ፤ የፀሐይንም፡ ብርሃን፡ በሥራይ፡ ኃይል፡ ይስባሉ። የአግዓዝያንን፡ ተግባር፡ ይመረምራሉ፤ የሥንዴውን፡ የወይንንና፡ የዘይትን፡ ፍሬዎች፡ በማዘጋጀት፡ ይህን፡ የመሰለውን፡ ቀያፋ፣ በሐሰት፡ ይናገር ነበር። ጲላጦስም፡ ከወንበሩ፡ ላይ፡ ተነሥቶ፡ አንተ እርሱን፡ ከመጥላትህ፡ የተነሣ፡ በዓለም ሁሉ፡ ላይ፡ መዐትን፡ ልታመጣ፡ ትወዳለህ ብሎ፡ ከቆዳ፡ በተሠራ፡ በደረቅ፡ በትር ደበደበው፤ ጽሕሙንም፡ ነጨው።
590Loading...
21
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡ ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡ ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
400Loading...
22
#ዓርብ_ስድስት_ሰዓት_የሚነበብ (የስምዖን ዐምዳዊ ጸሎት) ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ በዕንጨት መስቀል፡ ላይ፡ ራቁትህን፡ የሆንክ፡ ጨለማን ከለበሰና፡ ስሕተትን፡ ከሚያመጣ፡ ሰይጣን መንፈስ፡ ለየኝ። በኃይልህ፡ እታደስ፡ ዘንድ፡ በጥበብህም፡ እመገብ፡ ዘንድ፡ የሕይወት፡ ሐር፡ ልብስን፡ አልብሰኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን፡ የብርሃን፡ መጐናጸፊያ፡ የምታጐናጽፋቸው ኃይልንም የምታስታጥቃቸው በመስቀል፣ ላይ፡ ራቁትህን፡ ቆምክ። ልቡናዬን፡ ከፍጹም፡ ድንቁርና፡ ጨለማ፡ አርቅ፣ (አንፃ)፣ በልቤና፡ በሕዋሳቴ፡ ውስጥም፡ የጌትነትህን፡ ብርሃን፡ አብራ፤ ከምድራዊ፡ ሀሳብና፡ ጠባይ፡ ተለውጠው፡ ከሰማያውያን መላእክት፡ ጋራ፡ ያመሰግኑህ፡ ዘንድ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ የከበሩ፡ እጆችህን፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ የዘረጋህ፡ ፍቅርህ፡ በውስጡ፡ ያድርበት ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ እንዲከፈት፡ አድርገው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን ከእሳት፡ የፈጠርካቸው፡ ሰማይንም፡ እንደ ድንኳን፡ የዘረጋህ፡ የምድርንም፡ ስፋቷን ያበዛህ። በበላይዋም፡ ዓለማተ፡ ሰማይን፡ እጅግ፡ ከፍ አድርገህ፡ የፈጠርክ፡ ከበታችዋም፡ እጅግ ጥልቅ ያደረግህ፡ ዙሪያዋንም፡ በባህር፡ የከበብህ ትእዛዝህም፡ ምድርን፡ በባሕር፡ ላይ፡ ጸንታ እንድትኖር፡ ያደረጋት፡ በውስጥዋ፡ ያለውንም ሁሉ። በመስቀል፡ ላይ፡ እንዴት፡ እጅህን ዘረጋህ? እንዴትስ፡ በቀኖት፡ ተቸነከርክ፡ ወዴትስ ወረድክ? ለሞት፡ እስክትደርስ፡ ድረስ፡ የአዳምን፡ ማዳን፡ እንደምን፡ ወደድክ። አፍና፡ አንደበት፡ ካላቸው፡ ለጌትነትህ፡ ምስጋና፡ ማቅረብ፡ የሚችል፡ ማን፡ ነው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ፍቅርህን፡፡ በልቤ፡ ውስጥ፡ ቅረጽ፤ ከክፉ፡ ማሰሪያ፡ ፍታኝ፤ ለዘላለም፡ ጸንቶ፡ በሚኖር፡ ፍቅርህም፡ እሰረኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ማሕየዊ፡ መስቀልህን፡ አቅፌ፡ ከእርሱ፡ የሕይወትና፡ የመድኃኒት፡ መዐዛ፣ አሸት፡ ዘንድ፡ ስጠኝ። በልቡናዬም፡ ውስጥ፡ ንጹሕ፡ ደምህ፡ ይውረድ፤ ንጹሕ፡ መሠዊያ፡ ይሆን፡ ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ ያክብረው፤ በውስጡም፡ የሕይወትን፡ መንፈስ፡ ያንቀሳቅስ፤ የሕይወት፡ መንፈስ፡ አንተን፡ ይቀበል። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ በመስቀል ላይ፡ መጻጻንና፡ ሐሞትን፡ የጠጣህ ከታላቁ፡ ንጹሕ፡ ፍቅርህ፡ አጠጣኝ፤ ከመራራው፡ ሞተ፡ ነፍስም፡ አድነኝ። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ)
360Loading...
23
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: #የማርያም_ሐዘን (#ዓርብ_በሦስት_ስዓት_የሚነበብ አባ፡ ሕርያቆስ፡ የደረሰው፡ ድርሳን፡ ይህ፡ ነው።) ወዳጆቼ ሆይ የአባቶች አለቃ የያዕቆብ ልቅሶ፤ ዛሬ ታደሰ አለ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ለወለደችው ለተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። መከራ ስለተቀበለችበት ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። የድንግልና ጡቷን ለእጠባችው ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በቤተልሔም በበረት ስለወለደችው ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በማኅፀንዋ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ለተሸከመችው ተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ ወልዳ ላልሳመቻቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ፤ እንደ ሰው ሁሉ በብብቷ ለተሸከመችው ልጇ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቦታ ወደቦታ ይዛ ላልተሰደደችባቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። ከሀገር ወደ ሀገር አዝላ ለተሰደደችበት ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ መቃብራቸውን ላላአየች ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። በአንድ ልጅዋ መቃብር ደጃፍ ላይ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። የባለ መልካም ጽሕም ሽማግሌ የያዕቆብ ልቅሶ በብላቴናይቱ ድንግል ዘንድ ዛሬ ታደሰ። ወንድሞቹ ባሰሩት ጊዜ ያዕቆብ ወደ ዮሴፍ አልተመለከተም። ድንግል ግን ልጅዋን በዕንጨት መስቀል ላይ ተቸንክሮ አየችው። ዮሴፍ በሰፊ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ያዕቆብ በላዩ፡ ያለቅስ ዘንድ ወደ ዮሴፍ አላየም። ድንግል ግን በአይሁድ ጉባዔ መካከል ተሰቅሎ ልጅዋን አየችው። ዮሴፍን ወንድሞቹ ልብሱን ገፈው ሲያራቁቱት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን በጎ ምክር በሌላት በአይሁድ መካከል ልብሱን ተገፎ ራቁቱን ሁኖ አየችው። ወንድሞቹ ዮሴፍን በሃያ ብር ሲሸጡት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን ይሁዳ ልጅዋን በሠላሳ ብር ሲሸጠው አየች። አራዊት ባልቀደዱት ልብስና በሌላ ደም ላይ ያዕቆብ አለቀሰ። አምላካዊ ደም ግን ድንግል ማርያም ስለእርሱ በላዩ የምታለቅስበት በቀራንዮ አለት ላይ የፈሰሰው ነው። ድንግል ግን ዛሬ ያየችው ልጅዋን ያለበሱትን ሌላ ልብስ ነበረ፤ የራሱን ልብስ ግን እርስ በርሳቸው ተካፈሉት። የዮሴፍ ወንድሞች ወንድማቸው ዮሴፍን በሸጡት ጊዜ አለቀሱ ተጸጸቱ። የእስራኤል ልጆች ግን ጌታቸውን በሸጡት ጊዜ አላለቀሱም፤ አልተጸጸቱም። የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸው በነገሠ ጊዜ ተደሰቱ። አይሁድ ግን ጌታቸው ከሙታን ተለይቶ በተነሣ ጊዜ ደስ አላላቸውም። ድንግል ሆይ፤ በእውነት በልጅሽ መቃብር ላይ ልቅሶሽ ጣዕም ያለው አሳዛኝ ነበረ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምን ታደርጊያለሽ? ብለው የልጅሽን መሰቀሉን በነገሩሽ ጊዜ በመላእክት መካከልም ቃልሽ ያማረ ነበር። እነሆ ልጅሽን በመኰንኑ ፊት አቁመውታል፤ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትም ያሰቃዩታል፣ ያቃልሉታል፣ ማርያም ሆይ ምን ታደርጊያለሽ? እነሆ ልጅሽን በፍርድ አደባባይ መካከል ልብሱን ገፈው እያራቆቱት ነው። የኢያቄም ልጅ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምንስ ታደርጊያለሽ? እነሆ በኢየሩሳሌም ሜዳ የሚሰቀልበትን ግንድ ብቻውን ተሸክሞአል፤ አንድ እንኳ ወደ እርሱ የሚቀርብ የለም። የሐና ርግብ ሆይ ለምን ተቀመጥሽ? የምትሰሪውስ ምንድን ነው? እነሆ ልጅሽን ሰቅለውት በቀራንዮ ቦታ ቁሞአል። የዳዊት ዘር ሆይ ልጅሽን በመስቀል ላይ ለምን ከፍ ከፍ አደረጉት? እመቤት ድንግል ሆይ በዮሐንስ ቤት ዛሬ ልቅሶሽ በእውነት ጣዕም ያለው ነበረ እንዲህ ስትዪ። ወዮ ለዚህ መራራ ወሬ ነጋሪ ለኢዮብና እስራኤል ለተባለ ያዕቆብ ከአረዷቸው መርዶ የመረረ ነው። ዛሬ ወደእኔ ለሚመጣ ለዚህ ለክፉ ወሬ ወዮ። ልጄ ሆይ አገሩን በኢቃጠሉ ጊዜ ለሎጥ ከአረዱት መርዶ ያስጨንቃል። በእኔ ላይ ለደረሰው ለዚህ አስጨናቂ ስብከት ወዮ። ልጄ ሆይ ስለ ኃያላነ እስራኤል ሞት ከአረዱአቸው መርዶ ይበልጣል። በዚህ በክፉ ወሬ ወደእኔ ለመጣው ለዚህ ወሬ ነጋሪ ወዮ። ልጄ ሆይ እነሆ ስታረጋጋኝ ሠላሳ ዓመት ይሆናል፤ ልገሥጽህም አልተቻለኝም። ዛሬ ወደ እኔ ወሬህ እስከመጣ ድረስ ወጥተህ እስከምትገባ አንዲት ሰዓት እንኳ አላመንኩህም። ልጄ ሆይ ለሐዘኔ ሁሉ ጥንቱ ሰሎሜ ናት፤ እኔ ዳኛውን አየው ዘንድ ከቤቴ አልወጣም፤ በፈራጁም ፊት አልቆምም። ሌባውን ራሱን ሲቆርጡት ሽፍታውንም ይገድሉት ዘንድ ሲፈርዱበት አላየሁም። ከቶ ቀራንዮን አላየሁትም፤ የጎልጎታንም ቦታ አላውቅም፤ ሁል ጊዜም በሚጣሉበት ቦታ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ክፉ የሆነ ፍርድ አላየሁም፤ በፍርድ አደባባይም ከቶ ለዘላለሙ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ያደረኩብህን ግፍ አላውቅም እኔም በዮሐንስ ቤት ነበርኩ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በሊቀ ካህናቱ በሐና ግቢ የተቀበልከው ግፍ ወሬው መራራ ነው። ልጄ ወዳጄ ሆይ ዛሬ ከእኔ ላይ ነጻነቴን አስወገድክ፤ ስለልደትህ በናዝሬት መልካም የምስራች ነገሩኝ። ዛሬ ግን በኢየሩሳሌም ይህችን ክፉ መርዶ አረዱኝ። በዮሴፍ ቤት መልካም ዜና በዮሐንስ ቤት ግን የሞት ዜና መጣልኝ ። ልጄ ወዳጄ ሆይ እኔ በልቤ ደስ እያለኝ ተቀምጨ ነበር። በየዕለቱ ፋሲካ ደርሶአል በዓሉን እናከብር ዘንድ ወደሀገራችንም እንመለሳለን እያልኩ ነበር፤ የዚህ ዓይነት ፋሲካም ደረሰኝ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በእንባና በሐዘን በዓሌ ወደ ልቅሶ ተመለሰ፤ ፋሲካየም ወደልብ ሐዘን። በዮሐንስ ቤት ሳለች ስለ ልጅዋ የመከራ ወሬ በመጣበት ጊዜ ድንግል እመቤታችን ይኸንን ልቅሶ ታለቅስ ነበር። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ከንጹሐን ሐዋርያት አንድ ፈለገች አላገኘችም፤ አይሁድን ከመፍራት የተነሳ ሁሉም ትተውት ሸሽተዋልና። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ስለ ጴጥሮስ መረመረች፤ እርሱማ የካህናት አለቆችን ከመፍራቱ የተነሳ ልጅሽን ከቶ አላውቀውም አለ፤ ሒዶም ተሸሽጓል አልዋት። ዳግመኛም ስለ ጌታችን ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ ለያዙት ሰዎች በተራራ ላይ ልብሱን ትቶ እንደ ሸሸ ነገርዋት። እንድርያስንም ፈለገችው፤ እርሱስ ወደ ከተማ አብሮት አልመጣም አልዋት፤ እንደዚሁ ቶማስም ሽሽቶ ሔደ። ስለ በርተሎሜዎስም ጠየቀች፤ እርሱም ከወንድሞቹ አስቀድሞ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ፊልጶስም ጠየቀች፤ እርሱም የፋናዎችን ውጋገንና መብራቶችን ባየ ጊዜ ፈርቶ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ዮሐንስ ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ አንድ ጊዜ ስንኳ እንዳልቆመ ነገርዋት። ስለ ማቴዎስም መረመረች፤ እርሱም ግብር ስለሚቀበላቸው አይሁድንና የካህናት አለቆችን እጅግ ስለፈራ እነርሱም ስለሚጠሉት በሌሊት ጨለማ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ሁሉም መረመረች፤ አብሮ ወደ ቀራንዮና ወደጎልጎታ ከሔደው ዮሐንስ በቀር አንድም አላገኘችም። ድንግልም ከልጅዋ ደቀ መዛሙርቶች ከዮሐንስ በቀር አንድ እንኳ ባለማግኘቷ እንደገና ዳግም ወደ ጽኑ ልቅሶና ሐዘን ተመለሰች። እንዲህ እያለችም አለቀሰች፦ ልጄ ወዳጄ ሆይ ወዮልኝ ወንድሞችህ ሸሹ ትተውህም ተሸሸጉ። አባቴ ጴጥሮስ ሆይ ጌታህን እንዳትክድ ሁልቀን እጠራጠርህ ነበር፤ ስለ እርሱ ወርቅ ብር አልሰጠህ ለምን ጌታህን ፈጥነህ ካድከው? ስለርሱ መርከብ ወይም ቀዛፊ አልሰጠህም፤ መምህርህንና ጌታህን ዛሬ ለምን ካድከው? ስለርሱ ምንም አልሰጠህም ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ እርሱ ወንድምን ወይም ወዳጅን አልሰጠህም። ልጄን ለምን ካድከው? በዚህ ሁሉ ልብህ ለምን ቀላል ሆነ?
440Loading...
24
Media files
731Loading...
25
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ #ምክረ_አይሁድ_ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ #የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡ #የእንባ_ቀንም_ይባላል ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
741Loading...
26
Media files
560Loading...
27
ዐቢይ ጦም ሊጠናቀቅ ሲል የተሰጠ ምዕዳን እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግዚአብሔር ረድቶንም ወደ ወደቡ ልንደርስ ተጠግተናል፡፡ ነገር ግን እንዲህ በመኾኑ ልል ዘሊላን ልንኾን አይገባንም፤ ይህን ምክንያት አድርገን ከከዚህ በፊቱ ላይ ትጋታችንንና ንቃታችንን እጅጉን እንጨምር እንጂ፡፡ የመርከብ አለቆች ብዙ ባሕረኞችንና ዕቃ ጭነው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ወደ ወደቡ ሊደርሱ ሲሉ መርከባቸው ከዓለት ጋር እንዳትጋጭና ድካማቸውን ኹሉ ከንቱ ላለማድረግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ ሯጮችም እንደዚሁ ወደ መጨረሻው መስመር ሊቃረቡ ሲሉ ኃይላቸውን ኹሉ አሟጥጠው ተጠቅመው ሽልማቱን ለመውሰድ ይጥራሉ፡፡ ትግለኞችም ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌለው ቡጢ ቢደርስባቸውም፣ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ተመትተው ቢወድቁም ሽል ማቱን ይወስዱ ዘንድ የመጨረሻውን ዙር ትግል እጅግ ከፍ ባለ ጉልበ ት ይታገላሉ፡፡ ስለዚህ የመርከብ አለቆች፣ ሯጮችና ትግለኞች ድል ወደ ማድረግ ሲቃረቡ እጅግ ከፍ ያለ ትጋትና ጥንቃቄ ኃይልም እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ወደ ታላቁ ሳምንት ደርሰናልና እግዚአብሔር ስለረዳን እያመሰገንን ጸሎታችንን፣ ተአምኖ ኃጢአታችንን፣ በጎ ምግባራችንን፣ ምጽዋ ታችንን፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን መስተጋብራችንን፣ ራስን የመግዛት ጠባያችንን፣ እንደዚሁም ይህን የመሰለው ሌላው ምግባራችንን ከፍ ባለ ትጋትና ጥንቃቄ ልንፈጽም ይገባናል፡፡ እነዚህን በጎ በጎ ነገሮችን ወደ ጌታ ቀን (ወደ በዓለ ትንሣኤ) የምንደርስ ከኾነ ከጌታችን ዘንድ ባለሟልነትን እናገኛለን፤ ከማዕዱ ዘንድ መሳተፍ ይቻለናል፡፡  (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ ገጽ 148)     @beteafework  @beteafework 
871Loading...
28
#ንጉሥ_በአህያ_ላይ (ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ) "አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት።  የዚህች  በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው።  በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣  ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት። ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት። ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ  በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።  ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። "የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን  እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት  ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት? ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም። እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን  ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል።  መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም ሥልጣኑ እያላቸው  በትሕትና "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን። #ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
741Loading...
29
#ሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15) #የዘንባባ_ዝንጣፊ፡- ☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ #የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
552Loading...
30
“ፍቅርህ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደህ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደድክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠህ ክብርህን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ሰማይ ሰራዊት መሄድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤል ያመሰግኑሃል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልሃል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድህን ያነጥፉልሃል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትህ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድህን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲሆን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከመሆን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” #ሊቁ_ያዕቆብ_ዘሥሩግም
462Loading...
31
#ሆሳዕና (የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት) ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራ ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተዋቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡ #ለምን_ዘንባባ_ያዙ_ቢባል፡- ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡ #የተምር_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡- ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡ #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡- ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡ #ልብሳቸውንም_ማንጠፋቸው፡- እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡….. ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል። #መልዕክታት ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) 1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡  (ተጨማሪ ያንብቡ) #ግብረ_ሐዋርያት የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷   (ተጨማሪ ያንብቡ) #ምስባክ "ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3 ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡ ወይም "እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2 ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡ #ወንጌል ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) ቅዳሴ ፡- ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡
572Loading...
32
"የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
650Loading...
33
የሰውን ልጅ በሩህሩህነት አሸንፈው። ቀናተኛውን በመልካምነትህ እንዲደነቅ አድርገው፤ ሁሉንም ሰው ውደድ ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ርቀትህን ጠብቀህ ኑር። አባ እንጦንስ
700Loading...
34
“በደለኞች ወደ እርሱ መቅረብ ይችሉ ዘንድ በሥጋ ለተገለጠው ረቂቅ አምላክ ምስጋና ይሁን። ጌታችን ኃጢአተኛዋን ሴት ፈሪሳውያኑ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው እንዳሰቡት ከእርሱ አላረቃትም። ማንም ሊደርስበት ከማይችለው ሰማይ የወረደው እንደ ዘኬዎስ ያሉ አጭር ቀራጮች ይደርሱበት ዘንድ ነው። ሊይዘው የሚችል ምንም ነገር የሌለ አምላክ የሰውን ሥጋ የለበሰው ኃጢአተኛዋ ሴት እንዳደረገችው የተዳደፉ ከንፈሮች ሁሉ እግሮቹን በመሳም ይቀደሱ ዘንድ ነው” ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዲያቆን አቤል ካሳሁን @KaleEgziabeher
1321Loading...
35
#ሰው_እንደ_ዘር_ነው አባቶቻችን ሊቃውንት ሰው እንደ ዘር ነው ይላሉ። ሰው እንደ ዘር ነው ማለት ዘር ተዘርቶ የሚያድገው በሁለት መሠረታዊ ነገር ነው። በብርድ እና በጸሐይ። ዘር ዝናምና ጸሐይ ያስፈልገዋል። ዝናም ብቻ ከሆነ ሽባ ይሆናል ጸሐይ ብቻም ከሆነ ይደርቃል። ሰውም እንደ ዝናሙ የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል፤ እንደ ጸሐዩም መከራ ያስፈልገዋል። ዘር በዝናሙ እየለዘበ፣ በጸሐዩ እየበሰለ እንደሚያድገው ሁሉ ሰውም በመከራ እየጠነከረ በተስፋና በእግዚአብሔር ቸርነት እየተጽናና ያድጋል። ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቸርነት ብቻ ከሆነ የሚያስበው ሽባ ይሆናል። መከራ ባገኘው ጊዜ ወዲያው ተስፋ ይቆርጣል። ሃይማኖትን ሊክድ ይችላል። መከራ ብቻ ከሆነበት ደግሞ ወዲያው ደግሞ እንደዚሁ ተስፋ ቆርጦ ሊሠበር ይችላል። ስለዚህ ዘር ዝናምና ጸሐይ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ሰውም መከራና የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል። #አባ_ገብረ_ኪዳን (የብሉያት እና የሐዲሳት መምህር)
870Loading...
36
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው.... ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡ "ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡ አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡ #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
641Loading...
37
"እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ ሆይ! ወርሐ ጾሙ ሲያልቅ ባዶ እጃችንን እንዳንገኝ በኹሉም ረገድ እንበርታ ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ በጾም እየደከሙ ሳለ የጾምን ዋጋ ሳያገኙ መቅረት አለና፡፡ "ይህስ እንደምን ነው?" ያላችሁኝ እንደኾነም "ከምግበ ሥጋ እየጾምን ሳለ የኃጢአትን መብል ስንመገብ፣ ሥጋን ከመብላት ተከልክለን ሳለ የድኻውን ቤት ስንበረብር፣ ወይንን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፉ መሻቶች ስንሰክር፣ ቀን ሙሉ ምግብ ሳንበላ ውለን ሳለ ዓይናችን ግን ክፉ ነገሮችን ሲመለከት ነዋ" ብዬ እመልስላችኋለሁ፡፡" #ቅዱስ_ዮሃንስ_አፈወርቅ
660Loading...
38
እሺ ብትሉ… ልጆቼ! እስኪ ምላሴን ላሰናብትባችሁና እናንተም በትዕግሥት አድምጡኝ! የቤት ሠራተኛ አላችሁ እንበል፡፡ ይህቺ የቤት ሠራተኛችሁ የለበሰችውንና በወጥ፣ በአመድ እንዲሁም በሌላ ቆሻሻ እድፍ ያለ ልብሷን ትለብሱ ዘንድ ትፈቅዳላችሁን? በእርግጠኝነት አትፈቅዱም፡፡ ግን የብዙዎቻችን ሰውነት ከዚህ ልብስ በላይ መቆሸሽዋስ ታውቃላችሁን? ልጆቼ! ንግግሬ በጣም እንደሚያሳምም አውቃለሁ፤ ግን ምን ላድርግ? የተስተካከለ ሕይወት ቢኖረን እንዲህ የምናገር ይመስላችኋልን? በፍጹም! አንድ የቆሰለ የሰውነት ክፍል ቢኖራችሁ ሐኪሙ ይህን ቁስላችሁ በጣቱ ሳይነካካ ማከም ይችላልን? አይችልም! እኔም እንዲህ ቁስላችሁን ካልነካካሁት በስተቀር ማከም አልችልም፡፡ ለነገሩ ሰው ሰውነትህን አትንካ ማለት ይቻላልን አይቻልም! ታድያ እኔና እንናተ እኮ አንድ አካል ነን፡፡ በክርስቶስ አንድ ኾነን የለምን? እንግዲያውስ ንግግሬን አትጥሉት፤ ክፉ ግብራችሁን እንጂ፡፡ ችግሩ ከማን ነው ከእኛው ወይስ ከቆሻሻው? አንድ ወደ ትዕይንት (ቲያትር) ቤት የሄደ ወጣት ገላዋን ገላልጣ የምትተውን ተዋናይትን አይቶ ዝሙትን መፈጸም የማያስብ ማን ነው? ደጋግሞ የዝሙት ዘፈንን የሚሰማ ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መቋቋም እችላለሁ የሚል ማን ነው? ቀኑን ሙሉ የዝሙት ጽሑፎችን ሲያነብ የሚውል ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መጠበቅ እችላለሁ የሚል ማን ነው? ልጆቼ! ትዕይንቱን እያየነው፣ ዘፈኑን እየዘፈንነው፣ መጽሐፉንም እያነበብነው ኾኖም ግን መፍትሔ ካላገኘንበት ችግሩ እየባሰ የሚሄድ አይደለምን? እኛ ፈቃደኞች ከኾንን ግን መፍትሔው በሥጋችን ላይ ካለው ደዌ በላይ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም የሥጋችን ቁስል ሐኪም፣ መድኃኒት፣ ጊዜ ያስፈልጓል፡፡ የነፍሳችንን ቁስል ግን ፈቃድ በቂ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ከእኛ በላይ በንጽሕና ሲኖሩ ሳይ በጣም አፍራለሁ፡፡ እንግዲያውስ ልጆቼ እንመለስ፡፡ ያቆሸሹንን ነገሮች እንጣላቸው፤ እንቁረጣቸው፤ እናስወግዳቸው፡፡ ሰነፎች አንሁን፡፡ ውሳኔው የእኛው ነው፡፡ መጽሐፍ ሲናገር “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል” ይላል /ኢሳ.1፡19-20/፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር በእኛ እሺታና እምቢታ የተወሰነ ነው ማለት ነው፡፡ የምንኮነነውም የምንመሰገነውም በዚሁ መሠረት ነው ማለት ነው፡፡ መድኃኒዓለም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር በቸርነቱ ይደምረን አሜን፡፡ ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
660Loading...
39
"ድኃ በቤትኽ ደጃፍ ይጮኻልን? ተነስተህ በደስታ የቤትህን ደጅ ክፈትለት የድኃውን ልመና ቸል አትበል፡፡ በነፍሱ የመረረው ነውና ቢረግምህ እግዚአብሔር አቤቱታውን ይሰማዋል፡፡ ስለዚህ ይረግምህ ዘንድ ምክንያት አትሁነው አዝኖ ከሆነ በመልካም መስተንግዶ ደስ አሰኘው፡፡ በኀዘን የከበደው ልቡ በአንተ ይረፍ፤ በሕይወት ዘመንህ ማጣት የሚያመጣቸውን ስቃዮች ታውቃቸዋለህና ችግረኛውን ከቤትህ ደጅ አትመልሰው፡፡" #ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶሪያዊ
1181Loading...
40
Media files
831Loading...
#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል። እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል። የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና። በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል። ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።” ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ። የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ። በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)። በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል። አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163)
Hammasini ko'rsatish...