uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
2 406
Obunachilar
+124 soatlar
+407 kun
+33730 kun
Postlar arxiv
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2013 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አደረገ በ2013 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ዘግጅት ግምገማ ላይ የኮሌጁ ፑል አመራር አባላት የተሳተፉ ሲሆን የተጠናቀቀው በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2014 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር እና የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አብይ የስራ ሂደቶች ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይት መድረኩ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በ2013 በጀት ዓመት ስለነበረው የስራ አፈጻጸም ለተሳታፊዎችምስጋናቸውን አቅርበው በ2013 በጀት ዓመት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየትና ያጋጠሙ ችግሮችን አጥርቶ በማውጣት ላለንበት የ2014 በጀት ዓመት ችግሮቹን አስወግደንክፍተቶቻችንን በመሙላት በተለይም በKPI (key Performance Indicator ) ላይ በተመላከተው ልክ ውጤትን መሰረት በማድረግ ዕቅዱ መፈጸም እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ነጩ ፖሰታ ለነጩ ቤተመንግስት መርሃ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ! አሸባሪውና የእናት ጡት ነካሹ የህወሀት ጁንታ ቡድን ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ብሎም የውሸት ፕሮፖጋንዳ የአሜሪካ መንግስትናመላው አለማቀፍ ማህበረሰብ የሽብርተኛውን ቡድን ሴራ ይረዱት ዘንድ የኮሌጁን አመራር ፑል በማስተባበር ስለ አሸባሪው የህወሀት ሴራ ደብዳቤ ላይ በመፈረምና በፖሰታ በማድረግ በዛሬው ዕለት የኮሌጁ ዲን እና ም/ዲኖች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡ በቀሩት ጥቂት ቀናትም ኮሌጁ መሰል የተለያዩ መርሃ-ግብሮች በማዘጋጀት አጠቃላይ የኮሌጁን ማህበረሰብ ተሳታፊ እንዲሆን በማድረግ ለዚህ ሀገራዊ ጉዳይ ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ የኮሌጁ ዲን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሁሌም ያሸንፋል!

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2014 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም፣በጤና፣በፍቅር አደረሳችሁ ይላል።🌻🌻🌻🌻🌻 አዲሱ አመትም የሰላም፣የአብሮነት እና የእድገት ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።🌻🌻🌻 #መልካም_አዲስ_አመት🌻🌻

የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች እና ሰራተኞች የደሞዛቸውን ከ10 እስከ 50 ፐርሰንት ለኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ለመስጠት ወስነዋል። ………………………………………………… ነሀሴ 10/2013 ዓ.ም የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች የደሞዛቸውን 50% እንዲሁም የተቋሙ ሰራተኞች የደሞዛቸውን 10% ለኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል። በቀጣይም ለሰራዊቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች በዛሬው ቀን በተካሄደው በአስተዳደራችን በአንድ ጀምበር 500 ሺ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ላይ በመሳተፍ እንደ ተቋም አሻራቸውን አኑረዋል።

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ ይላል።

የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ዋና የስራ ሂደት አዘጋጅነት በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና የፈጠራ አስተባባሪዎች በቴ/ሙ/ት/ስ ስትራቴጂ ገለጻ በማድረግ STEM እና INNOVATION እንዲሁም ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ግንዛቤ በመፍጠር የ2014 ረቂቅ ሰነድ ላይ በመወያየት የጋራ ስምምነት መድረስ ተችሏል፡፡ ሰኔ 11/2013 ዓ.ም