cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
771
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
+1130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 3 ጌታችን ከመረጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ አንዱ የሆነውና ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት የሾመው ሐዋርያው ቅዱስ ያሶን ዕረፍቱ ነው፡፡ ➥ ሰማዕቱ አባ ብሶይ ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡ ➥ "የንጉሥ ወግና ሰገድ እናቱ የሆነች የተባረከች ንግሥት ወለተ ማርያም" ዕረፍቷ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳታል፡፡ እርሷም በምግባር፣ በሃይማኖትና በመንፈሳዊ ተጋድሎ የከበረችና የተመሰገነች ናት፡፡ 🔥 ሰማዕቱ አባ ብሶይ ይኽንንም ቅዱስ ክፉዎችና ጣኦት አምላኪዎች ይዘውት ሰውነቱን በማጣመምና በመቆልመም ብዙ አሠቃዩት፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ አክሊል ይዞ "አትፍራ ጽና፣ እነሆ በእጄ ውስጥ አክሊል አለ" አለው፡፡ ደግሞም ብዙ ካሠቃዩት በኋላ ወደ እሳት ውስጥ ጨመሩት፡፡ ጌታችንንም በማመን እስከመጨረሻው ጸንቶ ተጋድሎውንም በዚኹ ፈጸመ፡፡ መልአኩም አስቀድሞ አሳይቶ ተስፋ እንደሰጠው የሰማዕትነት አክሊልን አቀዳጀው፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ ብሶይ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 ሐዋርያው ቅዱስ ያሶን ይኽም ቅዱስ ሐዋርያ ከከበሩ ሐዋርያት ጋራ ወንጌልን በሰበከ ጊዜ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን በጌታችን ስም ተቀበለ፡፡ በ50ኛው ቀን ከሐዋርያት ጋራ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏልና ድንቅ ድንቅ የሆኑ ብዙ ተአምራትን አደረገ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ያሶን ትውልዱ ከጠርሴስ አገር ነው፡፡ ጠርሴስም ሰዎች አስቀድሞ በወንጌል ያመነው እርሱ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከተጠራና ካመነ በኋላ ወንጌልን ዞሮ ሲሰብክ ቅዱስ ያሶን ተከትሎት በብዙ አገሮች በወንጌል ትምህርት አገልግሎታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ያሶን በተሰሎንቄ ከተማ ወንጌልን ሲሰብኩ ክፉዎች ይዘዋቸው እየጎተቱ ወስደው ከተሰሎንቄ አገር ገዥ ፊት አቅርበዋቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ያሶንን በጠርሴስ አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾመው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ያሶንም ቤተ ክርስቲያንን በመልካም አጠባበቅ ጠበቃት፡፡ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ካጸናቸውና በበጎ ምግባር ካነጻቸው በኋላ ወደ ምዕራብ አገር ሄዶ በዚያ ወንጌልን ሰበከ፡፡ ስሟ ኮራኮራስ ወደምትባል ደሴትም ገብቶ በውስጧ ወንጌልን ሰብኮ ነዋሪዎቿን እግዚአብሔርን ወደማመን መለሳቸው፡፡ በደሴቷም ውስጥ በዲያቆናት አለቃ በሰማዕቱ በቅዱስ እስጢፋኖስ ስም ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው፡፡ የአገሪቱ ገዥም ይኽንን ባወቀ ጊዜ ቅዱስ ያሶንን ይዞ ከእሥር ቤት ጣለው፡፡ ሐዋርያው ግን በእሥር ቤት ያገኛቸውን ሰባት ኃይለኛ ወንበዴዎችን አስተምሯቸው ካሳመናቸው በኋላ አጠመቃቸው፡፡ እነርሱም በከሃዲው መኮንን ፊት በጌታችን ታመኑ፡፡ "በቅዱስ ያሶን አምላክ እናምናለን" ብለውም በጮኹ ጊዜ መኮንኑ ዝፍጥና ድን በተመላ ምጣድ ውስጥ አግብቶ አቃጠላቸው፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ከዚኽም በኋላ መኮንኑ ቅዱስ ያሶንን ከእሥር ቤት አውጥቶ ብዙ አሠቃየው ነገር ግን ጌታችን መከራውን ያስታግስለት ነበርና ምንም እንዳልነካው ሆነ፡፡ በተአምራቱም ብዙዎችን አሳመናቸው፡፡ የንጉሡም ሴት ልጅ ከቤቷ መስኮት ሆና አይታ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች፡፡ ልብሶቿንና ጌጦቿንም ሁሉ አውጥታ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጠችና በሐዋርያው በቅዱስ ያሶን አምላክ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነች፡፡ ንጉሡ አባቷም ይኽንን በሰማ ጊዜ ይዞ አሠራት፡፡ ጌታችንንም በማመን ስለጸናች አባቷ ብዙ ሥቃጦችን አደረሰባት፡፡ በጢስ አፍኖ አሠቃያት፣ ልብሷን አውልቆ ካራቆታት በኋላ ሰውነቷን በፍለጻ ነደፋት እርሷም በዚሁ ሰማዕትነቷን ፈጽማ ነፍሷን ለእግዚአብሔር ሰጠች፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡ ከዚኽም በኋላ ሐዋርያው ቅዱስ ያሶንን አሠቃይተው ይገድሉት ዘንድ ከአንድ መኮንንና ከሠራዊቱ ጋራ ወደ ደሴት ሰደደው፡፡ መኮንኑም በመርከብ ወደዚያ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር መኮንኑን ከነሠራዊቱ አሰጠመው፡፡ ቅዱስ ያሶንም ወንጌልን ተዘዋውሮ እየሰበከ ብዙ ዘመናት ኖረ፡፡ ሁለተኛም ሌላ መኮንን በተሾመ ጊዜ ቅዱስ ያሶንን ይዞ በምጣድ ውስጥ ድኝና ዝፍጥ ሰም መልቶ ነበልባሉ ወደላይ እስኪወጣ ድረስ ከሥሩ አነደደና ሐዋርያውን በውስጡ ጨመረው፡፡ ነገር ግን የክብር ባለቤት ጌታችን አገልጋዩን ያለምንም ጉዳት አዳነው፡፡ መኮንኑም ይኽንን ድንቅ ሥራ ባየጊዜ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመነ፡፡ ቤተሰቦቹና የአገሪቱ ሰዎችም ሁሉ አብረው አመኑ፡፡ ቅዱስ ያሶንም አጠመቃቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ከሠራላቸው በኋላ የከበረች የወንጌልን ሕግና ትእዛዝ ሠራላቸው፡፡ እነርሱም በምግባር በሃይማኖት ጸኑ፡፡ ሐዋርያውም ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አደረገላቸው፡፡ መልካም የሆነውን አገልግለቱንም ፈጽሞ በበጎ ሽምግልና ሆኖ በዚኽች ዕለት ዐረፈ፡፡ የሐዋርያው የቅዱስ ያሶን ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 3️⃣ ቀን ስንክሳር ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ግንቦት 2️⃣ ቀን 2011 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

👍 1
. 🔥 ዓርብ - ቤተክርስቲያን 🔥 ዓርብ የእግዚአብሔር ቅድስት ማደሪያ በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ተሰይማለች። ይህም ሁሉም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመባት ዕለት በመሆኗ ነው። ዕለተ ዐርብ የሥራ መከተቻ፤ ምዕራብና መግቢያ በሚሉት ስያሜዎችም ትጠራለች፡፡ በክርስቶስ ደም ተዋጅታ ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያ በመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዓርብ "ቤተ ክርስቲያን" ተብላ ትጠራለች፡፡ ማቴ. 26-26-29 የሐ. ሥራ. 20-28 በዕለቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ያደረገውን ተአምር በመስቀሉ ድኅነትን እንዳሳየ፤ በቀራንዮ የሕንጻዋ መሠረት እንደተተከለላትና ሥጋ መለኮት እንደተቆረሰላት፤ ልጆቿን ከማሕፀነ ዮርዳኖስና ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ እንደፈሰሰላት ተገልጾባታል። (ኤፍ.፪፥፲፱፤ራዕ.፩፥፮-፰) ይህች ዕለትም እንደ ዕለተ ኀሙስ ሦስት ስያሜዎች አሏት፡፡ ይኸውም፡- ➛ አንደኛው ከሆሳዕና ቅዳሜ በፊት ያለችው ዓርብ የጌታችን ጾም የሚፈጸምባት፤ የጾመ ድጓው ቁመትም የሚያበቃባት፣ በመሆኗ በቤተ ክርስተያን "ተጽዒኖ" ስትባል፤ በሕዝቡም ዘንድ በሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤው ከባዱን ሥራ ስለሚያቆምባት "የወፍጮ መድፊያ፣ የቀንበር መስቀያ" ትባላለች፡፡ ➛ ሁለተኛውም በመጀመሪያ የሰው አባትና እናት አዳምና ሔዋን ስለተፈጠሩባት፣ ኋላም በሐዲስ ኪዳን ጌታችን ለቤዛ ዓለም መከራ ተቀብሎ ስለተሰቀለባትና የማዳን ሥራውን ስለፈጸመባት " ዕለተ ስቅለት አማናዊቷ ዓርብ" ትባላለች። ➛ ሦስተኛው በሰሙነ ትንሣኤው ያለችው ደግሞ "ቤተ ክርስቲያን" ትባላለች ማለት ነው፡፡ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2597592030394633&id=100004315844056&mibextid=Nif5oz
Hammasini ko'rsatish...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 2 በዘመኑ እንደ እርሱ ያለ ዕውነተኛ ደግ ሰው እንደሌለ እግዚአብሔር የመሰከረለት ጻድቁ ኢዮብ ዕረፍቱ ነው፡፡ ➛ የመንፈሳዊ ማኅበር አባት የሆነው የአባ ጳኩሚስ ረድእ የሆነው የከበረ አባ ቴዎድሮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ➛ አባ ኤሲ ከሃያ ሁለት ሰዎች ጋር በሰማዕትነት እንዳረፉ ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡ 🔥 ቅዱስ ቴዎድሮስ ረድኡ ለአባ ጳኩሚስ የአባ ጳኩሚስ ረድእ የነበሩና እጅግ የከበሩ አባት ናቸው፡፡ በትሑትነትቸውና በታዛዥነታቸው ይታወቃሉ፡፡ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍጹም ናቸው፡፡ ከታናሽነታቸው ጀምረው መንኩሰው ለአባ ጳኩሚስ ለፈጣሪያቸው እንደሚታዘዙት ሆነው ይታዘዟቸው ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ ጠቢብና ሊቅ ናቸው፡፡ አባ ጳኩሚስም እጅግ ይወዷቸው ነበር፡፡ እርሳቸውም በአባ ቴዎድሮስ ላይ ያደረውን ጸጋ ዐውቀው ገና ታናሽ በብላቴና ሆነው ሳለ በመነኮሳቱ ሁሉ ላይ የበላይ አድርው ሾሟቸው፡፡ አባ ጳኩሚስም በሞት ካረፉ በኋለ በእሳቸው ፈንታ አበ ምኔት ሆነው ገዳሙን በጽድቅ በትሩፋት እያስተዳደሩ መርተዋል፡፡ ገዳሙንም በተለያየ መንገድ አገልግለዋል፡፡ አባ ቴዎድሮስ የዚኽን ዓለም ክብር እጅግ አድርገው ይሸሹና ይጸየፉ ነበር፡፡ ጻድቁ መልካም የሆነ አገልግሎታቸውን ፈጽመው እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተው በዚኽ ዕለት በሰላም በክብር ዐርፈዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብ ለዚኽም ጻድቅ በዘመኑ እንደ እርሱ ያለ ዕውነተኛ ደግ ሰው እንደሌለ በቅዱሳት መጻሕፍትም ስለእርሱ እንደተነገረ እግዚአብሔር መሰከረለት፡፡ የበጎ ነገር ሁሉ ጥንተ ጠላት ሰይጣንም ቀንቶበት በገንዘቡና በልጆቹ ላይ ያሰለጥነው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመነ፡፡ እግዚአብሔርም የጻድቅ ወዳጁን ትዕግሥት ስለሚያውቅ ሰይጣንን አሰለጠነው፡፡ የቅዱስ ኢዮብ ትዕግሥት ለመጪው ትውልድም አርአያና ምሳሌ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ኢዮብ እንዲፈተን ፈቀደ፡፡ ስለዚኽም ነገር ሐዋርያው ሲጽፍ ‹‹እነሆ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደታገሠ ሰምታችኋል፣ ጌታም እንደፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና›› ብሏል፡፡ ያዕ 5፡11፡፡ ከዚኽም በኋላ የቅዱስ ኢዮብ ገንዘቡን ሁሉ በአንዲት ቀን ጠፋ፡፡ እርሱም በሥጋ ደዌ ከራሱ እስከ እግሩ ድረስ ተመታ፡፡ በዚኽም በአስጨናቂ ደዌ ውስጥ እየኖረ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ያመሰግን ነበር፡፡ አንዲት ቃልን እንኳ በመናገር በእግዚአብሔር ላይ አላጉረመረመም፡፡ ይልቁንም እንስሶቹና ገንዘቡ ሁሉ በጠፋ ጊዜ ‹‹እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔርም ነሣ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን›› አለ፡፡ በመከራም በነበረበት ዘመን በተራራ ላይ ተጥሎ ሳለ የወዳጆቹና የሚስቱ ዘለፋ በዝቶበት ኖረ፡፡ ሚስቱም ‹‹እስከመቼ ድረስ በሞኝነት ትኖራለህ? እንግዲህስ እግዚአብሔርን ስደበውና ሙት፤ ዳግመኛ እግዚአብሔርን ደጅ እጠናዋለሁ፣ መከራውንም እታገሣለሁ የቀድሞ ኑሮዬን ተስፋ አደርጋለሁ ትላለህን? እንዲህስ እንዳትል እነሆ ከዚህ ዓለም ስም አጠራርህ ጠፋ፣ ሴቶችና ወንዶች ልጆቼ ሞቱ…. ከእንግዲህስ እግዚአብሔርን የማይገባ ቃል ተናግረኸው ሙት›› አለችው፡፡ ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብም ‹‹ሥርዓት እንዳልተሠራባቸው ከአሕዛብ ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽን? ከዚህ ቀደም በጎውን ነገር ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበልን፤ ከዚህም በኋላ ደግሞ መከራውን አንታገሥምን?›› አላት፡፡ ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብ ባገኘው እጅግ አሳዛኝ መከራ ሁሉ ጌታን የበደለው በደል የለም፡፡ እርሱም ወርቅ በእሳት እንዲፈተን ፈጽሞ ተፈተነ፡፡ የትዕግሥቱንም ጽናት ካየ በኋላ እግዚአብሔርም በደመና ውስጥ ተነጋገረው፡፡ ከደዌውም ፈወሰው፡፡ ጥሪቱንም ሁሉ ከቀድሞ እጥፍ አደረገለት፡፡ ሌሎች ልጆችንም ሴቶችንና ወንዶችን ሰጠው፡፡ ኢዮብም ከደዌው ከተፈወሰ በኋላ 170 ዘመን ኖረ፡፡ አጠቃላይ ዘመኑም 248 ዓመት ነው፡፡ እግዚአብሔርን አገልግሎ በበጎ ሽምግልና ሆኖ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🔥 የኢዮብ አማላጅነት እግዚአብሔር ስለ ጻድቁ ስለ ኢዮብ ሃይማኖትና በጎ ምግባር ብቻ ሳይሆን ስለ ኢዮብ አማላጅነትም መስክሮለታል ። ጻድቁ ኢዮብ በታመመበት ወቅት በዙሪያው ቆመው በቁስሉ ላይጥዝጣዜን ሲጨምሩበት የነበሩት ሦስት ጓደኞቹ ላይ እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ለአንዱ ለቴማናዊውኤልፋዝ፦ እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል አለው፡፡ እግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን «እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ አንዲት ቅን ነገርን በፊቴ አልተናገራችሁምና አንተና ሁለ ቱ ባልንጀሮችህ በድላችኋል። አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘን ድ ሂዱ፥ እርሱም የሚቃጠል መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ ያሳርግላችሁ። ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልይ፥ እኔም ፊቱን እቀ በላለሁ። ስለ እርሱ ባይሆን ባጠፋኋችሁ ነበር። በባሪያዬ በኢዮብ ላይ ቅን ነገርን በፊቴ አልተናገራችሁምና።» ያለው ለዚህ ነው። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመዓዛ ቅዳሴው ላይ እመቤታችንን ‹‹የኢዮብ ደመና ማርያም ሆይ! በረድኤት ነይ›› በማለት አመስግኗታል፡፡ እግዚአብሔርን ጻድቁ ኢዮብን ከደዌው ፈውሶ ምሕረትን ሊሰጠው ሲል በደመና ተገልጦ ድኅነትን እንደሰጠው ሁሉ በዘመነ ሐዲስም እግዚአብሔር ደዌ ነፍስ ጸንቶባቸው የነበሩ ሰዎችን ለማዳን ሲል ከድንግል እናቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወልዶ ምሕረትን ለዓመለሙ ሁሉ ሰጥቷልና ነው ሊቁ ‹‹የኢዮብ ደመና ማርያም ሆይ! በረድኤት ነይ›› ያላት፡፡ (መዓዛ ቅዳሴ ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቁ 26፡፡) ዳግመኛም እመቤታችን በፍቅሯ በቃልኪዳኗ ከቁስለ ሥጋ ከቁስለ ነፍስ ከዘላለም ሞት የምንድንባት ነትና አባቶች ‹‹የኢዮብ የሰሜናዊው ምሥራቅ ዓምባ መጠጊያው ማርያም ይኽቺ ናት›› ዳግመኛም ‹‹በቁስለ ሥጋ በታመመ ጊዜ የኢዮብ የልመናው መቀበያ አንቺ ነሽ›› በማለት አማላጅነቷን አመስጥረው አመስግነዋታል፡፡ (መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 89፣ ዝኒ ከማሁ ገጽ 160፡፡) ዳግምት ሰማይ፤ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ መውጫ ምሥራቅ ፤ የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ በድጋሚ ከልደቷ ረድኤት በረከት ትክፈለን፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ምልጃ ፤ በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡ ምንጭ፡- የግንቦት ❷ ስንክሳር 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን።
Hammasini ko'rsatish...
ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ግንቦት ➊ ቀን 2011 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
"ሔዋን በገነት ዛፎች መካከል ቆማ የሠራችውን የጥፋት ታሪክ ድንግል ማርያም በናዝሬት ገሊላ ቆማ አረመችው፡፡ ሔዋን በገነት ሳለች ማድረግ ያልተቻላትን ነገር ሁሉ ታናሽዋ ብላቴና አድርጋ አሳየቻት፡፡ የሰው ልጅን ከገነት ያስወጣው የእባቡና የሔዋን ቃለ ምልልስም ሰውን ወደ ገነት በመለሰው በገብርኤልና በማርያም ቃለ ምልልስ ተተካ፡፡ ሰይጣን በእባብ አድሮ የሠራውን ሰውን የማታለሉ የውድቀታችን ታሪክ 'እባብ ለሴቲቱ እንዲህ አላት' ተብሎ በየዕለቱ ሲተረክና የሰው ልጅን አንገት ሲያስደፋ እንዳልኖረ አሁን በተራችን የገብርኤልና የማርያምን ንግግር 'መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ እንዲህ አላት' እያልን በዘወትር ጸሎታችን ሳይቀር እየደጋገምን የምንጸልየውና የምንዘምረው የክብራችን ማስታወሻ ሆነ፡፡ በሴት ልጅ ይሁንታ ወደ ሞት ፍርድ የወረደውን የሰው ልጅ በሴት ልጅ ይሁንታ ወደ ሕይወት መመለሱን ፣ እየዘመርን የዲያብሎስን ሴራ መክሸፍ እናበሥራለን፡፡" የብርሃን እናት (ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ) ድንግል ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው
Hammasini ko'rsatish...
ሐና እና ኢያቄም በምድር እየኖሩ በሚኖሩባት ምድር ላይ ሰማይን ወለዱ። ሰማይና ምድር የማይችሉትን ጌታ በማሕፀኗ የተሸከመች ከሰማይ የምትገዝፍ ሰማይ፤ የድኅነታችን መሠረት የተጣለባት ለሰማይና ለምድር ሁሉ ጌጥ የሆነች ሁለተኛዋ ሰማይ በሐና እና በኢያቄም ቤት ግንቦት 1 ቀን ተወለደች። ይህች ቀን የሕይወታችን አዲሱ ምዕራፍ የተጀመረባት ታሪካዊት ቀን ናት። እንኳን ለፀሐይ እናት ለዳግሚት ሰማይ ለድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!! አሜን!!! Mesele Nigatu Deko
Hammasini ko'rsatish...
1
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 1 አራት መቶ ሰባ ሺህ ሦስት መቶ አጋንንትን በጸሎታቸው እሳት ከሰማይ አውርደው ያቃጠሏቸው የመሐግሉ አቡነ ቀውስጦስ ልደታቸው ነው፡፡ ➛ በእመቤታችን አብሳሪነት የተወለዱና በጸሎታቸው ኃይል ተራራን ያፈለሱት ታላቁ ጻድቅ አቡነ እንድርያስ ልደታቸውን ነው። 🔥 ጻድቅ አቡነ እንድርያስ በጸሎታቸው ኃይል የአርያም ስንዴ ከሰማይ እያወረዱ ልጆቻቸውን ይመግቡ የነበሩ፣ ቅዳሴ ሲቀድሱ ክንድ ከስንዝር ከመሬት ከፍ ብለው ይታዩ የነበሩ፣ በእመቤታችን አብሳሪነት የተወለዱና ከሕፃንነታቸው ጀምሮ እንደ እመቤታችን በቤተ መቅደስ ቅዱሳን መላእክት ሰማያዊ ኅብስት እየመገቡ ያሳደጓቸው፣ ዳግመኛም በጸሎታቸው ኃይል ተራራን ያፈለሱት (ያንቀሳቀሱት) ታላቁ ጻድቅ አቡነ እንድርያስ ልደታቸውን ነው። ልደታቸው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ጋር የተባበረላቸው ናቸው፡፡ ሀብት ንብረትና ጸጋ እግዚአብሔር ከሞላቸው ደጋግ ወላጆቻው ከዘአማኑኤልና ከአመተ መንፈስ ቅዱስ ግንቦት 1 ቀን 1235 ዓ.ም በእመቤታችን አብሳሪነት ተወለዱ፡፡ የልደታቸውም ነገር ድንቅ ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ አልነበራቸውምና ብዙ ምህላና ጸሎት እያቀረቡ ‹‹ልጅ ከሰጠኽን አንተን እንዲያገለግል ብፅዓት አድርገን ለቤትህ እንሰጣለን›› ብለው ለእግዚብሔር ተሳሉ፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን እንደልማዳቸው ከእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተው በሌሊት ሲጸልዩ እመቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹ከአብራካችሁ የተመረጠ ሕፃን በመንፈሳዊ ትምህርቱና ስብከቱ ታላቅ፣ በገድሉና በቃልኪዳኑ የጸና ለብዙዎች አባት የሚሆን በልደቴ ቀን የሚወለድ ታላቅ ልጅ እግዚአብሔር ሰጥቷቋችኋል›› ብላ አበሰረቻቸው፡፡ በእመቤታችን ብስራት መሠረት ጻድቁም በተወለዱ ዕለት ታላላቅ ተአምራት ተድርገው ስለታዩ በቦታው የነበሩ ሰዎች ዕፁብ ዕፁብ ብለው አድንዋል፡፡ የአቡነ እንድርያስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 የመሐግሉ አቡነ ቀውስጦስ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት አርሲ ፈንታሌ ተራራ ላይ ሠሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሦስት መቶ አጋንንትን በጸሎታቸው እሳት ከሰማይ አውርደው ያቃጠሏቸው የመሐግሉ አቡነ ቀውስጦስ ልደታቸው ነው፡፡ እርሳቸውም ልደታቸውና ዕረፍታቸው ከእመቤታችን ልደትና ዕረፍት ጋር የተባበረላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ አቡነ ቀውስጦስ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የቅርብ ዘመድ ናቸው፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እናት እግዚእ ኀረያና የአቡነ ቀውስጦስ እናት እብነ ጽዮን ታላቅና ታናሸ ናችው፡፡ በአባትም በኩል ወረደ ምሕረት ዘካርያስን ወለደ፡፡ ዘካርያስም የእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የሆኑ 6 ወንድማማች ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም እንድርያስ፣ አርከሌድስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ፣ ቀሲስ ዮሐንስና ቀሲስ ዮናስ ናቸው፡፡ እንድርያስም ሳሙኤል ዘወገግን ወለደ፤ አርከሌድስም ሕፃን ሞዐን ወለደ፤ ዘርዐ አብርሃምም ታላቁን አኖርዮስን ወለደ፤ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብም ተክለ ሃይማኖትን ወለደ፤ ቀሲስ ዮሐንስም ዜና ማርቆስን ወለደ፣ ቀሲስ ዮናስ ደግሞ የፈጠጋሩን ማትያስንና ገላውዲዮስን ወለዳቸው፡፡ ገላውዲዮስም የመሐግሉ ቀውስጦስን ወለደ፡፡ አቡነ ቀውስጦስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሾሙአቸው ከ12ቱ ንብረ ዕድ ወስጥ አንዱ ሲሆኑ ደብረ ሊባኖስንም የሚያጥኑበትም ወር በመጋቢት ወር ነበር። ሕዝቡ አጥብቆ የሚወዳቸውና የሚያከበራቸው አባት ናቸው፡፡ ግብፃዊው አቡነ ያዕቆብ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የደብረ ሊባኖሱን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን አስጠርተው፤ ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት “ኢትዮጵያ በአንድ ጳጳስ መወሰን የለባትም፡፡ ስለዚህ ዐሥራ ሁለት አበው መርጠን ክርስትና ይስፋፋ” ብለው ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት፤ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ /ኤጲስ ቆጶስ/፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘሞረት፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘወረብ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘግድም፣ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመርሐ ቤቴ፣ አቡነ አድኃኒ ዘዳሞት፣ አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል፣ አቡነ ኢዮስያስ ዘወጅ፣ አቡነ ዮሴፍ ዘእናርያን መርጠው ሀገረ ስብከት ተሰጥቷቸው ለሐዋርያዊ ተልእኮ ተሠማሩ፡፡ ዐሥራ ሁለቱን ንቡራነ ዕድ ለስብከተ ወንጌል በመላዋ አገሪቱ ሲሠማሩ፡፡ ጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ አርሲ ፈንታሌ ተራራ ላይ ሠሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ 470300 (አራት መቶ ሰባ ሺህ ሦስት መቶ) አጋንንትን በጸሎታቸው እሳት ከሰማይ አውርደው ተራውንን ደምስሰው አጋንንቱን ያቃጠሉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ የታናሽ ወንድማቸው የዐፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ ዐፄ አምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን እቁባት በማግባቱ አቡነ ቀውስጦስ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሄደው ንጉሡን ስለገሠፁት በግዞት ወስዶ ጎናቸው በጦር ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡ ጻድቁ ልደታቸውም ሆነ ዕረፍታቸው ከእመቤታችን ልደትና ዕረፍት ጋር የተባበረላቸው ናቸው፡፡ ግንቦት አንድ ቀን ተወልደው ጥር 21 ቀን ዐርፈዋል፡፡ የአቡነ ቀውስጦስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ምልጃ ፤ በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡ ምንጭ፡- የግንቦት ❶ ስንክሳር 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ ᴅᴇᴋᴏ ሚያዝያ ❸⓪ ቀን 2011 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...